English
1/ For the purpose of Article 7 Sub-Article
(2) lit.
(a) Of this Proclamation, personal data should
be processed on the basis of the consent given
prior to the commencement of the processing.
2/ For the consent of the data subject to be valid,
it must be free, informed, specific, clear and
require an active action from the data subject.
3/ The data subject may withdraw his consent at
any time. Information with regard to
withdrawal of consent shall be given prior to
giving his consent.
[[[[[
4/ The data controller shall not make the
provision of any goods or services or the
quality thereof, the performance of any
contract, or the enjoyment of any legal right
or claim, conditional on consent to
processing of any personal data not necessary
for that purpose. The application of this
provision shall be decided on a case-by-case
basis.
5/ The data controller shall bear the burden of
proof to establish that consent has been given
by the data subject for processing of personal
data in accordance with Sub-Article
(2) of this
Article. The request for consent shall be
presented in a manner which is clearly
distinguishable and separate from other
matters; request for consent cannot be bundled
with other terms and conditions.
6/ Where the data subject withdraws consent for
the processing of any personal data necessary
for the performance of a contract to which he is
a party, reasonable legal consequences for the
effects of such withdrawal shall be borne by
him. The withdrawal of consent by the data
subject shall not affect the lawfulness of
processing based on consent before its
withdrawal.
አማርኛ
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ ንዑስ አንቀጽ
(፪) ፊደል
ተራ
(ሀ) አፈጻጸም የግል ዳታ ማቀናበር የሚቻለው
ማቀናበሩ ከመጀመሩ በፊት በዳታ ባለቤቱ በሚሰጥ
ፈቃድ ላይ ተመስርቶ ነው።
፪/ የዳታ ባለቤቱ የሰጠው ፈቃድ ሕጋዊ ውጤት
እንዲኖረው ፈቃዱ በነፃነት ፣ በመረጃ ላይ
በመመስረት ፣ በግልጽ ፣ እንደዚሁም በዳታ
ባለቤቱ ግልጽ ተግባራትን በመፈጸም የተሰጠ
መሆን አለበት።
፫/ የዳታ ባለቤቱ የሰጠውን ፈቃድ በማንኛውም ጊዜ
ሊያነሳ ይችላል። ሆኖም የዳታ ባለቤቱ ፈቃዱን
በሚሰጥበት ወቅት ፈቃድ ማንሳትን የተመለከተ
መረጃ አስቀድሞ ሊሰጠው ይገባል።
፬/ ዳታ ተቆጣጣሪው የዕቃዎችንና የአገልግሎቶችን
አቅርቦት ፣ ወይም የጥራት ደረጃቸውን ፤ የውል
አፈፃጸምን ፣ ወይም የመብት አፈፃጸምን ከዚህ
ዓላማ ጋር ተያያዥ ካልሆነና የግል ዳታን
ለማቀናበር ከሚሰጥ ፈቃድ ጋር ማቆራኘት
የለበትም ። የዚህ ድንጋጌ ተፈጻሚነት ጉዳዮችን
አንድ በአንድ በመመልከት ይወስናል።
፭/ የዳታ ባለቤቱ ዳታ እንዲቀናበር ፈቃድ የሰጠው
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፪) መሠረት መሆኑን
የማስረዳት ሸክም በዳታ ተቆጣጣሪው ላይ ያርፋል።
የፈቃድ ጥያቄ ከሌሎች ጉዳዮች ተለይቶ
መቅረብ አለበት፤ በተለይም ከደንብና ግዴታዎች
ጋር መቀላቀል የለበትም።
[[[[[
፮/ የዳታ ባለቤቱ ለውል አፈጻጸም ዓላማ ሲባል የግል
ዳታው እንዲቀናበር ሰጥቶ የነበረውን ፈቃድ ሲያነሳ፤
ፈቃድ በመነሳቱ ምክንያት ለሚመጣው ተገቢ ለሆነ
ሕጋዊ ውጤት ኃላፊ ነው። ፈቃድ መነሳቱ ፈቃድ
በነበረበት ጊዜ የተደረገው ማቀናበር ሕጋዊነት ላይ
አሉታዊ ተፅዕኖ የለውም።