English
1/ Notwithstanding the provision of Sub-Article
(1) of Article 6 of this Proclamation, personal
data shall not be processed unless there is
compliance with at least one of the conditions set
out in Sub-Articles
(2) and
(3) of this Article; or
in the case of sensitive personal data, Article 9 of
this Proclamation.
2/ The processing of personal data shall be
regarded as lawful when:-
a) The data subject has given his consent;
b) Processing is necessary and is related to the
fulfillment of a contract with the data
subject or in order to take steps at the
request of the data subject prior to entering
into a contract;
c) The processing is necessary for compliance
with a legal obligation to which the data
controller is subject;
d) The processing is necessary to protect vitally
important interests of the data subject,
including life and health;
e) The processing is necessary in order to
respond to a public health crisis or national
emergency or to fulfill functions of public
authority which necessarily includes the
processing of personal data for the
fulfillment of its mandate within the limits of
a law issued for this purpose; or
f) The processing is necessary for the purposes
of the legitimate interests pursued by the
personal data controller to whom the data is
disclosed, except where such interests are
overridden by fundamental rights and
freedoms of the data subject which require
protection of personal data.
3/ For the purpose of Sub-Article
(2) lit.
(e) of this
Article,
a) The impact of data proceccing on privacy
right of the data subject shall be necessary and
proportionate;
b) The law shall determine the essential elements
of processing such as the categories of data,
the purpose, storage period, and possible
disclosure; and
c) Further processing of personal data after the
expiry of such law shall be prohibited.
4/ The data processing should be proportionate to
the legal aim it complies.
አማርኛ
፩/ በዚህ አዋጅ የአንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ድንጋጌ
እንደተጠበቀ ሆኖ የግል ዳታ በዚህ አንቀጽ ንዑስ
አንቀጽ
(፪) እና
(፫) እንደዚሁም ጥንቃቄ የሚፈልግ
የግል ዳታ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፱ ላይ የተመለከቱትን
ሁኔታዎች ማሟላት አለበት።
፪/ የግል ዳታ ማቀናበር ሕጋዊ ነው የሚባለው
ሀ) የዳታው ባለቤት ፈቃዱን የገለጸ፤
ለ) ማቀናበሩ አስፈላጊና ከዳታ ባለቤቱ ጋር የተገባን
ውል ከመፈጸም ጋር የተገናኘ ፣ ወይም የዳታ
ባለቤቱ ውል ከመግባቱ በፊት በጠየቀው መሠረት
እርምጃዎችን ለመውሰድ ማቀናበሩ አስፈላጊ፤
[[
ሐ) ማቀናበሩ የዳታ ተቆጣጣሪው ያለበትን ግዴታ
ለመወጣት አስፈላጊ፤
መ) ማቀናበሩ የዳታ ባለቤቱን ሕይወትና ጤናን
ጨምሮ ወሳኝና አስፈላጊ የሆኑ ጥቅሞቹን
ለማስጠበቅ አስፈላጊ፤
ሠ) ማቀናበሩ ለሕብረተሰብ የጤና ቀውስ ወይም
ለብሔራዊ አደጋ ምላሽ ለመስጠት ፣ ወይም
መንግሥታዊ ተቋሞ የግል ዳታ ማቀናበርን
ጨምሮ በሕግ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት
ለመወጣት አስፈላጊ ፤ ወይም
ረ) ማቀናበሩ ዳታው ለተሰጠው ዳታ ተቆጣጣሪ
ሕጋዊ ጥቅሞች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና፤ እነዚህ
ጥቅሞች የግል ዳታ ጥበቃ በሚያስፈልጋቸው
የዳታ ባለቤቱ ሌሎች መሠረታዊ መብቶች
የማይገደቡ፤ ከሆነ ነው።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፪) ፊደል ተራ
(ሠ) አፈጻጸም ፣
ሀ)ዳታ ማቀናበሩ በግለሰቦች የግላዊነት መብት ላይ
የሚያሳድረው ጫና አስፈላጊና ተመጣጣኝ፤
ለ) የዳታ ማቀናበሩ ዋነኛ ክፍሎች በተለይም የዳታውን
ምድብ ፣ የማቀናበሩን ዓላማ፣ዳታው የሚከማችበትን
ጊዜ፣ዳታው ይፋ የሚደረግበትን አግባብ የሚወስን፤
እንደዚሁም
ሐ) ሕጉ ተፈጻሚ መሆን ካቆመ በኋላ የሚደረግ
የግል ዳታ ማቀናበር የተከለከለ፤ መሆን
አለበት።
፬/ የዳታ ማቀናበር ከተከተለው ሕጋዊ ዓላማ ጋር
ተመጣጣኝ መሆን አለበት።