English
1/ Any person who
a) does not to notify personal data breach
b) does not implement technical and
organizational measures when a breach is
committed; or
c) Processes personal data in contravention of the
provisions of this Proclamation; Shall be
punished with simple imprisonment from one
to three years or fined from 60,000 – 100,000
birr or both.
2/ Any person who against the rights of the data
subject
a) fails to erase personal data;
b) fails to respect the right to object processing;
c) restricts processing; or
d) Does not respect the right against automated
decisions shall be punished with imprisonment
for a period starting from three years to five
years or fined from 100,000 – 200,000 birr or
both.
3/ Any person
a) Re-identifies personal data which has been de-
identified; or
b) Processes Re-identified personal data which is
identified in Sub Article 3 let
(a) of this
article;
c) sells or offers to sell personal data; or
d) Transfers of personal data outside Ethiopia in
violation of this Proclamation; shall be
punished with serious imprisonment from five
years to ten years or fined from 200,000 -
600,000 birr or both.
4/ Notwithstanding the provisions of Sub-Article
(1),
(2) and
(3) of this Article, if the offence
a) has been committed by an institution; or
b) has caused any damage and as a result became
a serious offence;
[[
c) has been committed in relation to sensitive
personal data; or
d) has been committed in relation the personal
data of a minor, the offence shall be
punishable with a fine up to four per cent of
its total worldwide turnover of the preceding
financial year.
አማርኛ
፩/ ማንኛውም ሰው
ሀ) የግል ዳታ ጥሰትን ካላሳወቀ፣
ለ) የግል ዳታ ጥሰት ተፈጽሞ ሲገኝ ተገቢውን
የቴክኒክና ተቋማዊ እርምጃዎች ካልወሰደ፤
ሐ) የግል ዳታ በአዋጁ ከተደነገጉት የማቀናበር መርሆዎች
ውጪ ካቀናበረ፤ከአንድ ዓመት እስከ ሦስት ዓመት
በሚደርስ ቀላል እስራ ወይም ከብር ከ፷ሺ እስከ
፩፻ሺ በሚደርስ መቀጮ ወይም በሁለቱም
ይቀጣል።
፪/ ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ የተደነገጉና የግል ዳታ
ባለቤት የግል ዳታው
ሀ) እንዲደመሰስ የማድረግ፣
ለ) እንዳይቀናበር የመቃወም፣
ሐ) ማቀናበር እንዲገደብ የመጠየቅ፣
መ)ራስ አዘዝ በሆኑ መሳሪያዎች በሚሰጡ ውሳኔዎች
ላይ ያለውን መብቱን ካላከበረ ከሶስት እስከ
አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከብር
፩፻ሺ እስከ ፪፻ሺ በሚደርስ መቀጮ ወይም
በሁለቱም ይቀጣል።
፫/ ማንኛውም ሰው
ሀ)የግል ዳታ ባለቤቱ ተለይቶ እንዳይታወቅ
የተደረገን የግል ዳታ ተለይቶ እንዲታወቅ
ካደረገ፤
ለ) በዚህ ንዑስ አንቀጽ በፊደል ተራ
(ሀ) አግባብ
መሠረት ተለይቶ የታወቀውን የግል ዳታ
ካቀናበረ፤
ሐ) የግል ዳታን ከሸጠ ወይም ለሽያጭ ካቀረበ፤
ወይም ለሽያጭ ካቀረበ፤ ወይም
መ) የግል ዳታን በአዋጁ ከተደነገገው ውጪ ከአገር
ውጪ ካስተላለፈ አምስት ዓመት አስር ዓመት
በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከብር ፪፻ሺ እስከ
፮፻ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩)፣
(፪) እና
(፫) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣
ሀ) ጥፋቱ የተፈጸመው በተቋም ከሆነ፣ ወይም
ለ) የተፈጸመው ጥፋት ጉዳት አድርሶ ከሆነ ከዚህም
የተነሳ የወንጀሉን አፈጻጸም ከባድ አድርጎት
ከሆነ፣ ወይም
ሐ) ጥፋቱ ጥንቃቄ በሚፈልግ የግል ዳታ ዙሪያ
የተፈጸመ ከሆነ፣ ወይም
መ) ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን የሚመለከት
ከሆነ በጉዳዩ ላይ አቤቱታ ከተመሰረተበት ዓመት
በፊት ባለው የሥራ ዘመን ተቋሙ ከሚያካሂደው
የንግድ ሥራው ካገኘው ጠቅላላ ሽያጭ
እስከ አራት ፐርሰንት ያህል መቀጮ ይቀጣል።