English
1/ Where a personal data breach has occurred,
the controller shall communicate the
personal data breach to the data subject
within 72 hours after having become aware
of it.
2/ The communication to the data subject shall
describe in clear language the nature of the
personal data breach and set out the
information in Article 43 Sub-Article
(4) lit.
(b)-
(d) Of this Proclamation.
3/ The communication of a personal data
breach to the data subject shall not be
required where:
a) The data controller has implemented
appropriate technical and organizational
protection measures, and those measures
were applied to the personal data affected
by the breach, in particular, those that
render the data unintelligible to any
person who is not authorized to access it,
such as encryption;
b) The data controller has taken subsequent
measures to ensure that the high risk to the
rights and freedoms of the data subject
referred to in Sub-Article
(1) of this
Article is no longer likely to materialize;
or
c) It would involve disproportionate effort and
the data controller has made a public
communication or similar measure whereby
data subject is informed in an equally
effective manner.
4/ Where the data controller has not already
communicated the personal data breach to the
data subject, the Authority may require it to do
so.
አማርኛ
፩/ የግል ዳታ ጥሰት ከተፈፀመ ዳታ ተቆጣጣሪው
ጥሰቱን ባወቀ ከ ፸፪ ሠዓታት ባልበለጠ ጊዜ
ውስጥ ሁኔታውን ለዳታ ባለቤቱ መግለጽ
አለበት።
፪/ ለዳታ ባለቤቱ የሚቀርበው መግለጫ የግል ዳታ ጥሰቱን
ባህርይ በግልጽ ቋንቋ የሚያብራራና በዚህ አዋጅ
አንቀጽ ፵፫ ንዑስ አንቀጽ
(፬) ፊደል ተራ
(ለ) እስከ
(መ) የተዘረዘረውን መረጃ ያካተተ መሆን
አለበት።
፫/ ዳታ ተቆጣጣሪው :-
ሀ)ተገቢውን የቴክኒክና ተቋማዊ የመከላከል
እርምጃዎችን ከወሰደ፣ እና እነዚህ እርምጃዎች
በጥሰቱ በተጎዱ የግል ዳታዎች ላይ ከተተገበሩ፣
በተለይም ዳታ ከተፈቀደለት ሰው በስተቀር
ሊረዳው እንዳይችል ለማድረግ የመመስጠር እና
ሌሎች ተመሳሳይ እርምጃዎች የተወሰዱ ከሆነ፣
ለ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ላይ የተገለጸው
የዳታ ባለቤትን መብቶችና ነፃነቶች አደጋ ላይ
የሚጥሉ ሁኔታዎች ከዚህ በኋላ ሊከሰቱ እንዳይችሉ
ለማድረግ ተከታታይ እርምጃዎች ከወሰደ፣ ወይም
ሐ) የዳታ ባለቤቱን ለማሳወቅ ተመጣጣኝ ያልሆነ ጥረት
ውስጥ የሚከተውከሆነና፤ ዳታ ተቆጣጣሪው ለህዝብ
የማሳወቅ ሥራዎች በመሥራቱ ወይም ተመሳሳይ
እርምጃዎችን በመውስዱ የዳታ ባለቤቱ ጥሰቱን
በተመለከተ መረጃ ያገኘ ከሆነ የግል ዳታ ጥሰቱን
ለዳታ ባለቤቱ እንዲገልጽ አይጠበቅም።
፬/ የዳታ ተቆጣጣሪው የግል ዳታ ጥሰቱን ለዳታ ባለቤቱ
ካላሳወቀ፣ ባለሥልጣኑ የዳታ ጥሰቱን ለዳታ
ባለቤቱ እንዲያሳውቅ ሊያዘው ይችላል።