English
1/ Processing of personal data for historical,
statistical or scientific research may be exempt
from the provisions of this Proclamation.
2/ Without prejudice Sub Article 1 of this article,
personal data may be processed without the
consent of the data subject for the needs of
scientific and historical research and official
statistic, in a pseudonymised format or a format
which provides an equivalent level of protection.
3/Pseudonymisation or any other method by which
the data not enabling identification of persons are
changed again into the data which enable
identification of persons are only permitted for
the needs of additional scientific and historical
research or official statistics.
4/ Processing of data concerning any data subjects
for the needs of scientific and historical research
or official statistics without the consent of the
data subject in a format which enables
identification of the data subject is permitted
only in the case the following conditions are
met:
a) the purposes of data processing can no longer
be achieved after removal of the data enabling
identification or it would be unreasonably
difficult to achieve these purposes;
b) There is overriding public interest for it in the
estimation of the persons conducting scientific
and historical research or compiling official
statistics.
5/ The processing of personal data for the purpose
of historical, statistical or scientific research may
be exempt from the provisions of this
Proclamation where the data protection principles,
rights of data subject and obligations put on data
controllers and data processors, and the security
and organizational measures specified in Article 17 Sub- Article (4),
(5) and
(6) of this
Proclamation are implemented to protect the
rights and freedoms of data subjects involved.
‹‹‹
አማርኛ
፩/ የግል ዳታ ለታሪካዊ፣ ለስታስቲክስ ወይም
ለሳይንሳዊ ምርምሮች ዓላማ ለማሳካት ገደብ
ሊጣልበት ይችላል።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የግል ዳታ ለምርምር
የሚቀናበረው ስውር ስያሜ ወይም ሌላ ተመሳሳይ
የጥበቃ ደረጃ የሚሰጥ የአሠራር ሥርዓትን
በመተግበር ነው።
፫/ ስውር ስያሜን ወይም ተመሳሳይ የጥበቃ ደረጃ የሚሠጥና
ባለቤቱ እንዳይታወቅ የሚያስችል ሌላ አሠራርን
በመጠቀም ዳታን ወደ ቀደመው ደረጃ መመለስ
የሚፈቀደ ለተጫማሪ የሳይንሳዊ ፣ ታሪካዊ ወይም
የስታቲስቲክ ዓላማ አስፈላጊ ከሆነ ብቻ ነው።
፬/ የግል ዳታ ያለ ስውር ስያሜ ማቀናበር
የሚፈቀደው
(ሀ) የማቀናበሩ ዓላማ የዳታው ባለቤትን ለማወቅ
የሚያስችሉ መለያዎችን ካስወገዱ በኃላ ማሳካት
የማይቻል ከሆነ ወይም ይህን ዓላማ ማሳካት
ከሚገመተው በላይ አስቸጋሪ
(ለ) በሚቀናበረው የግል ዳታ ምክንያት የግል ዳታ
ባለቤቱ የግዴታ ተፈጻሚነት ወሰን የማይቀየር
ከሆነ ወይም የዳታ ባለቤቱ መብት ተመጣጣኝ
ከሆነው በላይ አሉታዊ ጫና የማያርፍበት ከሆነ
ነው።
፭/ የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች የግል ዳታን ለታሪካዊ ፣
ለስታስቲክስ ወይም ለሳይንሳዊ ምርምሮች ዓላማ
ማቀናበርን በተመለከተ ገደብ የሚጣልባቸው ፤ የዳታ
ማቀናበር መርሆዎች ፣ የዳታ ባለቤቶች መብቶች ፣
የዳታ ተቆጣጣሪውና ዳታ አቀናባሪው ግዴታዎች ፣
እንደዚሁም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ
(፬) ፣
(፭) እና
(፮) የተደነገጉት የደህንነትና ተቋማዊ
እርምጃዎች የዳታ ባለቤቱን መብቶችና ነጻነቶች
ለመጠበቅ የሚተገበሩ ከሆነ ነው።