English
1/ Exception to the provisions of this Proclamation
shall be allowed where it constitutes a necessary
and proportionate measure in a democratic
society.
2/ Notwithstanding the provisions of Sub-Article
(1) of this article :
a) the protection of national security, defense or
public security;
b) historical, statistical and scientific research;
c) an objective of general public interest,
including an economic or financial interest of
the State;
d) the protection of judicial independence and
judicial proceedings; or
e) The protection of a data subject or the rights
and freedoms of others shall be governed by
Regulation.
3/ If the data subject, the Authority or third party is
convinced that the exception introduced is not
necessary and proportionate, he or it may
institute a case in a court of law.
አማርኛ
፩/ በዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ላይ የሚጣል
ገደብ ተፈጻሚ የሚሆነው ፣ ገደብ መጣሉ በዲሞክራሲያዊ
ማኅበረሰብ ውስጥ አስፈላጊና ተመጣጣኝ እርምጃ
ከሆነ ነው።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ :-
ሀ) ለብሔራዊ ደህንነት፣ ለአገር መከላከያ እና
ለሕዝብ ሠላም፤
ለ) ለታሪካዊ፣ ለስታስቲክስ ወይም ለሳይንሳዊ
ምርምሮች ዓላማ፤
ሐ) የመንግሥት የኢኮኖሚና የፋይናንስ ጥቅሞችን
ጨምሮ ለአጠቃላይ የሕዝብ ጥቅም ዓላማ፤
መ) የዳኝነት ነጻነትና የፍርድ ሂደቶችን ለመጠበቅ፤
ወይም
ሠ) የዳታ ባለቤቱን ወይም የሌሎችን መብትና ነጻነት
ለመጠበቅ የግል ዳታ የማቀናበር ገደብ የሚጥል
ዝርዝር ሕግ በደንብ ማውጣት ይቻላል።
፫/ የዳታ ባለቤቱ ወይም ባለሥልጣኑ ወይም ሦስተኛ
ወገን በዚህ አዋጅ መሠረት የተጣለ ገደብ
አስፈላጊና ተመጣጣኝ አይደለም ብሎ ካመነ የግለ
ሰቦች መብት እንዲከበር በፍርድ ቤት ክስ
መመስረት ይችላል።