English
1/ This Proclamation shall apply to the processing
of personal data, wholly or partly, by automated
means and to any processing other than by
automated means where the personal data form
part of a filing system or are intended to form
part of a filing system.
2/ Except as otherwise provided, this Proclamation
applies to a data controller or data processor in
respect of any personal data only if:
a) It is established in Ethiopia and the data are
processed in the context of that
establishment, or
b) It is not established in Ethiopia but uses
equipment in Ethiopia for processing the
data otherwise than for the purposes of
transit through Ethiopia and has a
representative established in Ethiopia.
3/ For the purpose of the application of Sub-Article
(2) lit.
(a) Of this Article, this Proclamation shall
apply on private and public institutions of the
federal and regional governments, including the
City Administrations of Addis Abeba and Dire
Dawa, which have the power and function to
process personal data.
4/ Notwithstanding the provisions of Sub-Article
(1) to
(3) of this Article, this Proclamation shall not
apply to processing of personal data:
a) By an individual in the course of purely
personal or household activity;
b) Which involves the exchange of information
between Government Agencies where such
exchange is required on a need-to-know
basis;
c) where the application of the proclamation is
restricted; and
d) Originating from a country outside of
Ethiopia and merely transiting through
Ethiopia to a third country. .
አማርኛ
፩/ ይህ አዋጅ በሙሉ ወይም በከፊል ራስ አዘዝ
በሆነ መሳሪያ ፣ እንደዚሁም የመዝገብ ሥርዓት አካል
የሆነ ወይም የመዝገብ ሥርዓት አካል እንዲሆን
የታሰበና ራስ አዘዝ ባልሆነ መሳሪያ በሌላ መንገድ
በሚደረግ የግል ዳታ ማቀናበር ላይ ተፈጻሚ ነው።
፪/ ከዚህ በተቃራኒ ካልተደነገገ በስተቀር፣ ይህ አዋጅ
ማንኛውንም የግል ዳታ በተመለከተ በዳታ
ተቆጣጣሪ ወይም በዳታ አቀናባሪ ላይ ተፈጻሚ
የሚሆነው :-
ሀ) የተቋቋመው በኢትዮጵያ ከሆነና ዳታው
የተቀናበረው ድርጅቱ ከተቋቋመበት አውድ
አንፃር፣ ወይም
ለ) የተቋቋመው በኢትዮጵያ ባይሆንም ዳታው
በኢትዮጵያ አልፎ ለመሻገር ሳይሆን
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ መሳሪያን
በመጠቀም የሚቀናበር እና መቀመጫውን
በኢትዮጵያ ያደረገ ወኪል ያለው ከሆነ ብቻ
ነው።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፪) ፊደል ተራ
(ሀ) አፈጻጸም ይህ አዋጅ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ
ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በፌደራልና ክልል
መንግስት ውስጥ የግል ዳታ የማቀናበር ኃላፊነትና
ተግባር ባላቸው የግል እና የመንግስት ተቋሞች
ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።
፬/ በዚህ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ
(፩) እስከ
(፫) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁ፡ሀ) አንድ ግለሰብ ለግሉ ወይም ለቤተሰቡ
ግልጋሎት ለመስጠት በሚደረጉ፤
ለ) በመንግስት ተቋማት መካከል አንድን ጉዳይ
ለማጣራት በሚደረጉ የመረጃ ልውውጦች ላይ
የሚያተኩሩ፤
ሐ) በዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት
ላይ የተጣሉ ገደቦች ተብለው በተለዩ፣ እና
መ) ከውጭ አገራት በመነጩ እና በኢትዮጵያ
አልፈው ወደ ሶስተኛ አገራት የሚሻገሩ የግል
ዳታ ማቀናበሮች ላይ ተፈፃሚ አይሆንም።