English
1/ A Regulation may prescribe further categories
of personal data which may be classified as
sensitive personal data.
2/ Where categories of personal data have been
specified as sensitive personal data under
Sub-Article
(1) of this Article, the Authority
may specify any further grounds on which
such specified categories may be processed,
having regard to:
a) the risk of significant harm that may be caused
to a data subject by the processing of such
category of personal data;
b) the level of confidentiality attached to such
category of personal data;
c) whether a significantly discernible class of data
subjects may suffer significant harm from the
processing of such category of personal data;
and
d) The adequacy of protection afforded by
ordinary provisions applicable to personal
data.
3/ The Authority may specify other categories of
personal data based on study which require
additional safeguards or restrictions.
አማርኛ
፩/ ተጨማሪ የግል ዳታ ምድቦችን ጥንቃቄ የሚፈልግ
የግል ዳታ በማለት በደንብ ሊመደብ ይችላል።
፪/ የግል ዳታ ምድቦች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) መሠረት ጥንቃቄ የሚፈልግ የግል ዳታ ተብለው
በሚመደቡበት ጊዜ፣
ሀ) በዚህ ምድብ ውስጥ የተካተተ የግል ዳታ
ማቀናበር በዳታው ባለቤት ላይ ሊያስከትለው
የሚችለውን የአደጋ የሥጋት ደረጃ፣
ለ) በዚህ ምድብ ውስጥ የተካተተ የግል ዳታ
የሚጠበቅበትን የሚስጥራዊነት ደረጃ፣
ሐ) በዚህ ምድብ የተካተተ ዳታ ማቀናበሩ በቁጥር
ከፍ ባሉና በሚታወቁ የዳታ ባለቤቶች ላይ
ሊያስከትል የሚችለውን የአደጋ የሥጋት ደረጃ፣
እና
መ) መደበኛ የሆኑ የግል ዳታ ድንጋጌዎች የሚሰጡት
ጥበቃ በቂ መሆናቸውን መነሻ በማድረግ በዚህ
ሥር የተካተቱ የግል ዳታዎች የሚቀናበሩበትን
ተጨማሪ ምክንያቶች መወሰን ይችላል።
፫/ ባለሥልጣኑ ተጨማሪ ቴክኒካዊ የደህንነት
እርምጃዎችን ወይም ገደቦችን የሚጠይቁ ሌሎች
የግል የዳታ ምድቦችን በተመለከተ በጥናት
የተደገፈ ሀሳብ ሊያቀርብ ይችላል።