English
1/ The responsibility of a data protection officer
shall be to:
a) Support the data controller or data processor
and their employees on data processing
requirements provided under this
Proclamation or any other law;
b) Ensure on behalf of the data controller or
data processor that this Proclamation is
complied with;
c) Facilitate capacity building of staff involved
in data processing operations;
d) Provide advice on data protection impact
assessment; and
e) Cooperate with the Authority and any other
authority on matters relating to data
protection.
2/ Notwithstanding the provisions of Sub-Article
(1) of this Article, a data protection officer may be a
staff member of the data controller or data
processor and may fulfill other tasks and duties
provided that any such tasks and duties do not
result in a conflict of interest.
አማርኛ
፩/ የግል ዳታ ጥበቃ መኮንኑ፡ሀ) በዚህ አዋጅ እና በሌሎች ሕጎች በተደነገጉት
የዳታ ማቀናበር መስፈርቶች ዙሪያ የዳታ
ተቆጣጣሪው ወይም የዳታ አቀናባሪው እና
ሠራተኞቻቸው ሥራቸውን በአግባቡ እንዲፈጽሙ
የማገዝ፤
ለ) ዳታ ተቆጣጣሪውን ወይም ዳታ አቀናባሪውን
በመወከል ይህ አዋጅ መከበሩን የማረጋገጥ፤
ሐ) በዳታ ማቀናበር ሥራዎች ውስጥ የሚሳተፉ
ሠራተኞች አቅም እንዲጎለብት ሁኔታዎችን
የማመቻቸት፤
መ) የዳታ ጥበቃ ባመጣው የተጽዕኖ ግምገማ ላይ
አስተያየት የማቅረብ፤
ሠ) ከባለሥልጣኑና ከሌሎች በዳታ ጥበቃ ዙሪያ ከሚሰሩ
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቶች ጋር የመተባባር ፤
ኃላፊነት አለበት።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገው እንደተጠበቀ
ሆኖ የዳታ ጥበቃ መኮንኑ የዳታ ተቆጣጣሪው ወይም
የዳታ አቀናባሪው ሠራተኛና የጥቅም ግጭት እስከሌለ
ድረስ በተደራቢነት ሌሎች ሥራዎችና ግዴታዎችን
የሚፈጽም ሊሆን ይችላል።