English
1/The Authority shall ensure that the imposition of
administrative fines pursuant to this
Proclamation is effective, proportional and
dissuasive.
2/ Notwithstanding the provision of Sub
Article
(1) of this this article while deciding to
impose administrative fines, the Authority
shall have due regard, inter alias, to the
following factors, namely :
a) Nature, duration and extent of violation;
b) Nature and extent of harm suffered by the
data subject;
c) Intentional or negligent character of the
violation;
d) Transparency and accountability measures
implemented by the data controller or the
data processor, as the case may be, including
adherence to any relevant code of practice
relating to security safeguards;
e) Action taken by the data controller or the data
processor, as the case may be, to mitigate the
damage suffered by the data subject;
f) Previous history of any, or such, violation by
the data controller or the data processor, as
the case may be;
g) Whether the arrangement between the data
controller and data processor contains
adequate transparency and accountability
measures to safeguard the personal data
being processed by the data processor on
behalf of the data controller;
h) The accrual of undue benefits which can be
measured; and
i) Any other aggravating or mitigating factor
relevant to the circumstances of the case.
አማርኛ
፩/ ባለሥልጣኑ በዚህ አዋጅ መሠረት አስተዳደራዊ
እርምጃ ሲወሰን ውሳኔው ውጤታማ፣ ተመጣጣኝና
አስተማሪ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አስተዳደራዊ እርምጃ
በመወሰን ሂደት ባለሥልጣኑ ከሌሎች
መመዘኛዎች ባሻገር :-
(ሀ) የጥሰቱ ባህርይ፣ የጊዜ ርዝማኔና ስፋትን፣
(ለ) በዳታ ባለቤቱ ላይ የደረሰው የጉዳት ባህርይና
መጠንን፣
(ሐ) ጥሰቱ ሆነ ተብሎ ወይም በቸልተኝነት
የተፈጸመ መሆኑን፣
(መ) የዳታ ተቆጣጣሪው ወይም የዳታ አቀናባሪው
ተግባራዊ ያደረገው የርዕታዊነትና የተጠያቂነት
እርምጃዎች እንደዚሁም አግባብነት ያላቸው
የሥነምግባር ደንቦችን የተተገበሩ መሆናቸውን፣
(ሠ) በዳታ ባለቤቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመቀነስ
የዳታ ተቆጣጣሪው ወይም የዳታ አቀናባሪው
የወሰዳቸው እርምጃዎችን፣
(ረ) ከዚህ በፊት በዳታ ተቆጣጣሪው ወይም በዳታ
አቀናባሪው የተፈጸሙ ጥፋቶች ያሉ መሆናቸውን፣
(ሰ) ዳታ አቀናባሪው ዳታ ተቆጥጣሪውን ተክቶ
የሚያቀናብረውን የግል ዳታ በተመለከተ በዳታ
ተቆጣጣሪውና በዳታ አቀናባሪው መካከል የተደረጉ
ስምምነቶች በቂ የግልጸኛነትና የተጠያቂነት
እርምጃዎችን ያካተተ መሆኑን፣
(ሸ) ጥሰቱ በመፈጸሙ የተገኙና ሊለኩ የሚችሉ
ተገቢ ያልሆኑ ጥቅሞች ያሉ መሆናቸውን፣
እንደዚሁም
(ቀ) አግባብ የሆኑና ጥፋቱን ሊያከብዱ ወይም
ሊያቀሉ የሚችሉ ሌሎች ሁኔታዎች
መኖራቸውን ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት።