English
1/ A data controller or a data processer must
store and retain personal data for a
reasonable period of time necessary to achieve
the purpose of or the purpose for which it was
processd or for a period defined by law.
2/ Notwihthstanding to Sub Article
(1) of this article
; personal data may be stored indifinately in the
following circumstances :
(a) as provided by this law or any other law;
(b) when the data owner consents ;
(c) when its necessary for lawful purposes;or
(d) For historical, stastical, literally and
research purpose.
]
[[[[
3/ A person who retains records for historical,
statistical or research purposes shall ensure that
the records that contain the personal data are
adequately protected against access or use for
unauthorized purposes.
4/ A person who uses a record of the personal data
of a data subject to make a decision about the
data subject shall retain the record for a period
required or prescribed by law or a code of
conduct.
አማርኛ
፩/ የዳታ ተቆጣጣሪ ወይም የዳታ አቀናባሪ የግል
ዳታ የተቀናበረበትን ዓላማ ወይም ዓላማዎቹ
ለማሳካት አስፈላጊ ለሆነበት ምክንያታዊ ጊዜ
ወይም በሕግ ተገልጾ ለተቀመጠ ጊዜ አከማችቶ
ማቆየት አለበት።
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ድንጋጌ ቢኖርም፤
የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ የግል ዳታ ላልተወሰነ
ጊዜ ሊከማች ይችላል፡ሀ) በዚህ ወይም በሌላ ሕግ የተደነገገ ከሆነ፤
ለ) የዳታ ባለቤቱ ሲፈቅድ፤
ሐ ለሕጋዊ ዓላማ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤ወይም
መ) ለታሪክ፣ ለስታቲስቲክስ፣ ለሥነ-ጽሑፍ እና
ለምርምር ዓላማ።
፫/ የግል ዳታን ለታሪክ ፣ ለስታቲስቲክስ እና ለምርምር
ዓላማ የሚያስቀምጥ ሰው የግል ዳታን የያዙ ሰነዶች
ላልተፈቀዱ ዓላማዎች ይፋ እንዳይደረጉ ወይም
ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ለማድረግ በቂ ጥበቃ
ሚደረግላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
፬/ የዳታ ባለቤቱን የግል ዳታ ሰነድ በመጠቀም የዳታ
ባለቤቱን የሚመለከት ውሳኔ የሚወስን ሰው
ሰነዱን በሕግ ወይም በአሠራር ደንብ ለተቀመጠው
ጊዜ ያህል ጠብቆ ማቆየት አለበት።