English
1/ Where processing operations may result in a
risk to the rights and freedoms of data subjects
by virtue of their nature, scope, context and
purposes, every data controller or data
processor shall, prior to the processing, carry
out an assessment of the impact of the
envisaged processing operations on the
protection of personal data.
2/ The processing operations referred to in Sub-
Article
(1) of this Article are:
a) A systematic and extensive evaluation of
personal aspects relating to individuals
which is based on automated processing,
including profiling, and on which decisions
are based that produce legal effects
concerning the individual or significantly
affect the individual;
b) Processing on a large scale of sensitive
personal data;
c) A systematic monitoring of a publicly
accessible area on a large scale; and
d) Any other processing operations for which
consultation with the Authority is required.
3/ An assessment shall include:
a) systematic description of the envisaged
processing operations and the purposes of the
processing, including, where applicable, the
legitimate interest pursued by the data
controller or data processor;
b) an assessment of the necessity and
proportionality of the processing operations
in relation to the purposes;
c) an assessment of the risks to the rights and
freedoms of data subjects; and
d) The measures envisaged to address the risks
and the safeguards, security measures and
mechanisms to ensure the protection of
personal data and to demonstrate compliance
with this Proclamation, taking into account
the rights and legitimate interests of data
subjects and other persons concerned.
4/ Where appropriate, the data controller or data
processor shall seek the views of data subjects on
the intended processing, without prejudice to the
protection of commercial or public interests or
the security of the processing operations.
አማርኛ
፩/ የዳታ ማቀናበር ሥራ በባህርዩ ፣ በወሰኑ ፣ በአውዱ
እና በዓላማው የዳታ ባለቤቱ መብቶችና ነፃነቶች
ላይ ስጋት የሚደቅን ከሆነ፣ ማንኛውም የዳታ ተቆጣጣሪ
ወይም የዳታ አቀናባሪ ዳታን ከማቀናበሩ በፊት
የማቀናበር ሂደቱ በግል ዳታ ጥበቃ ላይ ሊያስከትል
የሚችለውን ተፅዕኖ መገምገም አለበት።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ
(፩) የተጠቀሰው
የማቀናበር ሂደት ;-
(ሀ) የግል ዳታ ባለቤት መገለጫ ቅንብርን ጨምሮ
በራስ አዘዝ መሳሪያዎች የተመሠረተ፣
የተደራጀና ሰፊ የሆነ ከግለሰቦች ግላዊ ሕይወት
ጋር የተያያዘ፣ እንደዚሁም በግለሰቦች ላይ
ለሚሰጥና ሕጋዊ ውጤት ለሚያመጣ ውሳኔ
መነሻ የሆነ ወይም በግለሰቦች ላይ ጉልህ ጫና
የሚያሳድር፣
(ለ) መጠነ ሰፊና ጥንቃቄ የሚፈልግ የግል ዳታ ላይ
የሚካሄድ፣
(ሐ) መጠነ ሰፊና ሕዝብ የሚሰበሰብበትን ቦታ
በተደራጀ መንገድ መቆጣጠርን የተመለከተ፣
እንደዚሁም፣
(መ) ሌላ ከባለሥልጣኑ ጋር ምክክር ማድረግ
የሚጠይቅ ማናቸውም ዓይነት ማቀናበርን
ያካትታል።
፫/ ግምገማው
(ሀ) ሊተገበር የተፈለገው የማቀናበር ሥራን በተደራጀ
አግባብ ማብራራት፣ እንዳግባቡ የዳታ ተቆጣጣሪው
ወይም የዳታ አቀናባሪው ሊያሳካ የሚፈልገው
ሕጋዊ ፍላጎትን ጨምሮ የማቀናበሩን ዓላማ፣
(ለ) የማቀናበሩ ሥራ ከዓላማው ጋር ሲነጻጸር
የአስፈላጊነቱንና ተመጣጣኝነቱን ግምገማ ፣
(ሐ) የዳታ ባለቤቱ መብቶችን እና ነፃነቶች ላይ
የሚጥለው የሥጋት ደረጃ ግምገማ፣ እንደዚሁም
(መ) የዳታ ባለቤቱን እና ሌሎች የሚመለከታቸው
ሰዎች መብቶች እና ሕጋዊ ጥቅሞች
ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ሥጋቱን ለመግታት
የሚወሰዱ ዕርምጃዎች፣ እንደዚሁም የግል ዳታ
ጥበቃን ለማረጋገጥ የሚወሰዱ የደህንነት
ዕርምጃዎች እና የግል ዳታ ጥበቃን ለማረጋገጥና
ከዚህ አዋጅ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን
ለማሳየት በዚህ አዋጅ መሠረት መደረጉን
የሚገልጽ መግለጫ ሊያካትት ይገባል።
፬/ ተገቢ ሆኖ ሲገኝና የንግድ ወይም የመንግሥት
ፍላጎቶችን ወይም የማቀናበር ሥራውን ደህንነት
በማይጣረስ መልኩ፤ የዳታ ተቆጣጣሪው ወይም
የዳታ አቀናባሪው ስለታሰበው ማቀናበር የዳታ
ባለቤቱን ዕይታ ሊጠይቅ ይችላል።
‹፵፰. ባለሥልጣኑን ፈቃድ መጠየቅና ማማከር
፩/ ማንኛውም የዳታ ተቆጣጣሪ ወይም የዳታ አቀናባሪ
የታሰበው የማቀናበር ሥራ ከአዋጁ ጋር የሚጣጣም
መሆኑን ለማረጋገጥና በተለይም ዳታ ተቆጣጣሪውም
ሆነ ዳታ አቀናባሪው የግል ዳታን ወደ ሶስተኛ ወገን
የሥልጣን ክልል ከማስተላለፍ ጋር በተያያዘ ተገቢውን
የጥበቃ እርምጃዎች መውስድ በማይቻልበት ጊዜ ፣
በዳታ ባለቤቱ ላይ የሚያደርሰውን ሥጋት ለመቀነስ
ከባለሥልጣኑ ቅድሚያ ፈቃድ ማግኘት አለበት።
፪/ የዳታ ተቆጣጣሪውም ሆነ የዳታ አቀናባሪው የግል
ዳታን ከማቀናበሩ በፊት የታቀደው የማቀናበር
ሥራ ከአዋጁ ጋር የማይጣረስ መሆኑን ለማረጋገጥና
በዳታ ባለቤቶች ላይ የሚያስከትለውን የሥጋት
ጫና ለመቀነስ :-
(ሀ) የዳታ ጥበቃ ተፅዕኖ ግምገማው የማቀናበሩ ሥራ
በባሕርዩ፣ በወሰኑ እና በዓላማው በከፍተኛ ደረጃ
ለሥጋት የተጋለጠ መሆኑን የሚያመላክት፣ ወይም
(ለ) ባለሥልጣኑ የማቀናበሩ ሥራ በባሕርዩ ፣ በወሰኑ
እና በዓላማው የዳታ ባለቤቶችን መብቶችና
ነጻነቶች በከፍተኛ ደረጃ ለሥጋት ያጋልጣል ብሎ
ሲገምት ባለሥልጣኑን አስቀድሞ ማማከር
አለበት።
፫/ ባለሥልጣኑ የታሰበው ማቀናበር ከአዋጁ ጋር
የማይጣጣም ሆኖ ካገኘው በተለይም ማቀናበሩ
ሊያስከትላቸው የሚችላቸው ሥጋቶች በበቂ ሁኔታ
ካልተለዩ እና ካልተቀነሱ ፣ የታቀደውን ማቀናበር
ይከለክላል ፤ ከአዋጁ ጋር አለው የተባለውን
አለመጣጣም በተመለከተ ሊወሰድ የሚገባውን ተገቢ
እርምጃምን እንደሆነ ያሳውቃል።
[[[
፬/ ባለሥልጣኑ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ ፪ ፊደል
ተራ
(ለ) መሠረት ቅድመ ምክክር
የሚያስፈልጋቸውን የማቀናበር ሥራዎች ዘርዝሮ
ለሕዝብ ማሳወቅ አለበት።
፭/ ዳታ ተቆጣጣሪው ወይም ዳታ አቀናባሪው የዳታ
ጥበቃ ተፅዕኖ ግምገማ ሰነድ እና ሌሎች ተጨማሪ
መረጃዎች በባለሥልጣኑ ሲጠየቅ በተጠየቀው
አግባብ ማቅረብ አለበት።