English
1/ The data controller shall take reasonable steps to
ensure the reliability of any employees of his
who have access to the personal data.
2/ Where processing of personal data is carried out
by a data processor on behalf of a data
controller, the data controller shall in order to
comply with this principle:
a) choose a data processor who provides
sufficient guarantees in respect of the technical
and organizational security measures
governing the processing to be carried out;
and
b) Take reasonable steps to ensure compliance
with those measures.
3/ Where processing of personal data is carried out
by a data processor on behalf of a data
controller, the data controller is not to be
regarded as complying with this principle
unless:
a) the processing is carried out under a contract
which is made or evidenced in writing;
b) the data processor is to act only on instructions
from the data controller; and
c) The contract requires the data processor to
comply with obligations equivalent to those
imposed on a data controller by the principle of
integrity and confidentiality.
4/ The data controller and data processor shall take
technical steps to ensure that any individual
acting under their authority and has access to
personal data does not process the personal data
except on instructions from the data controller,
unless he is required to do so by a law.
አማርኛ
፩/ ዳታ ተቆጣጣሪው በሥራቸው አጋጣሚ የግል ዳታ
የሚያገኙ ሠራተኞቹን ታማኝነት ለማረጋገጥ
አስፈላጊውን ቴክኒካዊ እርምጃ መውሰድ አለበት።
፪/ የግል ዳታ ማቀናበሩ በዳታ ተቆጣጣሪው ምትክ
በዳታ አቀናባሪው የሚከናወን ከሆነ፣ ይህን መርሕ
ለማክበር ዳታ ተቆጣጣሪው
ሀ) የሚከናወነውን የማቀናበር ሥራ ለመተግበር
አስፈላጊ የሆኑ የቴክኒክና ተቋማዊ የደህንነት
እርምጃዎች ያሉትና ለዚህም ማረጋገጫ ማቅረብ
የሚችል የዳታ አቀናባሪ መምረጥ ፣ እንደዚሁም
ለ) እነዚህ እርምጃዎች መተግበራቸውን ለማረጋገጥ
አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ መውሰድ፤ አለበት።
፫/ የግል ዳታ ማቀናበሩ በዳታ ተቆጣጣሪው ምትክ
ሆኖ በዳታ አቀናባሪው የተከናወነና :-
ሀ) የዳታ ማቀናበር ሥራው በፅሁፍ በተሰጠ ውል
ወይም በጽሑፍ በተደገፈ ሰነድ መከናወኑ
ማስረጃ ሊቀርብበት ካልቻለ፣
]
[[[[
ለ) ዳታ አቀናባሪው ከዳታ ተቆጣጣሪው በተሰጠው
ትዕዛዝ መሰረት ብቻ የማይሰራ ከሆነ፣ እና
ሐ) ለዳታ አቀናባሪው የተሰጠው ውል በዳታ ተቆጣጣሪው
ላይ የምሉዕነትና ምስጥራዊነት መርህ ከጣለበት
ግዴታ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ግዴታን በዳታ አቀናባሪው
ላይ የማይጥል ከሆነ፤ ዳታ ተቆጣጣሪው የምሉዕነትና
የምስጥራዊነት መርሕን እንዳከበረ አይቆጠርም።
፬/ ዳታ ተቆጣጣሪውና ዳታ አቀናባሪው በሥልጣናው
ሥር ያለና በሥራው አጋጣሚ የግል ዳታን
ማግኘት የሚችል ግለሰብ በሕግ ካልተገደደ በስተቀር
ከዳታ ተቆጣጣሪው ትዕዛዝ ውጪ የግል ዳታን
አለማቀናበሩን ለማረጋገጥ ተገቢውን የቴክኒክ እርምጃ
መውሰድ አለባቸው።
[፲፯. የቴክኒክ ደህንነት
፩/ ያልተፈቀደና ሕጋዊ ያልሆነ የግል ዳታ ማቀናበር
እንደዚሁም የግል ዳታ ድንገተኛ መጥፋትን ወይም
መውደምን ወይም መጎዳትን ለማስቀረት ተገቢ
የሆነ የቴክኒክና ተቋማዊ እርምጃዎች መወሰድ
አለበት።
፪/ የምሉዕነት እና የምስጥራዊነት መርሕን ለመተግበር
የቴክኖሎጂ እድገት ግምት ውስጥ መግባት
አለበት።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፪) ላይ የተቀመጠ
እርምጃ :-
ሀ) ካልተፈቀደ ወይም ሕጋዊ ካልሆነ
ማቀናበር፣ ወይም በድንገተኛ የዳታ መጥፋት፣
መውደም ወይም መጎዳት ምክንያት ሊደርስ
ከሚችል ጥፋት፣ እና
ለ) ጥበቃ ከሚደረግለት የዳታ ባህርይ ጋር
የሚመጣጠን የደህንነት ደረጃዎችን ማረጋገጥ
አለበት።
፬/ የቴክኖሎጂ የእድገት ደረጃን፣ የማቀናበሩን ባሕርይ፣
ወሰን፣ ዓውድ፣ እና ዓላማዎች፤ እንደዚሁም
በግለሰቦች ነጻነቶችና መብቶች ላይ ሊያመጣ
የሚችለውን የአደጋ ሥጋትና መጠን ከግምት
ውስጥ በማስገባት፤ የዳታ ተቆጣጣሪውና የዳታ
አቀናባሪው :-
ሀ) ግላዊ ዳታን በተመለከተ ስውር ስያሜ መጠቀምንና
ዳታውን መመስጠርን፤
ለ) የማቀናበሩን ሥርዓቶችና አገልግሎቶች ምስጢራዊነት፣
ምሉዑነት ፣ በቀላሉ የሚያገኘው መሆኑን እና አደጋ
የመቋቋም ብቃትን፤
ሐ) አካላዊና የቴክኒክ ተግዳሮቶች ሲያጋጥም የግል
ዳታን በፍጥነት እንዲያገኘውና ተደራሽ እንዲሆን
በማድረግ ወደ ነበረበት የመመለስ አቅም፤
እንደዚሁም
መ) የማቀናበሩን ደህንነት ለማረጋገጥና የቴክኒክና ተቋማዊ
እርምጃዎችን ውጤታማነት ለመገምገም የሚደረጉ
መደበኛ የሙከራ፣ የምዘናና የግምገማ
ሂደቶችን ጨምሮ ተገቢ የሆነ የቴክኒክና ተቋማዊ
እርምጃዎችን በመተግበር ለሥጋቱ ደረጃውን
የሚመጥን የደህንንነት ደረጃ ማረጋገጥ አለባቸው።
፭/ተገቢውን የደህንነት ደረጃ ለመመዘን በዋነኛነት
በማቀናበሩ ላይ ያሉ ሥጋቶች ከግምት ውስጥ
መግባት አለባቸው።
፮/ በማስተላለፍ ሂደት፣ በክምችት ወይም በሌላ ማንኛውም
መንገድ እየተቀናበረ ያለ የግል ዳታ ባልታሰበ ወይም
ሕጋዊ ባልሆነ አግባብ መውደም ፣ መጥፋት ፣ ይዘት
መቀየር፣ ይፋ መደረግ ፣ ተደራሽ መደረግ በዚህ አንቀጽ
ንዑስ አንቀጽ
(፭) መሠረት ሥጋት ተብሎ ይቆጠራል።