English
The Authority shall have the powers and functions
to:
1/ Ensure the enforcement of this Proclamation;
2/ Establish administriative structures it
considers appropriate to carry out its
responsibilities;
3/ Collect service fees for the services it provides
in accordance with a regulation to be issued to
implement this Proclamation;
4/ Promote public awareness on issues which fall
under this Proclamation;
5/ Ensure that personal data processed by data
controllers and data processors in compliance
with personal data processing principles ;
6/ Monitor the utilisation of of personal data and
sensitive personal data;
7/ Undertake research into, and monitor
developments in data processing and computer
technology to ensure that any adverse effects
of such developments on the privacy of
persons are minimized;
8/ By undertaking research on the interaction of
technology and the right to privacy, performs
knowledge creation and capacity building
works;
9/ Cooperate with supervisory authorities of
other countries;
10/ Make determination as to whether a third-
አማርኛ
ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት
ይኖሩታል፤
፩/ የዚህን አዋጅ ተፈጻሚነት ያረጋግጣል፤
፪/ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችለው አስፈላጊውን
አስተዳደራዊ መዋቅር ይፈጥራል፤
፫/ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ይህን አዋጅ ለማስፈጸም
በሚወጣ ደንብ መሠረት የአገልግሎት ክፍያ
ይሰበስባል፤
፬/ በዚህ አዋጅ ውስጥ በሚወድቁ ጉዳዮች ዙሪያ
ሕብረተሰቡን ግንዛቤ ያስጨብጣል፤
፭/ የዳታ ተቆጣጣሪዎችና የዳታ አቀናባሪዎች
የሚያቀናብሯቸው የግል ዳታ በዳታ ማቀናበር
መርሆዎች መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል፤
፮/ የግል ዳታና ጥንቃቄ የሚፈልግ የግል ዳታ
አጠቃቀምን በሚመለከት ቁጥጥር ያካሂዳል፤
፯/ የዳታ ማቀናበርና የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ
በግላዊነት መብት ላይ ያላቸው አሉታዊ ተፅዕኖ
አነስተኛ እንዲሆን በማድረግ ዙሪያ ጥናቶችን
ያጠናል፣ ዕድገቱን ይከታተላል፤
፰/ በቴክኖሎጂና በግላዊነት መብት መካከል ያለ
መስተጋብርን በማጥናት የዕውቀት ቋት የመፍጠርና
የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ይሠራል፤
፱/ ከሌሎች ሀገራት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን መሥሪያ
ቤቶች ጋር በትብብር ይሰራል፤
፲/ በሶስተኛ ወገን የሥልጣን ክልል ውስጥ ያሉ የግል
ዳታ ጥበቃ ሕጎች ከዚህ አዋጅና አዋጁን ተከትለው
በሚወጡ ሕጎች የተቀመጡ የግል ዳታ ጥበቃ
ደረጃዎች ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የጥበቃ ደረጃ
ያላቸው መሆኑን በተመለከተ ይወስናል፤
፲፩/ ቅሬታዎች ሲቀርቡለት አስተዳደራዊ እርምጃዎችን
ለመውሰድ የሚያስችለው ሕጋዊ የምርመራ
ሂደቶችንና መርሆዎችን በመከተል ይመረምራል፣
ለምርመራው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን
ይሰበስባል፤
፲፪/ የዳታ ተቆጣጣሪዎችንና የዳታ አቀናባሪዎችን
መዝገብ ይይዛል፣ ያስተዳድራል፤
፲፫/ የግል ዳታ ሊጠፋ ወይም ይዘቱ ሊቀየር ይችላል
ብሎ በበቂ ምክንያት ሲጠረጥር፣ የትራፊክ ዳታን
ጨምሮ ዳታውን ባለበት ሁኔታ ለማቆየት የእግድ
ትዕዛዝ እንዲሰጥ ይጠይቃል፤
፲፬/ ዳታ ተቆጣጣሪው ወይም ዳታ አቀናባሪው ይህንን
አዋጅ ተላልፏል፣ በመተላለፍ ላይ ነው ወይም
ሊተላለፍ ነው ብሎ በበቂ መረጃ ላይ ተመስርቶ
ሲያምን ይህን ለማስቆም ትዕዛዝ ይሰጣል፤
፲፭/ የአዋጁ ድንጋጌዎች ሲጣሱ አስተዳደራዊ
ቅጣቶችን ይወስናል፤
፲፮/ እንደ አስፈላጊነቱ ለፌደራል ወይም ለክልል አካል
ውክልና ይሰጣል፤
፲፯/ የዚህን አዋጅ አፈፃጸም በተመለከተ ለምክር ቤቱ
በዓመት ቢያንስ አንድ ጊዜ ሪፖርት ያቀርባል፤
፲፰/ በዚህ አዋጅ እና ይህንን አዋጅ መሠረት በማድረግ
በወጡ ሕጎች የተሰጡትን ተግባራቶችን፣
ኃላፊነቶችንና ግዴታዎችን ይፈጽማል።