English
1/ Personal data of a minor shall be processed in a
manner that protects and advances the rights
and best interests of the minor. The data
controller shall bear the burden of proof.
2/ The processing of a minor’s personal data shall
be lawful where and to the extent that:
a) consent is given or authorized by the
parent or guardian or tutor of the minor;
or
[[
b) Processing is necessary to the minor’s vitally
important interest.
3/ The data controller shall make reasonable efforts
to verify the age of the data subject and that
consent is given or authorized by the parent or
guardian of a minor, taking into consideration
available technology.
4/ Notwithstanding the provisions of Sub-Article
(1) –
(3) of this Article, the processing of personal
data of a minor for the purposes of marketing,
profiling, or merging of profiles shall not be
allowed.
አማርኛ
፩/ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን የግል ዳታ
ማቀናበር የልጁን መብትና ጥቅም በሚያስከብር
እና በሚያስቀድም መንገድ መከናወን አለበት ።
ይህን የማስረዳት ሸክም በዳታ ተቆጣጣሪው ላይ
ያርፋል።
፪/ ለአካል መጠን ያልደረሰ ልጅ የግል ዳታ
የማቀናበር ሂደት ሕጋዊ የሚሆነው
ሀ) ወላጆቹ ወይም አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ
ፈቃድ ወይም ሥልጣን የሰጠ ፣ ወይም
[[
ለ) ማቀናበሩ ለልጁ ወሳኝ ጥቅሞች አስፈላጊ ከሆነ
ነው።
፫/ የዳታ ተቆጣጣሪው በወቅቱ ያለውን ቴክኖሎጂ
ግምት ውስጥ በማስገባት የዳታ ባለቤቱን ዕድሜ፣
እንዲሁም ፈቃድ በልጁ ወላጅ ወይም ሞግዚት
መሰጠቱን ማረጋገጥ አለበት።
፬/ በዚህ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ
(፩) እስከ
(፫) የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን የግል
ዳታ ለማሻሻጥ ሥራ ፣ የግል ዳታ ባለቤት መገለጫ
ለማቀናበር ወይም የግል ዳታ ባለቤት መገለጫ ቅንብርን
ለማዋሃድ በማሰብ ማቀናበር የተከለከለ ነው።