Article text
1. ክልሎች፣ በክልል መስተዳድርና በድርጅት ተቀጣሪዎች ላይ የሥራ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ።
2. የመሬት መጠቀሚያ ክፍያ ይወስናሉ፣ ይሰበስባሉ።
3. በግል የሚያደርሱና በኅብረት ሥራ ማኅበራት በተደራጁ ገበሬዎች ላይ የእርሻ ሥራ ገቢ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ።
4. በክልሉ በሚገኙ ግለሰብ ነጋድዎች ላይ የንግድ ትርፍ ግብርና የሽያጭ ታክስ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ።
5. በክልሉ ውስጥ በውኃ ላይ ከሚደረግ ትራንስፖርት በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ።
6. በክልል መስተዳድር በግል ባለቤትነት ሥር ካሉ ቤቶችና ልሎች ንብረቶች በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ፣ በባለቤትነታቸው ሥር ባሉ
ቤቶችና ልሎች ንብረቶች ላይ ኪራይ ያስከፍላሉ።
7. በክልል መስተዳድር ባለቤትነት ሥር በሚገኙ የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ፣ የሥራ ግብር፣ የሽያጭና ኤክሳይስ ታክስ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ።
8. ብአንቀጽ 98 ንዑስ አንቀጽ 3 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በማዕድን ሥራዎች ላይ የማዕድን ገቢ ግብር፣ የሮያላቲና የመሬት ኪራይ ክፍያዎች
ይጥላሉ፣ይሰበስባሉ።
9. በክልል መስተዳድር አካላት ከሚሰጡ ፈቃዶችና አገልግሎቶች የሚመነጩ ክፍያዎች ይወስናሉ፣ ይሰበስባሉ።
10. ከደን የሚገኝ የሮያላቲ ክፍያ ይወስናሉ፣ ይሰበስባሉ።