Article text
1. ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል።
2. ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው። ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት
በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘድ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ
የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን የካትታል።
3. የኘሬስና የልሎች መገናኛ ብዙኃን፣ እንዲሁም የሥነ ጥበብ ፈጠራ ነጻነት ተረጋግጧል። የኘሬስ ነጻነት በተለይ የሚከተሉትን መብቶች ያጠኝልላል፣
ሀ/ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን፣
ለ/ የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን።
4. ለድሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሐሳቦችና አመለካከቶች በነጻ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ኘሬስ በተቋምነቱ የአሰራር
ነጻነትና የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ይደረግለታል።
5. በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ
እንዲመራ ይደረጋል።
6. እነዚህ መብቶች ገደብ ላጣልባቸው የሚችለው የሀሳብና መረጃ የማግኘት ነጻነት በአስተሳሰባዊ ይዘቱና ላያስከትል በሚችለው አስተሳሰባዊ ውጤት
ላገታ አይገባውም በሚል መርህ ላይ ተመስርተው በሚወጡ ሕጐች ብቻ ይሆናል።
የወጣቶችን ደህንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስም ለመጠበቅ ሲባል ሕጋዊ ገደቦች በነዚህ መብቶች ላይ ላደነገጉ ይችላሉ። የጦር ቅስቃሴዎች
እንዲሁም ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎች በህግ የሚከለከሉ ይሆናል።
7. ማንኛውም ዜጋ ከላይ በተጠቀሱት መብቶች አጠቃቀም ረገድ የሚጣሉ ሕጋዊ ገደቦችን ጥሶ ከተገኘ በሕግ ተጠያቂ ላሆን የችላል።
Article 6
ስለ ዜግነት
Choose an article to open it.