Article text
1. ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ/መሆኗ ይከበርለታል/ ይከበርላታል። ይህ መብት የሕዝብን ጥቅም ለመጠበቅ በልላ ሁኔታ
በሕግ እስካልተወሰነ ድረስ ንብረት የመያዝና በንብረት የመጠቀም ወይም የልሎችን
ዜጐች መብቶች እስካልተቃረነ ድረስ ንብረትን የመሸጥ የማውረስ ወይም በልላ መንገድ የማስተላለፍ መብቶችን ያካትታል።
2. ለዚህ አንቀጽ ዓላማ «የግል ንብረት» ማለት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም ሕጋዊ ሰውነት በሕግ የተሰጣቸው ኢትዮጵያዊ ማኅበራት ወይም
አግባብ በአላቸው ሁኔታዎች በሕግ በተለየ በጋራ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የተፈቀደላቸው
ማኅበረሰቦች በጉልበታቸው፣ በመፍጠር ችሎታቸው ወይም በካፒታላቸው ያፈሩት ተጨባጭ የሆነና የተጨባጭነት ጠባይ ሳይኖረው ዋጋ ያለው ውጤት
ነው።
3. የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ ነው። መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ
ብሕሮች፣ብሕረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው።
4. የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነጻ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው። አፈጻጸሙን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ
ይወጣል።
5. የኢትዮጵያ ዘላኖች ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነጻ የማግኘት፣የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው። ዝርዝር
አፈጻጸሙ በሕግ ይወሰናል።
6. የመሬት ባለቤትነት የኢትዮጵያ ብሕሮች፣ ብሕረሰቦችና ሕዝቦች መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት ለግል ባለሀብቶች በሕግ በሚወሰን ክፍያ
በመሬት የመጠቀም መብታቸውን ያስከብርላቸዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል።
7. ማንም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ፣ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙሉ መብት አለው።
ይህ መብት የመሸጥ፣ የመለወጥ፣ የማውረስ፣ የመሬት ተጠቃሚነቱ ሲቋረጥ ንብረቱን የማንሳት፣ ባለቤትነቱን የማዛወር ወይም የካሳ ክፍያ
የመጠየቅ መብትን ያካትታል። ዝርዝር አፈጻጸሙ በሕግ ይወሰናል።
8. የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መንግሥት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ በመክፈል የግል
ንብረትን ለመውሰድ ይችላል።
Article 6
ስለ ዜግነት
Choose an article to open it.