Article text
1. ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለ ገደብ
የተጠበቀ ነው።
2. ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ በቋንቋው የመናገር፣ የመጻፍ፣ቋንቋውን የማሳደግ እና ባሕሉን የመግለጽ፣ የማዳበርና
የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለው።
3. ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው። ይህ መብት ብሕሩ፣ ብሕረሰቡ፣ ሕዝቡ በሰፈረበት
መልክዓ ምድር ራሱን የሚያስተዳድርበት መንግሥታዊ ተቋማት የማቋቋም እንዲሁም በክልልና በፍድራል አስተዳደሮች ውስጥ ሚዛናዊ ውክልና
የማግኘት መብትን ያጠቃልላል።
4. የብሕር፣ ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት ከሥራ ላይ የሚውለው፤
ሀ/ የመገንጠል ጥያቄ በብሕር፣ በብሕረሰቡ ወይም በሕዝቡ የሕግ አውጪ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ የድምጽ ድጋፍ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥ፤
ለ/ የፍድራሉ መንግሥት የብሕር፣ የብሕረሰቡ ወይም የሕዝቡ ምክር ቤት ውሳኔ በደረሰው በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠያቂው ብሕር፣ብሕረሰብ
ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ ሲያደራጅ፤
ሐ/ የመገንጠሉ ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔው በአብላጫ ድምጽ ሲደገፍ፤
መ/ የፍድራሉ መንግሥት መገንጠሉን ለመረጠው ብሕር፣ ብሕረሰብ ወይም ሕዝብ ምክር ቤት ሥልጣኑን ሲያስረክብ፤
ሰ/ በሕግ በሚወሰነው መሰረት የንብረት ክፍፍል ሲደረግ ነው።
5. በዚህ ሕገ መንግሥት ውስጥ «ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸውን ባህርይ የሚያሳይ ማኅበረሰብ ነው። ሰፋ ያለ የጋራ
ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባሕል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ላግባቡት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልውና አለን
ብለው የሚያምኑ፣የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ ናቸው።
Article 6
ስለ ዜግነት
Choose an article to open it.