Article text
1. ወንጀል ፈጽመዋል በመባል የተያዙ ሰዎች የቀረበባቸው ክስና ምክንያቶቹ በዝርዝር ወዲያውኑ በሚገባቸው ቋንቋ እንዲነገራቸው መብት
አላቸው።
2. የተያዙ ሰዎች ላለመናገር መብት አላቸው፤ የሚሰጡት ማንኛውም ቃል ፍርድ ቤት በማስረጃነት ላቀርብባቸው እንደሚችል መረዳት በሚችሉት
ቋንቋ እንደተያዙ ወዲያውኑ ማስገንዘቢያ እንዲሰጣቸው መብት አላቸው።
3. የተያዙ ሰዎች በአርባ ስምንት ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው። ይህም ጊዜ ሰዎቹ ከተያዙበት ቦታ ወደ ፍርድ ቤት ለመምጣት
አግባብ ባለው ግምት የሚጠይቀውን ጊዜ አይጨምርም። ወዲያውኑ ፍርድ ቤት እንደቀረቡ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለመታሰር የሚያበቃ ምክንያት
ያለ መሆኑ ተለይቶ አንዲገለጽላቸው መብት አላቸው።
4. የያዛቸው የፖላስ መኮንን ወይም የሕግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ፣ ፍርድ ቤቱ የአካል
ነጻነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ላጣስ የማይችል መብት አላቸው። ሆኖም ፍትሕ
እንዳይጓደል ሁኔታው የሚጠይቅ ከሆነ ፍርድ ቤቱ የተያዘው ሰው በጥበቃ ሥር እንዲቆይ ለማዘዝ ወይም ምርመራ ለማካሄድ ተጨማሪ የምርመራ
ጊዜ ሲጠየቅ አስፈላጊ በሆነ መጠን ብቻ ላፈቅድ ይችላል። የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ጊዜ
ፍርድ ቤቱ ሲወስን ኃላፊ የሆኑት የሕግ አስከባሪ ባለሥልጣኖች ምርመራውን አጣርተው የተያዘው ሰው በተቻለ ፍጥነት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ያለውን
መብት የሚያስከብር መሆን አለበት።
5. የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ላቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም።
በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም።
6. የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት መብት አላቸው። ሆኖም በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ዋስትና ላለመቀበል ወይም በገደብ መፍታትን
ጨምሮ በቂ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል።
Article 6
ስለ ዜግነት
Choose an article to open it.