Article text
1. በፍድራልም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ነው።
2. በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ልላ ተጽዕኖ ነጻ ነው።
3. ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ። ከሕግ በስተቀር በልላ ሁኔታ አይመሩም።
4. ማንኛውም ዳኛ ከዚህ በታች በተመለከቱት ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር በሕግ ከተወሰነው የጡረታ ዕድሜ ከመድረሱ በፊት ከፈቃዱ ውጭ ከዳኝነት
ሥራው አይነሳም፤
ሀ/ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በዳኞች የዲሲኘላን ሕግ መሰረት ጥፋት ፈጽሟል ወይም ጉልህ የሆነ የሥራ ችሎታና ቅልጥፍና አንሶታል ብሎ ብሎ
ሲወስን፣ ወይም
ለ/ በህመም ምክንያት ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን አይችልም ብሎ ሲወስን፣ እና
ሐ/ የጉባኤው ውሳኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤቶች ከግማሽ በላይ ድምጽ ሲጸድቅ።
5. የማንኛውም ዳኛ የጡረታ መውጫ ጊዜ አይራዘምም።
6. የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍድራሉን መንግሥት የዳኝነት አካል የሚያስተዳድርበትን በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል፣
ሲፈቀድም በጀቱን ያስተዳድራል።
7. የክልል የዳኝነት አካሎች በጀት በየክልሉ ምክር ቤቶች ይመደባል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍድራሉን የከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ
ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን ደርበው ለሚሰሩት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችና የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የበጀት ማካካሻ ይሰጣል።