Article text
1. የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ ሕጐችና የተሰጡ ውሳኔዎች በሥራ መተርጐማቸውን ያረጋግጣል፣ መመሪያዎችን
ይሰጣል።
2. የሚኒስትሮችንና በቀጥታ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆኑ ልሎች የመንግሥት አካላትን አደረጃጀት ይወስናል፣ ሥራቸውን ያስተባብራል፣
ይመራል።
3. የፍድራሉን መንግሥት ዓመታዊ በጀት ያዘጋጃል፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል።
4. የገንዘብና የፋይናንስ ፖላሲን ተግባራዊነት ያረጋግጣል፣ ብሕራዊ ባንክን ያስተዳድራል፣ ገንዘብ ያትማል፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ይበደራል፣
የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ልውውጥን ይቆጣጠራል።
5. የፈጠራና የኪነ ጥበብ መብቶችን ያስጠብቃል።
6. የኢኮኖሚያዊ፣ የማኅበራዊና የልማት ፖላሲዎች እና ስትራቴጂዎችን ይነድፋል፣ ያስፈጽማል።
7. አንድ ወጥ የመለኪያ ደረጃዎችና የጊዜ ቀመር ያወጣል።
8. የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት ፖላሲ ያወጣል፣ የስፈጽማል።
9. ሕግና ሥርዓት መከበሩን ያረጋግጣል።
10. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፣ በዚህ ሕገ መንግሥት በተደነገገው የጊዜ ወሰን ውስጥ፣ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት አቅርቦ ያስጸድኝል።
11. የጦርነት ጉዳዮችን ጨምሮ በማናቸውም ጉዳዮች ላይ የሕግ ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል።
12. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰጡትን ልሎች ተግባሮች ያከናውናል።
13. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚሰጠው ሥልጣን መሰረት ደንቦችን ያወጣል።