Article text
1. ሴቶች ይህ ሕገ መንግሥት በአረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው።
2. ሴቶች በዚህ ሕገ መንግሥት በተደነገገው መሰረት በጋብቻ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው።
3. ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ
የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው። በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ
መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ
ትኩረት ለመስጠት ነው።
4. ሴቶች ከጐጂ ባሕል ተጽዕኖ የመላቀቅ መብታቸውን መንግሥት ማስከበር አለበት። ሴቶችን የሚጨቁኑ ወይም በአካላቸው ወይም በአዕምሮአቸው
ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ሕጐች፣ ወጐችና ልማዶች የተከለከሉ ናቸው።
5.
ሀ/ ሴቶች የወላድ ፈቃድ ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የማግኘት መብት አላቸው። የወላድ ፈቃድ ርዝመት ሴቷ የምትሰራውን ሥራ
ሁኔታ፣የሴቷን ጤንነት፣ የሕጻኑንና የቤተሰቡን ደህንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕግ ይወሰናል።
ለ/ የወላድ ፈቃድ በሕግ በሚወሰነው መሰረት ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የሚሰጥ የእርግዝና ፈቃድን ላጨምር ይችላል።
6. ሴቶች በብሕራዊ የልማት ፖላሲዎች ዕቅድና በኘሮጀክቶች ዝግጅትና አፈጻጸም፣በተለይ የሴቶችን ጥቅም በሚነኩ ኘሮጀክቶች ሐሳባቸውን በተሟላ
ሁኔታ እንዲሰጠ የመጠየቅ መብት አላቸው።
7. ሴቶች ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደር፣ የመቆጣጠር፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብት አላቸው። በተለይም መሬትን በመጠቀም፣
በማስተላለፍ፣ በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው። እንዲሁም ውርስን በሚመለከት በእኩልነት የመታየት መብት
አላቸው።
8. ሴቶች የቅጥር፣ የሥራ እድገት፣ የእኩል ክፍያና ጡረታን የማስተላለፍ እኩል መብት አላቸው።
9. ሴቶች በእርግዝናና በወላድ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመከላከልና ጤንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት፣
መረጃ እና አቅም የማግኘት መብት አላቸው።
Article 6
ስለ ዜግነት
Choose an article to open it.