Article text
1. ሕገ መንግሥቱን ይጠብቃል፤ ይከላከላል።
2. የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የልማት ፖላሲ፣ ስትራቴጂና ዕቅድ ያወጣል፤ ያስፈጽማል።
3. የጤና፣ የትምህርት፣ የባሕልና ታሪካዊ ቅርስ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሀገር አቀፍ መመዘኛዎችና መሰረታዊ የፖላሲ መለኪያዎችን ያወጣል፤
ያስፈጽማል።
4. የሀገሪቱን የፋይናንስ፣ የገንዘብ፣ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፖላሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ያወጣል፤ ያስፈጽማል።
5. የመሬት፣ የተፈጥሮ ሀብትና የታሪክ ቅርሶች አጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ ሕግ ያወጣል።
6. የሀገርና የሕዝብ የመከላከያና የደህንነት እንዲሁም የፍድራል መንግሥት የፖላስ ኃይል ያደራጃል፤ ይመራል።
7. ብሕራዊ ባንክን የስተዳድራል፤ ገንዘብ ያትማል፤ ይበደራል፤ የውጭ ምንዛሪና ገንዘብ ልውውጥን ይቆጣጠራል። ክልሎች ከውስጥ ምንጮች
ስለሚበደሩበት ሁኔታ ሕግና መመሪያ ያወጣል።
8. የውጭ ግንኙነት ፖላሲን ይወስናል፤ ፖላሲውንም ያስፈጽማል፤ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ይዋዋላል፤ ያጸድቃል።
9. የአየር፣ የባቡር፣ የባሕር መጓጓዣ፤ የፖስታና የቴልኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች እንደዚሁም ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ክልሎችን የሚያገናኙ አውራ
መንገዶችን ያስፋፋል፤ ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል።
10. ለፍድራሉ መንግሥት በተሰጡት የገቢ ምንጮች ክልል ግብርና ቀረጥ ይጥላል፤ያስተዳድራል፤ የፍድራል መንግሥት በጀት ያረቃል፤ ያጸድቃል፤
ያስተዳድራል።
11. ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክልሎችን የሚያስተሳስሩ ወይም ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ወንዞችና ሀይቆችን አጠቃቀም ይወስናል፤
ያስተዳድራል።
12. በክልሎች መካከል የሚደረግን የንግድ ግንኙነትና የውጭ ንግድን ይመራል፤ይቆጣጠራል።
13. በፍድራል መንግሥት ገንዘብ የተቋቋሙ አንድ ወይም ከአንድ ክልል በላይ የሚሸፍኑ የአገልግሎት ተቋሞችን ያስተዳድራል፤ ያስፋፋል።
14. ከክልል አቅም በላይ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ መሰረት የሀገሪቱን የመከላከያ ኃይል ያሰማራል።
15. በዚህ ሕገ መንግሥት የተረጋገጡትን የፖለቲካ መብቶች ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን እንዲሁም ምርጫን በሚመለከት
ሕጐች ያወጣል።
16. በሀገሪቱ በአጠኝላይም ሆነ በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፤ አዋጁን ያነሳል።
17. የዜግነት ጥያቄ ይወስናል።
18. የኢምግሬሽንና የስፖርት፤ ወደ ሀገር የመግቢያና፤ የመውጫ ጉዳዮችን፤ ስለስደተኞችና ስለ ፖለቲካ ጥገኝነት ይወስናል፤ ይመራል።
19. የፈጠራና የድርሰት መብቶችን ይፈቅዳል፤ ይጠብቃል።
20. አንድ ወጥ የመለኪያ ደረጃዎችና የጊዜ ቀመር ያወጣል።
21. የጦር መሳሪያ ስለመያዝ የጦር መሣሪያ ሕግ ያወጣል።
Article 6
ስለ ዜግነት
Choose an article to open it.