ይህ ሕገ መንግሥት ፍድራላዊና ድሞክራሲያዊ የመንግሥት አወቃቀር ይደነግጋል።በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ በሚል ስም ይጠራል።
የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን የፍድራሉን አባሎች ወሰን የሚያጠቃልል ሆኖ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት የተወሰነው ነው።
1. የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከላይ አረንጓድ፣ ከመሐል ቢጫ፣ ከታች ቀይ ሆኖበመሐሉ ብሕራዊ ዓርማ ይኖረዋል። ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም ይቀመጣሉ። 2. ከሰንደቅ ዓላማው ላይ የሚቀመጠው ብሕራዊ ዓርማ የኢትዮጵያ ብሕሮች፣ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች እና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንጸባርቅ ይሆናል። 3. የፍድራሉ አባሎች የየራሳቸው ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ ላኖራቸው ይችላል። ዝርዝሩን በየራሳቸው ምክር ቤት ይወስናሉ።
የኢትዮጵያ ብሕራዊ መዝሙር የሕገ መንግሥቱን ዓላማዎችና የኢትዮጵያ ሕዝቦች በድሞክራሲ ሥርዓት አብረው ለመኖር ያላቸውን እምነት፣ እንዲሁም የወደፊት የጋራ ዕድላቸውን የሚያንጸባርቅ ሆኖ በሕግ ይወሰናል።
1. ማናቸውም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በእኩልነት የመንግሥት እውቅና ይኖራቸዋል። 2. አማርኛ የፍድራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ይሆናል። 3. የፍድሬሽኑ አባሎች የየራሳቸውን የሥራ ቋንቋ በሕግ ይወስናሉ።
1. ወላጆቹ/ወላጆኟ ወይም ከወላጆቹ/ከወላጆኟ አንደኛቸው ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያዊት የሆነ/የሆነች የኢትዮጵያ ዜጋ ነው/ናት። 2. የውጭ ሀገር ዜጐች የኢትዮጵያ ዜግነት ላያገኙ ይችላሉ። 3. ዜግነትን በሚመለከት ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል።
በዚህ ሕገ መንግሥት ውስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ያካትታል።
1. የኢትዮጵያ ብሕሮች፣ ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣንባለቤቶች ናቸው። 2. ይህ ሕገ መንግሥት የሉዓላዊነታቸው መግለጫ ነው። 3. ሉዓላዊነታቸውም የሚገለጸው በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸውና በቀጥታ በሚያደርጉት ድሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካይነት ይሆናል።
1. ሕገ መንግሥቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ ነው። ማንኛውም ሕግ፣ ልማዳዊ አሰራር፣እንዲሁም የመንግሥት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም። 2. ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ልሎች ማኅበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው፣ ሕገ መንግሥቱን የማስከበርና ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው። 3. በዚህ ሕገ መንግሥት ከተደነገገው ውጭ በማናቸውም አኳኊን የመንግሥት ሥልጣን መያዝ የተከለከለ ነው። 4. ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ሕግ አካል ናቸው።
1. ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ፣ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው። 2. የዜጐች እና የሕዝቦች ሰብዓዊና ድሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ።
1. መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው። 2. መንግሥታዊ ሃይማኖት አይኖርም። 3. መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም። ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም።
1. የመንግሥት አሰራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት። 2. ማንኛውም ኃላፊና የሕዝብ ተመራጭ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ ይሆናል።ሕዝብ በመረጠው ተወካይ ላይ እምነት ባጣ ጊዜ ከቦታው ለማንሳት ይችላል።ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል።
1. በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፍድራል መንግሥትና የክልል ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካሎች በዚህ ምዕራፍ የተካተቱን ድንጋጌዎች የማክበርና የማስከበር ኃላፊነትና ግድታ አለባቸው። 2. በዚህ ምዕራፍ የተዘረዘሩት መሰረታዊ የመብቶችና የነጻነቶች ድንጋጌዎች ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋት፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ስምምነቶችና ዓለም አቀፍ ሰነዶች መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ ይተረጐማል።
መብት አለው።
ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው። ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም።
ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው።
1. በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ማንኛውም ሰው ወንድም ሆነ ሴት ነጻነቱን/ቷን አያጣም/አታጣም። 2. ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ላያዝ፣ ክስ ሳይቀርብበት ወይም ሳይፈረድበት ላታሰር አይችልም።
1. ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው። 2. ማንኛውም ሰው በባርነት ወይም በግድታ አገልጋይነት ላያዝ አይችልም።ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው። 3. ማንኛውም ሰው በኃይል ተገዶ ወይም ግድታ ለማሟላት ማንኛውንም ሥራ እንዲሰራ ማድረግ የተከለከለ ነው። 4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 «በኃይል ተገዶ ወይም ግድታን ለማሟላት»የሚለው ሐረግ የሚከተሉትን ሁኔታዎች አያካትትም፤ ሀ/ ማንኛውም እስረኛ በእስራት ላይ ባለበት ጊዜ በሕግ መሰረት አንዲሰራ የተወሰነውን ወይም በገደብ ከእስር በተለቀቀበት ጊዜ፣ የሚሰራውን ማንኛውም ሥራ፣ ለ/ ማንኛውም ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ሕላናው የማይፈቅድለት ሰው በምትክ የሚሰጠውን አገልግሎት፣ ሐ/ የማኅበረሰቡን ሕይወት ወይም ደህንነት የሚያሰጋ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ወይም አደጋ በሚያጋጥምበት ጊዜ የሚሰጥ ማንኛውም አገልግሎት፣ መ/ በሚመለከተው ሕዝብ ፈቃድ በአካባቢው የሚፈጸመውን ማንኛውንም ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ የልማት ሥራ።
1. ወንጀል ፈጽመዋል በመባል የተያዙ ሰዎች የቀረበባቸው ክስና ምክንያቶቹ በዝርዝር ወዲያውኑ በሚገባቸው ቋንቋ እንዲነገራቸው መብት አላቸው። 2. የተያዙ ሰዎች ላለመናገር መብት አላቸው፤ የሚሰጡት ማንኛውም ቃል ፍርድ ቤት በማስረጃነት ላቀርብባቸው እንደሚችል መረዳት በሚችሉት ቋንቋ እንደተያዙ ወዲያውኑ ማስገንዘቢያ እንዲሰጣቸው መብት አላቸው። 3. የተያዙ ሰዎች በአርባ ስምንት ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው። ይህም ጊዜ ሰዎቹ ከተያዙበት ቦታ ወደ ፍርድ ቤት ለመምጣት አግባብ ባለው ግምት የሚጠይቀውን ጊዜ አይጨምርም። ወዲያውኑ ፍርድ ቤት እንደቀረቡ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለመታሰር የሚያበቃ ምክንያት ያለ መሆኑ ተለይቶ አንዲገለጽላቸው መብት አላቸው። 4. የያዛቸው የፖላስ መኮንን ወይም የሕግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ፣ ፍርድ ቤቱ የአካል ነጻነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ላጣስ የማይችል መብት አላቸው። ሆኖም ፍትሕ እንዳይጓደል ሁኔታው የሚጠይቅ ከሆነ ፍርድ ቤቱ የተያዘው ሰው በጥበቃ ሥር እንዲቆይ ለማዘዝ ወይም ምርመራ ለማካሄድ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሲጠየቅ አስፈላጊ በሆነ መጠን ብቻ ላፈቅድ ይችላል። የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሲወስን ኃላፊ የሆኑት የሕግ አስከባሪ ባለሥልጣኖች ምርመራውን አጣርተው የተያዘው ሰው በተቻለ ፍጥነት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ያለውን መብት የሚያስከብር መሆን አለበት። 5. የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ላቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም። በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም። 6. የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት መብት አላቸው። ሆኖም በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ዋስትና ላለመቀበል ወይም በገደብ መፍታትን ጨምሮ በቂ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል።
1. የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በኃላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለሕዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመሰማት መብት አላቸው። ሆኖም የተከራካሪዎቹን የግል ሕይወት፣ የሕዝብን የሞራል ሁኔታና የሀገሪቱን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ብቻ ክርክሩ በዝግ ችሎት ላሰማ ይችላል። 2. ክሱ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዲነገራቸው እና ክሱን በጽሁፍ የማግኘት መብት አላቸው። 3. በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር፣በምስክርነት እንዲቀርቡም ያለመገደድ መብት አላቸው። 4. የቀረበባቸውን ማናቸውንም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ፣ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዲሁም ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዲሰሙላቸው የመጠየቅ መብት አላቸው። 5. በመረጡት የሕግ ጠበቃ የመወከል ወይም ጠበቃ ለማቆም አቅም በማጣታቸው ፍትሕ ላጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲያጋጥም ከመንግሥት ጠበቃ የማግኘት መብት አላቸው። 6. ክርክሩ በሚታይበት ፍርድ ቤት በተሰጠባቸው ትእዛዝ ወይም ፍርድ ላይ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት አላቸው። 7. የፍርዱ ሂደት በማይገባቸው ቋንቋ በሚካሄድበት ሁኔታ በመንግሥት ወጪ ክርክሩ እንዲተረጐምላቸው የመጠየቅ መብት አላቸው።
1. በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቁ ሁኔታዎች የመያዝ መብት አላቸው። 2. ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከሃይማኖት አማካሪዎቻቸው፣ ከሐኪሞቻቸው እና ከሕግ አማካሪዎቸው ጋር ለመገናኘትና እንዲጐበቿቸውም ዕድል የማግኘት መብት አላቸው።
1. ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት ድርጊት በተፈጸመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈጸሙ ወይም አለመፈጸሙ ወንጀል መሆኑ በሕግ የተደነገገ ካልሆነ በስተቀር ላቀጣ አይችልም። እንዲሁም ወንጀሉን በፈጸመበት ጊዜ ለወንጀሉ ተፈጻሚ ከነበረው የቅጣት ጣሪያ በላይ የከበደ ቅጣት በማንኛውም ሰው ላይ አይወሰንም። 2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ቢኖርም፣ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኊላ የወጣ ሕግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ከድርጊቱ በኊላ የወጣው ሕግ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።
ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕግና ሥነ ሥርዓት መሰረት ተከሶ የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፋተኛነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነጻ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም።
1. ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው። 2. ማንኛውም ሰው የራሱን ስብዕና ከልሎች ዜጐች መብቶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በነጻ የማሳደግ መብት አለው። 3. ማንኛውም ሰው በማንኛውም ስፍራ በሰብዓዊነቱ እውቅና የማግኘት መብት አለው።
ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል። በዚህ ረገድ በዘር፣በብሕር፣ ብሕረሰብ፣በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣በትውልድ ወይም በልላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው።
1. ማንኛውም ሰው የግል ሕይወቱ፣ ግላዊነቱ፣ የመከበር መብት አለው። ይህ መብት መኖሪያ ቤቱ፣ ሰውነቱና ንብረቱ ከመመርመር እንዲሁም በግል ይዞታው ያለ ንብረት ከመያዝ የመጠበቅ መብትን ያካትታል። 2. ማንኛውም ሰው በግል የሚጽፋቸውንና የሚጻጻፋቸው፣ በፖስታ የሚልካቸው ደብዳቤዎች፣ እንዲሁም በቴልፎን፣ በቴልኮሙኒኬሽንና በኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች አይደፈሩም። 3. የመንግሥት ባለሥለጣኖች እነዚህን መብቶች የማክበርና የማስከበር ግድታ አለባቸው። አስገዳጅ ሁኔታዎቸ ሲፈጠሩና ብሕራዊ ደህንነትን፣ የሕዝብን ሰላም፣ወንጀልን በመከላከል፣ ጤናንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ በመጠበቅ ወይም የልሎችን መብትና ነጻነት በማስከበር ዓላማዎች ላይ በተመሰረቱ ዝርዝር ሕጐች መሰረት ካልሆነ በስተቀር የእነዚህ መብቶች አጠቃቀም ላገደብ አይችለም።
1. ማንኛውም ሰው የማሰብ፣ የሕላና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው። ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፣ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከልሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣ የመተግበር፣ የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል። 2. በአንቀጽ 90 ንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው አንደተጠበቀ ሆኖ የሃይማኖት ተከታዮች ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችሐቸው የሃይማኖት ትምህርትና የአስተዳደር ተቋማት ማቋቋም ይችላሉ። 3. ማንኛውንም ሰው የሚፈልገውን እምነት ለመያዝ ያለውን ነጻነት በኃይል ወይም በልላ ሁኔታ በማስገደድ መገደብ ወይም መከልከል አይቻልም። 4. ወላጆችና ሕጋዊ ሞግዚቶች በእምነታቸው መሰረት የሃይማኖታቸውንና የመልካም ሥነ ምግባር ትምህርት በመስጠት ልጆቻቸውን የማሳደግ መብት አላቸው። 5. ሃይማኖትና እምነትን የመግለጽ መብት ላገደብ የሚችለው የሕዝብን ደህንነት፣ሰላምን፣ ጤናን፣ ትምህርትን፣ የሕዝብን የሞራል ሁኔታ፣ የልሎች ዜችን መሰረታዊ መብቶች፣ ነጻነቶች እና መንግስት ከሃይማኖት ነጻ መሆኑን ለማረጋረገጥ በሚወጡ ሕጐች ይሆናል።
1. ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በልሎች የኢትዮጵያ ሕጐች በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች፤የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር፣ ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም። በሕግ አውጪው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግሥት አካል ውሳኔዎች በምሕረት ወይም በይቅርታ አይታለፉም። 2. ከዚህ በላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተቀሱትን ወንጀሎች ፈጽመው የሞት ቅጣት ለተፈረደባቸው ሰዎች ርዕሰ ብሕሩ ቅጣቱን ወደ ዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ላያሻሽለው ይችላል። ድሞክራሲያዊ መብቶች
1. ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል። 2. ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው። ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘድ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን የካትታል። 3. የኘሬስና የልሎች መገናኛ ብዙኃን፣ እንዲሁም የሥነ ጥበብ ፈጠራ ነጻነት ተረጋግጧል። የኘሬስ ነጻነት በተለይ የሚከተሉትን መብቶች ያጠኝልላል፣ ሀ/ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን፣ ለ/ የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን። 4. ለድሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሐሳቦችና አመለካከቶች በነጻ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ኘሬስ በተቋምነቱ የአሰራር ነጻነትና የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ይደረግለታል። 5. በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል። 6. እነዚህ መብቶች ገደብ ላጣልባቸው የሚችለው የሀሳብና መረጃ የማግኘት ነጻነት በአስተሳሰባዊ ይዘቱና ላያስከትል በሚችለው አስተሳሰባዊ ውጤት ላገታ አይገባውም በሚል መርህ ላይ ተመስርተው በሚወጡ ሕጐች ብቻ ይሆናል። የወጣቶችን ደህንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስም ለመጠበቅ ሲባል ሕጋዊ ገደቦች በነዚህ መብቶች ላይ ላደነገጉ ይችላሉ። የጦር ቅስቃሴዎች እንዲሁም ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎች በህግ የሚከለከሉ ይሆናል። 7. ማንኛውም ዜጋ ከላይ በተጠቀሱት መብቶች አጠቃቀም ረገድ የሚጣሉ ሕጋዊ ገደቦችን ጥሶ ከተገኘ በሕግ ተጠያቂ ላሆን የችላል።
1. ማንኛውም ሰው ከልሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው። ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች በሕዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ ወይም በመካሕድ ላይ ያለ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምን፣ ድሞክራሲያዊ መብቶችንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ እንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሥርዓቶች ላደነገጉ ይችላሉ። 2. ይህ መብት የወጣቶችን ደህንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስምን ለመጠበቅ፣የጦርነት ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎችን ለመከላከል ሲባል በሚወጡ ሕጐች መሰረት ተጠያቂ ከመሆን አያድንም።
ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማኅበር የመደራጀት መብት አለው። ሆኖም አግባብያለውን ሕግ በመጣስ ወይም ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሕገ ወጥ መንገድ ለማፍረስ የተመሰረቱ ወይም የተጠቀሱትን ተግባራት የሚያራምዱ ድርጅቶች የተከለከሉ ይሆናሉ።
1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት፣እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነጻነት አለው። 2. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገሩ የመመለስ መብት አለው።
1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያዊት ከፈቃዱ/ከፈቃዷ ውጭ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን/ዜግነትዋን ላገፈፍ ወይም ልትገፈፍ አይችልም/አትችልም።ኢትዮጵያዊ / ኢትዮጵያዊት ዜጋ ከልላ ሀገር ዜጋ ጋር የሚፈጽመው/የምጽትፈጽመው ጋብቻ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን / ዜግነትዋን አያስቀርም። 2. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ የሚያስገኘውን መብት ጥበቃና ጥቅም የማግኘት መብት አለው። 3. ማንኛውም ዜጋ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን የመለወጥ መብት አለው። 4. ኢትዮጵያ ከአጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር በማይቃረን መንገድ በሚወጣ ሕግ እና በሚደነገግ ሥርዓት መሰረት የኢትዮጵያ ዜግነት ለውጭ ሀገር ሰዎች ላሰጥ ይችላል።
1. በሕግ ከተወሰነው የጋብቻ ዕድሜ የደረሱ ወንዶችና ሴቶች በዘር፣ በበሕር፣በብሕረሰብ ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግባቸው የማግባትና ቤተሰብ የመመስረት መብት አላቸው። በጋብቻ አፈጻጸም፣ በጋብቻው ዘመንና በፍቺ ጊዜ እኩል መብት አላቸው። በፍቺም ጊዜ የልጆችን መብትና ጥቅም እንዲከበር የሚያደርጉ ድንጋጌዎች ይደነገጋሉ። 2. ጋብቻ በተጋቢዎች ነጻና ሙሉ ፈኝድ ላይ ብቻ ይመሰረታል። 3. ቤተሰብ የኅብረተሰብ የተፈጥሮ መሰረታዊ መነሻ ነው። ከኅብረተሰብና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው። 4. በሕግ በተለይ በሚዘረዘረው መሰረት በሃይማኖት፣ በባሕል የሕግ ሥርዓቶች ላይ ተመስርትው ለሚፈጸሙ ጋብቻዎች እውቅና የሚሰጥ ሕግ ላወጣ ይችላል። 5. ይህ ሕገ መንግሥት የግል እና የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ፈቃድ በሃይማኖቶች ወይም በባሕሎች ሕጐች መሰረት መዳኘትን አይከለክልም። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል።
1. ሴቶች ይህ ሕገ መንግሥት በአረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው። 2. ሴቶች በዚህ ሕገ መንግሥት በተደነገገው መሰረት በጋብቻ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው። 3. ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው። በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው። 4. ሴቶች ከጐጂ ባሕል ተጽዕኖ የመላቀቅ መብታቸውን መንግሥት ማስከበር አለበት። ሴቶችን የሚጨቁኑ ወይም በአካላቸው ወይም በአዕምሮአቸው ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ሕጐች፣ ወጐችና ልማዶች የተከለከሉ ናቸው። 5. ሀ/ ሴቶች የወላድ ፈቃድ ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የማግኘት መብት አላቸው። የወላድ ፈቃድ ርዝመት ሴቷ የምትሰራውን ሥራ ሁኔታ፣የሴቷን ጤንነት፣ የሕጻኑንና የቤተሰቡን ደህንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕግ ይወሰናል። ለ/ የወላድ ፈቃድ በሕግ በሚወሰነው መሰረት ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር የሚሰጥ የእርግዝና ፈቃድን ላጨምር ይችላል። 6. ሴቶች በብሕራዊ የልማት ፖላሲዎች ዕቅድና በኘሮጀክቶች ዝግጅትና አፈጻጸም፣በተለይ የሴቶችን ጥቅም በሚነኩ ኘሮጀክቶች ሐሳባቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲሰጠ የመጠየቅ መብት አላቸው። 7. ሴቶች ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደር፣ የመቆጣጠር፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብት አላቸው። በተለይም መሬትን በመጠቀም፣ በማስተላለፍ፣ በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው። እንዲሁም ውርስን በሚመለከት በእኩልነት የመታየት መብት አላቸው። 8. ሴቶች የቅጥር፣ የሥራ እድገት፣ የእኩል ክፍያና ጡረታን የማስተላለፍ እኩል መብት አላቸው። 9. ሴቶች በእርግዝናና በወላድ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመከላከልና ጤንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት፣ መረጃ እና አቅም የማግኘት መብት አላቸው።
1. ማንኛውም ሕጻን የሚከተሉት መብቶች አሉት፤ ሀ/ በሕይወት የመኖር፣ ለ/ ስምና ዜግነት የማግኘት፣ ሐ/ ወላጆቹን ወይም በሕግ የማሳደግ መብት ያላቸውን ሰዎች የማወቅና የእነሱንም እንክብካቤ የማግኘት፣ መ/ ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፣ በትምህርት½ በጤናውና በደህንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎች እንዲሰራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ፣ ሰ/ በትምህርት ቤቶች ወይም በሕጻናት ማሳደጊያ ተቋሞች ውስጥ በአካሉ ከሚፈጸም ወይም ከጭካኔና ኢሰብዓዊ ከሆነ ቅጣት ነጻ የመሆን። 2. ሕጻናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜ በመንግሥታዊ ወይም በግል የበጐ አድራጐት ተቋሞች፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዳደር ባለሥልጣኖች ወይም በሕግ አውጪ አካላት የሕጻናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ አለበት። 3. ወጣት አጥፊዎች፣ በማረሚያ ወይም በመቋቋሚያ ተቋሞች የሚገኙ፣ በመንግሥት እርዳታ የሚያድጉ ወጣቶች፣ በመንግሥት ወይም በግል እጓለ ማውታን ተቋሞች ውስጥ የሚገኙ መጣቶች ከአወቂዎች ተለይተው መያዝ አለባቸው። 4. ከጋብቻ ውጭ የተወለዱ ሕጻናት በጋብቻ ከተወለዱ ሕጻናት ጋር እኩል መብት አላቸው። 5. መንግሥት ለእጓለ ማውታን ልዩ ጥበቃ ያደርግላቸዋል። በጉዲፈቻ የሚያድጉበትን ሥርዓት የሚያመቻቹና የሚያስፋፉ እንዲሁም ደህንነታቸውን ትምህርታቸውን የሚያራምዱ ተቋሞች እንዲመሰረቱ ያበረታታል።
1. ማንኛውም ሰው በፍርድ ላወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለልላ በሕግ የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው። 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን ውሳኔ ወይም ፍርድ፤ ሀ/ ማንኛውም ማኅበር የአባላቱን የጋራ ወይም የግል ጥቅም በመወከል፣ ለ/ ማንኛውም ቡድን ወይም ተመሳሳይ ጥቅም ያላቸውን ሰዎች የሚወክል ግለሰብ ወይም የቡድን አባል የመጠየቅና የማግኘት መብት አለው።
1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሕር፣ በብሕረሰብ፣ በጾታ፣በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በልላ አመለከካከት ወይም በልላ አቋም ላይ የተመሰረተ ልዩነት ሳይደረግበት የሚከተሉት መብቶች አሉት፤ ሀ/ በቀጥታ እና በነጻነት በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በሕዝብ ጉዳይ አስተዳደር የመሳተፍ፣ ለ/ ዕድማው 18 ዓመት ሲሞላ በሕግ መሰረት የመምረጥ ፣ ሐ/ በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ። ምርጫው ሁሉ አቀፍ፣ በሁሉም እኩልነት ላይ የተመሰረተና በሚስጥር ድምጽ አሰጣጥ መራጩ ፈቃዱን በነጻነት የሚገልጽበት ዋስትና የሚሰጥ መሆን አለበት። 2. በፖለቲካ ድርጅቶች፣ በሰራተኞች፣ በንግድ፣ በአሰሪዎችና በሙያ ማኅበራት ለተሳትፎ ድርጅቱ የሚጠይቀውን ጠቅላላና ልዩ የአባልነት መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ሰው በፍላጐቱ አባል የመሆን መብቱ የተከበረ መሆን አለበት። 3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 በተመለከቱት ድርጅቶች ውስጥ ለኃላፊነት ቦታዎች የሚካሄዱ ምርጫዎች ነጻና ድሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ይፈጸማሉ። 4. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 ድንጋጌዎች የሕዝብን ጥቅም ሰፋ ባለ ሁኔታ የሚነኩ እስከሆነ ድረስ በሕዝባዊ ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
1. ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው። 2. ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ በቋንቋው የመናገር፣ የመጻፍ፣ቋንቋውን የማሳደግ እና ባሕሉን የመግለጽ፣ የማዳበርና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለው። 3. ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው። ይህ መብት ብሕሩ፣ ብሕረሰቡ፣ ሕዝቡ በሰፈረበት መልክዓ ምድር ራሱን የሚያስተዳድርበት መንግሥታዊ ተቋማት የማቋቋም እንዲሁም በክልልና በፍድራል አስተዳደሮች ውስጥ ሚዛናዊ ውክልና የማግኘት መብትን ያጠቃልላል። 4. የብሕር፣ ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት ከሥራ ላይ የሚውለው፤ ሀ/ የመገንጠል ጥያቄ በብሕር፣ በብሕረሰቡ ወይም በሕዝቡ የሕግ አውጪ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ የድምጽ ድጋፍ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥ፤ ለ/ የፍድራሉ መንግሥት የብሕር፣ የብሕረሰቡ ወይም የሕዝቡ ምክር ቤት ውሳኔ በደረሰው በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠያቂው ብሕር፣ብሕረሰብ ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ ሲያደራጅ፤ ሐ/ የመገንጠሉ ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔው በአብላጫ ድምጽ ሲደገፍ፤ መ/ የፍድራሉ መንግሥት መገንጠሉን ለመረጠው ብሕር፣ ብሕረሰብ ወይም ሕዝብ ምክር ቤት ሥልጣኑን ሲያስረክብ፤ ሰ/ በሕግ በሚወሰነው መሰረት የንብረት ክፍፍል ሲደረግ ነው። 5. በዚህ ሕገ መንግሥት ውስጥ «ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸውን ባህርይ የሚያሳይ ማኅበረሰብ ነው። ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባሕል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ላግባቡት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ ናቸው።
1. ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ/መሆኗ ይከበርለታል/ ይከበርላታል። ይህ መብት የሕዝብን ጥቅም ለመጠበቅ በልላ ሁኔታ በሕግ እስካልተወሰነ ድረስ ንብረት የመያዝና በንብረት የመጠቀም ወይም የልሎችን ዜጐች መብቶች እስካልተቃረነ ድረስ ንብረትን የመሸጥ የማውረስ ወይም በልላ መንገድ የማስተላለፍ መብቶችን ያካትታል። 2. ለዚህ አንቀጽ ዓላማ «የግል ንብረት» ማለት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም ሕጋዊ ሰውነት በሕግ የተሰጣቸው ኢትዮጵያዊ ማኅበራት ወይም አግባብ በአላቸው ሁኔታዎች በሕግ በተለየ በጋራ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የተፈቀደላቸው ማኅበረሰቦች በጉልበታቸው፣ በመፍጠር ችሎታቸው ወይም በካፒታላቸው ያፈሩት ተጨባጭ የሆነና የተጨባጭነት ጠባይ ሳይኖረው ዋጋ ያለው ውጤት ነው። 3. የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ ነው። መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሕሮች፣ብሕረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው። 4. የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነጻ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው። አፈጻጸሙን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ ይወጣል። 5. የኢትዮጵያ ዘላኖች ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነጻ የማግኘት፣የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው። ዝርዝር አፈጻጸሙ በሕግ ይወሰናል። 6. የመሬት ባለቤትነት የኢትዮጵያ ብሕሮች፣ ብሕረሰቦችና ሕዝቦች መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት ለግል ባለሀብቶች በሕግ በሚወሰን ክፍያ በመሬት የመጠቀም መብታቸውን ያስከብርላቸዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። 7. ማንም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ፣ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙሉ መብት አለው። ይህ መብት የመሸጥ፣ የመለወጥ፣ የማውረስ፣ የመሬት ተጠቃሚነቱ ሲቋረጥ ንብረቱን የማንሳት፣ ባለቤትነቱን የማዛወር ወይም የካሳ ክፍያ የመጠየቅ መብትን ያካትታል። ዝርዝር አፈጻጸሙ በሕግ ይወሰናል። 8. የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መንግሥት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ በመክፈል የግል ንብረትን ለመውሰድ ይችላል።
1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ በማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራትና ለመተዳደሪያው የመረጠውን ሥራ የመሥራት መብት አለው። 2. ሁሉም ኢትዮጵያዊ መተዳደሪያውን፣ ሥራውንና ሙያውን የመምረጥ መብት አለው። 3. የኢትዮጵያ ዜጐች ሁሉ በመንግሥት ገንዘብ በሚካሄዱ ማኅበራዊ አገልግሎቶች በእኩልነት የመጠቀም መብት አላቸው። 4. መንግሥት የጤና፣ የትምህርትና ልሎች የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሀብት ይመድባል። 5. መንግሥት የአካል እና የአዕምሮ ጉዳተኞችን፣ አረጋዊያንንና ያለወላጅ ወይም ያለአሳዳጊ የቀሩ ሕጻናትን ለማቋቋምና ለመርዳት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም በፈቀደው ደረጃ እንክብካቤ ያደርጋል። 6. መንግሥት ለሥራ አጦችና ለችግረኞች ሥራ ለመፍጠር የሚያስችል ፖላሲ ይከተላል፤ እንዲሁም በሚያካሂደው የሥራ ዘርፍ ውስጥ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሥራ ኘሮግራሞችን ያወጣል፣ ኘሮጀክቶችን ያካሂዳል። 7. መንግሥት ዜጐች ጠቃሚ ሥራ የማግኘት ዕድላቸው እየሰፋ እንዲሄድ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳል። 8. ገበሬዎችና ዘላን ኢትዮጵውያን በየጊዜው እየተሻሻለ የሚሄድ ኑሮ ለመኖር የሚያስችላቸውና ለምርት ካደረጉት አስተዋጽኦ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ተገቢ ዋጋ ለምርት ውጤቶቻቸው የማግኘት መብት አላቸው። መንግሥት የኢኮኖሚ፣የማኅበራዊና የልማት ፖላሲዎችን በሚተልምበት ጊዜ በዚህ ዓላማ መመራት አለበት። 9. መንግሥት የባሕልና የታሪክ ቅርሶችን የመንከባከብና ለሥነ ጥበብና ለስፖርትመስፋፋት አስተዋጽኦ የማድረግ ኃላፊነት አለበት።
ሀ/ የፋብሪካና የአገልግሎት ሰራተኞች፣ ገበሬዎች፣ የእርሻ ሰራተኞች፣ ልሎች የገጠር ሰራተኞች፣ከተወሰነ ኃላፊነት ደረጃ በታች ያሉና የሥራ ጠባያቸው የሚፈቅድላቸ የመንግሥት ሰራተኞች የሥራና የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን ለማሻሻል በማኅበር የመደራጀት መብት አላቸው። ይህ መብት የሰራተኛ ማኅበራትና ልሎች ማኅበራትን የማደራጀት፣ ከአሰሪዎችና ጥቅማቸውን ከሚነኩ ልሎች ድርጅቶች ጋር የመደራደር መብትን ያካትታል። ለ/ በንዑስ አንቀጽ /ሀ/ የተመለከቱት የሰራተኛ ክፍሎች ሥራ ማቆምን ጨምሮ ቅሬታቸውን የማሰማት መብት አላቸው። ሐ/ በንዑስ አንቀጽ /ሀ/ እና /ለ/ መሰረት እውቅና ባገኙት መብቶች ለመቀም የሚችሉት የመንግሥት ሰራተኞች በሕግ ይወሰናሉ። መ/ ሴቶች ሰራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው። 2. ሰራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀኖች፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማና አደጋ የማያደረስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት አላቸው። 3. እነዚህን መብቶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚወጡ ሕጐች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት እውቅና ያገኙትን መብቶች ሳይቀንሱ የተጠቀሱት ዓይነት የሰራተኛ ማኅበራት ስለሚቋቋሙበትና የጋራ ድርድር ስለሚካሄድበት ሥርዓት ይደነግጋሉ።
1. የኢትዮጵያ ሕዝቦች በአጠቃላይም ሆነ በኢትዮጵያ ያሉ ብሕሮች፣ ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች በተናጠል የኑሮ ሁኔታቸውን የማሻሻልና የማያቋርጥ እድገት የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው። 2. ዜጐች በብሕራዊ ልማት የመሳተፍ በተለይም አባል የሆኑበትን ማኅበረሰብ የሚመለከቱ ፖላሲዎችና ኘሮጀክቶች ላይ ሐሳባቸውን እንዲሰጡ የመጠየቅ መብት አላቸው። 3. መንግሥት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገባቸው ስምምነቶችም ሆኑ የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች የኢትዮጵያን የማያቋርጥ እድገት መብት የሚያስከብሩ መሆን አለባቸው። 4. የልማት እንቅስቀሴ ዋና ዓላማ የዜጐችን እድገትና መሰረታዊ ፍላጐቶች ማሟላት ይሆናል።
1. ሁሉም ሰዎች ንoህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው። 2. መንግሥት በሚያካሂዳቸው ኘሮግራሞች ምክንያት የተፈናቀሉ ወይም ኑሮአቸው የተነካባቸው ሰዎች ሁሉ በመንግሥት በቂ እርዳታ ወደ ልላ አካባቢ መዘዋወርን ጨምሮ ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ወይም ልላ አማራጭ ማካካሻ የማግኘት መብት አላቸው።
የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ሥርዓተ መንግሥት ርላሜንታዊ ነው።
1. ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ የማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነው።
1. የትግራይ ክልል 2. የአፋር ክልል 3. የአማራ ክልል 4. የኦሮሚያ ክልል 5. የሱማል ክልል 6. የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል 7. የደቡብ ብሕሮች፣ ብሕረሰቦችና ሕዝቦች ክልል 8. የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል 9. የሐረሪ ሕዝብ ክልል 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከቱት ክልሎች ውስጥ የተካተቱ ብሕሮች፣ ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች በማንኛውም ጊዜ የየራሳቸውን ክልል የማቋቋም መብት አላቸው። 3. የማንኛውም ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ክልል የመመስረት መብት ሥራ ላይ የሚውለው፤ ሀ/ የክልል መመስረት ጥያቄው በብሕሩ፣ በብሕረሰቡ ወይም በሕዝቡ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥና ጥያቄው በጽሑፍ ለክልሉ ምክር ቤት ሲቀርብ፤ ለ/ ጥያቄው የቀረበለት የክልል ምክር ቤት ጥያቄው በደረሰው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠየቀው ብሕር፣ ብሕረሰብ ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ ሲያደራጅ፤ ሐ/ ክልል የመመስረት ጥያቄው በብሕሩ፣ በብሕረሰቡ ወይም ሕዝቡ ሕዝበ ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሲደገፍ፤ መ/ የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣኑን ለጠየቀው ብሕር፣ ብሕረሰብ ወይም ሕዝብ ሲያስረክብ፤ ሰ/ በሕዝበ ውሳኔ የሚፈጠረው አዲስ ክልል ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልገው በቀጥታ የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ አባል ሲሆን ነው። 4. የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ አባላት እኩል መብትና ሥልጣን አላቸው።
1. የክልሎች ወሰን በሚመለከት ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ክልሎች ስምምነት ይፈጸማል። የሚመለከታቸው ክልሎች መስማማት ካልቻሉ የፍድሬሽኑ ምክር ቤት የሕዝብን አሰፋፈርና ፍላጐት መሰረት በማድረግ ይወስናል። 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አስቀጽ 1 መሰረት የቀረበ ጉዳይ ከሁለት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በፍድሬሽኑ ምክር ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥበታል።
1. የፍድራሉ መንግሥት ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ ነው። 2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ይኖረዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። 3. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፍድራሉ መንግሥት ይሆናል። 4. የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በዚህ ሕገ መንግሥት በተደነገገው መሰረት በፍድራሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይወከላሉ። የኦሮሚያ ክልል፤ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮች በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል።
1. የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ በፍድራል መንግሥትና በክልሎች የተዋቀረ ነው። 2. የፍድራሉ መንግሥትና ክልሎች የሕግ አውጪነት፣ የሕግ አስፈጻሚነትና የዳኝነት ሥልጣን አላቸው። 3. የፍድራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የፍድራሉ መንግሥት የሕዝብተወካዮች ምክር ቤት ነው። ተጠሪነቱም ለሀገሪቱ ሕዝብ ነው። የክልል ከፍተኛ የሥልጣን አካል የክልሉ ምክር ቤት ነው፤ ተጠሪነቱም ለወከለው ክልል ሕዝብ ነው። 4. ክልሎች፤ በክልልነትና ክልሎች አስፈላጊ ሆነው በሚያገኙአቸው የአስተዳደር እርከኖች ይዋቀራሉ። ሕዝቡ በዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች በቀጥታ ይሳተፍ ዘንድ ለዝቅተኛ እርከኖች በቂ ሥልጣን ይሰጣል። 5. የክልል ምክር ቤት በክልሉ ሥልጣን ስር በሆኑ ጉዳዮች የክልሉ የሕግ አውጪ አካል ነው። ይህንን ሕገ መንግሥት መሰረት በማድረግ የክልሉን ሕገ መንግሥት ያዘጋጃል፣ ያጸድኝል፣ ያሻሽላል። 6. የክልል መስተዳድር የክልሉ ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካል ነው። 7. የክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ነው። 8. የፍድራሉ መንግሥትና የክልሎች ሥልጣን በዚህ ሕገ መንግሥት ተወስኗል። ለፍድራሉ መንግሥት የተሰጠው ሥልጣን በክልሎች መከበር አለበት። ለክልሎች የተሰጠው ሥልጣን በፍድራሉ መንግሥት መከበር አለበት። 9. የፍድራል መንግሥት በዚህ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 51 ከተሰጡት ሥልጣን እና ተግባሮች እንደአስፈላጊነቱ ለክልሎች በውክልና ላሰጥ ይችላል።
1. ሕገ መንግሥቱን ይጠብቃል፤ ይከላከላል። 2. የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የልማት ፖላሲ፣ ስትራቴጂና ዕቅድ ያወጣል፤ ያስፈጽማል። 3. የጤና፣ የትምህርት፣ የባሕልና ታሪካዊ ቅርስ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሀገር አቀፍ መመዘኛዎችና መሰረታዊ የፖላሲ መለኪያዎችን ያወጣል፤ ያስፈጽማል። 4. የሀገሪቱን የፋይናንስ፣ የገንዘብ፣ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፖላሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ያወጣል፤ ያስፈጽማል። 5. የመሬት፣ የተፈጥሮ ሀብትና የታሪክ ቅርሶች አጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ ሕግ ያወጣል። 6. የሀገርና የሕዝብ የመከላከያና የደህንነት እንዲሁም የፍድራል መንግሥት የፖላስ ኃይል ያደራጃል፤ ይመራል። 7. ብሕራዊ ባንክን የስተዳድራል፤ ገንዘብ ያትማል፤ ይበደራል፤ የውጭ ምንዛሪና ገንዘብ ልውውጥን ይቆጣጠራል። ክልሎች ከውስጥ ምንጮች ስለሚበደሩበት ሁኔታ ሕግና መመሪያ ያወጣል። 8. የውጭ ግንኙነት ፖላሲን ይወስናል፤ ፖላሲውንም ያስፈጽማል፤ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ይዋዋላል፤ ያጸድቃል። 9. የአየር፣ የባቡር፣ የባሕር መጓጓዣ፤ የፖስታና የቴልኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች እንደዚሁም ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ክልሎችን የሚያገናኙ አውራ መንገዶችን ያስፋፋል፤ ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል። 10. ለፍድራሉ መንግሥት በተሰጡት የገቢ ምንጮች ክልል ግብርና ቀረጥ ይጥላል፤ያስተዳድራል፤ የፍድራል መንግሥት በጀት ያረቃል፤ ያጸድቃል፤ ያስተዳድራል። 11. ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክልሎችን የሚያስተሳስሩ ወይም ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ወንዞችና ሀይቆችን አጠቃቀም ይወስናል፤ ያስተዳድራል። 12. በክልሎች መካከል የሚደረግን የንግድ ግንኙነትና የውጭ ንግድን ይመራል፤ይቆጣጠራል። 13. በፍድራል መንግሥት ገንዘብ የተቋቋሙ አንድ ወይም ከአንድ ክልል በላይ የሚሸፍኑ የአገልግሎት ተቋሞችን ያስተዳድራል፤ ያስፋፋል። 14. ከክልል አቅም በላይ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ መሰረት የሀገሪቱን የመከላከያ ኃይል ያሰማራል። 15. በዚህ ሕገ መንግሥት የተረጋገጡትን የፖለቲካ መብቶች ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን እንዲሁም ምርጫን በሚመለከት ሕጐች ያወጣል። 16. በሀገሪቱ በአጠኝላይም ሆነ በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፤ አዋጁን ያነሳል። 17. የዜግነት ጥያቄ ይወስናል። 18. የኢምግሬሽንና የስፖርት፤ ወደ ሀገር የመግቢያና፤ የመውጫ ጉዳዮችን፤ ስለስደተኞችና ስለ ፖለቲካ ጥገኝነት ይወስናል፤ ይመራል። 19. የፈጠራና የድርሰት መብቶችን ይፈቅዳል፤ ይጠብቃል። 20. አንድ ወጥ የመለኪያ ደረጃዎችና የጊዜ ቀመር ያወጣል። 21. የጦር መሳሪያ ስለመያዝ የጦር መሣሪያ ሕግ ያወጣል።
1. በሕገ መንግሥቱ ለፍድራሉ መንግሥት በተለይ ወይም ለፍድራሉ መንግሥትና ለክልሎች በጋራ በግልጽ ያልተሰጠ ሥልጣን የክልል ሥልጣን ይሆናል። 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የክልሎች ሥልጣንና ተግባር የሚከተሉትን ያጠቃልላል፤ ሀ/ ራስን በራስ ማስተዳደርን ዓላማ ያደረገ ክልላዊ መስተዳደር ያዋቅራል፤ የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ድሞክራሲያዊ ሥርዓት ይገነባል፤ ይህን ሕገ መንግሥት ይጠብቃል፤ ይከላከላል፤ ለ/ የክልል ሕገ መንግሥትና ልሎች ሕጐችን ያወጣል፤ ያስፈጽማል፤ ሐ/ የክልሉን የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የልማት ፖላሲ፣ ስትራቴጂና እቅድ ያወጣል፤ ያስፈጽማል፤ መ/ የፍድራሉ መንግሥት በሚያወጣው ሕግ መሰረት መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን ያስተዳድራል፤ ሰ/ ለክልሉ በተወሰነው የገቢ ምንጭ ክልል ግብርና ታክስ ይጥላል፤ ይሰበስባል፤ የክልሉን በጀት ያወጣል፤ ያስፈጽማል፤ ረ/ የክልሉን መስተዳድር ሰራተኞች አስተዳደር የሥራ ሁኔታዎች በተመለከተ ሕግ ያወጣል፤ ያስፈጽማል፤ ሆኖም ለአንድ የሥራ መደብ የሚያስፈልጉ የትምህርት የሥልጠናና የልምድ መመዘኛዎች ከአጠቃላይ የሀገሪቱ መመዘኛዎች ጋር የተቀራረቡ መሆናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርበታል። ሰ/ የክልሉን የፖላስ ኃይል ያደራጃል፤ ይመራል፤ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስብቃል።
የፍድራሉ መንግሥት ሁለት ምክር ቤቶች ይኖሩታል፤ እነዚህም የሕዝብተወካዮች ምክር ቤት እና የፍድሬሽን ምክር ቤት ናቸው።
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ሁሉ አቀፍ፣ ነጻ ፣ ቀጥተኛ፣ ትክክለኛ በሆነና ድምጽ በሚስጥር በሚሰጥበት ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ ይመረጣሉ። 2. የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከልሎች ተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ። የተለየ ውክልና ያሰፈልጋቸዋል ተብሎ የታመነባቸው አናሳ ብሕረሰቦች እና ሕዝቦች በምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ይሆናሉ። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። 3. የምክር ቤቱ አባላት ቁጥር የሕዝብ ብዛትንና በልዩ ትኩረት ውክልና የሚሰጣቸው አናሳ ብሕረሰቦችና ሕዝቦችን ቁጥር መሰረት በማድረግ 550 የማይበልጥ ሆኖ ከዚህ ውስጥ አናሳ ብሕረሰቦች 20 የማያንስ መቀመጫ ይኖራቸዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይደነግጋል። 4. የምክር ቤቱ አባላት የመላው ሕዝብ ተወካዮች ናቸው።ተገዢነታቸውም፣ ሀ/ ለሕገ መንግሥቱ፤ ለ/ ለሕዝቡ፤ እና ሐ/ ለሕላናቸው ብቻ ይሆናሉ። 5. ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል በምክር ቤቱ ውስጥ በሚሰጠው ድምጽ ወይም አስተያየት ምክንያት አይከሰስም። አስተዳደራዊ እርምጃ አይወሰድበትም። 6. ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካለተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፤ በወንጀልም አይከሰስም። 7. ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል የመረጠው ሕዝብ አመኔታ ባጣበት ጊዜ በሕግ መሰረት ከምክር ቤት አባልነቱ ይወገዳል።
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት ለፍድራሉ መንግሥት በተሰጠው ሥልጣን ክልል ሕጐችን ያወጣል። 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ሕግ ያወጣል፤ ሀ/ የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት፤ እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ ወይም ከአንድ ክልል በላይ የሚያስተሳስሩ ወንዞችና ሐይቆች አጠቃቀምን በተመለከተ፤ ለ/ በክልሎች መካከል የሚኖረውን የንግድ ልውውጥ፤ እንዲሁም የውጭ ንግድ ግንኙነትን በተመለከተ፤ ሐ/ የአየር፣ የባቡርና የባሕር መጓጓዣ፤ የፖስታና የቴልኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን እንዲሁም ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ክልሎችን የሚያገናኙ አውራ መንገዶችን በተመለከተ፤ መ/ በዚህ ሕገ መንግሥት የተደነገጉትን የፖለቲካ መብቶች አፈጻጸምን እንዲሁም ምርጫን በተመለከተ፤ ሰ/ የዜግነት መብትን፤ የኢምግሬሽን፤ የስፖርትን፤ ወደ ሀገር የመግቢያና የመውጫ ጉዳዮችን እንዲሁም የስደተኞችና የፖለቲካ ጥገኝነት ጉዳዮችን በተመለከተ፤ ረ/ አንድ ወጥ የመጠን መለኪያ ደረጃና የጊዜ ቀመርን በተመለከተ፤ ሰ/ የፈጠራና የሥነ ጥበብ መብቶችን በተመለከተ፤ ሸ/ የጦር መሣሪያ መያዝን በተመለከተ። 3. የሰራተኛ ጉዳይ ሕግ ያወጣል። 4. የንግድ ሕግ /ኮድ/ ያወጣል። 5. የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ያወጣል። ይህ እንደተጠበቀ ሁኖ ክልሎች የፍድራሉ መንግሥት የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በግልጽ ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ሕግ የማውጣት ሥልጣን ይኖራቸዋል። 6. አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ሲባል በፍድራል መንግሥት ሕግ እንዲወጣላቸው የሚያስገድዱ ለመሆናቸው በፍድሬሽኑ ምክር ቤት የታመነባቸው የፍትሐብሕር ሕጐችን ያወጣል። 7. የፍድራል መንግሥት፤ የሀገርና የሕዝብ መከላከያ፤ የደህንነትና የፖላስ ኃይል አደረጃጀት ይወስናል። በሥራ አፈጻጸም ረገድ የሚታዩ መሰረታዊ የዜጐችን ሰብዓዊ መብቶችና የሀገርን ደህንነት የሚነኩ ጉዳዮች ሲከሰቱ ያጣራል፤ አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል። 8. በአንቀጽ 93 በተመለከተው መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፤ የሕግ አስፈጻሚው የሚያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተመልክቶ ይወስናል። 9. የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያቀርብለት የሕግ ረቂቅ መሰረት የጦርነት አዋጅ ያውጃል። 10. የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የልማት ፖላሲዎችንና ስትራቴጂዎችን፤ የፋይናንስና የገንዘብ ፖላሲን ያጸድቃል፤ ገንዘብን፤ የብሕራዊ ባንክ አስተዳደር፤ የውጭ ምንዛሪንና ልውውጥን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ ያወጣል። 11. ለፍድራል መንግሥት በተከለለው የገቢ ምንጭ ክልል ግብርና ታክስ ይጥላል።የፍድራል መንግሥት በጀት ያጸድቃል። 12. የሕግ አስፈጻሚው አካል የሚዋዋላቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ያጸድቃል። 13. የፍድራል መንግሥት ፍርድ ቤት ዳኞችን፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን፤የኮሚሽነሮችን፤ የዋናው ኦዲተርን እንዲሁም የልሎች ሹመታቸው በምክር ቤቱ መጽደቅ ያለበትን ባለሥለጣኖች ሹመት ያጸድቃል። 14. የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያቋቁማል፤ ሥልጣንና ተግባሩን በሕግ ይወስናል። 15. የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋምን ያቋቁማል፤ ተቋሙን የሚመሩ አባላትን ይመርጣል፤ይሰይማል። ሥልጣንና ተግባሩን በሕግ ይወስናል። 16. በማንኛውም ክልል ሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱና ክልሉ ድርጊቱን ማቆም ሳይችል ሲቀር፤ በራሱ አነሳሽነትና ያለክልሉ ፈቃድ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ለፍድሬሽኑ ምክር ቤትና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ጥያቄ ያቀርባል፤ በተደረሰበት ውሳኔ መሰረት ለክልሉ ምክር ቤት መመሪያ ይሰጣል። 17. ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ልሎች የፍድራሉ መንግሥት ባለሥለጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈጻሚውን አካል አሰራር የመመርመር ሥልጣን አለው። 18. ለሕግ አስፈጻሚው አካል በተሰጠ ማንኛውም ሥልጣን ላይ የምክር ቤቱ አባላት በአንድ ሦስተኛ ድምፅ ሲጠይቁ ምክር ቤቱ ይወያያል። ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ የመመካከርና አስፈላጊ መስሎ የታየውን እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን አለው። 19. ምክር ቤቱን የሚመሩ አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ ይመርጣል፤ ለምክር ቤቱ ሥራ የሚያስፈልጉትን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ያዋቅራል።
በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጣምራ ድርጅቶች የፍድራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል ያደራጃል/ያደራጃሉ፤ ይመራል/ይመራሉ።
ምክር ቤቱ መክሮ የተስማማበት ሕግ ለሀገሪቱ ኘሬዚዳንት ለፊርማ ይቀርባል፤ ኘሬዚዳንቱ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ይፈርማል። ኘሬዚዳንቱ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ካልፈረመ ሕጉ በሥራ ላይ ይውላል።
1. ከምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይኖራል። 2. የምክር ቤቱ የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ ሰላሳ ነው፤ በመካከሉም ምክር ቤቱ በሚወስነው ጊዜ የአንድ ወር ዕረፍት ይኖረዋል። 3. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመረጠው ለአምስት ዓመታት ነው፤ የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ይጠናቀቃል። 4. ምክር ቤቱ ዕረፍት ላይ በሚሆንበት ጊዜ የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ስብሰባ ላጠራ ይችላል። ከምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ ስብሰባ እንዲጠራ ከጠየቁ አፈ-ጉባኤው ስብሰባ የመጥራት ግድታ አለበት። 5. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባዎች በግልጽ ይካሄዳሉ፤ ሆኖም በምክር ቤቱ አባላት ወይም በፍድራል የሕግ አስፈጻሚ አካል በዝግ ስብሰባ እንዲደረግ ከተየቀና ከምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ ከደገፉት ዝግ ስብሰባ ላደረግ ይችላል።
1. በዚህ ሕገ መንግሥት በግልጽ በተለይ ካልተደነገገ በስተቀር ማናቸውም ውሳኔዎች የሚተላለፉት በምክር ቤቱ አባላት የአብላጫ ድምጽ ነው። 2. ምክር ቤቱ ስለ አሰራሩና ስለ ሕግ አወጣጡ ሂደት ደንቦችን ያወጣል።
1. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመኑ ከማለቁ በፊት አዲስ ምርጫ ለማካሄድ በምክር ቤቱ ፈቃድ ምክር ቤቱ እንዲበተን ለማድረግ ይችላል። 2. በጣምራ የመንግሥት ሥልጣን የያዙ የፖለቲካ ድርጅቶች ጣምራነታቸው ፈርሶ በምክር ቤቱ የነበራቸውን አብላጫነት ያጡ እንደሆነ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተበትኖ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ልላ ጣምራ መንግሥት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለመመስረት እንዲቻል ኘሬዚዳንቱ የፖለቲካ ድርጅቶችን ይጋብዛል። የፖለቲካ ድርጅቶቹ አዲስ መንግሥት ለመፍር ወይም የነበረውን ጣምራነት ለመቀጠል ካልቻሉ ምክር ቤቱ ተበትኖ አዲስ ምርጫ ይደረጋል። 3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ወይም 2 መሰረት ምክር ቤቱ የተበተነ እንደሆነ ከስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አዲስ ምርጫ መደረግ አለበት። 4. ምርጫው በተጠናቀቀ በሰላሳ ቀናት ውስጥ አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራውን ይጀምራል። 5. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተበተነ በኊላ ሀገሪቱን የሚወራው ሥልጣን ይዞ የነበረው የፖለቲካ ድርጅት ወይም የፖለቲካ ድርጅቶች ጣምራ የዕለት ተዕለት የመንግሥት ሥራ ከማከናወንና ምርጫ ከማካሕድ በስተቀር አዲስ አዋጆችን፣ ደንቦችንና ድንጋጌዎችን ማውጣት ወይም ነባር ሕጐችን ማሻርና ማሻሻል አይችልም።
1. የፍድሬሽን ምክር ቤት በፍድራሉ መንግሥት አባል ክልሎች የሚገኙ ብሕሮች፣ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች የሚልኩዋቸው አባላት የሚወከሉበት ምክር ቤት ነው። 2. እያንዳንዱ ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ ቢያንስ አንድ ተወካይ ይኖረዋል፤በተጨማሪም የብሕር ወይም ብሕረሰቡ አንድ ሚላዮን ሕዝብ አንድ ተጨማሪ ወኪል ይኖረዋል። 3. የፍድሬሽን ምክር ቤት አባላት በክልል ምክር ቤቶች ይመረጣሉ፤ የክልል ምክር ቤቶች በራሳቸው ወይም በቀጥታ በሕዝብ እንዲመረጡ በማድረግ የፍድሬሽን ምክር ቤት አባል እንዲወከሉ ያደርጋሉ።
1. ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥቱን የመተርጐም ሥልጣን ይኖረዋል። 2. የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤን ያደራጃል። 3. የብሕሮች፣ ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠን መብትን በተመለከተ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ይወሰናል። 4. በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው የሕዝቦች እኩልነትና በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር ያደርጋል። 5. ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በጣምራ የተሰጡትን ሥልጣኖች ያከናውናል። 6. በክልሎች መካከል ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሄ ይፈልጋል። 7. የክልሎችና የፍድራሉ መንግሥት የጋራ ተብለው የተመደቡ ገቢዎች በሁለቱ መካከል የሚከፋፈሉበትን፤ እንዲሁም የፍድራሉ መንግሥት ለክልሎች ድጐማ የሚሰጥበትን ቀመር ይወስናል። 8. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕግ ላወጣላቸው የሚገቡ የፍትሐብሕር ጉዳዮችን ይለያል። 9. ማንኛውም ክልል ይህን ሕገ መንግሥት በመጣስ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፍድራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል። 10. የምክር ቤቱን የተለያዩ ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ያቋቁማል። 11. ምክር ቤቱ የራሱን አፈጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ ይመርጣል፤ የራሱን የሥራ አፈጻጸምና የውስጥ አስተዳደር ደንብ ያወጣል።
1. ማንኛውም የፍድሬሽኑ ምክር ቤት አባል በማናቸውም የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ በሚሰጠው አስተያየት ወይም ድምጽ ምክንያት አይከሰስም፤ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወሰድበትም። 2. ማንኛውም የፍድሬሽኑ ምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያይዝም፤ በወንጀልም አይከሰስም።
1. የፍድሬሽኑ ምክር ቤት ምልዓተ ጉባኤ የሚኖረው ከአባላቱ ሁለት ሦስተኛው የተገኙ እንደሆነ ነው። ማናቸውም ውሳኔ የሚያልፈው ስብሰባ ላይ ከተገኙት የምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ ድምጽ ሲደገፍ ብቻ ነው። 2. አባላት ድምጽ መስጠት የሚችሉት በአካል ሲገኙ ብቻ ነው።
የፍድሬሽኑ ምክር ቤት በጀቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ያስወስናል።
1. የፍድሬሽኑ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የምክር ቤቱን ስብሰባዎች ይመራል። 2. ምክር ቤቱን በመወከል ጠቅላላ የአስተዳደር ሥራዎችን ይመራል። 3. ምክር ቤቱ በአባሎቹ ላይ የወሰነውን የዲስኘላን እርምጃ ያስፈጽማል።
1. የፍድሬሽኑ ምክር ቤት ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰበሰባል። 2. የፍድሬሽኑ ምክር ቤት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል።
ማንኛውም ሰው በአንድ ጊዜ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፍድሬሽኑ ምክር ቤት አባል ላሆን አይችልም።
ኘሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ርዕሰ ብሕር ነው።
1. ለኘሬዚዳንትነት እጩ የማቅረብ ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። 2. የቀረበው እጩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በፍድሬሽኑ ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ከተደገፈ ኘሬዚዳንት ይሆናል። 3. የምክር ቤት አባል ኘሬዚዳንት ሆኖ ከተመረጠ የተወከለበትን ምክር ቤት ወንበር ይለቃል። 4. የኘሬዚዳንቱ የሥራ ዘመን ስድስት ዓመት ይሆናል። አንድ ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ ለኘሬዚዳንትነት ላመረጥ አይችል። 5. የሪፐብላኩ ኘሬዚዳንት ምርጫ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ከጸደቀ በኊላ ሥራውን ከመጀመሩ በፊት የጋራ ስብሰባው በሚወስነው ጊዜ ስብሰባው ፊት ለሕገ መንግሥቱና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ያለውን ታማኝነት በሚቀጥሉት ቃላት ይገልጻል። «እኔ ....... በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ኘሬዚዳንት በመሆን ሥራዬን ስጀምር የተጣለብኝን ከፍተኛ ኃላፊነት በታማኝነት ለመፈጸም ቃል እገባለሁ።»
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፍድሬሽኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰበባ ይከፍታል። 2. በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቃቸው ሕጐችና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ ያውጃል። 3. ሀገሪቷን በውጭ ሀገሮች የሚወክሉትን አምባሳደሮችና ልሎች መልክተኞች በጠ ቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ይሾማል። 4. የውጭ ሀገር አምሳደሮችንና የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ይቀበላል። 5. በሕግ መሰረት ኒሻኖችና ሽልማቶችን ይሰጣል። 6. በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕግ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጐችን ይሰጣል። 7. በሕግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል።
1. የኢትዮጵያ ፍድራል መንግሥት ከፍተኛ የአስፈጻሚነት ሥልጣን የተሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው። 2. ጠቅላይ ሚኒስትሩና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪዎች ናቸው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት በመንግሥት ተግባራቸው በጋራ ለሚሰጡት ውሳኔ የጋራ ኃላፊነት አለባቸው። 3. በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት በልላ አኳኊን ካልተወሰነ በስተቀር የጠቅላይሚኒስትሩ የሥራ ዘመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ነው።
1. ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል ይመረጣል። 2. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው የፖለቲካ ድርጅት ወይም ያገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች የመንግሥት ሥልጣን ይረከባል/ይረከባሉ።
1. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነው። 2. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባሎችን ከሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ወይም ለሥራው ብቃት ካላቸው ልሎች ግለሰቦች መካከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርቦ ሹመታቸውን ያጸድቃል። 3. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣቸው ሕጐች፣ ፖላሲዎች፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል። 4. የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይወክላል። 5. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣቸውን ፖላሲዎች፣ ደንቦች መመሪያዎችና ውሳኔዎች ተፈጻሚነት ይከተተላል። 6. የሀገሪቱን የውጭ ፖላሲ በበላይነት ያስፈጽማል። 7. ኮሚሽነሮችን፣ የማዕከላዊ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንትና ምክትል ኘሬዚዳንትን እና ዋና ኦዲተርን መርጦ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመታቸውን ያጸድቃል። 8. የመስተዳድሩን ሥራ አፈጻጸምና ብኝት ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ የሆኑ የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል። 9. በዚሀ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እና 7 ከተዘረዘሩት ውጭ የሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሲቪል ሹመቶችን ይሰጣል። 10. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው ሕግ ወይም በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት ኒሻኖችንና ሽልማቶችን ለኘሬዚዳንቱ አቅርቦ ያሰጣል። 11. ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ፣ በመንግሥት ስለተከናወኑ ተግባራትና ስለወደፊት እቅዶች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየወቅቱ ሪፖረት ያቀርባል። 12. በዚህ ሕገ መንግሥትና በልሎች ሕጐች የተሰጡትን ልሎች ተግባሮች ያከናውናል። 13. ሕገ መንግሥቱን ያከብራል፤ የስከበራል።
1. ምክትል ጠቅላይሚኒስትሩ፣ ሀ/ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፤ ለ/ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖርበት ጊዜ ተክቶት ይሰራል። 2. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል።
1. የሚኒስትሮች ምክር ቤት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር፣ ሚኒስትሮችና በሕግ በሚወሰን መሰረት ልሎች አባሎች የሚገኙበት ምክር ቤት ነው። 2. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒሰትሩ ነው። 3. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለሚወስነው ውሳኔ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ ነው።
1. የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ ሕጐችና የተሰጡ ውሳኔዎች በሥራ መተርጐማቸውን ያረጋግጣል፣ መመሪያዎችን ይሰጣል። 2. የሚኒስትሮችንና በቀጥታ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆኑ ልሎች የመንግሥት አካላትን አደረጃጀት ይወስናል፣ ሥራቸውን ያስተባብራል፣ ይመራል። 3. የፍድራሉን መንግሥት ዓመታዊ በጀት ያዘጋጃል፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል። 4. የገንዘብና የፋይናንስ ፖላሲን ተግባራዊነት ያረጋግጣል፣ ብሕራዊ ባንክን ያስተዳድራል፣ ገንዘብ ያትማል፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ይበደራል፣ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ልውውጥን ይቆጣጠራል። 5. የፈጠራና የኪነ ጥበብ መብቶችን ያስጠብቃል። 6. የኢኮኖሚያዊ፣ የማኅበራዊና የልማት ፖላሲዎች እና ስትራቴጂዎችን ይነድፋል፣ ያስፈጽማል። 7. አንድ ወጥ የመለኪያ ደረጃዎችና የጊዜ ቀመር ያወጣል። 8. የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት ፖላሲ ያወጣል፣ የስፈጽማል። 9. ሕግና ሥርዓት መከበሩን ያረጋግጣል። 10. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፣ በዚህ ሕገ መንግሥት በተደነገገው የጊዜ ወሰን ውስጥ፣ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስጸድኝል። 11. የጦርነት ጉዳዮችን ጨምሮ በማናቸውም ጉዳዮች ላይ የሕግ ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል። 12. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰጡትን ልሎች ተግባሮች ያከናውናል። 13. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚሰጠው ሥልጣን መሰረት ደንቦችን ያወጣል።
1. ነጻ የዳኝነት አካል በዚህ ሕገ መንግሥት ተቋቁሟል። 2. የፍድራሉ መንግሥት ከፍተኛ የዳኝነት አካል የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሆናል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲደራጅ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ላወስን ይችላል። ጉዳዩ በዚህ አኳኊን ካልተወሰነ የፍድራል ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ለክልል ፍርድ ቤቶች ተሰጥቷል። 3. ክልሎች፣ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች፣ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችና የክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ይኖራቸዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይዋሰናል። 4. የዳኝነት ሥልጣንን ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ወይም በሕግ የመዳኘት ሥልጣን ከተሰጠው ተቋም ውጭ የሚያደርግ፣ በሕግ የተደነገገን የዳኝነት ሥርዓት የማይከተል ልዩ ፍርድ ቤት ወይም ጊዜያዊ ፍርድ ቤት አይቋቋምም።መሰረት የሃይማኖትና የባሕል ፍርድ ቤቶችን ላያቋቁሙ ወይም እውቅና ላሰጡ ይችላላላለላሉ። ይሀ ሕግ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በመንግሥት እውቅና አግኝተው ሲሰራባቸው የነበሩ ሃይማኖቶችና የባሕል ፍርድ ቤቶች በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት እውቅና አግኝተው ይደራጃሉ።
1. በፍድራልም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ነው። 2. በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ልላ ተጽዕኖ ነጻ ነው። 3. ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ። ከሕግ በስተቀር በልላ ሁኔታ አይመሩም። 4. ማንኛውም ዳኛ ከዚህ በታች በተመለከቱት ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር በሕግ ከተወሰነው የጡረታ ዕድሜ ከመድረሱ በፊት ከፈቃዱ ውጭ ከዳኝነት ሥራው አይነሳም፤ ሀ/ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በዳኞች የዲሲኘላን ሕግ መሰረት ጥፋት ፈጽሟል ወይም ጉልህ የሆነ የሥራ ችሎታና ቅልጥፍና አንሶታል ብሎ ብሎ ሲወስን፣ ወይም ለ/ በህመም ምክንያት ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን አይችልም ብሎ ሲወስን፣ እና ሐ/ የጉባኤው ውሳኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤቶች ከግማሽ በላይ ድምጽ ሲጸድቅ። 5. የማንኛውም ዳኛ የጡረታ መውጫ ጊዜ አይራዘምም። 6. የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍድራሉን መንግሥት የዳኝነት አካል የሚያስተዳድርበትን በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል፣ ሲፈቀድም በጀቱን ያስተዳድራል። 7. የክልል የዳኝነት አካሎች በጀት በየክልሉ ምክር ቤቶች ይመደባል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍድራሉን የከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን ደርበው ለሚሰሩት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችና የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የበጀት ማካካሻ ይሰጣል።
1. የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍድራል ጉዳዮች ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል። 2. የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ጉዳይ ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል። በተጨማሪ የፍድራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል። 3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተጠቀሰው ቢኖርም፣ ሀ/ የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየት ሥልጣን ይኖረዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። ለ/ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትንበክልል ጉዳዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየትሥልጣን ይኖረዋል። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል። 4. የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክልሉ ከሚኖረው የዳኝነት ሥልጣን በተጨማሪየፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል። 5. የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣኑ መሰረት በሚሰጠው ውሳኔ ላይ የሚቀርበው ይግባኝ በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይታያል። 6. የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍድራል የዳኝነት ሥልጣኑ በሚሰጠው ውሳኔ ላይየሚቀርበው ይግባኝ በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይታያል።
1. የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንትና ምክትል ኘሬዚዳንት በፍድራልመንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትይሾማሉ። 2. ልሎች የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን በተመለከተ በፍድራል የዳኞችአስተዳደር ጉባኤ የቀረቡለትን እጩዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያሾማል። 3. የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንትና ምክትል ኘሬዚዳንት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤት ይሾማሉ። 4. የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤት ይሾማሉ። የክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የዳኞችን ሹመት ለምክር ቤቱ ከማቅረቡ በፊት የፍድራሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በእጩዎቹ ላይ ያለውን አስተያየት መጠየቅና አስተያየቱን ከራሱ አስተያየት ጋር በማያያዝ ለክልሉ ምክር ቤት የማቅረብ ኃላፊነት አለበት። የፍድራሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አስተያየቱን በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላቀረበ የክልሉ ምክር ቤት ሹመቱን ያጸድቃል። 5. የክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤት ይሾማሉ። 6. በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች የዲሲፕላንና የዝውውር ጉዳይ በሚመለከተው የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ይወሰናል።
1. የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በዚህ ሕገ መንግሥት ተቋቁሟል። 2. የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አሥራ አንድ አባላት ይኖሩታል።አባላቱም የሚከተሉት ናቸው፣ ሀ/ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት፣ ሰብሳቢ፤ ለ/ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ኘሬዚዳንት፣ ምክትል ሰብሳቢ፤ ሐ/ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅራቢነት በሪፐብላኩ ኘሬዚዳንት የሚሾሙ በሙያ ብቃታቸውና በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው ስድስት የሕግ ባለሙያዎች፤ መ/ የፍድሬሽኑ ምክር ቤት ከአባላቱ መካከል የሚወክላቸው ሦስት ሰዎች። 3. የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሥራ ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ የሚያስችለው መዋቅር ላዘረጋ ይችላል።
1. የሕገ መንግሥታዊ ክርክር ጉዳይ ሲነሳ በፍድሬሽኑ ምክር ቤት ውሳኔ ያገኛል። 2. የፍድሬሽን ምክር ቤት፣ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በሚያቀርብለት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳይ ላይ በሰላሣ ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል።
1. የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራት ሥልጣን ይኖረዋል። በሚያደርገው ማጣራት መሰረት ሕገ መንግሥቱ መተርጐም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለፍድሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል። 2. በፍድራሉ መንግሥትም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ ሕጐች ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሳና ጉዳዩም በሚመለከተው ፍርድ ቤት ወይም በባለ ጉዳዩ ሲቀርብለት መርምሮ ለመጨረሻ ውሳኔ ለፍድሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል። 3. በፍርድ ቤቶች የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ሲነሳ፣ ሀ/ ሕገ መንግሥቱን መተርጐም አስፈላጊ ሆኖ ሳያገኘው ሲቀር ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ይመልሳል፤ በአጣሪ ጉባኤው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ባለጉዳይ ቅሬታውን ለፍድሬሽኑ ምክር ቤት በይግባኝ ማቅረብ ይችላል። ለ/ የትርጉም ጥያቄ መኖሩን ያመነበት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ለፍድሬሽኑ ምክር ቤት ለመጨረሻ ውሳኔ ያቀርባል። የሚመራበትን ሥነ ሥርዓት አርቅቆ ለፍድሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል።
1. ማንኛውም የመንግሥት አካል ሕገ መንግሥቱን፣ ልሎች ሕጐችንና ፖላሲዎችን ሥራ ላይ ሲያውል በዚህ ምዕራፍ በተመለከቱት መርሆዎችና ዓላማዎች ላይ መመስረት አለበት። 2. በዚህ ምዕራፍ ውስጥ «መንግሥት» ማለት እንደየሁኔታው የፍድራል መንግሥት ወይም የክልል መስተዳድሮች ማለት ይሆናል።
1. የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጥቅም የሚያስጠብቅና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር የውጭ ግንኙነት ፖላሲ ማራመድ። 2. የመንግሥታትን ሉዓላዊነትና እኩልነት ማክበር፣ በልሎች ሀገሮች ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ አለመግባት። 3. የሀገሪቱ የውጭ ግንኙነት ፖላሲ በጋራ ጥቅምና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ስምምነቶች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ። 4. የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብሩና የሕዝቦኟን ጥቅም የማይጻረሩ ዓለም አቀፍ ሕጐችና ስምምነቶችን ማክበር። 5. ከጐረቤት ሀገሮችና ከልሎችም የአፍሪካ ሀገሮች ጋር በየጊዜው እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚያዊ ኅብረትና የሕዝቦች ወንድማማችነትን ማጐልበት። 6. በሀገሮች መካከል የሚነሱ ግጭቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ ጥረት ማድረግ።
1. የሀገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት የብሕሮች፣ የብሕረሰቦች እና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል። 2. የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ የሚሾመው ሲቪል ይሆናል። 3. የመከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል። 4. የመከላከያ ሰራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ ይሆናል። 5. የመከላከያ ሰራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነጻ በሆነ አኳኊን ያከናውናል።
1. መንግሥት በድሞክራሲያዊ መርሆዎች ላይ በመመሥረት ሕዝቡ በሁሉም ደረጃዎች ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለበት፡ 2. መንግሥት የብሕሮችን፣ የብሕረሰቦችን፣ የሕዝቦችን ማንነት የማክበርና በዚሁ ላይ በመመርኮዝ በመካከላቸው እኩልነት፣ አንድነትና ወንድማማችነትን የማጠናከር ግድታ አለበት።
1. መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቱ የተጠራቀመ እውቀትና ሀብት ተጠ ቃሚዎች የሚሆኑበትን መንገድ የመቀየስ ኃላፊነት አለበት። 2. መንግሥት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ለማድረግና ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈሉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግድታ አለበት። 3. የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ እንዳይደርስ መከላከልና አደጋው ሲደርስም ለተጐጂው እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ። 4. በእድገት ወደኊላ ለቀሩ ብሕሮች፣ ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች መንግሥት ልዩ ድጋፍ ያደርጋል። 5. መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ሥም በይዞታው ሥር በማድረግ ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት። 6. የሀገር ልማት ፖላሲዎችና ኘሮግራሞች በሚዘጋጁበት ወቅት መንግሥት ሕዝቡን በየደረጃው ማሳተፍ አለበት። የሕዝብንም የልማት እንቅስቃሴዎች መደገፍ አለበት። 7. መንግሥት በሀገር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት የሚሳተፉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት። 8. መንግሥት የሰራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደህንነትና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር አለበት።
1. የሀየሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የንoህ ውሃ፣ የመኖሪያ፣ የምግብና የማኅበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ይደረጋል። 2. ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተፅእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሕድ አለበት።
1. መንግሥት መሰረታዊ መብቶችንና ሰብዓዊ ክብርን፣ ድሞክራሲንና ሕገ መንግሥቱን የማይቃረኑ ባሕሎችና ልማዶች በእኩልነት እንዲጐለብቱና እንዲያድጉ የመርዳት ኃላፊነት አለበት። 2. የሀገር የተፈጥሮ ሀብቶችንና የታሪክ ቅርሶችን መጠበቅ የመንግሥትና የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግድታ ነው። 3. መንግሥት አቅም በፈቀደ መጠን ኪነጥበብን፣ ሳይንስንና ቴኖሎጂን የማስፋፋት ግድታ አለበት።
1. መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንoሕና ጤናማ አካባቢ እንዲኖረው የመጣር ኃላፊነት አለበት። 2. ማንኛውም የኢኮኖሚ ልማት እርምጃ የአካባቢውን ደህንነት የሚያናጋ መሆን አለበት። 3. የሕዝብን የአካባቢ ደህንነት የሚመለከት ፖላሲና ኘሮግራም በሚነደፍበትና ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚመለከተው ሕዝብ ሁሉ ሐሳቡን እንዲገልጽ መደረግ አለበት። 4. መንግሥትና ዜጐች አካባቢያቸውን የመንከባከብ ግድታ አለባቸው።
1 ሀ/ የውጭ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን፣ ማናቸውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት፣ የፍድራሉ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመደንገግ ሥልጣን አለው። ለ/ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት የክልል መስተዳድሮች በክልላቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላያውጁ ይችላሉ።ዝርዝሩ ክልሎች ይህን ሕገ መንግሥት መሰረት በማድረግ በሚያወጧቸው ሕገመንግሥቶች ይወሰናል። 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1ሀ/ መሰረት የሚታወጅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በታወጀ በአርባ ስምንት ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ አለበት አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ሦስተኛው ድምጽ ተቀባይነት ካላገኘ ወዲያውኑ ይሻራል። ለ/ ከላይ በንዑስ አንቀጽ /ሀ/ ሥር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባልሆነበት ወቅት የሚታወጅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ ያለበት አዋጁ በታወጀ በአሥራ አምሥት ቀናት ውስጥ ነው። 3. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በምክር ቤቱ ተቀባይነት ካገኘ በኝላ ላቆይ የሚችለው እስከ ስድስት ወራት ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ አንድን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በየአራት ወሩ በተደጋጋሚ እንዲታደስ ላያደርግ ይችላል። 4. ሀ/ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚታወጅበት ጊዜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣቸው ደንቦች መሰረት የሀገርን ሰላምና ሕልውና፣ የሕዝብን ደህንነት፣ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥልጣን ይኖረዋል። ለ/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣን በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሰረታዊ የፖለቲካና የድሞክራሲ መብቶችን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማወጅ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማስወገድ ተፈላጊ ሆኖ በተገኘውደረጃ፣ እስከ ማገድ ላደርስ የሚችል ነው። ሐ/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥራ የሚያወጣቸው ድንጋጌዎችና የሚወስዳቸው እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ በዚህ ሕገመንግሥት አንቀጽ 1፣፣ 88፣ 25፣ እና 39 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተቀመጡትን መብቶች የሚገድቡ ላሆኑ አይችሉም። 5. በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚታወጅበት ወቅት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአባላቱና ከሕግ ባለሙያዎች መርጦ የሚመድባቸው ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ያቋቁማል። ቦርዱ አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚጸድቅበት ጊዜ ይቋቋማል፣ 6. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነቶች አሉት። ሀ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የታሰሩትን ግለሰቦች ስም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፋ ማድረግና የታሰሩበትን ምክንያት መግለጽ፣ ለ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የሚወሰዱት እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ ኢሰብዓዊ አለመሆናቸውን መቆጣጠርና መከታተል፣ ሐ/ ማናቸውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ ኢሰብዓዊ መሆኑን ሲያምንበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የሚኒስሮች ምክር ቤት እርምጃውን እንዲያስተካክል ሐሳብ መስጠት፣ መ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃዎች ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙትን ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ፣ ሰ/ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲቀጥል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ሲቀርብ ያለውን አስተያየት ለምክር ቤቱ ማቅረብ።
1. የፍድራሉ መንግሥትና ክልሎች በሕግ የተሰጧቸውን ኃላፊነቶችና ተግባሮች ለማከናወን የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በየበኩላቸው ይሸፍናሉ፤ ሆኖም ማንኛውም ክልል በውክልና ለሚፈጽመው ተግባር የሚያስፈልገው ወጪ ልላ ስምምነት ከልለ በቀር ውክልናውን በሰጠው ወገን ይሸፈናል። 2. የፍድራሉ መንግሥት ለክልሎች የተመጣጠነ እድገት እንቅፋት ካልሆነ በስተቀር ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ፣ ለመልሶ መቋቋምና ለልማት ማስፋፊያ ለክልሎች ብድርም ሆነ እርዳታ ላሰጥ ይችላል። የፍድራሉ መንግሥት ክልሎች ለሚያስፈልጋቸው ወጪ የሚያደርገውን ድጐማ በሚመለከት ኦዲትና ቁጥጥር የማድረግ ሥልጣን ይኖረዋል።
የፍድራሉ መንግሥትና ክልሎች የሚዋቀረውን የፍድራል አደረጃጀት የተከተለ የገቢ ክፍፍል ያደርጋሉ።
1. የፍድራል መንግሥት በወጪና ገቢ ዕቃዎች ላይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ የታክስና ልሎች ክፍያዎች ይጥላል፣ ይሰበስባል። 2. በፍድራል መንግሥትና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተቀጣሪዎች ላይ የሥራ ግብር ይጥላል፣ ይሰበስባል። 3. በፍድራል መንግሥት ባለቤትነት ሥር በሆኑ የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የሥራ ግብር፣ የሽያጭና የኤክሳይስ ታክስ ይጥላል፣ ይሰበስባል። 4. በብሕራዊ የሎተሪ እና ልሎች የዕድል ሙከራ ገቢዎች ላይ ታክስ ይጥላል፣ይሰበስባል። 5. በአየር፣ በባቡርና በባሕር ትራንስፖርት ገቢዎች ላይ ታክስ ይጥላል፣ ይሰበስባል። 6. በፍድራል መንግሥት ባለቤትነት ሥር በሚገኙ ቤቶችና ልሎች ንብረቶች ገቢ ላይ ግብር ይጥላል፣ ይሰበስባል፤ ኪራይ ይወስናል። 7. የፍድራል መንግሥት አካላት ከሚሰጧቸው ፈቃዶችና አገልግሎቶች የሚመነጩ ክፍያዎችን ይወስናል፣ ይሰበስባል። 8. የሞኖፖል ታክስ ይጥላል፣ ይሰብሰባል። 9. የፍድራል የቴምብር ሽያጭ ቀረጥ ይጥላል፣ ይሰበስባል።
1. ክልሎች፣ በክልል መስተዳድርና በድርጅት ተቀጣሪዎች ላይ የሥራ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። 2. የመሬት መጠቀሚያ ክፍያ ይወስናሉ፣ ይሰበስባሉ። 3. በግል የሚያደርሱና በኅብረት ሥራ ማኅበራት በተደራጁ ገበሬዎች ላይ የእርሻ ሥራ ገቢ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። 4. በክልሉ በሚገኙ ግለሰብ ነጋድዎች ላይ የንግድ ትርፍ ግብርና የሽያጭ ታክስ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። 5. በክልሉ ውስጥ በውኃ ላይ ከሚደረግ ትራንስፖርት በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። 6. በክልል መስተዳድር በግል ባለቤትነት ሥር ካሉ ቤቶችና ልሎች ንብረቶች በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ፣ በባለቤትነታቸው ሥር ባሉ ቤቶችና ልሎች ንብረቶች ላይ ኪራይ ያስከፍላሉ። 7. በክልል መስተዳድር ባለቤትነት ሥር በሚገኙ የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ፣ የሥራ ግብር፣ የሽያጭና ኤክሳይስ ታክስ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። 8. ብአንቀጽ 98 ንዑስ አንቀጽ 3 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በማዕድን ሥራዎች ላይ የማዕድን ገቢ ግብር፣ የሮያላቲና የመሬት ኪራይ ክፍያዎች ይጥላሉ፣ይሰበስባሉ። 9. በክልል መስተዳድር አካላት ከሚሰጡ ፈቃዶችና አገልግሎቶች የሚመነጩ ክፍያዎች ይወስናሉ፣ ይሰበስባሉ። 10. ከደን የሚገኝ የሮያላቲ ክፍያ ይወስናሉ፣ ይሰበስባሉ።
1. የፍድራል መንግሥትና ክልሎች በጋር በሚያቋቁሟቸው የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የሥራ ግብር፣ የሽያጭና የኤክሳይስ ታክስ በጋራ ይጥላሉ፣ይሰበስባሉ። 2. በድርጅቶች የንግድ ትርፍ ላይ እና በባለ አክሲዮኖች የትርፍ ድርሻ ላይ ግብርና የሽያጭ ታክስ በጋራ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። 3. በከፍተኛ የማዕድን ሥራዎችና በማናቸውም የፔትሮላየምና የጋዝ ሥራዎች ላይ የገቢ ግብርና የሮያላቲ ክፍያዎች በጋራ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ።
በዚህ ሕገ መንግሥት ተለይተው ያልተሰጡ ታክስና ግብር የመጣል ሥልጣኖችን በሚመለከት የፍድሬሽኑ ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ይወስናሉ።
1. ክልሎችና የፍድራሉ መንግሥት ታክስና ግብር በሚጥሉበት ጊዜ የሚጠየቀው ታክስና ግብር ከምንጩ ጋር የተያያዘና በአግባቡ ተጠንቶ የተወሰነ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው። 2. በመካከላቸው የሚኖረውን መልካም ግንኙነት የማይጐዳና ከሚቀርበው አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው። 3. ለትርፍ የቆመ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ክልሎች በፍድራሉ መንግሥት ንብረት ላይ፣ የፍድራሉ መንግሥትም በክልሎች ንብረት ላይ ግብር ወይም ቀረጥ የማስከፈል ሥልጣን አይኖራቸውም።
1. ዋናው ኦዲተር በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርቢነት በሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት ይሾማል። 2. ዋናው ኦዲተር የፍድራሉን የሚኒስቴርና ልሎች መሥሪያ ቤቶች ሂሳቦች በመቆጣጠር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመደበው ዓመታዊ በጀት፣ በበጀት ዓመቱ ለተሰሩት ሥራዎች በሚገባ መዋሉን መርምሮ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል። 3. ዋናው ኦዲተር የመሥሪያ ቤቱን በጀት በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስጸድቃል። 4. የዋናው ኦዲተር ዝርዝር ተግባር በሕግ ይወሰናል።
1. በፍድራልና በክልል የምርጫ ክልሎች ነጻና ትክክለኛ ምርጫ በገለለተኝነት እንዲያካሂድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ የሆነ ብሕራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል። 2. የቦርዱ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ። ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል።
1. የሀገሪቱን የሕዝብ ቁጥር በየጊዜው የሚያጠናና ቆጠራ የሚያካሂድ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ይኖራል። 2. የኮሚሽኑ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ። 3. ኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊ፣ አስፈላጊ ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ይኖሩታል። 4. የኮሚሽኑ ዓመታዊ በጀት በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይጸድቃል። 5. የሕዝብ ቆጠራ በየአሥር ዓመቱ ይካሕዳል። በውጤቱም መሰረት የምርጫ ክልሎችን አከላለል የምርጫ ቦርድ በሚያቀርበው ረቂቅ መሰረት የፍድሬሽኑ ምክር ቤት ይወስናል። 6. የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት ነው። ስለ ሥራው አፈጻጸፍ በየጊዜው ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል።
አንድ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሐሳብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የደገፈው፣ የፍድሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የደገፈው ወይም ከፍድሬሽኑ አባል ክልሎች ውስጥ አንድ ሦስተኛው የክልል ምክር ቤቶች በድምጽ ብልጫየደገፉት ከሆነ ለውይይትና ለውሳኔ ለመላው ሕዝብና የሕገ መንግሥቱ መሻሻል ለሚመለከታቸው ክፍሎች ይቀርባል።
1 በዚህ ሕገ መንግሥት ምዕራፍ ሦስት የተዘረዘሩት መብቶችና ነጻነቶች በሙሉ፣ይህ አንቀጽ፣ እንዲሁም አንቀጽ 104 ላሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳቃን ብቻ ይሆናል። ሀ/ ሁሉም የክልል ምክር ቤቶች የቀረበውን ማሻሻያ በድምጽ ብልጫ ሲያጸድቁት፣ ለ/ የፍድራሉ መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቀው፣ እና ሐ/ የፍድሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ማሻሻያውን ሲያጸድቀው ነው። 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ከተዘረዘሩት ውጭ ያሉት የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ላሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳኊን ብቻ ይሆናል፤ ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፍድሬሽኑ ምክር ቤት በጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት፣ እና ለ/ ከፍድሬሽኑ አባል ክልሎቸ ምክር ቤቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛ ክልሎች ምክር ቤቶች በድምጽ ብልጫ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት ነው።
የዚህ ሕገመንግሥት የአማርኛ ቅጂ የመጨረሻው ሕጋዊ እውቅና ያለው ሰነድ ነው።
Choose an article to open it.