Article text
1. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነው።
2. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባሎችን ከሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ወይም ለሥራው ብቃት ካላቸው ልሎች ግለሰቦች መካከል
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርቦ ሹመታቸውን ያጸድቃል።
3. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣቸው ሕጐች፣ ፖላሲዎች፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል።
4. የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይወክላል።
5. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣቸውን ፖላሲዎች፣ ደንቦች መመሪያዎችና ውሳኔዎች ተፈጻሚነት ይከተተላል።
6. የሀገሪቱን የውጭ ፖላሲ በበላይነት ያስፈጽማል።
7. ኮሚሽነሮችን፣ የማዕከላዊ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንትና ምክትል ኘሬዚዳንትን እና ዋና ኦዲተርን መርጦ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
ሹመታቸውን ያጸድቃል።
8. የመስተዳድሩን ሥራ አፈጻጸምና ብኝት ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ የሆኑ የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል።
9. በዚሀ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እና 7 ከተዘረዘሩት ውጭ የሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሲቪል ሹመቶችን ይሰጣል።
10. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው ሕግ ወይም በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት ኒሻኖችንና ሽልማቶችን ለኘሬዚዳንቱ አቅርቦ ያሰጣል።
11. ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ፣ በመንግሥት ስለተከናወኑ ተግባራትና ስለወደፊት እቅዶች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየወቅቱ ሪፖረት ያቀርባል።
12. በዚህ ሕገ መንግሥትና በልሎች ሕጐች የተሰጡትን ልሎች ተግባሮች ያከናውናል።
13. ሕገ መንግሥቱን ያከብራል፤ የስከበራል።