Article text
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት ለፍድራሉ መንግሥት በተሰጠው ሥልጣን ክልል ሕጐችን ያወጣል።
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ
ዝርዝር ሕግ ያወጣል፤
ሀ/ የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት፤ እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ ወይም ከአንድ ክልል በላይ የሚያስተሳስሩ ወንዞችና ሐይቆች አጠቃቀምን በተመለከተ፤
ለ/ በክልሎች መካከል የሚኖረውን የንግድ ልውውጥ፤ እንዲሁም የውጭ ንግድ ግንኙነትን በተመለከተ፤
ሐ/ የአየር፣ የባቡርና የባሕር መጓጓዣ፤ የፖስታና የቴልኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን እንዲሁም ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ክልሎችን የሚያገናኙ
አውራ መንገዶችን በተመለከተ፤
መ/ በዚህ ሕገ መንግሥት የተደነገጉትን የፖለቲካ መብቶች አፈጻጸምን እንዲሁም ምርጫን በተመለከተ፤
ሰ/ የዜግነት መብትን፤ የኢምግሬሽን፤ የስፖርትን፤ ወደ ሀገር የመግቢያና የመውጫ ጉዳዮችን እንዲሁም የስደተኞችና የፖለቲካ ጥገኝነት ጉዳዮችን
በተመለከተ፤
ረ/ አንድ ወጥ የመጠን መለኪያ ደረጃና የጊዜ ቀመርን በተመለከተ፤
ሰ/ የፈጠራና የሥነ ጥበብ መብቶችን በተመለከተ፤
ሸ/ የጦር መሣሪያ መያዝን በተመለከተ።
3. የሰራተኛ ጉዳይ ሕግ ያወጣል።
4. የንግድ ሕግ /ኮድ/ ያወጣል።
5. የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ያወጣል። ይህ እንደተጠበቀ ሁኖ ክልሎች የፍድራሉ መንግሥት የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በግልጽ ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ
ሕግ የማውጣት ሥልጣን ይኖራቸዋል።
6. አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ሲባል በፍድራል መንግሥት ሕግ እንዲወጣላቸው የሚያስገድዱ ለመሆናቸው በፍድሬሽኑ ምክር ቤት
የታመነባቸው የፍትሐብሕር ሕጐችን ያወጣል።
7. የፍድራል መንግሥት፤ የሀገርና የሕዝብ መከላከያ፤ የደህንነትና የፖላስ ኃይል አደረጃጀት ይወስናል። በሥራ አፈጻጸም ረገድ የሚታዩ መሰረታዊ
የዜጐችን ሰብዓዊ መብቶችና የሀገርን ደህንነት የሚነኩ ጉዳዮች ሲከሰቱ ያጣራል፤ አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል።
8. በአንቀጽ 93 በተመለከተው መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፤ የሕግ አስፈጻሚው የሚያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተመልክቶ
ይወስናል።
9. የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያቀርብለት የሕግ ረቂቅ መሰረት የጦርነት አዋጅ ያውጃል።
10. የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የልማት ፖላሲዎችንና ስትራቴጂዎችን፤ የፋይናንስና የገንዘብ ፖላሲን ያጸድቃል፤ ገንዘብን፤
የብሕራዊ ባንክ አስተዳደር፤ የውጭ ምንዛሪንና ልውውጥን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ ያወጣል።
11. ለፍድራል መንግሥት በተከለለው የገቢ ምንጭ ክልል ግብርና ታክስ ይጥላል።የፍድራል መንግሥት በጀት ያጸድቃል።
12. የሕግ አስፈጻሚው አካል የሚዋዋላቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ያጸድቃል።
13. የፍድራል መንግሥት ፍርድ ቤት ዳኞችን፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን፤የኮሚሽነሮችን፤ የዋናው ኦዲተርን እንዲሁም የልሎች ሹመታቸው
በምክር ቤቱ መጽደቅ ያለበትን ባለሥለጣኖች ሹመት ያጸድቃል።
14. የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያቋቁማል፤ ሥልጣንና ተግባሩን በሕግ ይወስናል።
15. የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋምን ያቋቁማል፤ ተቋሙን የሚመሩ አባላትን ይመርጣል፤ይሰይማል። ሥልጣንና ተግባሩን በሕግ ይወስናል።
16. በማንኛውም ክልል ሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱና ክልሉ ድርጊቱን ማቆም ሳይችል ሲቀር፤ በራሱ አነሳሽነትና ያለክልሉ ፈቃድ ተገቢው እርምጃ
እንዲወሰድ ለፍድሬሽኑ ምክር ቤትና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ጥያቄ ያቀርባል፤ በተደረሰበት ውሳኔ መሰረት ለክልሉ ምክር ቤት
መመሪያ ይሰጣል።
17. ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ልሎች የፍድራሉ መንግሥት ባለሥለጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈጻሚውን አካል አሰራር
የመመርመር ሥልጣን አለው።
18. ለሕግ አስፈጻሚው አካል በተሰጠ ማንኛውም ሥልጣን ላይ የምክር ቤቱ አባላት በአንድ ሦስተኛ ድምፅ ሲጠይቁ ምክር ቤቱ ይወያያል። ምክር ቤቱ
በጉዳዩ ላይ የመመካከርና አስፈላጊ መስሎ የታየውን እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን አለው።
19. ምክር ቤቱን የሚመሩ አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ ይመርጣል፤ ለምክር ቤቱ ሥራ የሚያስፈልጉትን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ያዋቅራል።
Article 6
ስለ ዜግነት
Choose an article to open it.