Article text
1. የትግራይ ክልል
2. የአፋር ክልል
3. የአማራ ክልል
4. የኦሮሚያ ክልል
5. የሱማል ክልል
6. የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል
7. የደቡብ ብሕሮች፣ ብሕረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
8. የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል
9. የሐረሪ ሕዝብ ክልል
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከቱት ክልሎች ውስጥ የተካተቱ ብሕሮች፣
ብሕረሰቦች፣ ሕዝቦች በማንኛውም ጊዜ የየራሳቸውን ክልል የማቋቋም መብት አላቸው።
3. የማንኛውም ብሕር፣ ብሕረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ክልል የመመስረት መብት ሥራ ላይ የሚውለው፤
ሀ/ የክልል መመስረት ጥያቄው በብሕሩ፣ በብሕረሰቡ ወይም በሕዝቡ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥና ጥያቄው
በጽሑፍ ለክልሉ ምክር ቤት ሲቀርብ፤
ለ/ ጥያቄው የቀረበለት የክልል ምክር ቤት ጥያቄው በደረሰው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠየቀው ብሕር፣ ብሕረሰብ ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ
ሲያደራጅ፤
ሐ/ ክልል የመመስረት ጥያቄው በብሕሩ፣ በብሕረሰቡ ወይም ሕዝቡ ሕዝበ ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሲደገፍ፤
መ/ የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣኑን ለጠየቀው ብሕር፣ ብሕረሰብ ወይም ሕዝብ ሲያስረክብ፤
ሰ/ በሕዝበ ውሳኔ የሚፈጠረው አዲስ ክልል ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልገው በቀጥታ የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ አባል ሲሆን ነው።
4. የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ አባላት እኩል መብትና ሥልጣን አላቸው።