Article text
1. የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብላክ በፍድራል መንግሥትና በክልሎች የተዋቀረ ነው።
2. የፍድራሉ መንግሥትና ክልሎች የሕግ አውጪነት፣ የሕግ አስፈጻሚነትና የዳኝነት ሥልጣን አላቸው።
3. የፍድራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የፍድራሉ መንግሥት የሕዝብተወካዮች ምክር ቤት ነው። ተጠሪነቱም ለሀገሪቱ ሕዝብ ነው። የክልል
ከፍተኛ የሥልጣን አካል የክልሉ ምክር ቤት ነው፤ ተጠሪነቱም ለወከለው ክልል ሕዝብ ነው።
4. ክልሎች፤ በክልልነትና ክልሎች አስፈላጊ ሆነው በሚያገኙአቸው የአስተዳደር እርከኖች ይዋቀራሉ። ሕዝቡ በዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች በቀጥታ
ይሳተፍ ዘንድ ለዝቅተኛ እርከኖች በቂ ሥልጣን ይሰጣል።
5. የክልል ምክር ቤት በክልሉ ሥልጣን ስር በሆኑ ጉዳዮች የክልሉ የሕግ አውጪ አካል ነው። ይህንን ሕገ መንግሥት መሰረት በማድረግ የክልሉን ሕገ
መንግሥት ያዘጋጃል፣ ያጸድኝል፣ ያሻሽላል።
6. የክልል መስተዳድር የክልሉ ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካል ነው።
7. የክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ነው።
8. የፍድራሉ መንግሥትና የክልሎች ሥልጣን በዚህ ሕገ መንግሥት ተወስኗል። ለፍድራሉ መንግሥት የተሰጠው ሥልጣን በክልሎች መከበር አለበት።
ለክልሎች የተሰጠው ሥልጣን በፍድራሉ መንግሥት መከበር አለበት።
9. የፍድራል መንግሥት በዚህ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 51 ከተሰጡት ሥልጣን እና ተግባሮች እንደአስፈላጊነቱ ለክልሎች በውክልና ላሰጥ ይችላል።