English
1/ The Repealed Law continue to apply to
accounting periods prior to the
commencement of this Proclamation.
2/ A reference in this Proclamation to a
previous accounting period shall include,
where the context requires, a reference to
an accounting period under the repealed
law.
3/ Regulations and Directives issued under
the Repealed Law shall continue to apply
to the extent that they are not
inconsistent with this Proclamation and
until such time as they are replaced by
Regulations and Directives issued under
this Proclamation.
4/ The Repealed Law shall be applicable to
goods imported into Ethiopia within Six
months from the effective date of this
Proclamation using the Letter of Credit
issued prior to the issuance of this
Proclamation.
5/ The delegation of power granted to
Regional tax authorities by the Ministry
of Revenue under the Repealed Law
shall continue to be applicable until a
procedure and a system of delegation is
developed in accordance with this
Proclamation.
6/ The residential buildings of a registered
person engaged in real estate business,
who has credited the input tax paid on
creditable acquisition used for residential
buildings under construction before entry
into force of this Proclamation, may only
be exempt from VAT upon returning to
the Tax Authority the input tax credited.
‹
7/ Notwithstanding the provisions of this
Proclamation, a registered person
engaged in tour operation business shall
for Three years from the date of
effectiveness of this Proclamation pay
Value Added Tax on the net amount of
the fee received for Inbound tourism
product after deducting the cost incurred
in Ethiopia for accommodation, meals,
transportation and tours or on
commission received.
8/In this Article, “Repealed Law” means
that Value Added Tax Proclamation No.
285/2002.
አማርኛ
፩/ የተሻረው አዋጅ ይህ አዋጅ ተፈጻሚ ከመሆኑ
በፊት ስራ ላይ የቆዩ ነባር የሒሣብ ጊዜዎችን
በሚመለከት ተፈጻሚነት ይኖረዋል።
፲፮ሺ፹፫
፪/ በዚህ አዋጅ ነባር የሒሣብ ጊዜዎች በሚል
የተጠቀሰው አግባብነት እስካለው ድረስ በተሻረው
አዋጅ የነበረውን የሒሣብ ጊዜ ይጨምራል።
፫/ በተሻረው አዋጅ መሠረት የወጡ ደንቦችና
መመሪያዎች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ
እስካልሆነ እና በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ
ደንብና መመሪያ እስከሚተኩ ድረስ
ተፈጻሚነታቸው ይቀጥላል።
፬/ ይህ አዋጅ ከመወጣቱ በፊት በተሰጠ የባንክ
ፈቃድ አዋጁ ከጸናበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወር
ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች በተሻረው
አዋጅ መሠረት ይስተናገዳሉ።
፭/ የገቢዎች ሚኒስቴር በዚህ አዋጅ በተደነገገው
መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስን የመሰብሰብ
ውክልና አሰጣጥን እና የአፈጻጸም ሥርዓቱን
እስከሚዘረጋ ድረስ ቀደም ሲል በተሻረው አዋጅ
መሠረት ለክልል የታክስ ባለሥልጣናት የሰጠው
ውክልና ተፈጻሚነት ይቀጥላል።
፮/ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በመሸጥ ስራ ላይ
የተሰማራ እና ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት
በግንባታ ላይ ላሉ የመኖሪያ ቤቶች በሚውሉ
ግብአቶች ላይ የከፈለውን የግብአት ታክስ
ያቀናነሰ የተመዘገበ ሰው የሚሸጠው የመኖሪያ
ቤት ከታክሱ ነጻ እንዲሆን ለማድረግ የሚቻለው
በእነዚህ የግንባታ ዕቃዎች ላይ ያቀናነሰውን
የግብዓት ታክስ ለባለሥልጣኑ ተመላሽ ሲያደርግ
ነው።
፲፮ሺ፹፬
፯/ በዚህ አዋጅ የተደነገገው ቢኖርም በቱሪስት
አስጎብኚነት የንግድ ስራ ላይ የተሰማራ
የተመዘገበ ሰው ይህ አዋጅ ከጸናበት ቀን አንስቶ
ለሦስት ዓመታት ያህል የተጨማሪ እሴት ታክስ
የሚከፍለው በሀገር ውስጥ ጥቅል የቱሪዝም
አገልግሎት ለመስጠት ከተቀበለው ክፍያ ላይ
ለመኝታ፣ ለምግብ እና ለትራንስፖርት
የሚያወጣው ወጪ ተቀንሶ በሚቀረው ሂሳብ
ወይም በሚከፈለው ኮሚሽን ላይ ይሆናል።
፰/ በዚህ አንቀጽ ‹‹የተሻረው አዋጅ›› ማለት
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር
፪፻፹፭/፩ሺ፱፻፺፬ ከነማሻሻያዎቹ ነው።