English
1/ Subject to Sub-Article
(2) of this Article,
the Tax Authority may require a person
carrying on a taxable activity outside
Ethiopia who is liable to be registered
under Article 12 of this Proclamation but
who does not have a fixed place of
business in Ethiopia to lodge security
with the Tax Authority in accordance
with the Tax Administration
Proclamation.
2/ Sub-Article
(1) of this Article shall apply
only if the Tax Authority has reasonable
grounds to believe that the person will
not comply with their obligations under
this Proclamation.
3/ If a person who has lodged security under
Sub-Article
(1) of this Article fails to
comply with their obligations under this
Proclamation, the Tax Authority may
require the person to appoint a VAT
representative in Ethiopia.
4/ A VAT representative appointed under
Sub-Article
(3) of this Article shall be
responsible for doing all things required
under this Proclamation of the person
they represent, including applying for
registration, filing of VAT returns, and
paying VAT.
5/ The registration of a VAT representative
shall be made in the name of the person
they represent.
6/ A person may be a VAT representative
for more than One person but shall have
a separate registration for each person
they represent.
7/ A VAT representative of a person under
this Article shall be:
a) a representative of the person for the
purposes of the Tax Administration
Proclamation; and
b) personally liable for the VAT liability
of the person they represent.
8/ The Tax Authority may specify the mode,
manner, and requirements for
appointment of a VAT representative
and the responsibilities of the
representative.
አማርኛ
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፪) የተመለከተው
እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የታክሱ ባለስልጣን በዚህ
አዋጅ አንቀጽ ፲፪ መሠረት የመመዝገብ ግዴታ
ያለበት እና ከኢትዮጵያ ውጪ ታክስ
የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ የሚያከናውን
በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት
የሌለው ሰው በታክስ አስተዳደር አዋጅ
በተደነገገው መሠረት ለታክሱ መከፈል ዋስትና
እንዲያቀርብ ሊጠይቅ ይችላል።
፲፮ሺ፸
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ተፈጻሚ
የሚሆነው የታክሱ ባለሥልጣን የውጭ ሀገር
አገልግሎት ሰጪው በዚህ አዋጅ የተጣሉበትን
ግዴታዎች የማይወጣ መሆኑን የሚያሳምን በቂ
ምክንያት ሲኖረው ነው።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) መሠረት ዋስትና
ያቀረበ ሰው በዚህ አዋጅ በተጣለበት ግዴታ
መሠረት ያልፈጸመ እንደሆነ የታክሱ ባልስልጣን
ይህ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ለተጨማሪ እሴት
ታክስ ወኪል እንዲሰይም ሊያስገድደው ይችላል።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፫) መሠረት
የተጨማሪ እሴት ታክስ ወኪል የሆነ ሰው
ለተጨማሪ እሴት ታክስ ለመመዝገብ ማመልከቻ
ማቅረብን፤ የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብን፤
የተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈልን ጨምሮ
በወከለው ሰው ስም በዚህ አዋጅ የተመለከቱ
ተግባሮችን የመፈጸም ኃላፊነት አለበት።
፭/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወኪል ምዝገባ
የሚከናወነው በወካዩ ስም ነው።
፮/ አንድ ሰው ለብዙ ሰዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ
ወኪል መሆን የሚችል ሲሆን፤ ሆኖም
ለእያንዳንዱ ለሚወክለው ሰው የተለያየ ምዝገባ
መፈፀም አለበት።
፯/ በዚህ አንቀጽ መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክስ
ወኪል የሚሆን ሰው፡ሀ) ለታክስ አስተዳደር አዋጅ አፈጻጸም የወካዩ
የታክስ እንደራሴ ሆኖ ይቆጠራል፤ እና
ለ) ለሚወክለው ሰው የተጨማሪ እሴት ታክስ
ግዴታ የግል ተጠያቂነት ይኖርበታል።
፲፮ሺ፸፩
፰/ የታክሱ ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ ወኪል
የሚሾምበትን መንገድ፣ አኳኋን እና ተፈላጊ
ሁኔታዎች በመመሪያ ሊወስን ይችላል።