ለ) ከሁለት ወራት በታች ለሆነ ጊዜ የተከራየን ሳይጨምር የመኖሪያ ቤት ኪራይ፤ ሐ) ፈቃድ በተሰጠው ባንክ ወይም የፋይንናስ ተቋም ወይም በሌላ ማናቸውም ሰው የሚሰጥ የፋይናንስ አገልግሎት አቅርቦት፤ መ) አቅራቢው የትምህርት ፕሮግራም ለሚከታተሉ ተማሪዎች የሚያቀርባቸውን ዋጋቸው ለፕሮግራሙ የሚከፈለው ዋጋ ውስጥ የተካተተ የመማሪያ መጻህፍት፣ ቁሳቁሶች ወይም መሣሪያዎችን ጨምሮ የትምህርት ፕሮግራሞች አቅርቦት፤ ሠ) ፈቃድ በተሰጠው አገልግሎት ሰጪ የሚከናወን የህጻናት ማቆያ አገልግሎት፤ ረ) የሕክምና አገልግሎት አቅርቦት፤ ሰ) በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች አቅርቦት፤ ሸ) የብዙሐን ትራንስፖርት አገልግሎት ፲፮ሺ፺ ቀ) ቅዱሳን መጻህፍትን ማቅረብን ጨምሮ በእምነት ተቋማት የሚሰጡ ከእምነቱ ወይም ከኃይማኖቱ ሥርዓት ጋር በቀጥታ የተያያዙ አገልግሎቶች፤ በ) የሕክምና መገልገያ፣ የሕክምና መሣሪያ፣ የወባ አጐበር አቅርቦት፤ ተ) ለትርፍ ባልተቋቋሙ ድርጅቶች የሚቀርቡ በእርዳታ የሚሰጡ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች፤ ቸ) ለግብርና አገልግሎት ብቻ የሚውል የምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የጸረ - ተባይ፣ የጸረ - አረም፣ የአፈርን አሲዳማነት ለመከላከል የሚውል ካልሲየም ሃይድሮክሳይድ (ውህድ ኖራ) ወይም የፈንገስ መከላከያ ኬሚካሎች፤ ኅ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ በተደነገገው መሠረት ኢንቨስተሮች ወደ ሀገር የሚያስገቡት ወይም ከሀገር ውስጥ የሚገዙት ዕቃ፤ ነ) ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከሚወሰን ወርሃዊ ፍጆታ ያልበለጠ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የታሸገ ወሃን ሳይጨምር የውሃ አቅርቦት፤ ኘ) ፷ በመቶና ከዚያ በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኛ የሆነ ሰው የሚያቀርባቸው ማናቸውም አቅርቦቶች፤ አ) ሚኒስቴሩ በሚያቀርበው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከታክስ ነጻ እንዲሆኑ የሚፈቅዳቸው እቃዎች፤ ከ) አምቡላንስ እና የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች እና መሣሪያዎች አቅርቦት። This Proclamation may be cited as the “Value Added Tax Proclamation No. 1341/2024”.
‹‹በእርዳታ የሚሰጡ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች›› ማለት ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን በሚመለከት ለእነዚህ ድርጅቶች በስጦታ የሚቀርቡ ወይም በስጦታ በተገኘ የሚገዙ እና ድርጅቱ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማስፈጸም የሚውሉ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች። ‹‹የትምህርት ፕሮግራም›› በሚከተሉት የሚሰጥ የትምህርት ፕሮግራም ነው፡ሀ) አግባብ ባለው ክልል የትምህርት ቢሮ ፈቃድ የተሰጠው ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ አንደኛ ደረጃ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ ለ) በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር ፩፻፶፪/፪ሺ፲፩ መሠረት በትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና የተሰጠው ዩኒቨርሲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኮሌጅ ወይም ኢንስቲትዩት፣ ሆኖም የትምህርት ፕሮግራሙ ዲግሪ ወይም ተመሳሳይ የብቃት ማስረጃ የሚያስገኝ ከሆነ፤ ሐ) በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና አዋጅ ቁጥር ፱፻፶፬/፪ሺ፰ መሠረት ዕውቅና የተሰጠው የሥልጠና ተቋም፣ ሆኖም የትምህርት ፕሮግራሙ በአዋጁ መሠረት ዕውቅና የተሰጠው የቴክኒክ ወይም የሙያ ሥልጠና ፕሮግራም ከሆነ፤ መ) የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፲፮ሺ፺፩ ‹‹የፋይናንስ አገልግሎት›› ማለት፡ሀ) በአበዳሪው የሚከናወንን ብድር፣ ክሬዲት ወይም የክሬዲት ዋስትናን ማስተዳደርን ጨምሮ ብድር መስጠት፣ መደራደር፣ ወይም በብድር፣ በክሬዲት፣ በክሬዲት ዋስትና ወይም ለገንዘብ በሚሰጥ ዋስትና መነገድ፤ ለ) ዕዳ መሰብሰብን እና ተሰብሳቢ ሒሣብን መሸጥን ሳይጨምር ገንዘብ፣ ተቀማጭ ሒሣብን፤ ቁጠባን እና ሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦችን፣ ክፍያዎችን፣ የገንዘብ ማስተላለፍ ተግባራትን (የፋይናንስ ቴክኖሎጂ አገልግሎትን ሳይጨምር)፣ ዕዳን፣ ቼክን ወይም የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን የሚመለከቱ ተግባራት፤ ሐ) የፋይናንስ ዴሪቬቲቭ ሀብትን የመግዛትና የመሸጥ ውሎች፣ የፋይናንስ ሀብትን ወደፊት በሚውል ቀን ለመግዛት ወይም ለመሸጥ የሚደረግ ስምምነት፣ የፋይናንስ ሰነዶችን ለመግዛት የሚኖር ምርጫን የመግዛትና የመሸጥ ውሎች እና ተመሳሳይ ተግባራትን፣፤ መ) የአደራ አገልግሎት ሳይጨምር በአክሲዩን፣ ድርሻ፣ ቦንድ እና ሌሎች የግዴታ ምስክር ወረቀቶች መገበያየት እና ከእነዚህ ጋር የተያያዘ ማናቸውም ምርጫ ወይም ዋስትና፤ ሠ)የኢንቨስትመንት ፈንድን ማስተዳደር፤ ረ) የረዥም ጊዜ የመድን ውል መስጠት ወይም የባለቤትነት መብት ማስተላለፍ ወይም ለዚህ ዓይነቱ ውል የጠለፋ መድን መስጠት ወይም አነስተኛ የመድህን ውል መስጠት፤ ሰ) የጡረታ ፈንድ፣ የፕሮቪደንት ፈንድን ወይም ሌላ ተመሳሳይ የጥቅም ፈንድ፤ የመድን ጡረታ ፈንድ፤ የጡረታ ሂሳብን ለማስጠበቅ የሚቋቋም ፈንድ ማቋቋም ወይም የባለቤትነት መብትን ማስተላለፍ፤ ሸ) ለዕቃው በሚሰጠው ብድር ላይ የተለየ ክፍያ የሚጠየቅ እና ክፍያው ለዕቃው ተጠቃሚ የተገለጸ እስከሆነ ድረስ በኪራይ ግዥ ስምምነት ወይም በፋይናንስ ሊዝ መሠረት የሚከናወን አቅርቦት፤ ቀ) ብር ወይም የውጭ ምንዛሪ የመግዛት ወይም የመሸጥ ውል፤ በ) ከፊደል ተራ (ሀ) እስከ (ቀ) የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ማመቻቸት፤ ወይም ተ) በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ በሚወሰነው መሠረት የእስልምና ባንክ አገልግሎት መስጠት። ‹‹የእረፍት ጊዜ ወይም የሆቴል መስተንግዶ›› ማለት፡ሀ) በሆቴል፣ በሞቴል፣ በኢን፣ በመኝታ ቤቶች፣ በእንግዳ ማረፊያ፣ በሆስቴል ወይም በተመሳሳይ ሌላ ተቋም በተለምዶ በሚሰጥ መስተንግዶ ለበርካታ ሰዎች በቀን፣ በሣምንት፣ በወር ወይም በሌላ በተወሰነ የጊዜ ልዩነት በሚፈጸም ክፍያ አገልግሎት መስጠት፤ ወይም ለ) በዚህ የትርጉም ክፍል ፊደል ተራ (ሀ) ከተመለከተው የመስተንግዶ አቅርቦት ውጪ በግለሰቦች ለአጭር ጊዜ ለሚደረግ ቆይታ የሚሰጥ መስተንግዶ፣ ፲፮ሺ፺፪ ‹‹የረዥም ጊዜ የመድን ስራ›› የሚለው ሐረግ በመድን ስራዎች አዋጅ ቁጥር ፯፻፵፮/፪ሺ፬ (እንደተሻሻለ) የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል። ‹‹የረዥም ጊዜ የመድን ስራ ውል›› ማለት የረዥም ጊዜ የመድን ስራ በማከናወን ሂደት የሚፈጸም የመድን ስራ ውል ነው። ‹‹የሕክምና አገልግሎት›› ማለት በምግብ፣ መድኃኒትና የጤና እንክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፲፪/፪ሺ፲፪ መሠረት ፈቃድ በተሰጠው የጤና ባለሙያ ወይም የሕክምና ባለሙያ በታወቀ የህክምና ተቋም ውስጥ የሚሰጥ የህክምና ሙያ አገልግሎት ነው። ‹‹አነስተኛ መድህን ውል›› የሚለው ሐረግ በመድን ስራዎች አዋጅ ቁጥር ፯፻፵፮/፪ሺ፬ (እንደተሻሻለ) የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል። ‹‹ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት›› ማለት በፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፱፻፸፱/፪ሺ፰ አንቀጽ ፷፭ ንኡስ አንቀጽ (፩) ፊደል ተራ (ነ) አፈጻጸም ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሆኖ የሚቆጠር አካል ነው። ‹‹በሐኪም የሚታዘዝ መድኃኒት›› ማለት በምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፲፪/፪ሺ፲፩ መሠረት በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ የሚወሰድ መድኃኒት ነው። ‹‹የብዙሐን ትራንስፖርት አገልግሎት›› ማለት ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት በስተቀር ለመንገደኞች እና ለግል መገልገያ ዕቃዎቻቸው እንዲሁም ለጭነት ዕቃዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በመንገድ፣ በባቡር ወይም በጀልባ በክፍያ የሚሰጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ነው፡ሀ) ባለሦስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር፣ አሽከርካሪውን ጨምሮ ከስምንት ሰው በታች የመጫን አቅም ያለው ተሽከርካሪን በመጠቀም የሚሰጥ የትራንስፖርት አገልግሎት፤ ለ) ከነሹፌሩ ቢሆንም ባይሆንም የሚሰጥ የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት፤ እና ሐ) ቱሪስቶችን ማጓጓዝ። ‹‹የታወቀ የህክምና ተቋም›› ማለት በደንቡ የተመለከተው የህክምና ተቋም ነው። “የህክምና ሙያ አገልግሎት›› ማለት በደንቡ የተመለከተው የህክምና አገልግሎት ነው። ‹‹የመኖሪያ ቤት›› ማለት ሆቴልን ወይም የእረፍት ጊዜ መኖሪያን ሳይጨምር ለግል መኖሪያነት በማገልገል ላይ የሚገኝ ወይም የሚያገለግል የማይንቀሳቀስ ንብረት ነው። ‹‹ሽያጭ›› ማለት ከመኖሪያ ሕንጻዎች ጋር በተያያዘ የረጅም ጊዜ የሊዝ ውል መስጠትን ወይም ማስተላለፍን ፲፮ሺ፺፫ አባሪ ሦስት (አንቀጽ ፲፩) ከታክስ ነጻ የሆኑ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ከታክሱ ነጻ ተደርገዋል፡ሀ) በቪዬና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ኮንቬንሽን ሚሲዮኖች፣ ዲፕሎማቶች ወይም የኩንሱላር ጽ/ቤቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እስከሆኑ ድረስ እነዚህ ሚሲዮኖች፣ ዲፕሎማቶች ወይም የኩንሱላር ጽ/ቤቶች ወደ ሀገር የሚያስገቡዋቸው ዕቃዎች፤ ለ) በዓለም አቀፍ ስምምነት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የተደረጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፤ ሐ) በፋይናንስ፣ በቴክኒክ፣ በሰብዓዊ ዕርዳታ ወይም በአስተዳደር ድጋፍ የዓለም አቀፍ ስምምነት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እስከተደረገ ድረስ የውጭ ሀገር መንግሥት ወደ ሀገር የሚያስገባቸው ዕቃዎች፤ መ) በጉምሩክ ደንብ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ እስከተደረገ ድረስ መንገደኛው ይዞት የሚመጣ የግል መገልገያ ዕቃ፤ ሠ) ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከሚወስነው እስካልበለጠ ድረስ ተመላሾች ወደ ሀገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፤ ረ) ወደ ሀገር የሚገባ ለግብርና ሥራ ብቻ የሚውል ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የተባይ ማጥፊያ፣ የአረም ማጥፊያ ወይም የፈንገስ ማጥፊያ፤ ሰ) ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚቀርብ ወደ ሀገር የሚገባ ወርቅ፤ ሸ) የውሃ ማከሚያ፤ አጐበር፣ የሕክምና መገልገያ፣ እና የሕክምና መሣሪያ፤ ቀ) በአባሪ ፪ ትርጉም የተሰጠው ወደ ሀገር የሚገባ በሐኪም የሚታዘዝ መድኃኒት፤ በ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር ፭፻፲፯/፪ሺ፲፬ በተደነገገው መሠረት ኢንቨስተሮች ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር የሚያስገቡት ዕቃ፤ ተ) ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር እንዲገቡ የተፈቀዱ የካፒታል ዕቃዎች፤ ቸ) በጉምሩክ ታሪፍ ደንብ ከጉምሩክ ቀረጥና ከማናቸውም ታክስ ነጻ የሆኑ ያልተመደቡ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች፤ እና ኀ) አምቡላንስ እና የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎችና መሣሪያዎች ወደ ሀገር ፲፮ሺ፺፬ In this Proclamation, unless the context otherwise requires: 1/ “Accounting Period” means each calendar month. The months of August and Pagumen shall be aggregated and treated as One calendar month; 2/ “Adjustment Event” in relation to a supply, means: a) the cancellation of the supply, b) the nature of the supply is fundamentally varied or altered, c) the alteration of the consideration for the supply, whether due to an offer of a discount or for any other reason, or d) for a supply of goods; the return of the goods or some of the goods, that are the subject of the supply to the supplier. 3/ “Administrative Penality” means an administrative penalty imposed under
አቅርቦቱ ከተከናወነ በኋላ ተቀባዩ የተላለፈለትን ዕቃ እና አገልግሎት ከታክስ ነጻ የሆኑ አቅርቦቶችን ለማቅረብ ያዋለ ወይም የተላለፉለትን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ለግል ጥቅም ያዋለ እንደሆነ፣ የዚህ አባሪ አንቀጽ ፩ ፊደል ተራ (ሀ) ተፈጻሚ የሆነባቸውን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በተመለከተ ተቀባዩ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት እንዳከናወነ በመቁጠር፡ሀ) ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ታክስ የሚከፈልበት ግብይት በተከናወነበት ጊዜ ከታክሱ ነጻ ለሆነ አቅርቦት ወይም የተላለፈው ዕቃ ወይም አገልግሎት ለግል ጥቅም እንደዋለ ይቆጠራል፤ እና ለ) ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ዋጋ በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ፫ ፊደል ተራ (ሀ) በተገለጸው ጊዜ የዕቃዎቹ ወይም የአገልግሎቶቹ ትክክለኛ የገበያ ዋጋ ነው። The Value Added Tax imposed by this Proclamation is applicable to Taxable Supplies carried out within the territory of Ethiopia, Taxable Imports, and Reverse Charged Supplies made to a person in Ethiopia by a person outside of Ethiopia without a fixed place of business in Ethiopia.
በዚህ አዋጅ የተጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚወሰነው እና የሚሰበሰበው እንደአግባብነቱ በገቢዎች ሚኒስቴር ወይም በጉምሩክ ኮሚሽን ይሆናል። ሆኖም የገቢዎች ሚኒስቴር ስለእርሱ ሆነው የተጨማሪ እሴት ታክስን እንዲወስኑ እና እንዲሰበስቡ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮዎች ውክልና ሊሰጥ ይችላል። The Value Added Tax imposed by this Proclamation shall be assessed and collected by the Ministry of Revenue or the Customs Commission, as appropriate. However, the Ministry of Revenue may delegate the Regional and City Administration Revenue Bureaus to assess and collect the Value Added Tax on its behalf.
፩/ በዚህ አንቀጽ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የአንድ አቅርቦት የግብይት ዋጋ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጠቅላላ ድምር ይሆናል፡- ፲፭ሺ፱፻፺፩ ሀ) ማናቸውም ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለአቅርቦቱ የከፈለው ወይም የሚከፍለው የገንዘብ መጠን፣ ለ) ማናቸውም ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለአቅርቦቱ በዓይነት የከፈለው ወይም የሚከፍለው ትክክለኛ የገበያ ዋጋ፤ ሐ) የዕቃ አቅርቦትን በሚመለከት የዕቃው አቅርቦት ለተፈጸመበት የእቃ መያዣ የተከፈለውን ወይም የሚከፈለውን እና የዕቃው መያዣ ሲመለስ ተመላሽ የሚደረገውን ተቀማጭ ገንዘብ፤ መ) ለአቅርቦቱ የተከፈለው ወይም የሚከፈለው የአገልግሎት ክፍያ፣ እና ሠ) በአቅርቦቱ ምክንያት የተከፈለው ወይም የሚከፈለው ማናቸውም ቀረጥ፣ የኤክሳይዝ ታክስ፣ ሱር ታክስ፣ የአገልግሎት ክፍያ እና ሌሎች ክፍያዎች። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተመለከተው የአቅርቦቱ የግብይት ዋጋ በአቅርቦቱ ላይ የተከፈለውን ወይም ሊከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አይጨምርም። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ከተመለከተው የአቅርቦቱ የግብይት ዋጋ ላይ አቅርቦቱ በተከናወነ ጊዜ የተፈቀደው የዋጋ ቅናሽ ወይም ተመላሽ ተቀናሽ መደረግ አለበት። ፬/ አቅርቦቱ ከተከናወነ በኋላ ከአቅርቦቱ ዋጋ ላይ የተፈቀደው ተቀናሽ፣ ተመላሽ ወይም ሌላ ማስተካከያ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፫ እና ፵፬ በተመለከተው የማስተካከያ ድንጋጌ መሠረት ሊሰላ ይገባል። ፲፭ሺ፱፻፺፪ ፭/ አቅራቢው የተቀማጩን ገንዘብ ለአቅርቦቱ ክፍያ እንዲውል ካላደረገ በስተቀር በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩)(ሐ) የተመለከተውን የተቀማጭ ገንዘብ ሳይጨምር የአቅርቦት የግብይት ዋጋ በተቀማጭ ገንዘብነት የተከፈለውን ወይም የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን አይጨምርም። ፮/ ከአቅርቦት ጋር በተያያዘ የተከፈለ ወይም ሊከፈል የሚገባ መያዣ ለአቅራቢው ቀሪ እንዲሆን ከተደረገ የአዋጁ አንቀጽ ፴፭ ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል። ፯/ የአዋጁ አንቀጽ ፳ ንዑስ አንቀጽ (፯) ተፈጻሚ የሚሆንበትን የዱቤ ግዢ ስምምነት ወይም የፋይናንስ ሊዝ በሚመለከት የዕቃው አቅርቦት ዋጋ በስምምነቱ ወይም በኪራዩ ውል መሠረት የሚከፈለውን የፋይናንስ አገልግሎት ክፍያ አይጨምርም። ፰/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም፡ሀ) ‹‹የኤክሳይዝ ታክስ›› ማለት በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፹፮/፪ሺ፲፪፣ እና በማሻሻያው የተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ ነው። ለ) ‹‹ሱር ታክስ›› ማለት ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ሱር ታክስ ለማስከፈል በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፴፫/፩ሺ፱፻፺፱ የተጣለ ሱር ታክስ ነው። 1/ Subject to this Article, the consideration for a supply shall be the total of the following amounts: a) the amount in money paid or payable by any person, directly or indirectly, for the supply, b) the fair market value of an amount in kind paid or payable by any person, directly or indirectly, for the supply; c) for a supply of goods, a deposit paid or payable for a container in which the goods are supplied that is refundable on the return of the container; d) a service charge paid or payable in respect of the supply, and e) any duty, excise tax, sur-tax, levy, fee, and charge paid or payable on, or by reason of the supply. 2/ The consideration for a supply under Sub- Article (1) of this Article shall not include any VAT paid or payable in respect of the supply. 3/ The amount determined under Sub-Article (1) of this Article as the consideration for a supply shall be reduced by any discounts or rebates allowed and accounted for at the time of supply. 4/ A discount, rebate, or other adjustment to the price for a supply shall be accounted for under the adjustment rules in Articles 43 and 44 of this Proclamation. 5/ The consideration for a supply shall not include a deposit, other than a deposit referred to in Sub-Article (1) (c) of this Article, paid or payable in connection with a supply unless and until the supplier applies the deposit in payment for the supply. 6/ Article 35 of this Proclamation shall apply where a deposit paid or payable in connection with a supply is forfeited to the supplier. 7/ The consideration for a supply of goods made under a hire purchase agreement or finance lease to which Article 20 Sub- Article(7) of this Proclamation applies shall not include any amount payable in relation to the supply of financial services under the agreement or lease. 8/ In this Article: a) “Excise Tax” means excise tax imposed under the Excise Tax Proclamation No. 1186/2020 (as amended); and b) “Sur-Tax” means Sur-tax imposed under the Council of Ministers Regulations No. 133/2007 Council of Ministers Regulations to Provide for the Payment of Sur-tax on Import of Goods.
፩/ በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት የሚባለው የሚከተለው የአገልግሎት አቅርቦት ነው፡ሀ) የተመዘገበ ሰው ቢሆንም ባይሆንም፤ አቅርቦቱ የተከናወነው ከኢትዮጵያ ውጪ ባለ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት በሚሠራ ድርጅት አማካኝነት ታክስ የሚከፈልበትን የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ በማያከናውን ሰው አማካኝነት ከሆነ፣ ፲፭ሺ፱፻፺፫ ለ) አቅርቦቱ የተሰጠው ለተመዘገበ ሰው፣ ለመንግስት ተቋም ወይም ከፍተኛ ግብይት ላለው ያልተመዘገበ ሰው ከሆነ፣ እና ሐ) አቅርቦቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኝ የንግድ ሥራ ቦታ ቢሰጥ ኖሮ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት የሆነ እንደሆነ ነው። ፪/ የተመዘገበ ወይም ከፍተኛ ግብይት ያለው ያልተመዘገበ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ታክስ የሚከፈልበት የሥራ እንቅስቃሴ የሚያከናውን ሆኖ፤ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚያከናውነው የስራ እንቅስቃሴ (ከዚህ በኋላ ‹‹የውጭ ሀገር የስራ ክፍል›› ተብሎ የሚጠራው) ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የሥራ እንቅስቃሴ (ከዚህ በኋላ ‹‹ኢትዮጵያ የሚገኝ የስራ ክፍል›› ተብሎ ለሚጠራው) የውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ፤ የተሰጠው የውስጥ አገልግሎት ከታክሱ ነጻ የተደረገ ካልሆነ በስተቀር በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ይሆናል። ፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በውጭ ሀገር የሥራ ክፍል እና በኢትዮጵያ የስራ ክፍል መካከል የተደረገው አቅርቦት በሁለት ግንኙነት ባላቸው ሰዎች መካከል የተከናወነ ግብይት ሆኖ ይቆጠራል። 1/ A reverse charged supply is a supply of services where: a) the supply is made by a person outside Ethiopia, whether or not a registered person, who does not carry on a taxable activity through a fixed place of business in Ethiopia, b) the supply is made to a registered person, Government institution or a large unregistered person, and c) the supply would have been a taxable supply if the supply had been made from a place of business in Ethiopia. 2/ Where a registered person or large unregistered person carries on a taxable activity both in and outside Ethiopia and there is an internal provision of services from the part of the taxable activity carried on outside Ethiopia (referred to as the “overseas part”) to the part of the taxable activity carried on in Ethiopia (referred to as the “Ethiopia part”), the internal provision of services shall be treated as a reverse charged supply unless the provision of the services is an exempt supply. 3/ Where Sub-Article (2) of this Article applies, the overseas part and Ethiopia part shall be treated as separate persons that are related persons for the purposes of this Proclamation.
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ እና በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ማናቸውም በተከታታይነት ወይም በመደበኛነት እና በሙሉ ወይም በከፊል የግብይት ዋጋን በማስከፈል አንድ ሰው ለሌላ ሰው የሚያቀርበው ወይም ለማቅረብ የሚፈልገው ዕቃ ወይም አገልግሎት ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ይሆናል። ፲፭ሺ፱፻፺፬ ፪/ ማናቸውም ሰው ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ በማስጀመር፣ በማቋረጥ ወይም መልሶ በማደራጀት ረገድ የሚያከናውነው ማናቸውም ሥራ ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት የተከናወነ እንደሆነ ይቆጠራል። ፫/ የሚከተሉት ታክስ የሚከፈልበት የሥራ እንቅስቃሴ ሆነው አይቆጠሩም፡ሀ) ተቀጣሪ የሚያከናውነው ሥራ፣ ለ) ማናቸውም ግለሰብ ለትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ ወይም ለመዝናናት የሚያከናውነው እንቅስቃሴ፣ ወይም ሐ) ከግለሰብ ውጪ ማናቸውም ሌላ ሰው ለማህበርተኞቹ ወይም ለባለቤቶቹ ወይም ግንኙነት ላላቸው ሰዎች ጥቅም የሚያከናውነው የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ ወይም የመዝናኛ እንቅስቃሴ። 1/ For the purposes of this Proclamation and subject to Article 6 of this Proclamation and Sub-Article (3) of this Article, any activity carried on continuously or regularly by a person that involves, or is intended to involve, in whole or part, the supply of goods or services to any other person for consideration shall be a taxable activity. 2/ Any activity done by a person in the course of commencing, terminating, or reorganising a taxable activity shall be treated as done in the course or furtherance of the taxable activity. 3/ The following shall not be treated as a taxable activity: a) the activity of an employee, b) a hobby or recreational activity of an individual, or c) an activity of a person, other than an individual, that is essentially carried on as a hobby or recreational activity for the benefit of a member or owner of the person or a related person.
ሸ) አገልግሎቱ በዚህ ፊደል ተራ (ረ) ተፈጻሚነት ባለው የአገልግሎት አቅርቦት አካል ሆኖ የሚቀርበው በአንድ አቅራቢ እስከሆነ ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ነው፤ ቀ) አገልግሎቱ የዚህ ፊደል ተራ ፊደል (ሀ) ተፈጻሚ ለሚደረግባቸው አገልግሎቶች የሚውል የመድን አገልግሎት፣ የመድን አገልግሎትን ማመቻቸት ወይም መንገደኞችን እና ዕቃዎችን የማጓጓዝ አገልግሎት ከሆነ፤ በ) አገልግሎቱ ረዳት የትራንስፖርት አገልግሎት ሆኖ ከኢትዮጵያ ውጭ ላሉ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የንግድ አድራሻ ለሌላቸው ሰዎች የሚቀርብ ከሆነ። ፪. ለሚከተሉት አገልግሎቶች አቅርቦት በዚህ ክፍል ፩ ፊደል ተራ (ሀ) መሠረት ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ አይደረግም፡ሀ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወን የቱሪዝም አገልግሎት ሲሆን፤ ለ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወን የቱሪዝም አገልግሎት እንቅስቃሴን ማመቻቸትን የሚመለከቱ ሲሆን፤ እና ሐ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝን የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚመለከቱ ሲሆን። 1/ Value added tax shall be imposed at the rate specified in Sub-Article (2) of this Article on the following: a) a taxable supply made by a registered person; b) a taxable import made by any person; and c) a reverse charged supply made to a registered person, Government entity or large unregistered person. 2/ The rate of VAT shall be: a) for a taxable supply that is a Zero-rated supply, Zero percent, or b) in any other case 15 percent. 3/ The amount of VAT payable in respect of a taxable supply, taxable import, or reverse charged supply shall be calculated by applying the rate specified in Sub-Article (2) of this Article to the value of the supply or import. 4/ The liability for VAT on a taxable supply arises at the time of the supply and shall be accounted for to the Tax Authority by the registered person making the supply in accordance with Article 59 Sub-Article(1) of this Proclamation. 5/ Despite anything contained in any law but subject to Sub-Article (6) of this Article, the VAT payable by a registered person in respect of a taxable supply shall be recoverable by the person from the recipient of the supply. 6/ Sub-Article (5) of this Article shall not apply to taxable supplies made by a person registered by the Tax Authority under Article 14 Sub-Article (2) of this Proclamation that are made prior to the date that the person is actually registered by the Tax Authority. 7/ The liability for VAT on a taxable import arise at the time of the import and shall be payable by the importer in accordance with Article 59 Sub-Article (3) of this Proclamation but subject to Article 28 of this Proclamation. 8/ The liability for VAT on a reverse charged supply arises at the time of the supply and shall be accounted for to the Tax Authority by the registered person, Government entity, or large unregistered person receiving the supply in accordance with Article 59 Sub-Article (1) or (2) of this Proclamation.
፩/ ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ፩ የተመለከቱ አቅርቦቶች ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ ይደረግላቸዋል። ፪/ በአቅርቦቱ ላይ ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ እንዲሆን ያደረገ የተመዘገበ ሰው በታክሱ ባለስልጣን ተቀባይነት ያላቸውን አቅርቦቱ ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ እንዲሆንለት ለማድረግ ያስቻሉትን የሰነድ ማስረጃዎች መቀበል እና መያዝ አለበት። 1/ A supply specified in Schedule 1 attached to this Proclamation shall be a Zero-rated supply. 2/ A registered person who has treated a supply as a Zero-rated supply shall obtain and retain such documentary proof acceptable to the Tax Authority substantiating the person’s entitlement to treat the supply as a Zero-rated supply.
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ፪ የተዘረዘሩ አቅርቦቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ተደርገዋል። ፪/ አንድ አቅርቦት ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ የሚደረግለት እንዲሁም ከታክሱ ነጻ የተደረገ ከሆነ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ዜሮ የማስከፈያ ልክ ብቻ ተፈጻሚ እንዲሆንለት ይደረጋል። 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article, a supply specified in Schedule 2 attached to this Proclamation shall be an exempt supply. 2/ A supply that is both a Zero-rated supply and an exempt supply shall be treated only as a Zero-rated supply for the purposes of this Proclamation.
ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ፫ የተዘረዘሩ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ተደርገዋል። ፲፭ሺ፱፻፺፯ An import specified in Schedule 3 attached to this Proclamation shall be an exempt import.
፩/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፯ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ማናቸውም ሰው ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የሚያሟላ ከሆነ የመመዝገብ ግዴታ አለበት። ሀ) በማናቸውም የ፲፪ ወራት ጊዜ መጀመሪያ በዚህ ሰው የሚከናወነው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ጠቅላላ ድምር በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ከተመለከተው የገንዘብ መጠን ሊበልጥ እንደሚችል የሚያሳምን ምክንያት ሲኖር፣ ወይም ለ) በማናቸውም የ፲፪ ወራት ጊዜ መጨረሻ ወይም ከዚህ ባነሰ ጊዜ ውስጥ በዚህ ሰው የተከናወነው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ጠቅላላ ድምር በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ከተመለከተው የገንዘብ መጠን የሚበልጥ ሆኖ ሲገኝ። ፪/ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የመመዝገብ ግዴታ የሚኖረው ብር ፪ ሚሊዮን (ሁለት ሚሊዮን ብር) የጠቅላላ አቅርቦት ድምር ሲኖር ወይም ሚኒስቴሩ በመመሪያ የሚወስነው ሌላ ታክስ የሚከፈልበት የአቅርቦት የገንዘብ መጠን ያለው ሰው ነው። ፫/ የታክሱ ባለስልጣን አንድ ሰው የመመዝገብ ግዴታ ከሚያስከትለው የገንዘብ መጠን መድረሱን በሚያሰላበት ጊዜ ከዚህ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው ሰው ያከናወነውን ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ጨምሮ መደመር አለበት። ፬/ አንድ ሰው የመመዝገብ ግዴታ የሚያስከትለው የገንዘብ መጠን ላይ መድረሱ በሚሰላበት ጊዜ የሚከተሉት ታክስ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች ከግምት ውስጥ አይገቡም፡- ፲፭ሺ፱፻፺፰ ሀ) ይህ ሰው ለሚያከናውነው ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ጥቅም ላይ የዋለን የካፒታል ዕቃ ሽያጭ የሚመለከት ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት፣ ለ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፭ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንድ ሰው የሚያከናውነውን ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በመሸጡ ምክንያት ወይም ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ በዘላቂነት በማቆሙ ምክንያት የሚኖረውን ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት። ፭/ የአንድ ሰው ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ወይም የዚህ ሰው ከፊል ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ በሙሉ ወይም በከፊል ገዝቶ መሸጥ በሚሆንበት ጊዜ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፬ ፊደል ተራ ፊደል (ለ) ድንጋጌ ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ በሙሉ ውይም በከፈል ገዝቶ በመሸጥ ተግባር ላይ ተፈጻሚ አይሆንም። ፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የመመዝገብ ግዴታ ያለበት ሰው የመመዝገብ ግዴታ ከሚኖርበት ቀን አንስቶ በ፯ ቀናት ውስጥ የጸደቀውን ቅጽ በመጠቀም ወይም በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ለታክሱ ባለስልጣን የምዝገባ ማመልከቻ ማቅረብ አለበት። ፯/ ከንግድ ሥራ ወይም በተመሳሳይ አቅርቦት ሥራ ላይ ከተሰማራ የንግድ ሥራ ጋር ተወዳዳሪ በሆነ አኳኃን በመደበኛነት በእቃ አቅርቦት ወይም አገልግሎት በመስጠት ሥራ ላይ የተሰማራን የመንግስት ተቋም አይጨምርም። ፲፭ሺ፱፻፺፱ ፰/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፯ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት የሚያከናውን የመንግሥት ተቋም በዚህ አንቀጽ መሰረት የመመዝገብ ግዴታ የለበትም፤ ሆኖም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፫ መሠረት በፈቃደኝነት ለመመዝገብ ሊያመለክት ይችላል። 1/ Subject to Sub-Article (7), a person shall be liable to be registered. a) at the beginning of any period of 12 calendar months, if there are reasonable grounds to believe that the total value of taxable supplies to be made by the person in that period will exceed the registration threshold specified in Sub- Article (2) of this Article, or b) at the end of any period of 12 calendar months or a lesser period, if, during the period, the total value of taxable supplies made by the person exceeds the registration threshold specified in Sub- Article (2) of this Article. 2/ The registration threshold is 2,000,000 Birr or such other amount as specified in the Directive to be issued by the Ministry. 3/ The Tax Authority may, in determining whether a person exceeds the registration threshold, have regard to the value of taxable supplies made by a related person. 4/ In determining whether a person exceeds the registration threshold, the value of the following taxable supplies shall be ignored: a) a taxable supply that is the sale of capital goods used in the taxable activity of the person, and (b) subject to Sub-Article (5) of this Article, a taxable supply made solely as a consequence of the person selling the whole or a part of the person’s taxable activity or permanently ceasing to carry on the person’s taxable activity. 5/ Sub-Article (4) (b) of this Article shall not apply to the sale of the whole or part of a person’s taxable activity if the person’s business involves the acquisition and sale of taxable activities or parts of taxable activities. 6/ A person, who is liable to be registered under Sub-Article (1) of this Article, shall apply to the Tax Authority, in the approved form, for registration within 7 days of becoming liable to be registered. 7/ It does not include a Government institution that is engaged in regular supply or service in a competitive environment with a business or a similar supply business. 8/ Subject to Sub-Article (7) of this Article a Gove rnment entity making taxable supplies shall not be liable to be registered under this Article but may apply for voluntary registration in accordance with Article 13 of this Proclamation.
፩/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ መሠረት የመመዝገብ ግዴታ የሌለበት ሰው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት የሚያከናውን ከሆነ ወይም ለማከናወን ያቀደ ከሆነ በፈቃደኝነት ለመመዝገብ ለታክሱ ባለስልጣን ማመልከቻ ሊያቀርብ ይችላል። ፪/ አንድ ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የምዝገባ ማመልከቻ ሊያቀርብ የሚችለው የዚህ ሰው በዓመቱ ያከናወነው ወይም ሊያከናውን የሚችለው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦቱ ዋጋ ከብር ፩ ሚሊዮን (አንድ ሚሊዮን ብር) ወይም ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከሚወስነው ሌላ የገንዘብ መጠን የሚበልጥ ሲሆን ነው። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የሚቀርበው ማመልከቻ የጸደቀውን ቅጽ በመጠቀም መቅረብ አለበት። 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article, a person who makes, or intends to make, taxable supplies, but who is not liable to be registered under Article 12 of this Proclamation, may apply to the Tax Authority for voluntary registration. 2/ A person may make an application under Sub-Article (1) of this Article only if the annual value of taxable supplies made, or to be made, by the person exceeds 1,000,000 Birr or more than the amount of money determined by directive issued by Minister. 3/ An application under Sub-Article (1) of this Article shall be in the approved form.
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ መሠረት የምዝገባ ማመልከቻ የቀረበለት የታክስ ባለስልጣን አመልካቹ የመመዝገብ ግዴታ ያለበት መሆኑን ሲያምንበት ይመዘግበዋል። ፪/ የታክሱ ባለስልጣን በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ መሠረት የመመዝገብ ግዴታ ያለበት ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ (፮) በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ለመመዝገብ ማመልከቻ ያላቀረበ መሆኑን ሲያረጋግጥ በራሱ ውሳኔ እንዲመዘገብ ያደርጋል። ፲፮ሺ ፫/ የታክሱ ባልስልጣን በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፫ መሠረት የምዝገባ ማመልከቻ ያቀረበ ሰው የሚከተሉትን ሁኔታዎች ማሟላቱን ሲያረጋግጥ መመዝገብ አለበት። ሀ) አመልካቹ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፫ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተመለከቱትን ሁኔታዎች የሚያሟላ ከሆነ፣ ለ) አመልካቹ ታክስ የሚከፈልበትን የስራ እንቅስቃሴ የሚያከናውንበት አድራሻ ያለው ወይም ታክስ የሚከፈልበት የስራ እንቅስቃሴ የኢንተርኔት አድራሻን፤ የማህበራዊ ሚዲያ አድራሻን ወይም ሌላ የኤሌክትሮኒክ መድረክ በመጠቀም የሚያከናውን ከሆነ፤፣ ሐ) አመልካቹ ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ ማከናወን የጀመረ ከሆነ፡- (1) የሥራ እንቅስቃሴውን የሚያሳዩ ተገቢ ሰነዶችን የያዘ ከሆነ፣ እና (2) በታክስ ሕጐች የተጣሉበትን ግዴታዎች የተወጣ ከሆነ፣ እና መ) ተገቢ የሆነ ሰነዶችን መያዝ እና በቋሚነት እና አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢን ማሳወቅን ጨምሮ አመልካቹ በዚህ አዋጅ እና አዋጁን መሠረት በማድረግ በወጡ ደንቦችና መመሪያዎች የተጣሉበትን ግዴታዎች የሚወጣ መሆኑን የሚያሳምኑ መረጃዎች ያሉ ከሆነ ነው። ፬/ የታክሱ ባለሥልጣን በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ እና ፲፫ መሠረት የምዝገባ ማመልከቻ ከቀረበለት ቀን አንስቶ በ፳፩ ቀናት ውስጥ በቀረበው ማመልከቻ ላይ የሰጠውን ውሳኔ የሚገልዕ ምላሽ ለአመልካቹ መስጠት አለበት። ፲፮ሺ፩ ፭/ የታክሱ ባለስልጣን በዚህ አንቀጽ መሠረት ለተመዘገበው ሰው በደንቡ የተዘረዘሩ መረጃዎችን የያዘ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት መስጠት አለበት። ፮/ ከአንድ የንግድ ሥራ ቦታ በላይ ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ የሚያከናውን የተመዘገበ ሰው የጸደቀውን ቅጽ በመጠቀም ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ቦታ የሚያገለግል የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ይፋዊ ቅጂ እንዲሰጠው ለታክሱ ባለስልጣን ማመልከቻ ማቅረብ የሚችል ሲሆን፣ የታክሱ ባለስልጣንም ይፋዊ ቅጂ ወይም ቅጂዎችን መስጠት አለበት። ፯/ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም አንድ ሰው ‹‹የተመዘገበ ሰው›› ነው ሊባል የሚችለው፡ሀ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ወይም (፫) መሠረት ለተመዘገበ ሰው በዚህ ሰው የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ላይ ከተመለከተው ቀን ጀምሮ፣ወይም ለ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት ለተመዘገበ ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ (፩) በተደነገገው መሠረት ይህ ሰው የመመዝገብ ግዴታ ከተጣለበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ነው። 1/ The Tax Authority shall register a person who has applied for registration under Article 12 of this Proclamation if satisfied that the person is liable to be registered. 2/ The Tax Authority shall, on its own motion, register a person who is liable to be registered under Article 12 of this Proclamation but who has not applied for registration within the time limit specified in Article 12(6) of this Proclamation. 3/ The Tax Authority shall register a person who has applied for registration under Article 13 of this Proclamation, but only if all of the following conditions are satisfied. a) the person satisfies the requirement in Article 13 Sub-Article (2) of this Proclamation, b) the person has a place from which the person carries on their taxable activity, or the taxable activity is carried on through an internet address, social media account, or other electronic platform, c) if the person has commenced carrying on a taxable activity, the person: (i) has kept proper records of its operations, and (ii) complied with its obligations under other tax laws, and d) there are reasonable grounds to believe that the person will comply with their obligations under this Proclamation, and any Regulations and Directives made under this Proclamation, including keeping proper records, and filing regular and reliable VAT returns. 4/ The Tax Authority shall, within 21 days after receipt of an application under Article 12 or 13 of this Proclamation, serve the applicant with a notice in writing of the Tax Authority’s decision on the application. 5/ The Tax Authority shall issue a person registered under this Article with a VAT registration certificate specifying the particulars required by the Regulations. 6/ A registered person who carries on a taxable activity at more than one place of business shall apply to the Tax Authority, in the approved form, for an official copy of the person’s VAT registration certificate for each place of business, and the Tax Authority shall issue the person with such copy or copies. 7/ A person shall be a “Registered Person” for the purposes of this Proclamation: a) for a person registered under Sub-Article (1) or (3) of this Article, from the date set out in the person’s VAT registration certificate, or b) for a person registered under Sub- Article (2) of this Article, from the date on which the person first became liable to be registered under Article 12 Sub- Article (1) of this Proclamation.
፩/ ታክስ የሚከፈልበትን የስራ እንቅስቅሴ በማይንቀሳቀስ የሥራ ቦታ የሚያከናውን ማናቸውም የተመዘገበ ሰው፡ሀ) ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ በሚያካሂድበት ዋንኛ የስራ ቦታ በግልጽ በሚታይ ሥፍራ ዋናውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የመለጠፍ፣ ፲፮ሺ፪ ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ ንዑስ አንቀጽ (፭) መሠረት የተሰጠውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ቅጂ ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ በሚያካሂድባቸው ሌሎች የስራ ቦታዎች ሁሉ በግልጽ በሚታይ ሥፍራ የመለጠፍ፣ ግዴታ አለበት። ፪/ የተመዘገበ ሰው ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ዝርዝር መረጃ ታክስ የሚከፈልበትን ስራ በሚያከናውንበት ዌብሳይት፤ የማህበራዊ ሚዲያ እና ሌላ የኤሌክትሮኒክ መድረክ ላይ ማስፈር አለበት። ፫/ በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ ፲ ከተዘረዘሩት መረጃዎች በተጨማሪ በሚከተሉት መረጃዎች ላይ ለውጥ ሲያጋጥም የተመዘገበ ሰው ይህንኑ በ፴ ቀን ጊዜ ውስጥ ለታክሱ ባለስልጣን ማስታወቅ አለበት። ሀ) የተመዘገበው ሰው የስልክ ቁጥር፣ የፋክስ ቁጥር፣ የኤሌክትሮኒክ እና ሌሎች የግንኙነት አድራሻዎች፣ ለ) አዳዲስ ቅርንጫፎችን ወይም የሥራ ክፍሎችን መክፈትና መዝጋትን እንዲሁም የኢንተርኔት፤ የማህበራዊ ሚዲያ ወይም ለንግድ ስራ እንቅስቃሴ ጥቅም ላይ የሚውል ሌላ የኤሌክትሮኒክ መድረክ አድራሻ መለወጥን ጨምሮ የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ በሚያከናውንበት ቦታ ወይም በሚያከናውንባቸው ቦታዎች፣ ሐ) የተመዘገበው ሰው የንግድ ሥራ ባህሪ፣ እና መ) በሚኒስቴሩ በሚወጣ መመሪያ የሚዘረዘሩ ሌሎች መረጃዎች። ፲፮ሺ፫ 1/ A registered person carrying on a taxable activity at physical premises shall display: a) the original of the person’s VAT registration certificate in a conspicuous place at the main business premises where the person carries on their taxable activity, and b) an official copy of the person’s VAT registration certificate issued under Article 14 Sub-Article (5) of this Proclamation in a conspicuous place at every other premises where the person carries on their taxable activity. 2/ A registered person must specify their VAT registration details on any website, social media account, and any other electronic platform through which the person carries on their taxable activity. 3/ In addition to the matters specified in Article 10 of the Tax Administration Proclamation, a registered person shall notify the Tax Authority, in writing, within 30 days of a change occurring for any of the following. a) the phone, facsimile, electronic, and other contact details of the registered person, b) the place or places through which the registered person carries on their taxable activity, including the opening or closing of new branches or divisions or a change in the person’s internet address, social media account, or other electronic platform used for business purposes, c) the nature of the business of the registered person, and d) any other matter as specified in a Directive to be issued by the Ministry.
፩/ የተመዘገበ ሰው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ማከናወኑን ሲያቆም ይህንኑ ለታክሱ ባለስልጣን ማስታወቅ አለበት። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የተመዘገበ ሰው የሚሰጠው ማስታወቂያ፡ሀ) በተፈቀደው ቅጽ በመጠቀም የሚቀርብ፣ ለ) የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ማከናወኑን ያቆመበትን ቀን፣ ሐ) በዚህ ፊደል ተራ ፊደል (ለ) ከተመለከተው ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ፲፪ ወራት ውስጥ የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ለማከናወን ፍላጐት ያለው ወይም የሌለው መሆኑን የሚገልጽ ሲሆን፣ እና መ) የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ካቆመበት ቀን አንስቶ በ፯ ቀናት ውስጥ መቅረብ አለበት። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የታክሱ ባለስልጣን ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ማከናወኑን ያቆመን የተመዘገበ ሰው የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የሚቀርብለትን ማስታወቂያ መሠረት በማድረግ ወይም በራሱ አነሳሽነት ለተመዘገበው ሰው የጽሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት ለመሠረዝ ይችላል። ፬/ የታክሱ ባለስልጣን የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ማከናወኑን ካቆመበት ቀን አንስቶ በ፲፪ ወራት ጊዜ መልሶ የሚጀምር መሆኑን የሚያሳምን በቂ ምክንያት ካገኘ፤ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) መሠረት ምዝገባውን በመሰረዝ ፈንታ የተመዘገበውን ሰው የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የማገድ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል። ፲፮ሺ፬ ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፫ መሠረት የተሰጠ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀትን የመሠረዝ ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ማከናወን ካቆመበት የሒሣብ ጊዜ የመጨረሻ ቀን ወይም በስረዛው ውሳኔ ማስታወቂያ ከተገለጸው ቀን ጀምሮ ይሆናል። ፮/ ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት የማከናወኑን ተግባር በጊዜያዊነት ያቋረጠ የተመዘገበ ሰው የጸደቀውን ቅጽ በመጠቀም ምዝገባው ለ፲፪ ወራት እንዲታገድለት ሊያመለክት ይችላል። ፯/ የታክሱ ባለስልጣን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፮ መሠረት ማመልከቻ ያቀረበው የተመዘገበ ሰው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ማከናወኑን ያቋረጠ መሆኑን እና ማመልከቻው ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር የ፲፪ ወራት ጊዜ ውስጥ መልሶ ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት የሚያከናውን መሆኑን ሲያምንበት ምዝገባውን ሊያግድ ይችላል። ፰/ የተመዘገበ ሰው ምዝገባ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፬ ወይም ፯ መሠረት ሊታገድ የሚችለው በደንቡ በሚዘረዘሩ ሁኔታዎች እና ግዴታዎች እንዲሁም የታክሱ ባለስልጣን ለተመዘገበው ሰው በሚሰጠው የእገዳ ማስታወቂያ በሚዘረዘሩ ሁኔታዎች እና ግዴታዎች መሰረት ይሆናል። ፲፮ሺ፭ Ceasing to Make Taxable Supplies 1/ A registered person shall notify the Tax Authority if the person has ceased to make taxable supplies. 2/ A notification by a registered person under Sub-Article (1) of this Article shall: a) be in the approved form, b) state the date upon which the registered person ceased to make taxable supplies, (c) state whether or not the registered person intends to make taxable supplies within 12 calendar months from the date mentioned in Paragraph (b) of this Sub- Article, and d) be filed with the Tax Authority within 7 days of the date the person ceased to carry to make taxable supplies. 3/ Subject to Sub-Article (4) of this Article, the Tax Authority shall, by notice in writing, cancel the registration of a person who has ceased to make taxable supplies either on notification by the person under Sub-Article (1) of this Article or on the Tax Authority’s own motion. 4/ Instead of cancelling the registration of a person under Sub-Article (3), the Tax Authority may decide to suspend the person’s registration where there are reasonable grounds to believe that the person will recommence making taxable supplies at any time within 12 calendar months from the date of cessation of making taxable supplies. 5/ The cancellation of the VAT registration of a person under Sub-Article (3) of this Article shall take effect from the last day of the accounting period in which the person ceased to make taxable supplies or from such later date as set out in the notice of cancellation. 6/ A registered person who temporarily ceases to make taxable supplies may apply to the Tax Authority, in the approved form, for a suspension of the person’s registration for a maximum period of 12 calendar months. 7/ The Tax Authority may suspend the registration of a person who has applied under Sub-Article (6) of this Article if satisfied that the person has ceased to make taxable supplies and will recommence making taxable supplies within 12 calendar months of the application being lodged. 8/ The suspension of the registration of a registered person under Sub-Articles (4) or (7) is subject to such conditions and obligations as may be specified in the regulations and the notice of suspension served by the Tax Authority on the registered person.
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የተመዘገበው ሰው የሚያከናውነው ዓመታዊ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ዋጋ የመመዝገብ ግዴታን ከሚያስከትለው የገንዘብ መጠን ሲወርድ የተመዘገበው ሰው የተፈቀደውን ቅጽ በመጠቀም ምዝገባው እንዲሰረዝለት ሊያመለክት ይችላል። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፫ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት ምዝገባ እንዲሰረዝ ጥያቄ ሊቀርብ የሚችለው ምዝገባው ከተከናወነበት ቀን ጀምሮ ከሚቆጠር የ፪ ዓመት ጊዜ በኋላ ነው። ፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ቢኖርም ለተጨማሪ እሴት ታክስ የመመዝገብ ግዴታ ያለበት መሆኑን በማመን በስህተት የተመዘገበ ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የምዝገባ ሥረዛ ማመልከቻውን ከተመዘገበበት ቀን በኋላ የመጀመሪያውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማስታወቂያ ማቅረብ ከሚገባው ቀን በፊት ሊያቀርብ ይችላል። ፬/ የታክሱ ባለስልጣን የተመዘገበው ሰው በአንድ ዓመት ውስጥ ያከናወነው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ዋጋ የመመዝገብ ግዴታን ከሚያስከትለው የገንዘብ መጠን በታች መሆኑን ሲያምንበት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ምዝገባው እንዲሠረዝ ተገቢውን ማመልከቻ ላቀረበው የተመዘገበ ሰው የጽሁፍ ማስታወቂያ በመስጠት ምዝገባውን ሊሰርዝ ይችላል። ፲፮ሺ፮ ፭/ የታክሱ ባለስልጣን የተመዘገበው ሰው በአንድ ዓመት ውስጥ ያከናወነው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ የመመዝገብ ግዴታን ከሚያስከትለው የገንዘብ መጠን በታች ሲሆን፣ እንዲሁም የታክሱ ባለስልጣን ከሚከተሉት ሁለቱ ወይም ከሁለቱ አንዱ መፈጸማቸውን ሲያምንበት፡ሀ) የተመዘገበው ሰው ተገቢ የሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃዎችን ወይም በዚህ አዋጅ የተመለከቱ ሰነዶችን ያለመያዙን ፣ ለ) የተመዘገበው ሰው በመደበኛነት እና በአስተማማኝነት የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢውን የማያስታውቅ መሆኑን ሲያምንበት፣ በራሱ ተነሳሽነት ለተመዘገበው ሰው የጽሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት ምዝገባውን ሊሠርዝ፣ ይችላል። ፮/ በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚከናወን የምዝገባ ሥረዛ ተፈጻሚ የሚሆነው በሥረዛ ማስታወቂያው ከተመለከተው ቀን ጀምሮ ይሆናል። Registration when Below the Registration Threshold 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article, a registered person may apply to the Tax Authority, in the approved form, for cancellation of the person’s registration if the total annual value of the taxable supplies made by the person is below the registration threshold. 2/ Subject to Sub-Article (3) of this Article, an application for cancellation of registration under Sub-Article (1) of this Article may be made only after the expiration of 2 years from the date of registration. 3/ Despite Sub-Article (2) of this Article, an application under Sub-Article (1) of this Article by a person who mistakenly believed that they were required to apply for registration may be made before the due date for filing the person’s First VAT return after being registered. 4/ The Tax Authority shall, by notice in writing, cancel the registration of a person who has properly applied for cancellation of registration under Sub-Article (1) of this Article if satisfied that the total annual value of the taxable supplies made by the person does not exceed the registration threshold. 5/ The Tax Authority may, on its own motion and by notice in writing, cancel the registration of a person where the total annual value of the taxable supplies made by the person is below the registration threshold and the Tax Authority is satisfied of either or both of the following: a) the person has not kept proper VAT records or provided VAT documentation as required under this Proclamation; b) the person has not filed regular and reliable VAT returns. 6/ The cancellation of a person’s registration under this Article shall take effect from the date specified in the notice of cancellation.
፩/ አንድ ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፮ ወይም ፲፯ መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የተሰረዘበት እንደሆነ፡ሀ) ታክስ የሚከፈልበትን የስራ እንቅስቃሴ ለማከናወን የሚጠቀምባቸውን ማናቸውንም ሰነዶች እና ማናቸውንም ዌብሳይት፤ ማህበራዊ ሚዲያ ወይም ሌላ የኤሌክትሮኒክ መድረክ ጨምሮ በማናቸውም መልኩ ይህ ሰው ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ መሆኑን የሚገልጹ ድርጊቶችን ወዲያውኑ ማቆም፣ ፲፮ሺ፯ ለ) ምዝገባው ከተሰረዘበት ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወይም የታክሱ ባለስልጣን በሚሰጠው የጽሑፍ ማስታወቂያ በሚገለጽ ቀደም ያለ ሌላ ጊዜ ውስጥ፣ የጸደቀውን ቅጽ በመጠቀም የመጨረሻውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የገቢ ማስታወቂያ ማቅረብ እና የሚፈለግበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል፣ እና ሐ) የተሰጠውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ዋና የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የዚህን የምስክር ወረቀት ይፋዊ ቅጂዎች ወዲያውኑ ለታክሱ ባለስልጣን የመመለስ፣ ግዴታ አለበት። ፪/ የተመዘገበ ሰው የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢውን በማስታወቅ እና የተጨማሪ እሴት ታክስን በመክፈል ረገድ ያለበትን ግዴታ ጨምሮ ምዝገባው ጸንቶ በነበረበት ጊዜ ውስጥ ካከናወናቸው ተግባራት ወይም ካልፈጸማቸው ግዴታዎች ጋር በተያያዘ የሚኖርበት ግዴታ እና ተጠያቂነት ምዝገባው በመሰረዙ ምክንያት ቀሪ አይሆንም። ፫/ ምዝገባው በሚሰረዝበት ቀን ያልተቀናነሰው የግብአት ታክስ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፱ በተመለከተው መሠረት እንዲፈጸም ይደረጋል። ፲፮ሺ፰ Registration 1/ If a person’s VAT registration is cancelled under Article 16 or 17 of this Proclamation, the person shall: (a) immediately cease to hold out that the person is a registered person, including on any documentation used by the person and on any website, social media account, or other electronic platform through which the person carries on their taxable activity, (b) file a final VAT return in the approved form and pay all VAT due, including the VAT due as a result of the application of Article 19 of this Proclamation, within one month after the date of cancellation of the person’s registration or by such earlier date as notified by the Tax Authority in writing, and (c) immediately return the person’s VAT registration certificate, and any official copies of the certificate, to the Tax Authority. 2/ The obligations and liabilities of a person under this Proclamation, including the filing of VAT returns and payment of VAT, in respect of anything done or omitted to be done by that person while being a registered person shall not be affected by cancellation of the person’s registration. 3/ The treatment of any excess input tax credit at the date of cancellation of registration is set out in Article 49 of this Proclamation.
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፯ እና ፲፰ መሠረት የተመዘገበ ሰው የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የተሰረዘ እንደሆነ ምዝገባው በተሰረዘ ጊዜ በእጁ የሚገኙትን የንግድ ዕቃዎች እና የካፒታል እቃዎች አቅርቦት እንዳከናወነ ይቆጠራል። ሆኖም እነዚህ ዕቃዎች ታክስ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች እንደሆኑ የሚቆጠረው የተመዘገበው ሰው እነዚህን የንግድ ዕቃዎች ወይም የካፒታል ዕቃዎች ሲገዛ ወይም ወደ ሀገር ሲያስገባ ለከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተቀናሽ (ክሬዲት) ያገኘ ወይም የንግድ ዕቃዎችን በሚመለከት ለእነዚህ ዕቃዎች ማምረቻ የዋሉ ግብአቶችን ሲገዛ ወይም ወደ ሀገር ሲያስገባ ለከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተቀናሽ ያገኘ እንደሆነ ነው። ፪/ የተመዘገበው ሰው ምዝገባው ከመሰረዙ በፊት ባለው ጊዜ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የንግድ ዕቃዎች ወይም የካፒታል ዕቃዎች ታክስ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች እንዲሆኑ የማድረግ ተግባር ያከናወነ እንደሆነ ተደርጐ ይቆጠራል። ፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ተፈጻሚ ሲሆን፣ ምዝገባው በተሰረዘ ጊዜ የንግድ ዕቃዎች በእጁ የሚገኙ የተመዘገበ ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) በተመለከተው ጊዜ እነዚህን ዕቃዎች በሚገዛበት ወይም ወደ ሀገር በሚያስገባበት ጊዜ ለከፈለው የግብአት ታክስ ካገኘው ቅናሽ ለእነዚህ የንግድ ዕቃዎች ማምረቻ በዋለው ግብዓት ላይ ለከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ካገኘው ቅናሽ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የውጤት ታክስ እንደተቀበለ ይቆጠራል። ፲፮ሺ፱ ፬/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ የተመዘገበ ሰው ምዝገባ በሚሰረዝበት ጊዜ በእጁ የሚገኙ የካፒታል ዕቃዎችን በሚመለከት ተፈጻሚ በሚደረግበት ጊዜ የተመዘገበው ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) በተመለከተው ጊዜ በእጁ ለሚገኙ የካፒታል ዕቃዎች ከዚህ በታች በተመለከተው ቀመር መሠረት የውጤት ታክስ እንደተቀበለ ይቆጠራል። ሀ ሀ) የተመዘገበው ሰው የካፒታል ዕቃዎችን በገዛበት ጊዜ ያገኘው የግብአት ታክስ ተቀናሽ፣ ለ) በገቢ ግብር አዋጅ በተደነገገው መሠረት የሚወሰን የተመዘገበው ሰው ምዝገባ በተሰረዘበት ጊዜ የካፒታል ዕቃዎች ያላቸው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ፣ እና ሐ) ለካፒታል ዕቃዎቹ የተደረገው የመጀመሪያው ወጪ። of Registration 1/ A person whose VAT registration is cancelled under Article 17 or 18 of this Proclamation shall be treated as having made a taxable supply of goods that are trading stock or capital goods on hand at the time the person’s registration is cancelled but only if the person was allowed an input tax credit on acquisition or import of the trading stock or capital goods, or, in the case of trading stock, on acquisition or import of inputs that have been subsumed into the trading stock. 2/ A registered person shall be treated as having made a taxable supply of trading stock or capital goods under Sub-Article (1) of this Article immediately before cancellation of the person’s registration. 3/ Where Sub-Article (1) applies to trading stock of a registered person on hand at the time of cancellation of the person’s registration, the person shall be treated as having received, at the time specified in Sub-Article (2) of this Article, an amount of output tax equal to the amount of the input tax credit allowed to the person in respect of the acquisition or import of the trading stock, or of inputs that have been subsumed into the trading stock. x ለ/ሐ 4/ Where Sub-Article (1) applies to capital goods of a registered person on hand at the time of cancellation of the person’s registration, the person shall be treated as having received, at the time specified in Sub-Article (2) of this Article, an amount of output tax calculated according to the following formula. A x B/C A) is the input tax credit allowed to the person on acquisition of the capital goods, and B) is the net book value of the capital goods at the time of cancellation of person’s registration as determined under the Income Tax Proclamation, and C) the original cost of the capital goods.
፩/ አገልግሎትን ከማቅረብ ጋር በተያያዘ የሚከናወን የዕቃ አቅርቦት የአገልግሎት አቅርቦት እንደሆነ ተደርጐ ይወሰዳል። ፪/ ከዕቃ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የሚከናወን የአገልግሎት አቅርቦት የዕቃ አቅርቦት እንደሆነ ተደርጐ ይወሰዳል። ፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፯ ንዑስ አንቀጽ (፩) (ሀ) መሠረት ከውጭ ሀገር የተሰጠ አገልግሎት ዋጋ ውስጥ የአገልግሎት አቅርቦት ዋጋ የተካተተ ከሆነ የአገልግሎቱ አቅርቦት ከውጭ ሀገር የተሰጠ አገልግሎት እንደሆነ ተደርጐ ይወሰዳል። ፲፮ሺ፲ ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፪) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንድ አቅርቦት የዕቃ አቅርቦት እና የአገልግሎት አቅርቦት ከሆነ፣ የታክሱ ባለስልጣን ምክንያታዊ በሆነ መንገድ አቅርቦቱ የዕቃ አቅርቦት ወይም የአገልግሎት አቅርቦት ተደርጐ የሚወሰድበትን ሁኔታ በመመሪያ ይወስናል። ፭/ አቅርቦቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በሙሉ ወይም በከፊል የሚይዝ በሚሆንበት ጊዜ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፮ ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል። ሀ) አቅርቦቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የማስከፈያ መጣኔ ተፈጻሚ የሚደረግበት ሲሆን፣ ለ) አቅርቦቱ ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ የሚደረግለት ሲሆን፣ ሐ) አቅርቦቱ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ በሚሆንበት ጊዜ። ፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፯ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) የተደነገገው የተሟላ ሲሆን አንድ ግብይት የማይቀር የሌላ ግብይት አካል ሆኖ፤ የማይቀረው ግብይት የሌላኛው ግብይት አካል ካልሆነ በስተቀር እያንዳንዱ የአቅርቦቱ ክፍል ራሱን የቻለ አቅርቦት እንደሆነ ተደርጐ ይወሰዳል። ፯/ በዱቤ ግዥ ወይም በፋይናንስ ሊዝ ውል ለሚቀርብ ዕቃ ራሱን የቻለ ክፍያ ሆኖ የተካተተ እና ለአቅርቦቱ ተጠቃሚ የተገለጸ የወለድ ክፍያን የሚጨምር ሲሆን፣ የዚህ ዓይነቱ አቅርቦት የዕቃ አቅርቦት እና የፋይናንስ አገልግሎትን የያዘ ሁለት አቅርቦት እንደሆነ ተደርጐ ይወሰዳል። 1/ A supply of goods that is incidental to a supply of services shall be treated as part of the supply of services. 2/ A supply of services that is incidental to a supply of goods shall be treated as part of the supply of goods. 3/ A supply of services shall be treated as part of an import of goods where the value of the supply is included in the value of the import under Article 27 Sub-Article (1) Paragraph (a) of this Proclamation. 4/ Subject to Sub-Articles (1) and (2) of this Article, if a supply is both a supply of goods and a supply of services, the Tax Authority may determine, on any reasonable basis, by a Directive the extent to which the supply shall be treated as a supply of goods or a supply of services. 5/ Sub-Article (6) of this Article shall apply where a supply consists of all or some of the following separate elements. a) a supply that is charged with VAT at a positive rate, b) a Zero-rated supply, c) an exempt supply. 6/ Where the conditions in Sub-Article (5) of this Article are satisfied and subject to Sub-Article (7) of this Article, One transaction is inevitably part of another transaction; unless the inevitable transaction is part of the other transaction, each element of the supply shall be treated as a separate supply. 7/ If a supply of goods under a hire purchase agreement or finance lease involves a credit charge that is specified as a separate charge and disclosed to the recipient of the supply, the supply shall be treated as Two supplies being a supply of goods and a supply of financial services.
፩/ በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አቅርቦቱ ተከናወነ የሚባለው ከሚከተሉት በቀደመው ጊዜ ነው፡- ፲፮ሺ፲፩ ሀ) ለአቅርቦቱ የታክስ ደረሰኝ በተሰጠበት ቀን፣ ለ) ለአቅርቦቱ ማናቸውም ዓይነት ክፍያ (ከፊል ክፍያን ጨምሮ) በተፈጸመበት ቀን፣ ሐ) ከሚከተሉት አንዱ በተፈጸመበት ቀን፡- (1) የዕቃ አቅርቦትን በሚመለከት፣ የዕቃው ርክክብ በተፈጸመበት ወይም ዕቃው ለአቅርቦቱ ተቀባይ ዝግጁ በሆነበት ቀን፣ ወይም (2) የአገልግሎት አቅርቦትን ወይም በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት በሚመለከት፣ አገልግሎት የመሰጠቱ ተግባር ሲጠናቀቅ። ፪/ የዕቃው አቅርቦት በሣንቲም፣ በወረቀት ገንዘብ ወይም ገንዘብን በሚተካ ነገር በሚሠራ ማሽን፣ የመቁጠሪያ መሣሪያ ወይም ሌላ መሣሪያ አማካኝነት የሚፈጸም ከሆነ፣ በአቅራቢው ወይም አቅራቢውን በሚወክለው ሰው አማካኝነት ሣንቲሙ፣ የወረቀት ገንዘቡ ወይም ገንዘብን የሚተካው ነገር ከማሽኑ፣ ከመቁጠሪያ መሣሪያው ወይም ከሌላ መሣሪያ በወጣበት ቀን አቅርቦቱ እንደተከናወነ ይቆጠራል። ፫/ ማናቸውም በተወሰነ ጊዜ ልዩነት የሚከናወን አቅርቦት፡ሀ) በኪራይ ውሉ ወይም በስምምነቱ መሠረት ወይም እንደሁኔታው በሕግ በተወሰነው መሠረት ክፍያው የሚፈጸመው ለውሉ ከፊል ጊዜ በተከታታይነት ከሆነ የዚህ አይነቱ አቅርቦት በተወሰነ ጊዜ ልዩነት በተከታታይነት ክፍያው የሚፈጸም ራሱን የቻለ አቅርቦት እንደሆነ፣ እና ለ) እያንዳንዱ ተከታታይ አቅርቦት ክፍያው ሊፈጸም በሚገባው ቀን ወይም ክፍያው በተፈጸመበት ቀን ከሁለቱ በቀደመው እንደተከናወነ፣ ይቆጠራል። ፲፮ሺ፲፪ ፬/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ‹‹በተወሰነ ጊዜ ልዩነት የሚከናወን አቅርቦት›› ማለት፡ሀ) በዱቤ ግዥ ወይም በፋይናንስ ሊዝ ውል መሠረት የሚቀርብ ዕቃ፣ ወይም ለ) የሚከተሉትን የሚያሟላ የአገልግሎት አቅርቦት፡- (1) በዕቃ ኪራይ ውል የተሰጠ (በዚህ ንዑስ አንቀጽ ፊደል ተራ (ሀ) የተመለከተውን ሊዝ ሳይጨምር)፤ ወይም (2) ክፍያው በተወሰነ ጊዜ ልዩነት እንዲፈጸም በሚያዝ ውል ወይም ሕግ መሠረት በየደረጃው የሚፈጸም አቅርቦት። 1/ Subject to this Proclamation, a supply shall occur on the earlier of: a) the date on which the tax invoice for the supply is issued, b) the date on which any payment (including part payment) for the supply is made, or c) the date on which: (i) for a supply of goods, the goods are delivered or made available to the recipient of the supply, or (ii) for a supply of services or a reverse charged supply, the performance of the services is complete. 2/ A supply of goods by means of a machine, meter, or other device operated by a coin, note, or token shall occur on the date that the coin, note, or token is taken from that machine, meter, or other device by or on behalf of the supplier. 3/ A periodic supply: a) shall be treated as a series of separate, successive supplies corresponding to the successive parts of the period of the lease or agreement, or as determined by law, as the case may be, and b) each successive supply shall be treated as occurring on the earlier of the date on which the payment for that successive supply is due or received. x 4/ In this Article, “Periodic Supply” means: a) a supply of goods under a hire purchase agreement or finance lease, or b) a supply of services: (i) by way of a lease of goods (other than a lease covered by Paragraph (a) of this Sub-Article); or (ii) supplied progressively under an agreement or law that provides for periodic payments.
፩/ በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የአቅርቦት እሴት ነው የሚባለው ለአቅርቦቱ የተከፈለው የግብይት ዋጋ ነው። ፪/ የተመዘገበ ሰው አቅርቦቱን ያከናወነው ግንኙነት ላለው ሰው ከአቅርቦቱ ትክክለኛ የገበያ ዋጋ በታች በሆነ ዋጋ (በነጻ የተከናወነ አቅርቦት ጭምር) የሆነ እንደሆነ የአቅርቦቱ ዋጋ እንደሆነ የሚቆጠረው አቅርቦቱ በተከናወነ ጊዜ ያለው የአቅርቦቱ ትክክለኛ የገበያ ዋጋ ይሆናል። ፫/ በዚህ አዋጅ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር በነጻ የተከናወነ አቅርቦት ዋጋ ዜሮ ይሆናል። ፬/ የተመዘገበ ሰው ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ሲያከናውን የተጨማሪ እሴት ታክሱን መጠን ለይቶ ያላሳየ እንደሆነ የአቅርቦቱ ዋጋ በሚከተለው ቀመር መሠረት ይሰላል። ሀ - (ሀ ለ) በዚህ ቀመር ውስጥ ሀ) ለአቅርቦቱ የተከፈለው ጠቅላላ ዋጋ፣ እና ለ) የታክሱ ክፍልፋይ ነው። ፲፮ሺ፲፫ ፭/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ የተመዘገበ ሰው ለሌላ የተመዘገበ ሰው የሚያከናውነውን ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት በሚመለከት ተፈጻሚ በሚደረግበት ጊዜ፣ አቅርቦቱን የተቀበለው የተመዘገበ ሰው የግብአት ታክስ የሚሰላው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) መሠረት በሚወሰነው የዕቃው ዋጋ ይሆናል። ፮/ ከውጭ ሀገር በገባ የዕቃ አቅርቦት ላይ የተከፈለው ዋጋ ከዕቃው የጉምሩክ ዋጋ በታች የሆነ እንደሆነ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ የዕቃው የጉምሩክ ዋጋ የአቅርቦቱ ዋጋ እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል። 1/ Subject to this Proclamation, the value of a supply shall be the consideration for the supply. 2/ The value of a supply shall be the fair market value of the supply determined at the time of the supply if the supply is made by a person to a related person for a price that is less than the fair market value of the supply (including a supply made for no consideration). 3/ Except as otherwise provided under this Proclamation, the value of a supply for no consideration shall be Zero. 4/ If a registered person makes a taxable supply without a separate amount being identified as VAT, the value of the supply shall be calculated according to the following formula. A – (A x B) where: A) is the total amount charged for the supply, and B) is the tax fraction. 5/ If Sub-Article (4) of this Article applies to a taxable supply made by a registered person to another registered person, the input tax payable by the registered person receiving the supply shall be calculated based on the value of the supply determined under Sub-Article (4) of this Article. 6/ If the consideration for a supply of imported goods is less than the Customs value of the goods, the Ministry may issue a Directive that treats the Customs value as the value of the supply.
፩/ የዕቃ አቅርቦት በኢትዮጵያ ውስጥ ተከናውኗል ለማለት የሚቻለው፡ሀ) የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚጨምር የዕቃ አቅርቦት ሲሆን፣ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ከኢትዮጵያ የሚነሳ ሲሆን፣ ወይም ለ) ለሌላ ማናቸውም የዕቃ አቅርቦት፣ አቅራቢው ዕቃዎቹን በኢትዮጵያ ውስጥ ለገበያ ዝግጁ ሲያደርግ ይሆናል። ፪/ ታክስ የሚከፈልበትን የስራ እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚያከናውን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የስራ ቦታ የሌለው ሰው በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የታዘዘን ዕቃ በኢትዮጵያ ውስጥ አቅርቧል የሚባለው የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲሟሉ ይሆናል፡ሀ) አቅራቢው ኢትዮጵያ ውስጥ እቃዎችን የሚስረክብ ወይም ግዢ የሚፈጽም፤ የሚያመቻች ወይም የሚያሰናዳ ሲሆን ፤ ለ) አቅርቦቱ የተከናወነው በኤሌክትሮኒክ የማከፋፈያ ገበያ ሲሆን፤ ፲፮ሺ፲፬ ሐ) የኤሌክትሮኒክ ማከፋፈያ ገበያውን የሚያስተዳድረው ሰው ዕቃውን ለማቅረብ ወይም አቅርቦቱን ለማመቻቸት የሚያስፈልገውን ግዥ ከኢትዮጵያ የሚፈጽም ከሆነ፤ እና መ) ዕቃዎቹ በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፹፮/፪ሺ፲፪ (እንደተሻሻለ) መሠረት የኤክሳይዝ ታክስ ያልተጣለባቸው ወይም የጉምሩክ ቀረጥ የማይከፈልባቸው ከሆነ። ፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ተፈጻሚ በሚሆንበት ሁኔታ የኤሌክትሮኒክ ማከፋፈያው ገበያ አንቀሳቃሽ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የዕቃ አቅርቦት እንደፈጸመ ይቆጠራል። 1/ A supply of goods shall occur in Ethiopia if: a) for a supply of goods that involves transportation, the transportation of the goods commences in Ethiopia, or b) for any other supply of goods, the goods are made available in Ethiopia by the supplier. 2/ A supply of electronically ordered goods by a person carrying on a taxable activity outside Ethiopia and who does not have a fixed place of business in Ethiopia occurs in Ethiopia if the following conditions are satisfied: a) The supplier handles, facilitates, or arranges the delivery or purchase of goods in Ethiopia; b) the supply is made through an electronic distribution platform; c) the operator of the platform procures, arranges, or facilitates the delivery of the goods in Ethiopia; and d) the goods are not excisable goods for the purposes of the Excise Proclamation No. 1186/2020 (As Amended) or goods that are subject to Customs duty. 3/ Where Sub-Article (2) of this Article applies, the operator of the electronic distribution platform shall be treated as having made the supply of the goods for the purposes of this Proclamation.
፩/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የአገልግሎት አቅርቦት በኢትዮጵያ ውስጥ ተከናውኗል ለማለት የሚቻለው አገልግሎቱ የተሰጠበት የአቅራቢው የንግድ ሥራ ቦታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ነው። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው ቢኖርም የሚከተሉት ሁኔታዎች ከተሟሉ በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ሳይጨምር ታክስ የሚከፈልበትን የስራ እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚያከናውን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የሥራ ቦታ የሌለው ሰው የሚያከናውነው የአገልግሎት አቅርቦት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደተከናወነ ይቆጠራል፤ ሀ) አገልግሎቱ በአካል በኢትዮጵያ ውስጥ የተከናወነ ሆኖ አቅርቦቱ በተሰጠ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በነበረ ሰው ከሆነ፣ ለ) አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኝ የማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር የተገናኘ ከሆነ፤ ፲፮ሺ፲፭ ሐ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) በተደነገገው መሠረት አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ነዋሪ ለሆነ ሰው ከሩቅ የሚሰጥ አገልግሎት ሲሆን፣ መ) አገልግሎቱ በጥቅል የሚሰጥ የቱሪዝም አገልግሎት ወይም በጥቅል ከሚሰጥ የቱሪዝም አገልግሎት ጋር የተያያዘ የውክልና ወይም የምዝገባ አገልግሎት ሲሆን፤ ሠ) አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ መጠቀም የሚቻል የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከሆነ፤ ወይም ረ) በዚህ ንዑስ አንቀጽ ፊደል ተራ (ሠ) የተመለከተውን ሳይጨምር የዓለም አቀፍ የስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ በሆነ ሰው ሞባይል ላይ የተጫነው የደንበኛ ማንነት ሞጁል ካርድ የሚያሳየው የሞባይል የሀገር መለያ ቁጥር የኢትዮጵያ ከሆነ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት እንደተሰጠ ይቆጠራል። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪)(ሐ) አፈጻጸም ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መለኪያዎች ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ ከተሟሉ ከሩቅ የሚሰጥ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነ ሰው በኢትዮጵያ ነዋሪ እንደሆነ ይቆጠራል፡ሀ) ለአገልግሎቱ ተቀባይ የክፍያ መጠየቂያ የሚላክበት አድራሻ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ፤ ለ) የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለክፍያ የሚጠቀምበትን የባንክ ሒሣብ ወይም በባንኩ ዘንድ የሚገኘውን የክፍያ መጠየቂያ አድራሻ ጨምሮ የተጠቃሚው የባንክ ሂሳብ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ፤ ሐ) ለተጠቃሚው የስልክ አገልግሎት የሚሰጥበት የማይንቀሳቀስ ስልክ መስመር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፤ ፲፮ሺ፲፮ መ) የዓለም አቀፍ የስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነ ሰው በሚገለገልበት የደንበኛ ማንነት ሞጁል ካርድ ላይ የተጫነው የተንቀሳቃሽ ስልክ የሀገር መለያ ቀጥር የኢትዮጵያ ከሆነ፣ ሠ) የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አገልግሎቱን የሚያገኝበት መሳሪያ የኢንተርኔት ፕሮቶኮል አድራሻ ወይም ሌላ የቦታ አድራሻ መለያ የኢትዮጵያ ከሆነ፤ ወይም ረ) ሌላ ማናቸውም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ ነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ ለንግድ አግባብነት ያለው መረጃ። ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) ከተዘረዘሩት መለኪያዎች ውስጥ ሁለቱ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በኢትዮጵያ ነዋሪ መሆኑን የሚደግፉ እና ሁለቱ ደግሞ በሌላ ሀገር ነዋሪ መሆኑን የሚደግፉ በሚሆንበት ጊዜ የአገልግሎቱን ተጠቃሚ አድራሻ ለመወሰን የበለጠ አስተማማኝ ናቸው የሚላቸውን መሠረት በማድረግ አቅራቢው የአገልግሎቱን ተጠቃሚ አድራሻ ይወስናል። ፭/ ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) አፈጻጸም በንዑስ አንቀጽ (፫) ከተመለከቱት መለኪያዎች ውስጥ አስተማማኝ ከሆነው በመጀመር አስተማማኝነትን መሠረት በማድረግ በቅደም ተከተል ተዘርዝረዋል። ፮/ አቅራቢው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) መሠረት በኢትዮጵያ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፷፭ መሰረት ካላስታወቀው በስተቀር የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አቅርቦቱን በተመለከተ በገዢው የሚሰበሰብ ታክስ የማይመለከተው እንደሆነ መቁጠር አለበት። ‹‹ ፲፮ሺ፲፯ 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article, a supply of services shall occur in Ethiopia if the place of business of the supplier from which the services are supplied is in Ethiopia. 2/ Despite Sub-Article (1) of this Article, a supply of services, other than a reverse charged supply, by a person who carries on business outside Ethiopia and does not have a fixed place of business in Ethiopia shall occur in Ethiopia if. a) the services are physically performed in Ethiopia by a person who is in Ethiopia at the time of the supply, (b) the services relate to immovable property in Ethiopia; (c) the services are remote services supplied to a resident of Ethiopia as determined under Sub-Article (3) of this Article, (d) the services are a supply of an inbound tourism product, or agency or booking services relating to a supply of an inbound tourism product; (e) the services are telecommunications services that can be used only in Ethiopia; or (f) except where Paragraph (e) of this Sub-Article applies, the services are telecommunication services where the mobile country code of the International mobile subscriber identity stored on the subscriber identity module card used by the recipient is Ethiopia. 3/ For the purposes of Sub-Article (2) Paragraph (c) of this Article and subject to Sub-Article (4) of this Article, a recipient of a supply of remote services shall be treated as a resident of Ethiopia if at least Two of the following apply: a) the recipient’s billing address is in Ethiopia; b) the recipient’s bank account is in Ethiopia, including the account the recipient uses for payment or the billing address held by the bank; c) the recipient’s fixed land line through which the service is supplied to the recipient is in Ethiopia; d) the mobile country code of the International mobile subscriber identity stored on the subscriber identity module card used by the recipient is Ethiopia; e) the internet protocol address of the device used by the recipient or another geolocation method is in Ethiopia; or f) any other commercially relevant information indicates that the recipient is resident in Ethiopia. ‹‹ 4/ If there are Two factors on the list in Sub- Article (3) of this Article supporting that the recipient is a resident of Ethiopia and Two factors supporting residence in another country, the supplier shall determine the recipient’s residence based on the factors that, in the circumstances, are the most reliable indicators of the recipient’s residence. 5/ For the purposes of Sub-Article (4) of this Article, the factors in Sub-Article (3) of this Article are listed in order of reliability starting with the most reliable. 6/ Having established that the recipient of a supply is a resident of Ethiopia under Sub-Article (3) of the Article, Unless the beneficiary of the service is notified under Article 65 of this Proclamation, the beneficiary of the service must be deemed irrelevant to the tax collected by the purchaser regarding the supply.
፩/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው የሚከተሉት ሲሟሉ ይሆናል፡ሀ) አቅራቢው (‹‹እውነተኛ አቅራቢ›› ተብሎ የሚታወቀው) ከሩቅ የሚከናወነውን አቅርቦት የሚያከናውነው በኤሌክትሮኒክ የማከፋፈያ ገበያ አማካኝነት ሲሆን፣ ለ) የኤሌክትሮኒክ የማክፋፈያ ገበያ ሥራ የሚያከናውነው ሰው (ከዚህ በኋላ ‹‹የሥራ አንቀሳቃሽ›› ተብሎ የሚጠራ) በኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ሥራ ቦታ የሌለው ከሆነ፣ ሐ) የሥራው አንቀሳቃሽ ከሚከተሉት አንዱን የሚያከናውን ከሆነ፡- (1) የአቅርቦቱን ዋጋ ከአቅርቦቱ ተጠቃሚ እንዲጠየቅ የሚያደርግ፤ (2) አቅርቦቱን ለአቅርቦቱ ተጠቃሚ የሚያደርስ ወይም እንዲደርስ የሚያደርግ፤ ወይም (3) በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ አቅርቦቱ የሚከናወንባቸውን የውል ቃሎችና ሁኔታዎች የሚወስን፤ እና መ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፬ ንዑስ አንቀጽ (፫) በተደነገገው መሰረት የአቅርቦቱ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ ነዋሪ እና ያልተመዘገበ ሰው፤ የመንግስት ተቋም ወይም ከፍተኛ ያልተመዘገበ ሰው፤ ከሆነ ነው። ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌዎች ሲሟሉ የኤሌክትሮኒክ ማከፋፈያ ገበያውን ሥራ የሚያከናውነው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት ከሩቅ የሚከናወን የአገልግሎት አቅርቦት ወይም በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚታዘዝ ዕቃ አቅርቦት እንደፈጸመ ተቆጥሮ የአዋጁ አንቀጽ ፳፬(፪) ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል። ፲፮ሺ፲፰ ፫/ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች ዋንኛው አቅራቢ የተመዘገበ ሰው በሚሆንበት ጊዜ ተፈጻሚ አይሆኑም። Electronic Distribution Platform 1/ This Article shall apply if the following conditions are satisfied: a) a supplier (referred to as the “Underlying Supplier”) makes a supply of remote services through an electronic distribution platform, b) the electronic distribution platform is operated by a person (referred to as the “Operator”) who does not have a fixed place of business in Ethiopia, c) the operator does any of the following: (i) authorises the charge for the supply to the recipient; (ii) makes or Authorises the delivery of the supply to the recipient; or (iii) directly or indirectly sets a term or condition under which the supply is made; and d) the recipient of the supply is a resident of Ethiopia as determined under Article 24(3) of this Proclamation and is not a registered person, Government entity, or large unregistered person. 2/ Where the conditions in Sub-Article (1) of this Article are satisfied and subject to Sub-Article (3) of this Article, Article 24 (2) of this Proclamation shall apply on the basis that the operator of the electronic distribution platform shall be treated as having made the supply of remote services in the course or furtherance of a taxable activity carried on by the operator. 3/ This Article shall not apply where the underlying supplier is a registered person.
፩/ ዕቃ ወደ ሀገር ገብቷል የሚባለው፡ሀ) በጉምሩክ አዋጅ መሠረት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎችን በሚመለከት፣ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓትን ባጠናቀቁበት ቀን፣ ወይም ለ) ለሌሎች ማናቸውም ዕቃዎች፣ ዕቃዎቹ ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ቀን ይሆናል። ፪/ ወደ ቦንድ የጉምሩክ መጋዘን የገባ እና የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓትን አጠናቆ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እንዲውል ያልወጣ ዕቃን በሚመለከት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እንዲውል ከመጋዘን ከመውጣቱ በፊት የተከናወነ አቅርቦት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ከግምት ውስጥ የሚገባ አይሆንም። ፫/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም “የተፈቀደ የጉምሩክ መጋዘን” የሚለው ሀረግ በጉምሩክ አዋጅ የተሰጠውን ትርጉም ይይዛል። 1/ An import of goods shall occur: a) for goods that are cleared for home use under the Customs Legislation, on the date on which they are so cleared, or b) for any other goods, on the date the goods are brought into Ethiopia. 2/ If any goods have been imported into a bonded warehouse but have not been cleared for home use, any supply of such goods before they are cleared for home use shall be disregarded for the purposes of this Proclamation. 3/ In this Article, “Bonded Warehouse” has the meaning under the Customs Legislation.
፩/ በዚህ አንቀጽ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ወደ ሀገር የገባ ዕቃ እሴት የሚከተሉት ድምር ይሆናል፡ሀ) ወደ ሀገር የገባው ዕቃ ቀረጥ የሚከፈልበት ቢሆንም ባይሆንም በጉምሩክ አዋጅ መሠረት የሚወሰነው የዕቃው ዋጋ፣ እና ለ) ወደ ሀገር በገባው ዕቃ ላይ የሚከፈል የጉምሩክ ቀረጥ፣ የኤክሳይዝ ታክስ እና ሌላ ማናቸውም ታክስ እንዲሁም ማናቸውም ክፍያ። ፲፮ሺ፲፱ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል ተራ(ለ) መሠረት የሚወሰነው የዕቃው እሴት የተጨማሪ እሴት ታክስን ወይም በዕቃው ላይ የሚከፈልን ወይም የተከፈለን የገቢ ግብር የቅድሚያ ክፍያን አይጨምርም። ፫/ ወደ ሀገር በገባው ዕቃ ላይ፡ሀ) የቅርጽ ወይም የባህሪ ለውጥ፣ እና ለ) ዕቃው ወደውጭ ከተላከበት ጊዜ አንስቶ የባለቤትነት ለውጥ፣ እስካልተደረገ ድረስ ለጥገና፣ ለዕድሳት ወይም ለማሻሻያ ወደውጭ ሀገር የተላከ ዕቃ ተመልሶ ወደ ሀገር በሚገባበት ጊዜ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ መሠረት የሚሆነው በጥገናው፣ በዕድሳቱ ወይም በማሻሻያው ምክንያት የታከለው ተጨማሪ እሴት ይሆናል። ፬/ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፮ (፪) ተፈጻሚ የሚደረግበት ወደ ሀገር የሚገባ እቃ እሴት ነው ተብሎ የሚወሰደው ከሚከተሉት ከፍተኛው ይሆናል፡ሀ) በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ፩ መሰረት የሚወሰነው እሴት፤ ወይም ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፮ (፪) መሰረት የሚወሰነው የእቃ አቅርቦት እሴት፣ ፲፮ሺ፳ ፭/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ‹‹የገቢ ግብር የቅድሚያ ክፍያ›› የሚባለው በገቢ ግብር አዋጅ አንቀጽ ፹፭ መሠረት ወደ ሀገር በሚገባ ዕቃ ላይ የሚከፈለው ግብር ነው። 1/ Subject to this Article, the value of an import of goods shall be the total of the following amounts: a) the value of the goods under the Customs Legislation, whether or not any duty is payable on the import, and b) the amount of any duty, excise tax, and other fiscal charge, and any fee or other charge, payable in respect of the import. 2/ The value of an import under Sub-Article (1) Paragraph (b) of this Article shall not include any VAT or advance tax paid or payable in respect of the import. 3/ If goods are re-imported after being exported for the purpose of undergoing repair, renovation, or improvement, the value of the import shall be the amount of the increase in value of the goods as a result of the repair, renovation, or improvement provided there has been no change in: a) the form or character of the goods, and b) the ownership of the goods since the goods were exported. 4/ Article 26 (2) of this Proclamation shall be the maximum of the following that are considered to be the value of an imported item to which it applies: a) the value determined under Sub-Article 1 of this Article; or b) the value of the supply to be determined under Article 26 Paragraph (2) of this Proclamation, 5/ In this Article, “Advance Tax” means advance tax payable in respect of an import under Article 85 of the Income Tax Proclamation.
፩/ የተመዘገበ ሰው የጸደቀውን ቅጽ በመጠቀም ወደ ሀገር በሚያስገባቸው የካፒታል ዕቃዎች ላይ ሊከፈል የሚገባው የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲዘገይ ለኮሚሽኑ ማመልከቻ ሊያቀርብ ይችላል። ፪/ ኮሚሽኑ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ማመልከቻ ሲቀርብለት፣ የሚከተሉት ሁኔታዎች መሟላታቸውን ሲያምንበት ክፍያው እንዲዘገይ ሊፈቅድ ይችላል፡ሀ) የተመዘገበው ሰው ተገቢውን መረጃ የሚይዝ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢውን በወቅቱ የሚያስታወቅ እና በዚህ አዋጅ የተጣሉበትን ሌሎች ግዴታዎች የሚወጣ፣ ለ) የተመዘገበው ሰው የሚፈለግበት የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ሌላ የግብር ዕዳ የሌለ፣ እና ሐ) አመልካቹ ሰው፡- (1) በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ ፩፻፲ መሠረት የሚፈለግበት አስተዳደራዊ መቀጫ የሌለ፣ (2) በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ ፩፻፲፰፣ ፩፻፲፱፣ ፩፻፳፩ ወይም ፩፻፳፭ መሠረት ለተመለከቱት ጥፋቶች ተከሶ ያልተፈረደበት፣ ወይም (3) በተመሳሳይ ጥፋት ምክንያት በጉምሩክ አዋጅ መሠረት አስተዳደራዊ ቅጣት የማይፈለግበት ወይም በወንጀል ያልተቀጣ። ፲፮ሺ፳፩ ፫/ ኮሚሽኑ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት ፈቃድ ከመስጠቱ በፊት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት ማመልከቻ ያቀረበው የተመዘገበ ሰው በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ ፴፭ መሠረት ዋስትና እንዲያቀርብ ሊጠይቅ ይችላል። ፬/ ኮሚሽኑ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ማመልከቻ ያቀረበው ሰው ማመልከቻውን ባቀረበ በ፲፬ ቀናት ውስጥ በጥያቄው መሠረት የተሰጠውን ውሳኔ እንዲያውቅ ማድረግ አለበት። ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፮) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት የሚሰጠው ፈቃድ ተፈጻሚ የሚሆነው፡ሀ) በፈቃዱ ለተመለከቱ ወደ ሀገር ለሚገቡ የካፒታል ዕቃዎች፣ ወይም ለ) በፈቃዱ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ለሚገቡ የካፒታል ዕቃዎች፣ ይሆናል። ፮/ የተመዘገበው ሰው፡ሀ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ቁጥር (፪) የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዋች ካጓደለ፣ ወይም ለ) የካፒታል ዕቃዎቹን ለሌላ ሰው ካስተላለፈ ወይም ካስወገደ፣ ኮሚሽኑ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት የሰጠውን ፈቃድ ሊሰርዝ ይችላል። ፲፮ሺ፳፪ ፯/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት ፈቃድ የተሰጠው የተመዘገበ ሰው ዕቃው ወደ ሀገር በገባበት የሒሣብ ጊዜ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፰ መሠረት ሊከፈል የሚገባውን የተጣራ የተጨማሪ እሴት ታክስ ስሌት በሚያከናውንበት ጊዜ በፈቃዱ በተመለከተው ታክስ በሚከፈልበት የካፒታል ዕቃ ላይ ሊከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ማካተት አለበት። ፰/ በዚህ አንቀጽ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሚኒስቴሩ ወደ ሀገር በሚገቡ የካፒታል ዕቃዎች ላይ ሊከፈል የሚገባው የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲዘገይ የሚደረግበትን ሁኔታ በመመሪያ ሊወሰን ይችላል። ፱/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ‹‹የካፒታል ዕቃ›› የሚለው ሀረግ የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት ለሽያጭ የሚያውለውን ወደ ሀገር የሚገባ የካፒታል ዕቃ አይጨምርም። Goods 1/ A registered person may apply to the Commission, in the approved form, for approval to defer the payment of VAT on imported capital goods. 2/ The Commission may approve an application under Sub-Article (1) of this Article if satisfied of the following: a) the person has kept proper records, regularly filed VAT returns by the due date, and otherwise complied with their obligations under this Proclamation, b) the person has no outstanding VAT or other tax liabilities, and c) the person has not been: (i) liable for a penalty under Article 110 of the Tax Administration Proclamation, (ii) convicted of an offence under Article 118, 119, 121, or 125 of the Tax Administration Proclamation, or (iii) liable for a similar penalty or convicted of a similar offence under the Customs Legislation. 3/ The Commission may require an applicant under Sub-Article (1) of this Article to provide security in accordance with Article 35 of the Tax Administration Proclamation as a condition of the grant of approval under Sub-Article (2) of this Article. 4/ The Commission shall notify an applicant under Sub-Article (1) of this Article of the decision on the application within 14 days of receiving the application. 5/ Subject to Sub-Article (6) of this Article, an approval under Sub-Article (2) of this Article shall apply to: a) the import of capital goods specified in the approval, or b) the import of capital goods made during a period specified in the approval. 6/ The Commission may revoke an approval under Sub-Article (2) of this Article, if the registered person: a) no longer satisfies the conditions in Sub-Article (2) of this Article, or b) the registered person transfers or disposes of the capital goods. 7/ A registered person who has been granted approval under Sub-Article (2) of this Article shall include the VAT payable on a taxable import covered by the approval in the calculation of the net VAT payable by the person under Article 48 of this Proclamation for the accounting period in which the taxable import occurred. 8/ Notwithstanding the provisions of this Article, the Ministry may, by Directive, provide the conditions under which the import VAT on capital goods may be deferred. 9/ In this Article, “Capital Goods” shall not include capital goods imported by a registered person for resale in the ordinary course of the person’s taxable activity.
፩/ በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አቅርቦቱ ወይም ወደ ሀገር የማስገባቱ ተግባር በተከናወነበት ጊዜ ግዢው የተፈጸመው ታክስ ለሚከፈልበት አቅርቦት መሆኑ ለተረጋገጠ ተቀናሽ ለሚደረግ ግዥ የተመዘገበ ሰው የከፈለው የግብአት ታክስ ተቀናሽ ይደረጋል። ፪/ የተመዘገበ ሰው በአንድ የሒሣብ ጊዜ ውስጥ ያከናወነው ተቀናሽ የሚደረግ ግዥ በከፊል ታክስ ለሚከፈልባቸው አቅርቦቶች በከፊል ደግሞ ለሌሎች አቅርቦቶች የዋለ ከሆነ ተቀናሽ የሚደረገው የግብአት ታክስ የሚሰላው በሚከተለው ቀመር መሠረት ይሆናል፡- ፲፮ሺ፳፫ ሀ ለዚህ ቀመር አፈጻጸም፡ሀ) የተመዘገበው ሰው በአንድ የሒሣብ ጊዜ ውስጥ ባከናወነው በከፊል ታክስ ለሚከፈልባቸው አቅርቦቶች በከፊል ደግሞ ለሌሎች አቅርቦቶች በዋለው ተቀናሽ የሚደረግ ግዥ ላይ የከፈለው የግብአት ታክስ ጠቅላላ ድምር፣ ለ) የተመዘገበው ሰው በአንድ የሒሣብ ጊዜ ውስጥ ያከናወነው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ ድምር፣ ሐ) የተመዘገበው ሰው በአንድ የሒሣብ ጊዜ ውስጥ ያከናወነው ጠቅላላ አቅርቦት ዋጋ ድምር። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ የተመለከተው የለ/ሐ ክፍልፋይ፡ሀ) 0.95 (ዜሮ ነጥብ ዘጠኝ አምስት) ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ የተመዘገበው ሰው ባከናወነው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) በተመለከተው ተቀናሽ የሚደረግ ግዥ ላይ የከፈለው የግብአት ታክስ ሙሉ በሙሉ ተቀናሽ ይደረጋል። ለ) ከ0.05 (ዜሮ ነጥብ ዜሮ አምስት) በታች ከሆነ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) በተመለከተው ተቀናሽ የሚደረግ ግዥ ላይ የከፈለው የግብዓት ታክስ ተቀናሽ አይደረግም። ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የግብአት ታክስ ተቀናሽ የሚደረገው ተቀናሽ የሚደረገው ግዥ አቅርቦት በተከናወነበት ወይም ወደ ሀገር በገባበት የሒሣብ ጊዜ ውስጥ መሆን አለበት። ፲፮ሺ፳፬ ፭/ በዚህ አዋጅ መሠረት ተቀናሽ እንዲሆን የተፈቀደ የግብአት ታክስ ያለው የተመዘገበ ሰው የአንድን የሒሣብ ጊዜ የገቢ ማስታወቂያ በሚያዘጋጅበት ጊዜ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፮ የተመለከተው ሰነድ በእጁ የሌለ ከሆነ፣ የግብአት ታክስ ተቀናሽ ሊደረግ የማይችል ስለሆነ፣ ተቀናሹ የሚደረገው የተመዘገበው ሰው ሰነዱ በእጁ የገባበት የመጀመሪያው የሒሣብ ጊዜ ይሆናል። ፮/ ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) አፈጻጸም ተፈላጊ የሚሆኑት ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው፡ሀ) ወደ ሀገር ከገባ ዕቃ ጋር በተያያዘ ተቀናሽ የሚደረግን ግዥ በሚመለከት በኮሚሽኑ የተሰጠ የጉምሩክ ዲክላራሲዩን ወይም ወደ ሀገር በገባው ዕቃ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሌላ ሰነድ፣ ለ) ታክስ ከሚከፈልበት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ተቀናሽ የሚደረግን ግዥ በሚመለከት ታክስ ከሚከፈልበት አቅርቦት ግዥ ጋር በተያያዘ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለበት የታክስ ደረሰኝ፣ ሐ) በቀጥታ በገዢው ታክስ ከሚከፈልበት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ተቀናሽ የሚደረግ ግዥን በሚመለከት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፪(፬) መሠረት የአገልግሎቱ ተቀባይ ያዘጋጀው የታክስ ደረሰኝ፣ መ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፫ (፫) (ለ) ከተመለከተው የግብአት ታክስ ጋር በተያያዘ የተፈቀደውን የግብአት ታክስ ተቀናሽ በሚመለከት በአዋጁ አንቀጽ ፵፫ (፫) (ሀ) መሠረት ሊዘጋጅ የሚገባው የዴቢት ሰነድ፣ ፲፮ሺ፳፭ ሠ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፬ (፪) የተፈቀደውን የግብአት ታክስ ተቀናሽ በሚመለከት በአዋጁ አንቀጽ ፵፬ ንዑስ አንቀጽ (፫) ፊደል ተራ (ሀ) መሠረት ለአቅርቦቱ ተቀባይ የሚሰጠው የክሬዲት ሰነድ ቅጂ፣ ወይም ረ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፮ (፫) (ለ) የተፈቀደውን የግብአት ታክስ ተቀናሽ በሚመለከት በአዋጁ አንቀጽ ፵፮ ንዑስ አንቀጽ (፫) ፊደል ተራ (ሀ) መሠረት የሚዘጋጀው የዴቢት ሰነድ። ፯/ በማናቸውም ምክንያት የተመዘገበው ሰው በአንድ የሒሣብ ጊዜ ተቀናሽ ሊደረግ የሚገባን የግብዓት ታክስ በዚያው የሒሣብ ጊዜ ባቀረበው የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቂያ ውስጥ ያልጠየቀ እንደሆነ፣ በሚቀጥለው የሒሣብ ጊዜ በሚያቀርበው የተጨማሪ እሴት ታክስ የሂሳብ ማስታወቂያ ውስጥ ሊጠይቅ ይችላል። ሆኖም በዚህ ዓይነት የተቀናሽ ጥያቄ ሊቀርብ የሚችለው ተቀናሹ ሊጠየቅ ከሚገባበት የሒሣብ ጊዜ ጀምሮ ከ፲፪ ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ነው። 1/ Subject to this Proclamation, a registered person shall be allowed a credit for the input tax imposed on a creditable acquisition made by the person to the extent that the acquisition was for the purpose of making taxable supplies as determined at the time of the supply or import comprising the acquisition. 2/ The input tax credit allowed to a registered person for creditable acquisitions made by the person during an accounting period partly to make taxable supplies and partly to make other supplies shall be calculated according to the following formula: x ለ/ሐ A x B/C where: A) is the total amount of input tax payable in respect of creditable acquisitions made by the registered person during the accounting period partly to make taxable supplies and partly to make other supplies, B) is the total value of taxable supplies made by the registered person during the accounting period, and C) is the total value of all supplies made by the registered person during the accounting period. 3/ Where the fraction B/C in Sub-Article (2) of this Article is: a) 0.95 or more, the registered person shall be allowed a credit for the total amount of input tax in respect of creditable acquisitions referred to in Sub-Article (2) of this Article. b) less than 0.05, the registered person shall not be allowed a credit for any input tax in respect of creditable acquisitions referred to in Sub-Article (2) of this Article. 4/ Subject to Sub-Article (5) of this Article, an input tax credit shall be allowed in the accounting period in which the supply or import to which the creditable acquisition relates occurred. 5/ If, at the time a registered person files a VAT return for an accounting period in which an input tax credit would otherwise be allowable under this Proclamation, the person does not hold the documentation referred to in Sub- Article (6) of this Article, the input tax credit shall not be allowed in that accounting period but instead shall be allowed in the First accounting period in which the person holds the required documentation. 6/ The documentation required for the purposes of Sub-Article (5) of this Proclamation is the following: a) for a creditable acquisition that is a taxable import, a Customs declaration or other document issued by the Commission evidencing the payment of VAT in respect of the import, b) for a creditable acquisition that is a taxable supply, the tax invoice for the taxable supply, c) for a creditable acquisition that is a reverse charged supply, the recipient- created tax invoice for the supply as required under Article 52 Sub-Article (4) of this Proclamation, d) for an input tax credit allowed in respect of input tax referred to in Article 43 Sub-Article (3) (b) of this Proclamation, the debit note required to be issued under Article 43 Sub- Article (3) (a) of this Proclamation, e) for an input tax credit allowed in respect of input tax referred to in Article 44 Sub-Article (2) of this Proclamation, a copy of the credit note issued to the recipient of the supply under Article 44 (3) (a) of this Proclamation, or f) for an input tax credit allowed under Article 46 Sub-Article (3) Paragraph (b) of this Proclamation, the debit note required to be issued under Article 46 Sub-Article (3) Paragraph (a). 7/ If, for whatever reason, a registered person fails to claim an input tax credit in the VAT return for the accounting period in which the credit arises, the registered person can claim the credit in the VAT return for a subsequent accounting period but only if that accounting period is within 12 calendar months after the accounting period in which the credit arose.
፩/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የተመዘገበ ሰው ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት የከፈለው የግብአት ታክስ ተቀናሽ አይደረግም፡ሀ) የተመዘገበው ሰው የመንገደኛ ተሽከርካሪ ግብይት ወይም ኪራይ ላይ የተሰማራ እና ተሽከርካሪው የተገዛው እና ፈቃድ የተሰጠው ለዚህ ታክስ የሚከፈልበት የሥራ እንቅስቃሴ ካልሆነ በስተቀር የመንገደኞች ተሽከርካሪ ግዥ ወይም ከእነዚህ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ወይም ጥገና ወይም ዕድሳት ጋር በተያያዘ የከፈለው ታክስ፤ ፲፮ሺ፳፮ ለ) ከዚህ በታች ከተመለከቱት በስተቀር፤ የተመዘገበው ሰው ለመዝናኛ ወይም የመዝናኛ አገልግሎት ለመስጠት ያከናወነው ግዢ ከሆነ፤ እና (1) የመዝናኛው አገልግሎት የተሰጠው ማናቸውም ሰው ታክስ የሚከፈልበትን መደበኛ የመዝናኛ አገልግሎት በሚሰጥበት ሁኔታ ከሆነ እና የመዝናኛ አገልግሎቱ ግንኙነት ላለው ሰው ወይም ለሰራተኛ የተሰጠ ካልሆነ፤ (2) የመዝናኛ አገልግሎቱ የተሰጠው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ስራውን ለማከናወን ወይም የቀጣሪውን ስራ ለማከናወን ከመኖሪያ ቤቱ ርቆ ባለበት ጊዜ ከሆነ፤ወይም (3) ታክስ የሚከፈልበት የስራ እንቅስቃሴ የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚያካትት ሆኖ የመዝናኛው አገልግሎት የትራንስፖርቱ አካል ሆኖ ለመገደኞች የተሰጠ ከሆነ፤ ወይም ሐ) የተመዘገበው ሰው የአንድ ክበብ፣ ማህበር ወይም የስፖርት፣ የማህበራዊ ወይም የመዝናኛ ባህርይ ያለው ስብስብ አባል በመሆኑ ምክንያት የተፈጸመ ግዥ። ፪/ የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (፩) (ሐ) ድንጋጌ ታክስ የሚከፈልበት የስፖርት፤ የማህበራዊ ወይም የመዝናኛ አቅርቦት የሚያከናውን የተመዘገበ ሰው እነዚህን አገልግሎቶች ለመስጠት ላከናወነው ታክስ ተቀናሽ የሚደረግበት ግብይት የግብአት ታክስ ተቀናሽ የማግኘት መብቱን የሚያሳጣ አይሆንም። ፲፮ሺ፳፯ ፫/ በኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የንግድ ሥራ ቦታ ሳይኖረው ታክስ የሚከፈልበት የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ የሚያከናውን የተመዘገበ ሰው ከሚያከናውነው ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ጋር በተያያዘ ማናቸውንም አይነት የግብአት ታክስ ተቀናሽ ሊያገኝ አይችልም። ፬/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም፣ ሀ) ‹‹መዝናኛ›› ማለት ማናቸውም የምግብ፣ የመጠጥ፣ የመኝታ፣ የማዝናናት ወይም የመስተንግዶ አገልግሎት ነው። ለ) ‹‹የመንገደኛ ተሽከርካሪ›› ማለት ድርብ ጋቢና ያለውን ተሽከርካሪ ጨምሮ ከነአሽከርካሪው ስምንት ወይም ከዚያ በታች የሆኑ መንገደኞችን እንዲጭን ተደርጐ የተመረተ ወይም ማሻሻያ የተደረገበት ተሽከርካሪ ነው። 1/ Subject to Sub-Article (2), a registered person shall not be allowed an input tax credit under this Proclamation for input tax payable in respect of the following: a) a creditable acquisition by the registered person of a passenger vehicle, or spare parts or repair or maintenance services for such vehicle, unless the person’s taxable activity involves dealing in, or hiring out, such vehicles and the vehicle was acquired and is licensed for the purposes of that taxable activity; b) a creditable acquisition by a registered person to the extent that the acquisition is acquired for the purposes of entertainment or to provide entertainment, unless: (i) the entertainment is provided in the ordinary course of carrying on the taxable activity of the person to provide the entertainment and the entertainment is not provided to a related person or employee; (ii) the entertainment is provided while the recipient of the entertainment is away from home for the purposes of the business of the recipient or the recipient’s employer; or (iii) the person’s taxable activity involves the making of taxable supplies of transportation services and the entertainment is provided to passengers as part of the transportation service; or c) a creditable acquisition by a registered person of membership for any person of a club, association, or society of a sporting, social, or recreational nature. 2/ For the avoidance of doubt, Sub-Article (1)Paragraph (c) of this Article shall not prevent a registered person carrying on a taxable activity that involves making taxable supplies of sporting, social, or recreational services from claiming input tax credits for input tax incurred in respect of creditable acquisitions to make those supplies. 3/ A registered person who does not carry on a taxable activity through a fixed place of business in Ethiopia shall not be allowed any input tax credits in relation to the making of taxable supplies. 4/ In this Article: a) “Entertainment” means the provision of food, beverages, accommodation, recreation, or hospitality of any kind. b) “Passenger Vehicle” means a road vehicle designed or adapted for the transport of 8 or fewer seated passengers, including a double cab vehicle.
፩/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ አዲስ የተመዘገበ ሰው በተመዘገበበት ቀን በእጁ በሚገኙ እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ለማከናወን በሚውሉ የንግድ ዕቃዎች ወይም የካፒታል ዕቃዎች ላይ የከፈለው የግብዓት ታክስ ተቀናሽ እንዲደረግለት ለመጠየቅ ይችላል። ሀ) የተመዘገበው ሰው የንግድ ዕቃዎቹን ወይም የካፒታል ዕቃዎቹን ከተመዘገበበት ቀን በፊት ባለው የመጨረሻ ቀን በእጁ የያዘ ከሆነ፣ ለ) የተመዘገበው ሰው የንግድ ዕቃዎቹን ወይም የካፒታል ዕቃዎቹን ያገኘው ተቀናሽ በሚደረግ ግዥ ከሆነ፣ ሐ) ተቀናሽ የሚደረገው ግዥ የተፈጸመው፡- ፲፮ሺ፳፰ (1) የንግድ ዕቃዎችን በሚመለከት፣ ከተመዘገበበት ቀን በፊት ባለው የ፮ ወር ጊዜ ውስጥ ከሆነ፣ (2) የካፒታል ዕቃዎችን በሚመለከት፣ ከተመዘገበበት ቀን በፊት ባለው የ፫ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከሆነ፣ እና መ) የተመዘገበው ሰው የታክሱን ባለስልጣን በሚያረካ አኳኋን ተቀናሽ ለሚደረገው ግዥ የግብአት ታክስ የከፈለ መሆኑን እና የከፈለውን ታክስ መጠን የሚያሳይ የታክስ ደረሰኝ ወይም ሌላ የሰነድ ማስረጃ ካቀረበ:: ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የሚደረገው የግብአት ታክስ ተቀናሽ የተመዘገበው ሰው ከተመዘገበበት ቀን ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያ የሂሳብ ጊዜ መቅረብ አለበት። ፫/ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፱ እና ፴ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ ለንግድ እቃዎች ተፈጻሚ በሚሆንበት ሁኔታ የተመዘገበው ሰው የግብአት ታክስ ተቀናሽ ማግኘት የሚችለው በተመዘገበበት ቀን በእጁ የሚገኙ የንግድ ዕቃዎችን በገዛበት ጊዜ ለከፈለው የግብአት ታክስ ይሆናል። ፬/ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፱ እና ፴ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ መሠረት የተመዘገበው ሰው በተመዘገበበት ቀን በእጁ የሚገኙ የካፒታል ዕቃዎችን በሚመለከት ለተመዘገበው ሰው ተቀናሽ የሚደረገው የግብአት ታክስ የሚሰላው በሚከተለው ቀመር መሠረት ይሆናል፡- (ሐ-ለ) ሀ ______ ሐ ፲፮ሺ፳፱ ለዚህ ቀመር አፈጻጸም፡ሀ) የተመዘገበው ሰው የካፒታል ዕቃዎቹን በገዛበት ጊዜ የከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ለ) በገቢ ግብር አዋጅ መሠረት የሚወሰነው ይህ ሰው በተመዘገበበት ቀን የካፒታል ዕቃዎቹ ያላቸው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ፣ እና ሐ) ለካፒታል ዕቃዎቹ የተደረገው የመጀመሪያው ወጪ። ፭/ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፱ (፭) ድንጋጌ በዚህ አንቀጽ መሠረት ተቀናሽ የሚደረገውን የግብዓት ታክስ በሚመለከት ተፈጻሚ አይሆንም። Person 1/ A registered person may claim an input tax credit in respect of goods that are trading stock or capital goods held at the date of registration wholly or partly for the purpose of making taxable supplies provided the following conditions are satisfied. a) the person held the trading stock or capital goods at the end of the last day before the date of the person’s registration, b) the trading stock or capital goods were acquired by the person in a creditable acquisition, c) the creditable acquisition occurred no more than: (i) for trading stock, 6 months prior to the date of registration, or (ii) for capital goods, 3 years prior to the date of registration, and (d) the person can provide a tax invoice or other documentary evidence satisfactory to the Tax Authority that the person has paid input tax, and the amount of the payment, in respect of the creditable acquisition. 2/ An input tax credit under Sub-Article (1) of this Article shall be allowed in the First accounting period after the person was registered. 3/ Subject to Articles 29 and 30 of this Proclamation, where Sub-Article (1) of this Article applies to trading stock of a person on hand at the time of the person’s registration, the amount of the input tax credit allowed to the person shall be the input tax paid in respect of the acquisition of the trading stock. 4/ Subject to Articles 29 and 30 of this Proclamation, where Sub-Article (1) of this Article applies to capital goods of a person on hand at the time of the person’s registration, the amount of input tax credit allowed to the person shall be calculated according to the following formula: (C-B) A ______ C A) is the VAT paid by the person on acquisition of the capital goods, and B) is the net book value of the capital goods at the time of person’s registration as determined under the Income Tax Proclamation, and C) is the original cost of the capital goods. 5/ Article 29 Sub-Article (5) of this Proclamation shall not apply for the purposes of an input tax credit allowed under this Article.
፩/ የዕቃዎቹን ግዥ ሲፈጽም ወይም ወደ ሀገር ሲያስገባ የከፈለው የግብአት ታክስ ተቀናሽ የተደረገለት የተመዘገበ ሰው ዕቃዎቹን የግብአት ታክስ ተቀናሽ ለማይፈቀድለት ተግባር ያዋለ እንደሆነ ይህ ተግባር ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት እንደሆነ ተደርጐ ይወሰዳል። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት በተመዘገበ ሰው የተከናወነ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት የግብአት ታክስ ተቀናሽ ለማይፈቀድለት ተግባር በዋለ ጊዜ እንደተከናወነ ይቆጠራል። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት በተከናወነ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት የተመዘገበው ሰው የተቀበለው የውጤት ታክስ እንደሆነ የሚቆጠረው የተመዘገበው ሰው የግብአት ታክሽ ተቀናሽ ለማይደረግበት አቅርቦት ያዋለውን ዕቃ በገዛበት ወይም ወደ ሀገር ባስገባበት ጊዜ የከፈለው የግብአት ታክስ ነው። ፲፮ሺ፴ ፬/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ‹‹የግብአት ተቀናሽ የማይፈቀድለት ተግባር›› ማለት ዕቃን በሚመለከት ዕቃውን ታክስ ከሚከፈልበት አቅርቦት ውጪ ለሆነ አላማ ማዋል ነው:: 1/ An application of goods by a registered person to a non-creditable purpose shall be treated as a taxable supply made by the person, but only if the person has been allowed an input tax credit in respect of the acquisition or import of the goods. 2/ A taxable supply under Sub-Article (1) of this Article shall be treated as made by the registered person at the time that the goods are first applied to a non- creditable purpose. 3/ The amount of output tax payable by a registered person in respect of a taxable supply under Sub-Article (1) of this Article shall be the amount of the input tax credit allowed to the registered person in respect of the acquisition or import of the goods that have been applied to a non-creditable purpose. 4/ In this Article, “Non-creditable purpose”, in relation to goods, means the use of the goods other than to make taxable supplies.
፩/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ይሆናል፡ሀ) ያገለገሉ ዕቃዎች አቅራቢ ያገለገሉ ዕቃዎችን ካልተመዘገበ ሰው በሚገዛበት ጊዜ፣ ለ) ያገለገሉ ዕቃዎች አቅራቢ ያገለገሉትን ዕቃዎች ወደ ሀገር ያስገባ ካልሆነ፣ ሐ) ያገለገሉ ዕቃዎች አቅራቢ ያገለገሉ እቃዎችን የገዛው ከታክስ ነጻ በሆነ ወይም ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ በሚደረግበት ግብይት ካልሆነ፣ እና መ) ያገለገሉት ዕቃዎች አቅራቢ፡- (1) ያገለገሉትን እቃዎች በሚከፈልበት አቅርቦት በሽያጭ ወይም በለውጥ ያቀረበ ከሆነ፣ እና (2) ያገለገሉትን ዕቃዎች በገዛበት ጊዜ በነበሩበት ሁኔታ መልሶ የሚሸጥ ከሆነ። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተዘረዘሩት ሁኔታዎች በተሟሉ ጊዜ ያገለገሉ ዕቃዎች አቅራቢ፡ሀ) ያገለገሉትን ዕቃዎች የግብዓት ተቀናሽ በሚፈቀድለት ግዥ እንደገዛቸው፣ ለ) ያገለገሉትን ዕቃዎች በገዛበት ጊዜ ላገለገሉት ዕቃዎች ከከፈለው ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ በሆነ የታክስ ክፍልፋይ የግብዓት ታክስ እንደከፈለ ተቆጥሮ፤ እና ፲፮ሺ፴፩ ሐ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) (ለ) መሠረት ያገለገሉ ዕቃዎችን አቅርቦት ባከናወነበት የሒሣብ ጊዜ በዚህ ንዑስ አንቀጽ ፊደል ተራ (ለ) መሠረት በግብዓት ላይ ለከፈለው ታክስ የግብአት ታክስ ተቀናሽ ይፈቀድለታል። ፫/ ማናቸውም አቅራቢ ላልተመዘገበ ሰው ላከናወነው አቅርቦት በከፊል ክፍያ መልክ የተቀበለው ያገለገሉ ዕቃዎችን (ከዚህ በኋላ “ዕቃን በዕቃ መገበያየት” ተብሎ የሚጠቀስ) በሚሆንበት ጊዜ ዕቃን በዕቃ በመገበያየት በተከናወነው አቅርቦት የተሸጡ ያገለገሉ ዕቃዎችን ዋጋ ለመወሰን ጥቅም ላይ የዋለው ትክክለኛ የገበያ ዋጋ አቅራቢው እነዚህን ዕቃዎች ለመግዛት ያወጣውን ወጪ ለመወሰን ጥቅም ላይ ከዋለው ትክክለኛ የገበያ ዋጋ ጋር እኩል እንደሆነ ይቆጠራል። ፬/ ካልተመዘገበ ሰው ያገለገሉ ዕቃዎችን የሚገዛ ያገለገሉ ዕቃዎች አቅራቢ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የተገለጹትን ማስረጃዎችን መያዝ አለበት። ፭/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም፡ሀ) ‹‹ያገለገለ ዕቃ›› ማለት ከማይንቀሳቀስ ንብረት እና ከቁም እንስሳት በስተቀር ባልተመዘገበ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ቀደም ሲል ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ዕቃ ነው። ለ) ‹‹ያገለገሉ ዕቃዎች አቅራቢ›› ማለት በሚገዛቸው ጊዜ በነበሩበት ሁኔታ ላይ ያሉ ያገለገሉ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በመሸጥ እና ወይም በመለወጥ ሥራ ላይ የተሰማራ የተመዘገበ ሰው ነው። ፲፮ሺ፴፪ 1/ This Article shall apply where the following conditions are satisfied: a) a Second-hand goods supplier has purchased Second-hand goods from a person who is not a registered person, b) the Second-hand goods supplier did not import the Second-hand goods, c) the Second-hand goods supplier did not acquire the Second-hand goods in an exempt or Zero-rated supply,and d) the Second-hand goods supplier has: (i) supplied the Second-hand goods in a taxable supply by way of sale or exchange, and (ii) the goods are supplied in substantially the same state as they were in at the time the Second- hand goods supplier purchased the goods. 2/ Where the conditions in Sub-Article (1) of this Article are satisfied, the Second- hand goods supplier shall be: a) treated as having acquired the Second- hand goods in a creditable acquisition, b) treated as having paid an amount of input tax in respect of the acquisition of the Second-hand goods equal to the tax fraction of the consideration paid for the Second-hand goods; and c) allowed an input tax credit for the input tax treated as having been paid under Paragraph (b) of this Sub- Article in the accounting period in which the second-hand goods supplier makes the supply referred to in Sub- Article (1) (d) of this Article. 3/ If a supplier receives Second–hand goods (referred to as “traded-in goods”) as part payment for a supply that the supplier makes to a person who is not registered, the fair market value of the traded-in goods used to determine the price for the supply shall be the same as the fair market value used to determine the price paid by the supplier to acquire the traded-in goods. 4/ A Second-hand goods supplier acquiring Second-hand goods from a non- registered person shall maintain the records specified in the Regulations. 5/ In this Article: a) “Second-hand goods” means goods that have previously been used in Ethiopia by a person who is not a registered person other than immovable property or livestock. b) “Second-hand goods supplier” means a registered person whose taxable activity includes the sale or exchange of Second-hand goods in substantially the same state as they were in when purchased by the person.
፩/ የዕድል ሙከራ ጨዋታን በሚመለከት የተመዘገበ ሰው በሚያከናውነው በእያንዳንዱ ታክስ የሚከፈልበት ጨዋታ ሳይሆን በእያንዳንዱ የሒሣብ ጊዜ ውስጥ ካከናወነው ጨዋታ በሚገኘው ትርፍ ላይ በመመስረት የሚከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚሰላበት ዘዴ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ይወሰናል። ፪/ የተመዘገበ ሰው ለዕድል ሙከራ ጨዋታው በአቅርቦትነት ባዋላቸው የዕድል ሙከራ ማጫወቻ አቅርቦቶች ላይ የከፈለው የግብአት ታክስ ተቀናሽ አይደረግም እንዲሁም አቅርቦቱን ያከናወነው የተመዘገበ ሰው ለአቅርቦቱ የታክስ ደረሰኝ መስጠት የለበትም። 1/ The Regulations shall provide for the calculation of the VAT payable on gambling supplies made by a registered person on a margin basis for each accounting period rather than separately for each taxable gambling supply. 2/ A registered person shall not be allowed an input tax credit in respect of the acquisition of a gambling supply and the registered person making the supply shall not issue a tax invoice for the supply.
፩/ ማናቸውም አቅራቢ ከዕቃ ወይም ከአገልግሎት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ተቀማጭ ገንዘብ የተቀበለ እና ይህም ተቀማጭ ገንዘብ በአቅራቢው ውርስ የተደረገ እንደሆነ፣ ተቀማጩ ገንዘብ ውርስ በተደረገበት ጊዜ አቅራቢው የአገልግሎት አቅርቦት እንዳከናወነ ይቆጠራል። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተመለከተው የአገልግሎት አቅርቦት እና ውርስ የተደረገው የተቀማጭ ገንዘብ አቅርቦት አንድ ዓይነት ባህሪ ያላቸው እንደሆኑ ተደርገው ይወሰዳሉ። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተመለከተው የአገልግሎት አቅርቦት እሴት የሚከተለው ይሆናል፡ሀ) ተቀማጩ ገንዘብ ውርስ በተደረገ ጊዜ የተመዘገበ ሰው የነበረን አቅራቢ በሚመለከት፣ በተወረሰው ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ላይ ከተቀማጩ ገንዘብ ጋር እኩል የሆነ የገንዘብ መጠን ሲቀነስ እና በታክሱ ክፍልፋይ ሲበዛ፣ ወይም ፲፮ሺ፴፫ ለ) ሌላ ማናቸውንም አቅራቢ በሚመለከት ውርስ የተደረገው ተቀማጭ ገንዘብ መጠን። ፬/ ይህ አንቀጽ ለዕቃ ማሸጊያነት ለሚውሉ ዕቃዎች የሚሰጠውን ተቀማጭ ገንዘብ አይጨምርም። 1/ If a supplier has received a deposit in connection with a supply of goods or services and the deposit is forfeited to the supplier, the forfeiture of the deposit shall be treated as a supply of services by the supplier at the time of forfeiture of the deposit. 2/ A supply of services under Sub-Article (1) has the same character as the supply to which the forfeited deposit relates. 3/ The value of a supply of services under Sub-Article (1) of this Article shall be: a) for a supplier who is a registered person at the time of forfeiture of the deposit, the forfeited amount reduced by an amount equal to the forfeited amount multiplied by the tax fraction, or b) for any other supplier, the amount of the forfeited deposit. 4/ This Article shall not apply to a deposit on a returnable container.
፩/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡ሀ) የመብት፤ የምርጫ ወይም የቫውቸር አቅርቦት ሲኖር፣ እና ለ) መብቱን ወይም ምርጫውን በመጠቀም ሂደት ወይም ለተከታታይ አቅርቦት ክፍያ ቫውቸሩን በሙሉ ወይም በከፊል በመመለስ ሂደት ሌላ አቅርቦት (‹‹ተከታይ አቅርቦት››) ተፈጽሞ ከሆነ። ፪/ የቫውቸር አቅርቦቱ የሚፈጸመው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ከሆነ፣ ለተከታታይ ክፍያ ለተከታዩ አቅርቦት ወይም ከመብቱ ወይም ምርጫው አቅርቦት ጋር በተያያዘ በተጨማሪነት ከሚፈጸመው ክፍያ መጠን ሊበልጥ አይችልም። ፫/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ የመብት፤ የምርጫ ወይም የቫውቸር አቅርቦቱ ታክስ የማይከፈልበት አቅርቦት ከሆነ እና ተከታይ አቅርቦቱ ብቻ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ከሆነ ለተከታዩ አቅርቦት የሚፈጸመው ክፍያ ለመብቱ፤ ለምርጫው ወይም ለቫውቸሩ አቅርቦት የተፈጸመን ክፍያ ይጨምራል። ፬/ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ቫውቸርን ማዘጋጀት የአገልግሎት አቅርቦት እንደሆነ ይቆጠራል። ፭/ ይህ አንቀጽ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፯ ተፈጻሚ የሚሆንበትን ቫውቸር በሚመለከት ተፈጻሚ አይሆንም። ፲፮ሺ፴፬ 1/ This Article shall apply where the following conditions are satisfied: a) there is a supply of a right, option or voucher, and b) another supply (referred to as the “Subsequent supply”) is made on the exercise of the right or option, or in return for the voucher in full or part payment for the subsequent supply. 2/ Where this Article applies and the supply of the right, option, or voucher is a taxable supply, the amount of the consideration for the subsequent supply shall be limited to any additional consideration given for the subsequent supply or in connection with the exercise of the right or option. 3/ Where this Article applies and the supply of the right, option or voucher is not a taxable supply but the subsequent supply is a taxable supply, the amount of the consideration for the subsequent supply shall include any consideration given for the supply of the right, option, or voucher. 4/ The issue of a voucher shall be a supply of services for the purposes of this Proclamation. 5/ This Article shall not apply to a voucher to which Article 37 of this Proclamation applies.
፩/ የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ከተገኙ ቫውቸር ማዘጋጀት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት እንደሆነ አይቆጠርም፦ ሀ) ቫውቸሩ በእጁ የሚገኝ ሰው ቫውቸሩን በማስረከብ እስከተወሰነ የገንዘብ መጠን ድረስ ዋጋ ያላቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች የሚያገኝበት ከሆነ፤ ለ) ቫውቸሩን መጠቀም የሚቻልባቸው እቃዎች እና አገልግሎቶች የተለየ የተጨማሪ እሴት ታክስ አፈጻጸምን የሚከተሉ ከሆነ፤ እና ሐ) ቫውቸሩ የተወሰነ የገንዘብ መጠን ይዞ የሚታተም ከሆነ። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተመለከተው ቫውቸር ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ ከሚደረግበት በስተቀር የተመዘገበ ሰው ለሚያከናውነው አቅርቦት በክፍያ መልክ የሚሰጥ ከሆነ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል ተራ (ሐ) የተመለከተው የገንዘብ መጠን ሁለት መልኮች እንዳሉት ሆኖ ይቆጠራል፡ሀ) ለአቅርቦቱ ሙሉ ዋጋ ወይም ከፊል ዋጋ ክፍያ የሚውለው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) (ሐ) በተመለከተው የገንዘብ መጠን ላይ ተሰልቶ ሊከፈል የሚገባው የታክስ ክፍልፋይ መጠን ተቀናሽ ይደረጋል፣ እና ለ) በአቅርቦቱ ላይ የሚከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ በሙሉ ወይም ከፊሉ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) (ሐ) በተመለከተው የገንዘብ መጠን ላይ በማስከፈያው ታክስ ክፍልፋይ መሠረት እንዲሰላ ይደረጋል። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (፩) የተጠቀሰው ቫውቸር በሙሉ ወይም በከፊል ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ጊዜው ያለፈ እንደሆነ፡- ፲፮ሺ፴፭ ሀ) በቫውቸሩ ጊዜ ማለፍ የቫውቸሩ አቅራቢ ቫውቸሩ ለተሰጠው ሰው የአገልግሎት አቅርቦት እንዳከናወነ ይቆጠራል፤ ለ) በዚህ ንኡስ አንቀጽ ፊደል ተራ (ሀ) የተመለከተው አገልግሎት አቅርቦት ተፈጽሟል የሚባለው የቫውቸሩ መጠቀሚያ ጊዜ ባለፈበት ቀን ነው፤እና ሐ) በዚህ ንኡስ አንቀጽ (ሀ) የተመለከተው አቅርቦት ዋጋ፡- (1) የቫውቸሩ የመጠቀሚያ ጊዜ ባለፈበት ቀን የተመዘገበ ሰው የነበረን አቅራቢ በሚመለከት ጥቅም ላይ ካልዋለው የቫውቸሩ ዋጋ ላይ፤ ጥቅም ላይ ያልዋለው የቫውቸሩ ዋጋ ሲባዛ በታክስ ክፍልፋይ የሚገኘው ወጤት ተቀንሶ፤ ወይም (2) ለሌላ ማናቸውም አቅራቢ ጥቅም ላይ ያልዋለው የቫውቸሩ ዋጋ። ፬/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) ተፈጻሚ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ይሆናል፡ሀ) የተመዘገበ ሰው ያለአንዳች ክፍያ ቫውቸር ሲሰጥ፣ ለ) ቫውቸሩ የተሰጠው ሰው ቫውቸሩን በመጠቀም ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በቅናሽ ዋጋ ከሌላ አቅራቢ መግዛት የሚችል ሲሆን፣ እና ሐ) ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ ከሚሆንበት በስተቀር ቫውቸሩ ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ለመግዛት የሚውል በሚሆንበት ጊዜ። ፲፮ሺ፴፮ ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) የተዘረዘሩት የተሟሉ በሚሆንበት ጊዜ፤ የአቅርቦቱ ዋጋ እንደሆነ የሚወሰደው የቫውቸሩን የገንዘብ ዋጋ በታክስ ማስከፈያው መጣኔ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከቫውቸሩ ዋጋ ላይ በመቀነስ የሚገኘውን ሒሳብ ይጨምራል። ፮/ አቅራቢው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) የተመለከተውን ቫውቸር ለተመዘገበው ሰው በሚመልስበት ጊዜ የተመዘገበው ሰው ለአቅራቢው በከፈለው የገንዘብ መጠን ልክ የግብዓት ታክስ ተቀናሽ ያገኛል። ፯/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፮) መሠረት ተቀናሽ የሚደረገው የግብአት ታክስ ለአቅራቢው የተከፈለው የገንዘብ መጠን በታክሱ ክፍልፋይ ሲባዛ የሚገኘው ውጤት ሲሆን፣ የግብዓት ታክሱ ተቀናሽ የሚደረገው ለአቅራቢው ክፍያ በተፈጸመበት የሒሣብ ጊዜ ይሆናል። 1/ The issue of a voucher shall not be a supply for the purposes of this Proclamation if: a) the voucher entitles the holder to receive supplies of goods or services up to a monetary amount on redemption of the voucher; b) the possible goods or services for which the voucher can be redeemed have different VAT treatments; and c) the voucher is issued for an amount in money. 2/ If a voucher referred to in Sub-Article (1) of this Article is redeemed for a taxable supply, other than a Zero-rated supply, made by a registered person, the amount referred to in Sub-Article (1) Paragraph (c) of this Article shall be treated as comprising Two components: (a) an amount as the consideration, or part of the consideration, for the supply calculated as the amount referred to in Sub-Article (1)(c) of this Article reduced by the tax fraction of that amount, and (b) an amount as the VAT, or part of the VAT, payable in respect of the supply calculated as the tax fraction of the amount referred to in Sub-Article (1)Paragraph (c) of this Article. 3/ If a voucher referred to in Sub-Article (1) of this Article expires without being used, or fully used: a) the expiration of the voucher is treated as a supply of services by the supplier of the voucher to the person to whom the voucher is issued; b) the time of the supply of services under Paragraph (a) of this Sub- Article is the time when the voucher expired; and c) the value of a supply of services under Paragraph (a) of this Sub-Article is: (i) for a supplier who is a registered person at the time of expiration of the voucher, the unused amount of the voucher reduced by an amount equal to the unused amount multiplied by the tax fraction; or (ii) for any other supplier, the unused amount of the voucher. 4/ Sub-Article (5) of this Article shall apply where all the following conditions are satisfied: a) a registered person issues a voucher for no charge, b) the voucher entitles the holder to a discount on the price of goods or services supplied by another person, and c) the voucher is redeemed for a taxable supply, other than a Zero-rated supply. 5/ Where the conditions in Sub-Article (4) of this Article are satisfied, the consideration for the supply includes the monetary value of the voucher reduced by an amount equal to the monetary value multiplied by the tax fraction. 6/ A registered person shall be entitled to an input tax credit in respect of any amount paid to a supplier in respect of the redemption by the supplier of a voucher referred to in Sub-Articles (5) of this Article. 7/ The amount of the input tax credit referred to in Sub-Article (6) of this Article shall be the amount paid to the supplier multiplied by the tax fraction and the input tax credit shall be allowed in the accounting period in which the amount is paid to the supplier.
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው፡ሀ) የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ የቅድሚያ ክፍያ በማስከፈል የሚሰጠውን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ወይም ለ) በቅድመ-ክፍያ የሚቀርብን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በማቅረብ ረገድ አከፋፋይ፣ ወኪል ወይም የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አገናኝ ሆኖ የሚሰራ ሰው የሚያቀርበውን አገልግሎት በሚመለከት ነው። [ ፲፮ሺ፴፯ ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ አንድ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ ለሌላ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ የሚሰጠውን እና በዚህ አዋጅ መሠረት ከሚከናወን መደበኛ የሥራ እንቅስቃሴ ጋር የተገናኘን አቅርቦት በሚመለከት ተፈጻሚ አይሆንም። ፫/ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ በቅድመ ክፍያ የሚቀርብን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በታች በሆነ የቅናሽ ዋጋ ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አገናኝ በሚያቀርብ ጊዜ የአቅርቦቱ ዋጋ የሚሰላው የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አገናኙ አቅርቦቱን በችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደገዛ ተቆጥሮ ነው። ፬/ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አገናኝ በቅድመ ክፍያ የሚቀርብን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚገዛ እና የሚሸጥ በሚሆንበት ጊዜ፡ሀ) የሚፈጽመው ግዥ እንዳልተፈጸመ፣ እና ለ) የሚሸጠው አገልግሎት እንዳልቀረበ፣ ተደርጐ ይቆጠራል። ፭/ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ በቅድመ ክፍያ የሚቀርብን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ወኪል ሆኖ በሚሠራ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አገናኝ አማካኝነት የሚያቀርብ በሚሆንበት ጊዜ ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቱ ከሚከፈለው ዋጋ ላይ ለአገናኙ የሚከፈለው ኮሚሽን ተቀናሽ አይደረግም። ፲፮ሺ፴፰ Services 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article, this Article shall apply to: a) a supply, by a telecommunications service supplier, of a prepaid telecommunications product, or [ b) a supply by a person who acts as a distributor, agent, or telecommunications intermediary in relation to the supply of a prepaid telecommunications product. 2/ Sub-Article (1) of this Article shall not apply to a supply by one telecommunications service supplier to another telecommunications service supplier and such a supply is subject to the normal operation of this Proclamation. 3/ If a telecommunications service supplier supplies a prepaid telecommunications product to a telecommunications intermediary at a discount from the intended retail price, the consideration for the supply shall be calculated as if the intermediary had paid the intended retail price. 4/ If a telecommunications intermediary purchases and on-sells a prepaid telecommunications product: a) the acquisition by the intermediary shall be treated as if it were not an acquisition, and b) the supply by the intermediary shall be treated as if it were not a supply. 5/ Where a telecommunications service supplier supplies a prepaid telecommunications product through a telecommunications intermediary acting as agent for the telecommunications supplier, the consideration for the supply shall not be reduced by the commission paid to the intermediary.
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገበው ሰው ሠራተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ከሆነ እና ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ለሠራተኞች የሚሰጥ ጥቅማ ጥቅም አንድ ክፍል በማድረግ የሚያቀርብ ከሆነ፣ አቅርቦቱ ክፍያን በመቀበል በትክክለኛ የገበያ ዋጋ እንደተፈጸመ ይቆጠራል። ፪/ አሠሪው ለሠራተኞቹ ለሚያከናውነው አቅርቦት እንዲውል በፈጸመው ተቀናሽ የሚሆን ግዢ ላይ የታክስ ተቀናሽ ሊያገኝ የማይችል ከሆነ አቅርቦቱን ለሠራተኞቹ ያለክፍያ እንደፈጸመ ይቆጠራል። 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article, where a registered person is an employer who makes a taxable supply to an employee as part of the employee’s remuneration, the supply shall be treated as having been made for consideration equal to fair market value of the supply. 2/ A taxable supply made by an employer to an employee shall be treated as having a nil value if the employer is not entitled to an input tax credit in respect of a creditable acquisition to make the taxable supply to the employee.
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የውሉ አካል ቢሆንም ባይሆንም የተመዘገበ ሰው ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት በደረሰ ጉዳት ምክንያት የጠቅላላ መድን ካሣ የተቀበለ እንደሆነ፣ የዚህ ዓይነቱ ክፍያ የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት ለአገልግሎቱ አቅርቦት እንደተከፈለው ዋጋ ይቆጠራል። ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የሚከተሉትን በተመለከተ ተፈጻሚ አይሆንም፡ሀ) ክፍያ የተፈጸመበት የጠቅላላ የመድን ውል አቅርቦት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ወይም ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ የሚደረግበት ከሆነ፣ ወይም ለ) የካሣ ክፍያው የተፈጸመው በሰው አካል ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት ከሆነ። ፲፮ሺ፴፱ ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የተከናወነው አቅርቦት የተመዘገበው ሰው ክፍያውን በተቀበለ ቀን እንደተፈጸመ የሚቆጠር ሲሆን፣ የአቅርቦቱ ዋጋ ነው የሚባለው የተመዘገበው ሰው ከተቀበለው ገንዘብ ላይ የታክሱ ክፍልፋይ የገንዘብ መጠን ከተቀነሰ በኋላ የሚቀረው ሒሣብ ነው። ፬/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) እንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገበ የኢንሹራንስ ኩባንያ በአንድ ሌላ ሰው ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት በጠቅላላ መድን ውል መሠረት የካሣ ክፍያ የከፈለ እንደሆነ፣ ከዚህ በታች የተመለከቱት ተሟልተው ሲገኙ ከተከፈለው የካሣ ክፍያ ውስጥ የታክሱ ክፍልፋይ የግብአት ታክስ ተቀናሽ እንዲሆን ይደረጋል፡ሀ) የጠቅላላ መድን አቅርቦት ዜሮ የማስከፈያ መጣኔ ተፈጻሚ ከሚደረግበት ውጪ ያለ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ከሆነ፣ እና ለ) ክፍያው የተፈጸመው በኢትዮጵያ ነዋሪ ለሆነ ወይም በኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነ የተመዘገበ ሰው ከሆነ፣ እና ሐ) ክፍያው የተፈጸመው የኢንሹራንስ ኩባንያው ለሚያከናውነው አቅርቦት ወይም ወደ ሀገር የማስገባት ተግባር ካልሆነ። ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) መሠረት የግብአት ታክስ ተቀናሽ የሚደረገው የኢንሹራንስ ኩባንያው ክፍያውን በፈጸመበት የሒሣብ ጊዜ ነው። ፲፮ሺ፵ ፮/ የተመዘገበው የኢንሹራንስ ኩባንያ ለሞራል ወይም በቅጣት መልክ ከሚከፈል ካሣ በስተቀር በአጠቃላይ የመድኑ ውሉ መሠረት በተፈጸመ መዳረግ ምክንያት የከፈለውን ካሣ መልሶ የተቀበለ እና በዚህ መልክ መልሶ በተቀበለው ገንዘብ ላይ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆን ከሆነ፣ መልሶ የተቀበለው ገንዘብ የተመዘገበው የኢንሹራንስ ኩባንያ ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት ካቀረበው አገልግሎት የተቀበለው ገንዘብ እንደሆነ ይቆጠራል። ፯/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፮) የተመለከተው አቅርቦት የኢንሹራንሱ ኩባንያ የከፈለውን የካሣ ገንዘብ መልሶ በተቀበለበት ቀን እንደተከናወነ ይቆጠራል። ፰/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም፡- ‹‹ጠቅላላ መድን ስራ›› የሚለው ሐረግ በመድን ስራ አዋጅ ቁጥር ፯፻፵፮/፪ሺ፬ (እንደተሻሻለ) የተሰጠውን ትርጉም የሚይዝ ሲሆን፤ ሆኖም በዚያው አዋጅ በተተረጎመው መሠረት አነስተኛ የመድን ንግድ ስራ ማከናወንን አይጨምርም፤ እና ‹‹የጠቅላላ መድን ስራ ውል›› ማለት የጠቅላላ መድን የንግድ ሥራን በማከናወን ሂደት የተፈጸመ የመድን ውል ነው። 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article, if a registered person receives a payment under a general insurance contract that relates to a loss to the extent incurred in the course or furtherance of the person’s taxable activity, whether or not the person is a party to the contract, the payment shall be treated as consideration for a supply of services made by the registered person in the course or furtherance of the person’s taxable activity. 2/ Sub-Article (1) of this Article shall not apply where: a) the supply of the general insurance contract to which the payment relates is an exempt or Zero-rated supply, or b) the payment is compensation made for accidental personal injury. 3/ A supply under Sub-Article (1) of this Article shall occur on the date that the person receives the payment and the value of the supply is the amount received reduced by the tax fraction of that amount. 4/ Without prejudice to Sub Article 5 of this Article if a registered person that is an insurer makes a payment to another person to indemnify that other person under a general insurance contract, the insurer shall be allowed an input tax credit for an amount equal to the tax fraction of the payment made but only where: a) the supply of the general insurance contract was a taxable supply, other than a Zero-rated supply, b) the payment is made to a resident person or a non-resident person who is a registered person, and c) the payment is not made in respect of a supply to, or an import by, the insurer. 5/ The input tax credit allowed under Sub- Article (4) of this Article shall be allowed in the accounting period in which the insurer makes the payment. 6/ If a registered person that is an insurer recovers an amount, other than moral or exemplary damages, as a result of the exercise of rights acquired by subrogation under a general insurance contract and Sub-Article (4) of this Article applies to the payment to which the recovered amount relates, the payment shall be treated as consideration for a supply of services made by the insurer in the course or furtherance of the insurer’s taxable activity. 7/ A supply under Sub-Article (6) of this Article shall occur on the date that the insurer receives the payment. 8/ In this Article: “General insurance business” has the meaning in the Insurance Business Proclamation No. 746/2012 (as Amended) but does not include the business of providing micro-insurance as defined in that Proclamation; and “General insurance contract” means a contract of insurance entered into in the course of carrying on a general insurance business.
፩/ ማናቸውም ወኪል ወካዩን (ከዚህ በኋላ ‹‹ወካይ››) በመወከል የሚያከናውነው የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅርቦት በወካዩ የተከናወነ አቅርቦት እንደሆነ ተደርጐ ይቆጠራል. ፲፮ሺ፵፩ ፪/ ለታክስ አስተዳደር አዋጅ አፈጻጸም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተጠቀሰው ወኪል የታክስ እንደራሴ እንደሆነ ይቆጠራል። ፫/ ወኪል ለሆነ ሰው የሚቀርብ ዕቃ ወይም አገልግሎት ለወካዩ የተደረገ አቅርቦት እንደሆነ ይቆጠራል። ፬/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፫) ድንጋጌ ወኪሉ ለወካዩ የሚሰጠውን አገልግሎት በሚመለከት ተፈጻሚ አይሆንም። 1/ A supply of goods or services made by a person as agent for another person (the “principal”) shall be treated as a supply made by the principal. 2/ An agent of a principal under Sub-Article (1) of this Article shall be treated as a tax representative of the principal for the purposes of the Tax Administration Proclamation. 3/ A supply of goods or services made to a person as agent for a principal shall be treated as a supply made to the principal. 4/ Sub-Articles (1) and (3) of this Article shall not apply to a supply of services made by an agent to the agent’s principal.
፩/ የተመዘገበ ቢሆንም ባይሆንም ባለዕዳ ለባለገንዘብ መክፈል የሚገባውን ዕዳ በሙሉ ወይም በከፊል ለማስከፈል ባለገንዘቡ የባለዕዳውን ዕቃ ለሦስተኛ ወገን የሸጠ እንደሆነ፡ሀ) ለሦስተኛ ወገን የተከናወነው ሽያጭ በባለዕዳው የተፈጸመ እንደሆነ ተደርጐ የሚቆጠር ሲሆን፣ የግብይቱ ባህሪ በዚህ አዋጅ በተደነገገው መሠረት የሚወሰን ይሆናል፣ እና ለ) ባለዕዳው ለባለገንዘቡ አቅርቦቱ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆኑን በጽሑፍ እስካላረጋገጠለት ድረስ ባለገንዘቡ በዕቃው ላይ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ የመክፈል ግዴታ አለበት። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል ተራ (ለ) መሠረት ባለዕዳው ለባለገንዘቡ የሚሰጠው ማረጋገጫ አቅርቦቱ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የተደረገበትን ምክንያት የሚገልጽ መሆን አለበት። ፲፮ሺ፵፪ ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) (ለ) መሠረት ማረጋገጫ ያልተሰጠው ባለገንዘብ በእጁ ያለውን ማናቸውንም መረጃ መሠረት በማድረግ አቅርቦቱ በባለዕዳው ቢከናወን ኖሮ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ይሆን እንደነበር አድርጐ መውሰድ ይችላል። ፬/ የባለዕዳውን ዕቃ የሚሸጥ ባለገንዘብ የከፈለው የግብአት ታክስ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል ተራ (ለ) መሠረት ከሚሰበሰበው የውጤት ታክስ ላይ እንዲቀነስለት ማድረግ አይችልም። ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ ያለበት ባለገንዘብ፡- (ሀ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በሚወሰነው ጊዜ እና አኳኋን መሠረት የሰበሰበውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቅ እና ገቢ ማድረግ፤ እና (ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተደነገገው ቢኖርም፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የተመለከተውን ዝርዝር የያዘ የታክስ ደረሰኝ የአገልግሎቱ ተቀባይ ለሆነው የተመዘገበ ሰው መስጠት፤ አለበት። ፮/ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌ በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ ፵ መሠረት ባለገንዘቡን ወክሎ የሚሠራን ንብረት ተረካቢን በሚመለከትም ተፈጻሚ ይሆናል። ፲፮ሺ፵፫ 1/ If a creditor, whether registered or unregistered, supplies the goods of a debtor to a third person in full or partial satisfaction of a debt owed by the debtor to the creditor: a) the supply to the Third person shall be treated as having been made by the debtor and the nature of the supply under this Proclamation shall be determined accordingly, and b) the creditor shall be liable to pay the VAT payable on the supply unless the debtor provides the creditor with a written statement that the supply is not subject to VAT. 2/ A statement provided by a debtor under Sub-Article (1) Paragraph (b) of this Article shall set out the reasons why the supply is not subject to VAT. 3/ A creditor who has not received a statement under Sub-Article (1) (b) of this Article may, based on any reasonable information available to the creditor, treat the supply as a supply that would not have been subject to VAT if the supply had been made by the debtor. 4/ A creditor making a supply of the goods of a debtor shall not be entitled to a credit for any input tax incurred by the creditor in making the supply against the output tax referred to in Sub-Article (1) Paragraph (b) of this Article. 5/ A creditor who is required to pay VAT by operation of Sub-Article (1) of this Article shall: a) file a return and pay the VAT at such time and manner as may be prescribed in the Regulations; and b) despite Article 55 Sub-Article (2) of this Proclamation, provide a recipient who is a registered person with a tax invoice containing the particulars specified in the regulations. 6/ This Article shall apply to a receiver acting for a creditor under Article 40 of the Tax Administration Proclamation.
፩/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው፡ሀ) የተመዘገበ ሰው አቅርቦት ሲያከናውን፣ ለ) በአቅርቦቱ ላይ ማስተካከያ ማድረግ የሚያስገድድ ሁኔታ ሲፈጠር፣ እና ሐ) ማስተካከያ ማድረግ የሚያስገድድ ሁኔታ በመፈጠሩ ምክንያት የተመዘገበው ሰው በአቅርቦቱ ላይ ሊከፍል የሚገባው ትክክለኛው የተጨማሪ እሴት ታክስ መጠን ለታክስ ባለስልጣኑ ገቢ ለማድረግ ከተሰበሰበው የገንዘብ መጠን የበለጠ በሚሆንበት ጊዜ ነው። ፪/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል ተራ (ሐ) መሠረት በተጨማሪነት የተሰበሰበው ታክስ ማስተካከያው በተደረገበት የሒሣብ ጊዜ የአቅራቢው የውጤት ታክስ ሆኖ ይወሰዳል። ፫/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው በተመዘገበ ሰው ላይ በሚሆንበት እና አቅራቢው ለገዥው ዋነኛውን የታክስ ደረሰኝ የሰጠ በሚሆንበት ጊዜ፡ሀ) አቅራቢው በአቅርቦቱ ላይ በተጨማሪነት የተከፈለውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚያሳይ የዴቢት ሰነድ ለገዥው መስጠት አለበት፣ ለ) የአዋጁ አንቀጽ ፴ ተፈጻሚ የማይደረግ ሆኖ፤ ገዥው አቅርቦቱን ታክስ ለሚከፈልበት አቅርቦት እስካዋለው ድረስ በዴቤት ሰነዱ ለተመለከተው በተጨማሪነት ለተከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ የግብአት ተቀናሽ ማግኘት፤ ይፈቀድለታል፤ እና ፲፮ሺ፵፬ ሐ) በዚህ ንዑስ አንቀጽ ፊደል ተራ (ለ) በተመለከተው የገንዘብ መጠን ገዥው የዴቢት ሰነዱን በተቀበለበት የሒሣብ ጊዜ የግብዓት ታክስ ተቀናሽ ማግኘት አለበት። Being Under-Charged 1/ This Article shall apply where: a) a registered person has made a supply, b) an adjustment event has occurred in relation to the supply, and c) as a result of the occurrence of the adjustment event, the correct amount of VAT payable in respect of the supply exceeds the VAT that the registered person actually accounted for to the Tax Authority in respect of the supply. 2/ If this Article applies, the excess referred to in Sub-Article (1) (c) of this Article shall be treated as output tax of the supplier for the accounting period in which the adjustment event occurred. 3/ If the recipient of a supply to which this Article applies is a registered person and the supplier has provided the recipient with an original tax invoice for the supply: a) the supplier shall provide the recipient with a debit note specifying the additional VAT payable in respect of the supply, b) the recipient shall be allowed an input tax credit for the additional VAT specified in the debit note to the extent that the recipient used the supply to make taxable supplies and Article 30 of this Proclamation does not apply; and c) the recipient shall be allowed the input tax credit referred to in Paragraph (b) of this Sub-Article in the accounting period in which the recipient received the debit note.
፩/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው፡ሀ) የተመዘገበ ሰው አቅርቦት ሲያከናውን፣ ለ) በአቅርቦቱ ላይ ማስተካከያ ማድረግ የሚያስገድድ ሁኔታ ሲፈጠር፣ እና ሐ) ማስተካከያ ማድረግ የሚያስገድድ ሁኔታ በመፈጠሩ ምክንያት የተመዘገበው ሰው ለታክሱ ባለስልጣን ገቢ ለማድረግ የሰበሰበው የተጨማሪ እሴት ታክስ በአቅርቦቱ ላይ ሊከፈል ከሚገባው ትክክለኛው የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚበልጥ ሆኖ ሲገኝ ነው። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ አቅራቢው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) (ሐ) የተመለከተው በብልጫ የከፈለው ታክስ ድርጊቱ በተፈፀመበት የሒሣብ ጊዜ ውስጥ የግብአት ታክስ ተቀናሽ ሆኖ ይያዛል። ፫/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆንበት ግዥ ፈፃሚው የተመዘገበ ሰው በሚሆንበት እና አቅራቢው ለገዥው ዋነኛውን የታክስ ደረሰኝ የሰጠ በሚሆንበት ጊዜ፡ሀ) አቅራቢው በአቅርቦቱ ላይ ተከፋይ ሊሆን የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የቀነሰበትን መጠን የሚያሳይ የክሬዲት ሰነድ ለገዥው መስጠት፣ እና ፲፮ሺ፵፭ ለ) በዚህ ንዑስ አንቀጽ ፊደል ተራ (ሀ) የተመለከተው የገንዘብ መጠን ገዥው የክሬዲት ሰነድ በተቀበለበት የሒሣብ ጊዜ የውጤት ታክስ ሆኖ መያዝ አለበት። ፬/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ተፈጻሚ የሚሆንበት ገዢ ያልተመዘገበ ሰው በሚሆንበት ጊዜ አቅራቢው ለገዢው በብልጫ የተከፈለውን የተጨማሪ እሴት ታክስ በጥሬ ገንዘብ እስከሚመልስ ወይም ገዥው ለአቅራቢው ሊከፍል ለሚገባው ሌላ ሒሣብ ማካካሻ እስከሚያውል ድረስ በዚህ አንቀጽ የተመለከተውን የግብአት ታክስ ተቀናሽ ሊያገኝ አይችልም። being Over-Charged 1/ This Article shall apply where: a) a registered person has made a supply, b) an adjustment event has occurred in relation to the supply, and c) as a result of the occurrence of the adjustment event, the VAT that the registered person actually accounted for to the Tax Authority in respect of the supply exceeds the correct amount of VAT payable in respect of the supply. 2/ Subject to Sub-Article (4) of this Article, where this Article applies, the supplier shall be allowed an input tax credit for the excess referred to in Sub-Article (1) (c) of this Article in the accounting period in which the event occurred. 3/ If the recipient of a supply to which this Article applies is a registered person and the supplier has provided the recipient with an original tax invoice for the supply: a) supplier shall provide the recipient with a credit note specifying the amount by which the VAT payable in respect of the supply is reduced; and b) the amount referred to in Paragraph (a) of this Sub-Article shall be treated as output tax of the recipient for the accounting period in which the recipient received the credit note. 4/ If the recipient of a supply to which Sub- Article (2) of this Article applies is not a registered person, the supplier shall not be allowed a credit for the input tax referred to in that Sub-Article until the supplier has repaid the excess VAT to the recipient of the supply in cash or as a credit against any amount owing to the supplier by the recipient.
፩/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው የሚከተሉት ተሟልተው ሲገኙ ይሆናል፡ሀ) የተመዘገበው ሰው ባከናወነው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ላይ ለታክሱ ባለስልጣን የውጤት ታክስ ገቢ አድርጐ ከሆነ፣ እና ለ) ለአቅርቦቱ ሊከፈል የሚገባው ዋጋ በፋይናንስ ሪፖርት አዋጅ በተመለከተው የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃ መሰረት በሙሉ ወይም በከፊል በተመዘገበው ሰው የሒሣብ መግለጫ ውስጥ ሊሰበሰብ የማይችል ዕዳ ተብሎ የተያዘ ከሆነ፣እና (ሐ) ዕዳውን ለማስከፈል የሕግ እርምጃ የተወሰደ ቢሆንም ዕዳው ሊከፈል የማይችል ሆኖ ከተገኘ። ፲፮ሺ፵፮ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተመለከቱት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የተመዘገበው ሰው ሊሰበሰብ የማይችል ዕዳ ነው ከተባለው አቅርቦት ጋር በተያያዘ ለታክሱ ባለሥልጣን ገቢ ባደረገው የውጤት ታክስ መጠን የግብአት ታክስ ተቀናሽ ያገኛል። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት የግብዓት ታክስ ተቀናሽ ሊደረግ የሚችለው ከሚከተሉት በዘገየው ቀን ነው፡ሀ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ተሟልተው በተገኙበት ቀን፤ ወይም ለ) የተመዘገበው ሰው በአቅርቦቱ ላይ የሚከፈለውን የውጤት ታክስ ለታክሱ ባለስልጣን ገቢ ካደረገበት የሂሳብ ጊዜ መጨረሻ ጀምሮ ከሚቆጠር የ፲፪ ወራት ጊዜ በኋላ። ፬/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆንበትን ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት የገዛው ሰው የተመዘገበ ሰው ከሆነ እና በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) መሠረት የግብአት ታክስ ተቀናሽ በሚደረግበት ጊዜ ያለ ከሆነ፣ የግብአት ታክስ ተቀናሽ ሊደረግ የሚችለው አቅራቢው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት በሚሰላው ሊሰበሰብ የማይችል ዕዳ ላይ የተከፈለውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚያሳይ የክሬዲት ሰነድ የሰጠ እንደሆነ ብቻ ነው። ፲፮ሺ፵፯ ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) መሠረት የክሬዲት ሰነድ የተሰጠው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ገዥ በክሬዲት ሰነዱ ለተገለፀው የተጨማሪ እሴት ታክስ የግብአት ታክስ ተቀናሽ የጠየቀ ከሆነ፣ በክሬዲት ሰነዱ የተገለጸውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የክሬዲት ሰነዱ በተሰጠበት የሒሣብ ጊዜ ውስጥ በገዥው የሚከፈል የውጤት ታክስ እንደሆነ አድርጐ መያዝ አለበት። 1/ This Article applies if the following conditions are satisfied: a) a registered person has accounted to the Tax Authority for output tax payable in respect of a taxable supply made by the person, b) the whole or a part of the consideration for the supply is subsequently treated in the financial accounts of the person as a bad debt in accordance with financial reporting standards stipulated under the Financial Reporting Proclamation, and c) legal action has been taken to recover the debt but the debt is irrecoverable. 2/ Where the conditions in Sub-Article (1) of this Article are satisfied and subject to Sub-Article (4) of this Article, the registered person shall be allowed an input tax credit for the amount of output tax accounted for to the Tax Authority in respect of the supply that corresponds to the amount of the debt treated as bad. 3/ An input tax credit under Sub-Article (2) of this Article shall be allowed on the later of: a) the date on which the conditions in Sub-Article (1) of this Article are satisfied; or b) 12 calendar months after the end of the accounting period in which the registered person accounted for the output tax to the Tax Authority in respect of the supply. 4/ If the recipient of a taxable supply to which this Article applies is a registered person that is still in existence at the time the input tax credit arises under Sub- Article (3) of this Article, the input tax credit shall be allowed only if the supplier issues a credit note to the recipient specifying the amount of the VAT that relates to the bad debt calculated in accordance with Sub- Article (2) of this Article. x ለ/ሐ 5/ The recipient of a taxable supply issued with a credit note under Sub-Article (4) of this Article shall treat the amount of VAT specified in the credit note as output tax payable by the recipient in the accounting period in which the credit note was received to the extent that the recipient claimed an input tax credit for the VAT referred to in the credit note.
ለ) የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድን በሚመለከት የክሬዲት ሰነዱ ወይም የዴቢት ሰነዱ እንዲሰጥ ምክንያት የሆነው ሁኔታ ካጋጠመበት ቀን ጀምሮ በ፷ ቀናት ውስጥ፣ መቅረብ አለበት። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ጥያቄ የቀረበለት የተመዘገበ ሰው ጥያቄው ከቀረበለት ቀን አንስቶ በ፲፬ ቀናት ውስጥ በጥያቄው መሠረት መፈጸም አለበት። ፬/ የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት የተከናወነበት ዋንኛ የታክስ ደረሰኝ ወይም ማስተካከያ የተደረገበት የክሬዲት ወይም የዴቢት ሰነድ ዋንኛ ቅጂ የጠፋበት መሆኑን የገለጸ ከሆነ አቅርቦቱን ያከናወነው የተመዘገበው ሰው የዋንኛውን የታክስ ደረሰኝ ወይም የክሬዲት ሰነዱን ወይም የዴቢት ሰነዱን ቅጂ ሊሰጠው ይችላል። ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) መሠረት ለተመዘገበው ሰው የሚሰጠው የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ ቅጂ በላዩ ላይ ቅጂ በሚል ሊጻፍበት ይገባል።
በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፯ በተመለከተው ቀመር ‹‹ሀ›› ሒሣብ በልጦ የተገኘ እንደሆነ፣ በልጦ የተገኘው የገንዘብ መጠን ወደፊት እንዲሸጋገር ተደርጐ የሚቀጥለው የሒሣብ ጊዜ የተመዘገበው ሰው የግብአት ታክስ ሆኖ ተቀናሽ ይደረጋል። በሚቀጥለው የሒሣብ ጊዜ ተቀናሽ ያልተደረገው በብልጫ የተገኘው ማናቸውም ሒሣብ፣ ወደሚቀጥለው የሒሣብ ጊዜ እንዲሸጋገር ተደርጐ በዚያ የሒሣብ ጊዜ የግብአት ታክስ ተቀናሽ እንዲሆን ይደረጋል። በዚህ መንገድ በብልጫ የተገኘው የግብአት ታክስ ተመላሽ ሙሉ በሙሉ ተቀናሽ እስከሚሆን ድረስ ወደሚቀጥለው የሒሣብ ጊዜ እንዲሸጋገር ይደረጋል። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የተመዘገበው ሰው በብልጫ የከፈለው እና ከአንድ የሒሣብ ጊዜ በላይ እንዲሸጋገር የተደረገ ሒሣብ ያለው እንደሆነ፣ ቀደም ሲል እንዲሸጋገር የተደረገው በብልጫ የተከፈለው ሒሣብ በቅድሚያ እንዲቀነስ ይደረጋል። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው ቢኖርም የተመዘገበ ሰው በአንድ የሒሣብ ጊዜ ውስጥ ያለው በብልጫ የከፈለው ታክስ ለስድስት የሒሣብ ጊዜ ያህል የተሸጋገረ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ተቀናሽ ያልተደረገ ከሆነ፣ የተመዘገበው ሰው የጸደቀ ቅጽን በመጠቀም ተቀናሽ ያላደረገው የገንዘብ መጠን ተመላሽ እንዲደረግለት ለታክሱ ባለሥልጣን ሊያመለክት ይችላል። ፲፮ሺ፶፪ ፬/ የተመዘገበው ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) መሠረት ማመልከቻ ያቀረበ እንደሆነ እና የታክሱ ባስለልጣን የቀረበው ጥያቄ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን አጣርቶ፣ የተመላሽ ጥያቄ ማመልከቻው በቀረበለት በ፵፭ ቀናት ውስጥ ተመላሹን ገንዘብ መክፈል አለበት። ፭/ በዚህ አንቀጽ መሠረት የተመዘገበ ሰው የሚያቀርበው የተመላሽ ጥያቄ ስድስተኛው የሒሣብ ጊዜ በተጠናቀቀ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት። ፮/ የተመዘገበው ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) መሠረት ጥያቄውን ካላቀረበ ተመላሽ የማግኘት መብቱን እንደተወ ይቆጠራል። Period The net VAT payable by a registered person for an Accounting Period shall be calculated according to the following formula: A – B where: a) is the total of the following amounts: (i) the total amount of output tax receivable in respect of taxable supplies made by the person during the Accounting Period reduced by the total amount of withholding VAT credit allowed to the person under Article 62 Sub-Artcile (3) of this Proclamation in relation to taxable supplies made by the person during the accounting period, (ii) as per Article 8 Sub-Artcile (1) Paragraph (c) and Article 8 Sub- Artcile (8) of this Proclamation the total amount of value added tax to be paid directly by the registered person on the taxable supply made to him during the accounting period; (iii) the total amount treated as output tax of the person for the period under this Proclamation; and (iv) the VAT payable on a taxable import of capital goods by the registered person during the period to which an approval under Article 28 of this Proclamation applies. b) is the total of the following amounts: (i) the total amount of input tax payable in respect of creditable acquisitions made by the person during the accounting period for which an input tax credit is allowed, and (ii) the total input tax credit allowable to the person for the period under Articles 31 Sub-Article (1), 33 Sub- Article (2)(c), 37 Sub-Article (6), 40 Sub-Article (4), 43 Sub-Article (3), 44 Sub-Article (2), 45 Sub- Article (2), 46 Sub-Article (3), 48 Sub-Article (1), or the VAT regulations.
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) እና በዚህ አዋጅ 1/ Subject to Sub-Article (3) of this Article and Article 49 of this Proclamation, if, for any accounting period of a registered person, component “B” of the formula in Article 47 of this Proclamation exceeds component “A” of the formula in Article 47 of this Proclamation, the excess shall be carried forward and allowed to the person as an input tax credit in the next following accounting period and any amount of the excess not credited in that period shall be carried forward and allowed as an input tax credit in the next following accounting period, and so on until the excess has been fully credited. 2/ If a registered person has an excess under Sub-Article (1) of this Article carried forward under this Article for more than One accounting period, the excess of the earliest accounting period shall be allowed First. 3/ Despite Sub-Article (1) of this Article, if an excess amount for an accounting period has not been fully credited after being carried forward for 6 accounting periods, the registered person may apply to the Tax Authority, in the approved form, for a refund of the amount of the uncredited excess. 4/ If a registered person has made an application under Sub-Article (3) of this Article and the Tax Authority is satisfied that a refund is due to the person, the Tax Authority shall refund the amount within 45 days after the person filed the refund application. 5/ An application by a registered person for a refund under this Article shall be made within 6 months after the end of the Sixth accounting period. 6/ If a registered person fails to submit an application for refund within the period specified in Sub-Article (5) of this Article, it forfeits its right to the refund.
1/ የተመዘገበው ሰው በአንድ የሒሣብ ጊዜ ካከናወነው አቅርቦት ዋጋ ውስጥ ፶ በመቶ ወይም ከዚያ በላይ ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ የሚደረግበት ከሆነ፣ የተመዘገበው ሰው የሒሣብ ጊዜውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ካስታወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የታክሱ ባለሥልጣን በሒሣብ ጊዜው በብልጫ የተከፈለውን የግብአት ታክስ ተመላሽ ማድረግ አለበት። ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) ተፈተጻሚ የሚሆነው የሚከተሉት ተሟልተው ሲገኙ ይሆናል፡ሀ) ዓመታዊው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦቱ ከብር ፩፻ ሚሊዮን በላይ የሆነ የተመዘገበ ሰው ተቀናሽ የሚደረግ የካፒታል ዕቃዎች ግዢ የፈጸመ እንደሆነ፣ ፲፮ሺ፶፫ ለ) የተመዘገበው ሰው ተቀናሽ ለሚደረገው የካፒታል ዕቃዎች ግዢ የግብዓት ታክስ ተቀናሽ የማግኘት መብት ያለው ከሆነ፣ እና ሐ) ተቀናሽ የሚደረገው ግዥ በተከናወነበት የሒሣብ ጊዜ የግብዓት ታክሱ የገንዘብ መጠን ሙሉ በሙሉ ተቀናሽ ያልተደረገ ከሆነ። ፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ድንጋጌዎች ተሟልተው ሲገኙ የታክሱ ባለስልጣን የተመዘገበው ሰው የካፒታል ዕቃው ለተገዛበት የሂሳብ ጊዜ ተመላሽ እንዲፈቀድለት ማመልከቻ ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተመላሹን መክፈል አለበት። ፬/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፰ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአንቀጽ ፲፮ ወይም ፲፯ መሠረት ምዝገባው የተሰረዘበት ሰው ምዝገባው በተሰረዘበት እለት ያልተቀናነሰለት እና ለወደፊት እንዲሸጋገር የተደረገው የግብአት ታክስ ተመላሽ እንዲደረግለት ለታክሱ ባለስልጣን በጽሁፍ ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል። ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) መሠረት የሚቀርብ ማመልከቻ ታክስ ከፋዩ ለተመዘገበበት የመጨረሻ የሂሳብ ጊዜ የሂሳብ ማስታወቂያ ማቅረብ በሚገባው ጊዜ ውስጥ ወይም በታክሱ ባለሥልጣን በሚፈቀድ ሌላ ቀን ለታክሱ ባለሥልጣን መቅረብ አለበት። ፲፮ሺ፶፬ ፮/ የታክሱ ባለስልጣን ምዝገባው የተሰረዘ ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) እና (፭) መሠረት ተቀናሽ ያልተደረገ የግብዓት ተመላሽ እንዲደረግለት ያቀረበው ማመልከቻ በበቂ ማስረጃ የተደገፈ ሆኖ ሲያገኘው ማመልከቻው በቀረበለት በ፷ ቀን ጊዜ ውስጥ ተመላሹን መክፈል አለበት። ፯/ ምዝገባው በተሰረዘበት እለት ተቀናሽ ያልተደረገ የግብአት ታክስ ያለው ሰው ተቀናሽ ያልተደረገው የግብአት ታክስ ተመላሽ እንዲደረግለት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) እና (፭) መሠረት ማመልከቻ ያላቀረበ እንደሆነ መብቱ የሚቋረጥ ሲሆን፤ ተቀናሽ ያልተደረገው የግብአት ታክስ ተመላሽ ሊደረግለት አይችልም። Without Carry Forward 1/ If more than 50% of the value of taxable supplies made by a registered person in an accounting period are Zero-rated supplies, the Tax Authority shall refund any excess input tax credit of the person for the accounting period within One calendar month after the person filed the VAT return for the accounting period. 2/ Sub-Article (3) of this Article shall apply where the following conditions are satisfied: a) a registered person with an annual value of taxable supplies in excess of 100,000,000 Birr has made a creditable acquisition of capital goods, b) the registered person is allowed an input tax credit in respect of the creditable acquisition of the capital goods, and c) the amount of the input tax credit is not fully credited in the accounting period in which the creditable acquisition occurred. 3/ Where the conditions in Sub-Article (2) of this Article are satisfied, the Tax Authority shall refund the uncredited amount to the registered person within one calendar month after the person filed the VAT return for the accounting period in which the capital goods were acquired. 4/ Notwithstanding Article 48, a person whose registration is cancelled under Article 16 or 17 may apply to the Tax Authority, in writing, for a refund of any unapplied excess input tax credit as at the date of cancellation of registration. 5/ An application made by a person under Sub-Article (4) of this Article shall be lodged with the Tax Authority by the due date for filing the person’s tax return for the last accounting period that the person was registered or by such later date as the Tax Authority may allow. 6/ If the Tax Authority is satisfied that a person who has lodged an application in accordance with Sub-Articles (4) and (5) of this Article has an unapplied excess input tax credit at the time the person’s registration is cancelled, the Tax Authority shall refund the excess within 60 days after the person lodged the refund application. 7/ If, at the date on which the cancellation of the registration of a person takes effect, the person has an excess input tax credit in respect of which an application for a refund has not been made in accordance with Sub-Articles (4) and (5) of this Article, the excess credit shall lapse and is no longer refundable to the person.
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፰ ንዑስ አንቀጽ (፭) ወይም ፵፱ በተደነገገው መሠረት የታክሱ ባለሥልጣን የተመላሹን ሒሣብ ያልከፈለ ከሆነ፣ የተመላሹ ሒሣብ መከፈል ከነበረበት አግባብነት ካለው ጊዜ መጨረሻ ጀምሮ ተመላሹ ሒሣብ እስከተከፈለ ድረስ ላለው ጊዜ የታክሱ ባለሥልጣን ወለድ መክፈል አለበት። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የሚከፈለው ወለድ መጣኔ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ከተመለከተው ጊዜ በፊት ባለው የሩብ ዓመት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች የንግድ ብድር የሚሰጡበት ከፍተኛው የወለድ መጣኔ ይሆናል። ፲፮ሺ፶፭ Refunds 1/ If the Tax Authority fails to pay a refund to a taxpayer as required under Article 48 Sub-Article (5) or 49 of this Proclamation, the Tax Authority shall pay the registered person interest for the period commencing from the end of the relevant period in which the refund was to be paid until the refund is paid. 2/ The rate of interest under Sub-Article (1) of this Article shall be the highest commercial lending rate that prevailed in Ethiopia during the quarter before the commencement of the period specified in Sub-Article (1) of this Article.
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና (፫) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የታክሱ ባለሥልጣን የሚቀርብለትን ጥያቄ መሠረት በማድረግ የሚከተሉት አካላት የከፈሉትን የተጨማሪ እሴት ታክስ በሙሉ ወይም በከፊል ተገቢው ማስረጃ ተሟልቶ በቀረበበት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተመላሽ ማድረግ አለበት፡ሀ) በቪዬና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ኮንቬንሽን ለሚሲዮን፣ ለዲፕሎማት ወይም ለቆንስላ የሚፈጸም ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እስከሆነ ድረስ፣ ለውጭ ሀገር የዲፕሎማቲክ ወይም ለኰንስላር ሚሲዮኖች ወይም ለውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች እና ቆንስላዎች፤ ለ) በዓለም አቀፍ ስምምነት ለዓለም አቀፍ ድርጅቱ የሚፈጸም ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እስከሆነ ድረስ ለዓለም አቀፍ ድርጅት፤ ሐ) የውጭ ሀገር መንግሥት በፋይናንስ፤ በቴክኒክ፤ በሰብአዊ ዕርዳታ ወይም አስተዳደራዊ ድጋፍን በሚመለከት ዓለም አቀፍ ስምምነት ለውጭ ሀገር መንግስት የሚፈጻም ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የተደረገ ከሆነ፤ ወይም ፲፮ሺ፶፮ መ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር ፭፻፲፯/፪ሺ፲፬ ለኢንቨስተር የሚፈጸም ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የተደረገ ወይም ታክሱ ተመላሽ እንዲደረግ የተፈቀደ ከሆነ። ፪/ ለኢትዮጵያ ዜጐች ወይም በኢትዮጵያ ቋሚ ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ተመላሽ ማድረግ አይቻልም። ፫/ የታክሱ ባለስልጣን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የተመላሽ ሒሣብን የሚከፍለው እንደአግባብነቱ በሁኔታ ወይም በገደብ ሊሆን ይችላል። ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የሚቀርበው የተመላሽ ጥያቄ፡ሀ) የተመላሽ ጥያቄ የቀረበበት አቅርቦት ከተከናወነበት ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወይም የታክሱ ባለስልጣን በሚፈቅደው ተጨማሪ ጊዜ ውስጥ የጸደቀውን ቅጽ በመጠቀም መቅረብ፤ እና ለ) ከሚከተሉት ደጋፊ ማስረጃዎች ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡- (1) የተመላሽ ጥያቄ የቀረበበት የተጨማሪ እሴት ታክስ ከተከፈለበት የታክስ ደረሰኝ ወይም ሌላ ተመሳሳይ ማስረጃ፣ (2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት አመልካቹ የተመላሽ ጥያቄ እንዲያቀርብ የሚያስችለው ማስረጃ፣ እና (3) የታክሱ ባለስልጣን በሚያወጣው መመሪያ ሚጠየቀውን ማናቸውም ሌላ ማስረጃ። ፲፮ሺ፶፯ International Organisations and for Investors 1/ Subject to Sub-Articles (2) and (3) of this Article, the Tax Authority may, on application, grant a refund of part or all the VAT paid in relation to a taxable supply made to: a) a diplomatic or consular mission of a foreign country, or a diplomat or consular official of a foreign country, to the extent that the mission, diplomat, or consular official is exempt from VAT on the taxable supply under the Vienna Convention on Diplomatic Relations; b) an International organisation to the extent that the organisation is exempt from VAT on the taxable supply under an International agreement; c) a foreign Government to the extent that the foreign Government is exempt from VAT on the taxable supply under an International agreement for the provision of financial, technical, humanitarian, or administrative assistance to the Government; or d) an investor to the extent that the investor is exempt from VAT on the taxable supply, or entitled to a refund of VAT, under the Council of Ministers Investment Incentives Regulations No. 517/2022. 2/ A refund under Sub-Article (1) of this Article shall not be paid to an Ethiopian citizen or a permanent resident of Ethiopia. 3/ The Tax Authority may grant a refund under Sub-Article (1) of this Article based on such conditions and subject to such restrictions as appropriate. 4/ An application for a refund under Sub- Article (1) of this Article shall be: a) filed, in the approved form, within 1 calendar month after the time of the supply to which the application relates or within such further period as the Tax Authority may allow; and b) accompanied by the following supporting documentation: (i) a tax invoice or other evidence that the VAT for which the refund is sought was paid, (ii) evidence of the applicant’s entitlement to make an application for the refund under Sub-Article (1), and (iii) such other documentation that the Tax Authority may require.
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት የሚያከናውን የተመዘገበ ሰው አቅርቦቱን ባከናወነበት ጊዜ አቅርቦቱን ለገዛው ሰው መደበኛውን የታክስ ደረሰኝ መስጠት አለበት። ፪/ ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት የገዛው ሰው ካልጠየቀ በስተቀር የተመዘገበ ሰው የአቅርቦቱ ጠቅላላ ዋጋ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ከሚወሰነው የገንዘብ መጠን ላልበለጠ እና በጥሬ ገንዘብ ለሚፈጸም ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ክፍያ መደበኛውን የታክስ ደረሰኝ እንዲሰጥ አይገደድም። ፫/ ለሚከተሉት ታክስ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች የተመዘገበው ሰው በቀላል መንገድ የሚዘጋጅ የታክስ ደረሰኝ ሊሰጥ ይችላል፡ሀ) የአቅርቦቱ ጠቅላላ ዋጋ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ከሚወሰነው የገንዘብ መጠን ላልበለጠ እና በጥሬ ገንዘብ ለሚፈጸም ክፍያ፣ እና ለ) አቅርቦቱ የተከናወነው በችርቻሮ ንግድ ሥራ ላይ በተሠማራ የተመዘገበ ሰው ከሆነ። ፬/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ (፩) (ሐ) እና ንዑስ አንቀጽ ፰ በተመለከተው መሠረት በቀጥታ በገዢው ታክስ በሚከፈልበት አቅርቦት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ ያለበት የተመዘገበ ሰው አገልግሎቱን ባገኘበት ጊዜ ለአቅርቦቱ በገዥው የሚዘጋጅ የታክስ ደረሰኝ ማዘጋጀት አለበት። ፭/ የታክስ ደረሰኝ፣ በቀላል መንገድ የሚዘጋጅ የታክስ ደረሰኝ፣ እና በገዥው የሚዘጋጅ የታክስ ደረሰኝ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚወሰነውን ዝርዝር መያዝ አለበት። ፲፮ሺ፶፰ 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article, a registered person making a taxable supply shall, at the time of the supply, issue the recipient of the supply with the original tax invoice for the supply. 2/ Unless requested by the recipient of a taxable supply, a registered person shall not be required to provide a tax invoice for a taxable supply if the total consideration for the supply is paid in cash and does not exceed the amount specified in the Regulations. 3/ A registered person may provide a simplified tax invoice for a taxable supply where: a) the total consideration for the supply is paid in cash and does not exceed the amount specified in the Regulations, and b) the supply is made by a registered person who is a retailer. 4/ A registered person liable for VAT under Article 8 Sub-Article (1) Paragraph (c) and (8) of this Proclamation in respect of a reverse charged supply made to the person shall, at the time of the supply, prepare a recipient-created tax invoice for the supply. 5/ A tax invoice, simplified tax invoice, and a recipient-created tax invoice shall include the particulars specified in the Regulations.
፩/ በዚህ አዋጅ ክፍል ስምንት የተመለከቱት ሁኔታዎች በሚሟሉበት ጊዜ የተመዘገበው ሰው ለሌላው የተመዘገበ ሰው እንደሁኔታው የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ መስጠት አለበት። ፪/ የተመዘገበው ሰው ለአቅርቦቱ ገዢ የክሬዲት ወይም የዴቢት ሰነድ የሚሰጠው ሰነዱ እንዲሰጥ ምክንያት የሆነው የማስተካከያ ተግባር በተፈጸመበት የሒሣብ ጊዜ መጨረሻ ሊሆን ይገባል። ፫/ የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የተዘረዘሩ መረጃዎችን የሚይዝ መሆን አለበት። ፬/ ለዚህ አንቀጽ እንዲሁም ለአዋጁ አንቀጽ ፶፭ እና ፶፭ አፈጻጸም “የማስተካከያ ተግባር” የሚለው ሐረግ በአዋጁ አንቀጽ ፵፭ እና ፵፮ መሠረት የማይሰበሰብ ዕዳ በመኖሩ ምክንያት የሚደረግን ማስተካከያ ይጨምራል። 1/ A registered person shall issue a credit note or debit note, as the case may be, to a registered person in the circumstances specified in Part VIII of this Proclamation. 2/ A registered person shall issue a credit or debit note to the recipient of a supply by the end of the accounting period in which the adjustment event to which the note relates occurred. 3/ A credit note and a debit note shall include the particulars specified in the Regulations. 4/ In this Article and Articles 55 and 56 of this Proclamation, “Adjustment Event” includes an event giving rise to a bad debt adjustment under Articles 45 and
፩/ በዚህ የአዋጁ ክፍል መሠረት በማናቸውም ምክንያት ዋንኛው የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ ያልተሰጠው የተመዘገበ ሰው አቅራቢው የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ እንዲሰጠው በጽሑፍ ሊጠይቅ ይችላል። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የሚቀርበው ጥያቄ፡ሀ) የታክስ ደረሰኝን በሚመለከት የታክሱ ደረሰኝ እንዲሰጥ ምክንያት የሆነው አቅርቦት ከተከናወነበት ቀን አንስቶ በ፷ ቀናት ውስጥ፣ ወይም 1/ A registered person who, for any reason, has not been issued with an original tax invoice, credit note, or debit note as required under this Part may make a written request to the supplier to issue the tax invoice, credit note, or debit note to the person. 2/ A request under Sub-Article (1) of this Article shall be made: a) for a tax invoice, within 60 days after the time of the supply to which the tax invoice relates, or b) for a credit note or debit note, within 60 days after the date of the adjustment event to which the credit note or debit note relates. 3/ A registered person receiving a request under Sub-Article (1) of this Article shall comply with the request within 14 days of receiving the request. 4/ Where a registered person claims to have lost the original tax invoice for a taxable supply, or the original credit or debit note for an adjustment event, the registered person who made the supply may provide a copy of the tax invoice, credit note, or debit note. 5/ A copy of a tax invoice, credit note, or debit note provided to a registered person under Sub-Article (4) shall be clearly marked copy.
፩/ የተመዘገበ ሰው ለአንድ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ሊሰጥ የሚችለው አንድ ደረሰኝ ብቻ ሲሆን፣ ማስተካከያ ማድረግ ለሚያስገድድ አንድ ሁኔታ ሊሰጥ የሚችለው አንድ የክሬዲት ሰነድ ወይም አንድ የዴቤት ሰነድ ነው። ሆኖም ዋነኛው ቅጂ ጠፍቶብኛል ለሚል የተመዘገበ ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፬(፬) መሠረት ቅጂ የሚል ጽሑፍ የሰፈረበት ቅጂ ሊሰጠው ይችላል። ፪/ የተመዘገበ ሰው በዚህ የአዋጁ ክፍል ከተመለከተው ውጪ የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ ሊሰጥ አይችልም። ፫/ ለዚህ አዋጅ እና ለታክስ አስተዳደር አዋጅ አፈጻጸም የተመዘገበ ሰው የሚከተሉትን ሰነዶች መያዝ አለበት። ሀ) የተቀበላቸውን ዋንኛ የታክስ ደረሰኞች፣ የክሬዲት ሰነዶች እና የዴቢት ሰነዶች በሙሉ፣ ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፬(፬) መሠረት የተቀበላቸውን የታክስ ደረሰኞች፣ የክሬዲት ሰነዶች እና የዴቤት ሰነዶች ቅጂዎች በሙሉ፣ ሐ) የሰጣቸውን የታክስ ደረሰኞች፣ የክሬዲት ሰነዶች እና የዴቢት ሰነዶች ቅጂዎች በሙሉ፤ መ) ወደ ሀገር ካስገባቸው ወይም ወደ ውጭ ከላካቸው ዕቃዎች ጋር የተያያዙ የጉምሩክ ሰነዶች፣ እና ሠ) የአገልግሎቱ ተቀባይ በሆነ የተመዘገበ ሰው የተዘጋጁ ከሆነ ይህ ሰው በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት የሚመለከቱ የታክስ ደረሰኞች። ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫)(ሐ) የተጠቀሱት ሰነዶች በቅደም ተከተላቸው መሠረት መያዝ አለባቸው። 1/ A registered person shall issue only One original tax invoice for a taxable supply, or One original credit note or debit note for an adjustment event, but a copy clearly marked as such may be provided to a registered person in accordance with Article 54 Sub-Article (4) of this Proclamation who claims to have lost the original. 2/ A person shall not issue a tax invoice, credit note, or debit note other than in the circumstances specified in this Part. ፲፮ሺ፷ 3/ The following documents shall be maintained by a registered person for the purposes of this Proclamation and the Tax Administration Proclamation: a) the original of all tax invoices, credit notes, and debit notes received by the person, b) a copy of all tax invoices, credit notes, and debit notes received by the person under Article 54 Sub-Article (4) of this Proclamation, c) a copy of all tax invoices, credit notes, and debit notes issued by the person; d) customs documentation relating to imports and exports of goods by the person, and e) any recipient-created tax invoices prepared by the person in respect of reverse charged supplies made to the person. 4/ The documents referred to in Sub-Article (3) Paragraph (c) of this Article shall be maintained in chronological order.
፩/ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት የተከናወነው በተመዘገበው ወካይ ስም በተወካዩ አማካኝነት የሆነ እንደሆነ እና ወካይ እና ተወካይ ሁለቱም የተመዘገቡ ሰዎች ከሆኑ ወካዩ ለታክስ ለአቅርቦቱ ሊሰጥ የሚገባውን ማናቸውንም የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ ተወካዩ የወካዩን ስም፣ አድራሻ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ቁጥር በመጠቀም መስጠት ይችላል። ፲፮ሺ፷፩ ፪/ የተመዘገበ ሰው በተወካዩ አማካኝነት ለወካዩ ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ያከናወነ እና ወካይ እና ተወካይ ሁለቱም የተመዘገቡ ከሆነ፣ ከአቅርቦቱ ጋር በተያያዘ ለወካዩ ሊሰጥ የሚገባውን የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ እና የዴቢት ሰነድ የተወካዩን ስም፣ አድራሻ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ቁጥር በመጠቀም ለተወካዩ መስጠት ይችላል። ፫/ ተወካይ በተመዘገበ ወካይ ስም ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ያከናወነ እንደሆነ፣ እና ወካዩ የተመዘገበ ሰው ሆኖ ተወካዩ ያልተመዘገበ ከሆነ ከአቅርቦቱ ጋር በተያያዘ በወካዩ ሊሰጥ የሚገባውን የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ እና የዴቢት ሰነድ የወካዩን ስም፣ አድራሻ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ቁጥር በመጠቀም ተወካዩ ሊሰጥ ይችላል። ፬/ የተመዘገበ ሰው ለወካዩ በተወካዩ አማካኝነት ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ያከናወነ እንደሆነ፣ እና ወካዩ የተመዘገበ ሰው ሆኖ ተወካዩ ያልተመዘገበ ከሆነ ከአቅርቦቱ ጋር በተያያዘ ለወካዩ ሊሰጥ የሚገባው የታክስ ደረሰኝ የወካዩን ስም፣ አድራሻ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ቁጥር በመጠቀም ለተወካዩ መስጠት ይችላል። ፲፮ሺ፷፪ ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፪) መሠረት ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት በወካዩ ስም ለተወካዩ የቀረበ ወይም በወካዩ ስም በተወካዩ የቀረበ እንደሆነ፣ ከአቅርቦቱ ጋር በተያያዘ በዚህ አዋጅ መሠረት ሊሰጥ የሚገባው የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ አንድ ጊዜ ብቻ መሰጠት ያለበት ሲሆን፣ ለወካዩ እና ለተወካዩ ወይም በወካዩ እና ለተወካዩ ሊሰጥ አይችልም። ፮/ በዚህ አንቀጽ መሠረት በተወካዩ የተሰጠ ወይም ለተወካዩ የተሰጠ የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ እና የዴቢት ሰነድ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በወካዩ እና ለተወካዩ እንደተሰጠ ይቆጠራል። ፯/ በዚህ አንቀጽ መሠረት በወካዩ ወይም ለተወካዩ የታክስ ደረሰኝ፣ የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ የተሰጠ እንደሆነ፤ ተወካዩ የወካዩን ስም፤ አድራሻ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ቁጥር ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ መረጃ መያዝ አለበት። Involving Agents 1/ If a taxable supply is made by an agent on behalf of a principal and both the agent and principal are registered persons, the agent may issue any tax invoice, credit note, or debit note required to be issued by the principal in relation to the supply using the name, address, and VAT registration number of the agent. 2/ If a taxable supply is made by a registered person to an agent on behalf of a principal and both the agent and principal are registered persons, any tax invoice, credit note, or debit note required to be issued to the principal in relation to the supply may be issued to the agent, but using the name, address, and VAT registration number of the agent. 3/ If a taxable supply is made by an agent on behalf of a principal and the principal is a registered person but the agent is not, the agent may issue any tax invoice, credit note, or debit note required to be issued by the principal in relation to the supply, but using the name, address, and VAT registration number of the principal. 4/ If a taxable supply is made by a registered person to an agent on behalf of a principal and the principal is a registered person but the agent is not, any tax invoice, credit note, or debit note required to be issued to the principal in relation to the supply may be issued to the agent, but using the name, address, and VAT registration number of the principal. 5/ If a taxable supply is made by, or to, an agent on behalf of a principal in accordance with Sub-Article (1) or (2) of this Article, any tax invoice, credit note, or debit note required to be issued under this Proclamation in relation to the supply can be issued once only and shall not be issued by, or to, both the agent and the principal. 6/ A tax invoice, credit note, or debit note issued by, or to, an agent in accordance with this Article shall be treated as having been issued by, or to, the principal, as the case may be, for the purposes of this Proclamation. 7/ Where a tax invoice, credit note, or debit note in relation to a taxable supply has been issued by an agent, or to an agent, pursuant to this Article, the agent shall maintain sufficient records to enable the name, address, and VAT registration number of the principal to be ascertained.
Proclamation The Tax Administration Proclamation shall apply for the purposes of the administration of this Proclamation but subject to this Part. 58 VAT Returns 1/ A registered person shall file a VAT return for each accounting period on or before the last day of the calendar month following the end of the period. 2/ A registered person shall be obliged to file a VAT return under Sub-Article (1) of this Article for an accounting period whether or not the person has an amount of net VAT payable for the accounting period. 3/ A large unregistered person or an unregistered Government entity liable for VAT in respect of a reverse charged supply received during a calendar month shall file a tax declaration with the Tax Authority for the month by the last day of the following calendar month. 4/ A tax declaration required to be filed by a large unregistered person or unregistered Government entity under Sub-Article (3) of this Article is a “tax declaration” and “Self-assessment declaration” for the purposes of the Tax Administration Proclamation.
፩/ ማናቸውም የተመዘገበ ሰው የእያንዳንዱን የሒሣብ ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቂያ የሒሣብ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው ወር የመጨረሻ ቀን ድረስ ማቅረብ አለበት። ፲፮ሺ፷፫ ፪/ ማናቸውም የተመዘገበ ሰው በሒሣብ ጊዜው ውስጥ ተከፋይ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ቢኖረውም ባይኖረውም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የሒሣብ ጊዜውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቂያ የማቅረብ ግዴታ አለበት። ፫/ በአንድ ወር ውስጥ በቀጥታ በገዢው ታክስ በሚከፈልበት አቅርቦት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ ያለበት ከፍተኛ ግብይት ያለው ያልተመዘገበ ሰው ወይም ያልተመዘገበ የመንግሥት ተቋም ለዚህ ወር ግብይቱ በሚቀጥለው ወር የመጨረሻ ቀን ለታክሱ ባለስልጣን የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብ አለበት። ፬) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) መሠረት በከፍተኛ ያልተመዘገበ ሰው ወይም በመንግሥት ተቋም ሊቀርብ የሚገባው የታክስ ማስታወቂያ ለታክስ አስተዳደር አዋጁ አፈጻጸም“ የታክስ ማስታወቂያ›› እና ‹‹የራስ የታክስ ማስታወቂያ” ሆኖ ይቆጠራል።
፩/ የተመዘገበ ሰው በሒሣብ ጊዜው የሚኖረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተከፋይ የተጣራ ሒሣብ ታክሱን ሊያስታወቅ በሚገባው ጊዜ ውስጥ መክፈል አለበት። ፪/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፰(፫) የተመለከተው በቀጥታ በገዢው ታክስ በሚከፈልበት አቅርቦት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ ያለበት ከፍተኛ ግብይት ያለው ያልተመዘገበ ሰው ወይም ያልተመዘገበ የመንግሥት ተቋም በገዢው ተይዞ ታክስ የሚከፈልበትን ግብይት በፈጸመበት ወር ውስጥ ታክሱን የመክፈል ግዴታው የሚቋቋም ሲሆን፤ ይህ ሰው የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብ ባለበት ጊዜ ውስጥ ታክሱን መከፈል አለበት። ፲፮ሺ፷፬ ፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፰ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማናቸውም አስመጪ ወደ ሀገር ባስገባቸው ዕቃዎች ላይ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ ዕቃዎቹን ወደ ሀገር ባስገባበት ጊዜ መክፈል አለበት። 1/ The net VAT payable by a registered person for an accounting period shall be due by the due date for filing the person’s VAT return for that period. 2/ The VAT payable by a large unregistered person or an unregistered Government entity referred to in Article 58 Sub- Article (3) of this Proclamation for a calendar month in respect of a reverse charged supply received during the month shall be due and payable by the due date for filing the person’s tax declaration for the month. 3/ Subject to Article 28 of this Proclamation, the VAT payable by an importer in respect of a taxable import shall be due at the time of import.
፩/ ኮሚሽኑ፡ሀ) ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ዕቃዎቹ ወደ ሀገር በሚገቡበት ጊዜ ታክስን መሰብሰብ፣ ለ) የአስመጪውን የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (ካለ) እና የዕቃዎቹን የዋጋ ኢንቮይስ መቀበል፣ እና ሐ) የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በፖስታ ቤት በኩል ከሚመጡ ዕቃዎች ላይ ኮሚሽኑን በመወከል በዚህ አንቀጽ ተራ ፊደል (ሀ) የተመለከተውን ተግባር መፈጸም እንዲችል ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት። ፪/ በዚህ አዋጅ ወይም በሚኒስቴሩ በሚወጣ መመሪያ የተመለከተው ማስተካከያ ወይም የተለየ አሠራር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አግባብነት እስካላቸው ድረስ በጉምሩክ አዋጅ ወደ ሀገር ስለሚገቡ እና በትራንዚት ላይ ስላሉ ዕቃዎች፣ ወደ ሀገር ስለሚገቡ ዕቃዎች ክሊራንስ፣ የጉምሩክ ቀረጥን ስለመክፈል እና ታክስን ስለማስመለስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለመሰብሰብም ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል። ፫/ ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የሚከፈለውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ለመሰብሰብ ሲባል ኮሚሽኑ በጉምሩክ አዋጅ የተሰጠውን ሥልጣን በዚህ አዋጅ መሠረት ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ስለሚከፈል የተጨማሪ እሴት ታክስ ጭምር እንደተሰጠው በመቁጠር ሊሰራበት ይችላል። ፲፮ሺ፷፭ ፬/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ‹‹የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት›› ማለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፷፭/፪ሺ፱ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ነው። 1/ The Commission shall: a) collect the VAT payable on a taxable import at the time of import, b) obtain the name and TIN (if any) of the importer, and the invoice values for the import, and c) make arrangements for the function referred to in Paragraph (a) of this Sub-Article to be performed on behalf of the Commission by the Ethiopian Postal Service Enterprise for imports made by post. 2/ Except where this Proclamation provides to the contrary, the provisions of the Customs Legislation relating to the import, transit, and clearance of imported goods, and the payment and recovery of duty, in so far as they are relevant, and subject to such exceptions and modifications as prescribed by the Ministry in a Directive, shall apply in relation to the collection of the VAT payable on a taxable import. 3/ For the purposes of the collection of the VAT payable on a taxable import, the Commission may exercise any power conferred on the Commission by the Customs Legislation as if the reference to duty in that Legislation included a reference to VAT payable on a taxable import under this Proclamation. 4/ For the purposes of this Article, “Ethiopian Postal Service Enterprise” means the Ethiopian Postal Service Enterprise established under the Ethiopia Postal Service Enterprise Establishment Council of Ministers Regulation No. 165/2009.
፩/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው የአቅርቦቱ ተጠቃሚ በሰጠው የተሳሳተ መረጃ ወይም በፈጸመው የማጭበርበር ድርጊት ምክንያት የተመዘገበው ሰው፡ሀ) አቅርቦቱ ከታክስ ነጻ እንዲሆን፣ ለ) በአቅርቦቱ ላይ ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ እንዲሆን፣ ወይም ሐ) የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳይከፈልበት ያደረገ፣ እንደሆነ ነው። ፪/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ የታክሱ ባለሥልጣን የአቅርቦቱ ተጠቃሚ ተገቢ ባልሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ አወሳሰን ምክንያት በአቅርቦቱ ላይ ያልከፈለውን የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ክፍያው በመዘግየቱ የሚከፈለውን ወለድ፣ ክፍያው በዘገየበት የሚጣለውን መቀጫ እንዲከፍል ሊጠይቀው ይችላል። ፫/ የታክሱ ባለሥልጣን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት የአቅርቦቱ ተጠቃሚ ታክሱን እንዲከፍል ሲጠይቅ በደንቡ የተመለከቱትን ዝርዝር ሁኔታዎች የሚገልጽ ማስታወቂያ መስጠት አለበት። 165/2009. ፲፮ሺ፷፮ ፬/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ድንጋጌ የታክሱ ባለሥልጣን የተጨማሪ እሴት ታክሱን በሙሉ ወይም በከፊል፣ ክፍያ በመዘግየቱ የሚከፈል ወለድ እና ክፍያው በመዘግየቱ ከሚጣል መቀጫ ጋር አቅርቦቱን ካከናወነው ከተመዘገበው ሰው ላይ ከመጠየቅ አያግደውም። ሆኖም የታክሱ ባለስልጣን በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚጠይቀው ታክስ በአቅርቦቱ ላይ ሊከፈል ከሚገባው የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ክፍያ በመዘግየቱ ከሚከፈል ወለድ እና በዘገየበት ከሚጣል መቀጫ የበለጠ ሊሆን አይችልም። ፭/ በዚህ አንቀጽ መሠረት ከአቅርቦቱ ተጠቃሚ የሚሰበሰበው ታክስ አቅራቢው በአቅርቦቱ ላይ ሊከፈል ከሚገባው ታክስ ላይ ይቀነሳል እንዲሁም ከአቅራቢው የሚሰበሰበው ማናቸውም ገንዘብ የአቅርቦቱ ተጠቃሚ ሊከፍል ከሚገባው ታክስ ላይ ይካካሳል። ፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት በአቅርቦቱ ተጠቃሚ ሊከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ክፍያ በመዘግየቱ የሚከፈል ወለድ እና በዘገየበት የሚጣል መቀጫ የከፈለ አቅራቢ የከፈለውን ገንዘብ ከአቅርቦቱ ተጠቃሚ ሊጠይቅ ይችላል። ፯/ ለዚህ አዋጅ እና ለታክስ አስተዳደር አዋጅ አፈጻጸም በዚህ አንቀጽ መሠረት የተወሰነ ታክስ በዚህ አዋጅ መሠረት የተጠየቀ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሆኖ ይቆጠራል። ፰/ የታክስ አስተዳደር አዋጅ ድንጋጌዎች የታክሱ ባለሥልጣን የዚህን አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) ተፈጻሚ ለማድረግ የታክስ ከፋዩን የገቢ ማስታወቂያ ጨምሮ ማናቸውንም ውሳኔ ከማሻሻል አያግዱትም። ፲፮ሺ፷፯ ፱/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም፡- ‹‹ክፍያ በመዘግየቱ የሚከፈል ወለድ›› ማለት በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ ፴፯ መሠረት የታክስ ክፍያ በመዘግየቱ ምክንያት የሚከፈል ወለድ ነው። ‹‹ክፍያ በመዘግየቱ የተጣለ መቀጫ›› ማለት በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ ፩፻፬ መሠረት የታክስ ክፍያ በመዘግየቱ የሚጣል መቀጫ ነው። 1/ This Article shall apply where a registered person has, in consequence of misrepresentation or fraud by the recipient of a supply, incorrectly treated the supply as: a) an exempt supply, b) a Zero-rated supply, or c) not otherwise subject to VAT. 2/ Where this Article applies, the Tax Authority may assess the recipient of the supply for payment of the VAT due in respect of the supply, and any late payment interest and late payment penalty imposed as a result of the incorrect VAT treatment of the supply. 3/ The Tax Authority shall serve a notice of an assessment made under Sub-Article (2) of this Article on the recipient of the supply specifying the particulars set out in the Regulations. 4/ Sub-Article (2) of this Article shall not preclude the Tax Authority from recovering the whole or part of the VAT due in respect of the supply, together with any late payment interest and late payment penalty, from the registered person who made the supply, but the Tax Authority may not recover more than the total amount of VAT, and late payment interest and late payment penalty, payable in relation to the supply. 5/ Any amount recovered from the recipient of the supply under this Article is credited against the liability of the supplier in respect of the supply and any amount recovered from the supplier is credited against the liability of the recipient of the supply under this Article. 6/ A supplier who pays VAT, and late payment interest and late payment penalty, assessed to the recipient of the supply under Sub-Article (1) of this Article may recover the amount from the recipient of the supply. 7/ An amount assessed under this Article shall be treated, for all purposes of this Proclamation and the Tax Administration Proclamation, as VAT charged under this Proclamation. 8/ Nothing in the Tax Administration Proclamation shall limit the power of the Tax Authority to amend an assessment, including a self-assessment, of the registered person making the supply to give effect to Sub-Article (4) of this Article. 9/ In this Article: “Late payment interest” means late payment interest imposed under Article 37 of the Tax Administration Proclamation. “Late payment penalty” means late payment penalty imposed under Article 104 of the Tax Administration Proclamation.
፩/ የተመዘገበ ሰው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ያከናወነው ለመንግሥት ተቋም የሆነ እንደሆነ፣ አቅርቦቱ የተፈጸመለት የመንግሥት ተቋም፡ሀ) በአቅርቦቱ ላይ ሊከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ፶ በመቶ ቀንሶ የማስቀረት፣ ለ) ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ በሚወሰነው አኳኋን ቀንሶ ያስቀረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ለታክሱ ባለስልጣን ገቢ የማድረግ፣ እና ሐ) በአቅርቦቱ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ቀሪውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ሒሣብ ፶ በመቶ ለተመዘገበው ሰው የመክፈል፣ ግዴታ አለበት። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት በመንግሥት ተቋም ተቀንሶ የተያዘ ማናቸውም የተጨማሪ እሴት ታክስ አቅርቦቱን ባከናወነው የተመዘገበ ሰው ለታክሱ ባለስልጣን እንደተከፈለ ይቆጠራል። ፲፮ሺ፷፰ ፫/ ለመንግሥት ተቋም ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ያከናወነ እና በዚህ አንቀጽ መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክሱ ሒሣብ ከተከፋይ ሒሣብ ላይ ተቀንሶ የተያዘበት የተመዘገበ ሰው፣ አቅርቦቱ በተከናወነበት ወቅት ባለው የሒሣብ ጊዜ ከተከፋይ ሒሣብ ላይ ተቀናሽ ለተደረገበት የገንዘብ መጠን ተቀናሽ የማግኘት መብት ይኖረዋል። ፬/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ‹‹የመንግሥት ተቋማት›› ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ (፳) በተሰጠው ትርጉም ውስጥ የሚወድቅ እና በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) (ለ) በተጠቀሰው መመሪያ መሠረት ከተከፋይ ሂሳብ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስን ቀንሶ እንዲያስቀር በሚኒስቴሩ ኃላፊነት የተሰጠው የመንግሥት ተቋም ነው። 1/ If a taxable supply is made by a registered person to a Government entity, the Government entity shall: a) withhold 50% of the VAT payable in respect of the supply, b) pay the withheld VAT to the Tax Authority in accordance with the procedures specified in a Directive issued by the Ministry, and c) pay the remaining 50% of the VAT payable in respect of the supply to the registered person making the supply. 2/ Any VAT withheld by a Government entity under Sub-Article (1) of this Article shall be treated as having been paid to the Tax Authority by the registered person making the supply. 3/ A registered person who has made a taxable supply to a Government entity in respect of which VAT has been withheld under this Article shall be entitled to a credit for the withheld VAT in the accounting period in which the taxable supply occurred. 4/ In this Article, “Government entity” means a Government entity within the definition in Article 2 Sub-Article (20) of this Proclamation that is required by the Ministry to withhold VAT in accordance with the Directive referred to in Sub-Article (1) (b) of this Article.
፩/ የባለቤትነት ምዝገባ የሚያስፈልጋቸውን ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጠው አካል እነዚህን ዕቃዎች ወደ ኢትዮጵያ ያስገባው ሰው የሚከተሉትን ማስረጃዎች ካላቀረበ በስተቀር መመዝገብ የለበትም ፡ሀ) ወደ ሀገር በገቡት ዕቃዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ የጉምሩክ ዲከላራሲዮን፣ ወይም ለ) ወደ ሀገር የገቡት ዕቃዎች ከታክሱ ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ የጉምሩክ ሰነድ። ሐ) የአዋጁ አንቀጽ ፳፰ ተፈጻሚ በሚሆንበት ሁኔታ ወደ ሀገር በገቡት እቃዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ በታክሱ ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት። ፲፮ሺ፷፱ ፪/ መመዝገብ ያለባቸውን ዕቃዎች የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጠው አካል አቅርቦቱ የተፈጸመለት ሰው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ካላቀረበ በስተቀር መመዝገብ የለበትም፡ሀ) አቅርቦቱን ያከናወነው የተመዘገበ ሰው በታክሱ ባለሥልጣን የጸደቀውን ቅጽ በመጠቀም የሰጠውን በአቅርቦቱ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለ ወይም የሚከፈል መሆኑን የሚያረጋግጥ ዋንኛውን ደረሰኝ፣ ወይም ለ) የታክሱ ባለስልጣን የሰጠውን አቅርቦቱ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት። ፫/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም፡- ‹‹የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጠው አካል›› በሕግ የመመዝገብ ግዴታ የተጣለባቸውን ዕቃዎች የመመዝገብ ኃላፊነት የተሰጠው አካል ነው። ‹‹መመዝገብ ያለባቸው ዕቃዎች›› ማለት በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት መመዝገብ ያለባቸው ዕቃዎች ናቸው። Goods 1/ A registering authority authorized to register imported goods that need to be registered shall not register goods imported by a person into Ethiopia unless the person the person provides the following to the registering authority: a) a Customs Declaration showing that VAT has been paid in respect of the import of the goods, or b) a Customs document showing that the import is an exempt import. c) a certificate issued by the tax authority certifying that VAT is paid on goods imported under the terms of Article 28 of this Proclamation. 2/ A registering authority shall not register registrable goods acquired by a person in a supply unless the person provides the registering authority with the following: a) a declaration, in such form as the Tax Authority may specify, issued by the registered person making the supply of the registrable goods certifying that the VAT payable in respect of the supply has been, or will be, paid by the person, or b) a certificate issued by the Tax Authority stating that the supply is an exempt supply, Zero-rated supply, or not otherwise subject to VAT. 3/ In this Article: “Registering authority” means an authority responsible for the registration of registrable goods. “Registrable goods” means any goods that are required to be registered under a law in Ethiopia.
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የታክሱ ባለስልጣን በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ መሠረት የመመዝገብ ግዴታ ያለበት እና ከኢትዮጵያ ውጪ ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ የሚያከናውን በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት የሌለው ሰው በታክስ አስተዳደር አዋጅ በተደነገገው መሠረት ለታክሱ መከፈል ዋስትና እንዲያቀርብ ሊጠይቅ ይችላል። ፲፮ሺ፸ ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ተፈጻሚ የሚሆነው የታክሱ ባለሥልጣን የውጭ ሀገር አገልግሎት ሰጪው በዚህ አዋጅ የተጣሉበትን ግዴታዎች የማይወጣ መሆኑን የሚያሳምን በቂ ምክንያት ሲኖረው ነው። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ዋስትና ያቀረበ ሰው በዚህ አዋጅ በተጣለበት ግዴታ መሠረት ያልፈጸመ እንደሆነ የታክሱ ባልስልጣን ይህ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ወኪል እንዲሰይም ሊያስገድደው ይችላል። ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ወኪል የሆነ ሰው ለተጨማሪ እሴት ታክስ ለመመዝገብ ማመልከቻ ማቅረብን፤ የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብን፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈልን ጨምሮ በወከለው ሰው ስም በዚህ አዋጅ የተመለከቱ ተግባሮችን የመፈጸም ኃላፊነት አለበት። ፭/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወኪል ምዝገባ የሚከናወነው በወካዩ ስም ነው። ፮/ አንድ ሰው ለብዙ ሰዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወኪል መሆን የሚችል ሲሆን፤ ሆኖም ለእያንዳንዱ ለሚወክለው ሰው የተለያየ ምዝገባ መፈፀም አለበት። ፯/ በዚህ አንቀጽ መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ወኪል የሚሆን ሰው፡ሀ) ለታክስ አስተዳደር አዋጅ አፈጻጸም የወካዩ የታክስ እንደራሴ ሆኖ ይቆጠራል፤ እና ለ) ለሚወክለው ሰው የተጨማሪ እሴት ታክስ ግዴታ የግል ተጠያቂነት ይኖርበታል። ፲፮ሺ፸፩ ፰/ የታክሱ ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ ወኪል የሚሾምበትን መንገድ፣ አኳኋን እና ተፈላጊ ሁኔታዎች በመመሪያ ሊወስን ይችላል። 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article, the Tax Authority may require a person carrying on a taxable activity outside Ethiopia who is liable to be registered under Article 12 of this Proclamation but who does not have a fixed place of business in Ethiopia to lodge security with the Tax Authority in accordance with the Tax Administration Proclamation. 2/ Sub-Article (1) of this Article shall apply only if the Tax Authority has reasonable grounds to believe that the person will not comply with their obligations under this Proclamation. 3/ If a person who has lodged security under Sub-Article (1) of this Article fails to comply with their obligations under this Proclamation, the Tax Authority may require the person to appoint a VAT representative in Ethiopia. 4/ A VAT representative appointed under Sub-Article (3) of this Article shall be responsible for doing all things required under this Proclamation of the person they represent, including applying for registration, filing of VAT returns, and paying VAT. 5/ The registration of a VAT representative shall be made in the name of the person they represent. 6/ A person may be a VAT representative for more than One person but shall have a separate registration for each person they represent. 7/ A VAT representative of a person under this Article shall be: a) a representative of the person for the purposes of the Tax Administration Proclamation; and b) personally liable for the VAT liability of the person they represent. 8/ The Tax Authority may specify the mode, manner, and requirements for appointment of a VAT representative and the responsibilities of the representative.
፩/ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ድርጅት ሳይኖረው ከውጭ ሀገር ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ከሚያከናውን የተመዘገበ ሰው ግብይት የሚፈጽም የተመዘገበ ሰው፤ የመንግሥት ተቋም ወይም ከፍተኛ ግብይት ያለው ያልተመዘገበ ሰው በሚፈጽመው በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ ያለበት መሆኑን በታክስ ባለስልጣኑ የጸደቀውን ቅጽ በመጠቀም ለአቅራቢው ማሳወቅ አለበት። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ለአቅራቢው የሚላከው ማስታወቂያ አቅርቦቱ በተፈጸመ ጊዜ ወይም ከመፈጸሙ በፊት መሰጠት አለበት። 1/ A registered person, Government entity, or large unregistered person receiving a supply of services from a registered person carrying on a taxable activity outside Ethiopia without a fixed place of business in Ethiopia shall notify the supplier, in such form as the Tax Authority may specify, that they are liable for reverse charged VAT in respect of the supply. 2/ A notification under Sub-Article (1) of this Article shall be provided to the supplier of the services at or before the time of supply.
፩/ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ሰው ከዚህ በታች ለተመለከተው ለእያንዳንዱ ጥፋት ብር ፩፻ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) አስተዳደራዊ ቅጣት ይቀጣል፡ሀ) በአዋጁ አንቀጽ ፲፭(፩) በተደነገገው መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀቱን ዋነኛ ቅጂ ታክስ የሚከፈልበትን ግብይት በሚያከናውንበት ዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም የምዝገባ የምስክር ወረቀቱን ቅጂ ታክስ የሚከፈልበትን ግብይት በሚያከናውንበት በእያንዳንዱ የስራ ቦታ ያልለጠፈ እንደሆነ፤ ፲፮ሺ፸፪ ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፭(፪) በተደነገገው መሠረት ታክስ የሚከፈልበትን ግብይት በሚያከናውንበት ማናቸውም ዌብሳይት፤ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ወይም ሌላ የኤሌክትሮኒክ መድረክ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባውን ዝርዝር መረጃ ያልገለጸ እንደሆነ፤ ሐ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፭(፫) በተመለከተው መሠረት በስራው ላይ የተደረገውን ለውጥ ያላሳወቀ እንደሆነ፤ መ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፮(፩) በተደነገገው መሠረት ለታክስ ባለሥልጣኑ መረጃ ያልሰጠ እንደሆነ፤ ሠ) ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት በማከናወን ላይ እያለ ለታክሱ ባልስልጣን በአዋጁ አንቀጽ ፲፮ መሠረት ማመልከቻ ያቀረበ ወይም ለተጨማሪ እሴት ታክስ የመመዝገብ ግዴታው ፀንቶ ባለበት ሁኔታ ምዝገባው እንዲሰረዝለት በአዋጁ አንቀጽ ፲፯ መሠረት ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ፤ ረ) በአዋጁ አንቀጽ ፲፰(፩) (ሀ) ወይም (ሐ) የተመለከተውን ግዴታውን ያልተወጣ እንደሆነ፤ ሰ) በአዋጁ አንቀጽ ፶፪(፬) በተደነገገው መሠረት በተቀባዩ የሚዘጋጅ ደረሰኝ ባልቆረጠበት በእያንዳንዱ ግብይት፤ ሸ) በዚህ አዋጅ መሠረት የዴቢት ኖት ወይም የክሬዲት ኖት ባልቆረጠበት በእያንዳንዱ ግብይት፤ ቀ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፬ መሠረት በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ያልፈጸመ እንደሆነ፤ ወይም በ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፷፰ (፩) መሠረት ያልፈጸመ እንደሆነ። ፲፮ሺ፸፫ ፪/ በዚህ አዋጅ ከተደነገገው ውጪ የታክስ ደረሰኝ፤ የክሬዲት ኖት ወይም የዴቢት ኖት የሰጠ ማናቸውም ሰው ለእያንዳንዱ ድርጊት ብር ፶ሺ (ሃምሳ ሺህ ብር) የገንዘብ መቀጫ ይቀጣል። ፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፷፭ በተደነገገው መሠረት ያልፈጸመ የተመዘገበ ሰው፤ ከፍተኛ ግብይት ያለው ያልተመዘገበ ሰው ወይም የመንግሥት ተቋም ብር ፶ሺ (ሃምሳ ሺህ ብር) የገንዘብ መቀጫ ይቀጣል። 1/ A registered person shall be liable for a penalty equal to Birr 100,000 ( One Hundred Thousand Birr) for each of the failures specified below: a) for each failure to display the original of the person’s VAT registration certificate at the person’s main business premises and for each failure to display an official copy of the certificate at every other premises where the person carries on their taxable activity as required under Article 15(1) of this Proclamation; b) for each failure to specify their VAT registration details on any website, social medial account, or other electronic platform through which the person carries on their taxable activity as required under Article 15 Sub- Article (2) of this Proclamation; c) for each failure to notify a change in circumstances as required under Article 15 Sub-Article (3) of this Proclamation; d) for failing to notify the Tax Authority as required under Article 16 Sub- Article (1) of this Proclamation; e) for notifying the Tax Authority under Article 16 of this Proclamation when still making taxable supplies or making an application for cancellation of registration under Article 17 of this Proclamation when still required to be registered; f) for failing to comply with Article 18 Sub-Article (1)(a) or (c) of this Proclamation; g) for each failure to prepare a recipient- created tax invoice as required under Article 52 Sub-Article (4) of this Proclamation; h) for each failure to provide a credit note or debit note as required under this Proclamation; i) for each failure to comply with a request under Article 54 of this Proclamation; or j) for each failure to comply with Article 68 (1) of this Proclamation. 2) A person shall be liable for a penalty equal to Birr 50,000 (Fifty Thousand Birr) for each time the person issues a tax invoice, credit note, or debit note otherwise than as provided for under this Proclamation. 3) A registered person, large unregistered person, or Government entity that fails to comply with Article 65 shall be liable for a penalty equal to Birr 50,000 (Fifty Thousand Birr).
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፡ሀ) ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በቅርንጫፎች እና በሥራ ክፍሎች የተከናወነ ታክስ የሚከፈልበት የሥራ እንቅስቃሴ እንደ አንድ ታክስ የሚከፈልበት የሥራ እንቅስቃሴ ይቆጠራል፤ እና ለ) በቅርንጫፎች እና በሥራ ክፍሎች ታክስ የሚከፈልበት የሥራ እንቅስቃሴ የሚያከናውን ሰው መመዝገብ ያለበት በራሱ ስም እንጂ በቅርንጫፉ እና በሥራ ክፍሎቹ ስም ሊሆን አይችልም። ፲፮ሺ፸፬ ፪/ የታክሱ ባለስልጣን የተመዘገበው ሰው በጽሑፍ የሚያቀርበውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የተመዘገበው ሰው ለእያንዳንዱ ቅርንጫፍ ወይም የስራ ክፍል ወይም በተናጠል ለሚያከናውነው ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ራሱን የቻለ የሂሳብ አያያዝ ስርአት ያለው መሆኑን እና በሚያከናውነው የስራ እንቅስቃሴ የተለየ ባህሪ ወይም ባለበት አድራሻ ተለይቶ የሚታወቅ መሆኑን ሲያምንበት የተመዘገበው ሰው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በግለሰብ ደረጃ የሚከናውነውን አንድ ወይም ከአንድ በላይ ቅርንጫፍ ወይም የስራ ክፍል ወይም በተናጠል የሚያከናውነውን ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ራሱን የቻለ የተመዘገበ ሰው አድርጐ እንዲያስመዘግብ ሊፈቅድ ይችላል። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት ቅርንጫፍ፣ የሥራ ክፍል ወይም የተለየ ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ራሱን ችሎ እንዲመዘገብ የሚፈቀደው የታክሱ ባለስልጣን ለተመዘገበው ሰው በሚሰጠው የጽሑፍ ማስታወቂያ የተመለከቱ ሁኔታዎች እና ገደቦች እንደተጠበቁ ይሆናል። ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት የተመዘገበ ሰው ያሉት ቅርንጫፎች፤ የሥራ ክፍሎች ወይም የተለዩ ታክስ የሚከፈልባቸው የስራ እንቅስቃሴዎች ራሳቸውን ችለው እንዲመዘገቡ ከተደረገ፡ሀ) ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ቅርንጫፉ፤ የሥራ ክፍሉ ወይም የተለየው ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ራሱን እንደቻለ ሰው ይቆጠራል፤ እና ለ) የተመዘገበው ሰው እና የዚህ ሰው ቅርንጫፎች፤ የሥራ ክፍሎች እና የተለየው ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች እንደሆኑ ይቆጠራል። ፲፮ሺ፸፭ 1/ Subject to Sub-Article (2) of this Article: a) a taxable activity carried on by a person in branches or divisions is treated as a single taxable activity for the purposes of this Proclamation; and b) a person who carries on a taxable activity in branches or divisions shall be registered in the name of the person and not in the names of the branches or divisions. 2/ The Tax Authority may, upon application in writing by a registered person, authorise the registered person to register One or more of its branches or divisions, or separate taxable activities carried on by an individual in different parts of the country, as separate registered persons where the Tax Authority is satisfied that registered person maintains an independent accounting system for each branch, division, or separate taxable activity, and the branch, division, or taxable activity can be separately identified by the nature of its activities or location. 3/ The registration of a branch, division, or separate taxable activity under Sub-Article (2) of this Article shall be subject to such conditions and restrictions as the Tax Authority may specify in a notice in writing to the registered person. 4/ Where a branch, division, or separate taxable activity of a registered person is separately registered under Sub-Article (2) of this Article: a) the branch, division, or separate taxable activity shall be treated as a separate person for the purposes of this Proclamation; and b) the registered person and the branch, division, and separate taxable activity of that registered person shall be treated as related persons.
፩/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገበ ሰው ታክስ ለሚከፈልበት የሥራ እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቀው ወይም የሚሰጠው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ማካተት ያለበት ሲሆን፣ ይህም በማስታወቂያው ወይም በሚሰጠው ዋጋ በግልጽ መመልከት አለበት። ፪/ በሚከተሉት ሁኔታዎች የተመዘገበ ሰው የሚያስተዋውቀው ወይም የሚሰጠው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የማይጨምር ሊሆን ይችላል፡ሀ) ማስታወቂያው ወይም የሚሰጠው ዋጋ በአቅርቦቱ ላይ ሊከፈል የሚገባው የተጨማሪ እሴት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሲታከል የሚኖረውን የዕቃውን ዋጋ ጭምር የሚገልጽ ከሆነ፤እና ለ) የተጨማሪ እሴት ታክስ የታከለበትን ዋጋ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ያልታከለበትን ዋጋ በሚመለከት የሚወጣው ማስታወቂያ ወይም የሚሰጠው ዋጋ የሚኖረው ተፈላጊነት ወይም ውጤት እኩል ከሆነ። ፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገበ ሰው የሚያቀርባቸው ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ማስታወቂያ የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በሚያከናውንበት ቦታ የመግቢያ በሮች ወይም ደንበኞች ክፍያ በሚፈጽሙበት ቦታ በተገቢው ሁኔታ እስከተገለጸ ድረስ በክፍያ መቀበያ ቲኬቶች ላይ ዋጋው የተጨማሪ እሴት ታክስ የታከለበት መሆኑን መግለጽ አስፈላጊ አይሆንም። ፲፮ሺ፸፮ ፬/ የታክሱ ባለሥልጣን ማናቸውም የተመዘገበ ሰው ወይም የተመዘገቡ ሰዎች ቡድን የሚያቀርቡትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዋጋ የሚገልጹበትን ሌላ ዘዴ ሊወሰን ይችላል። ፭/ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገበ ሰው በጨረታ ተሳታፊ የሆነ እንደሆነ፡ሀ) በጨረታው የመወዳደሪያ ዋጋውን የሚያቀርበው የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር መሆን አለበት፤ እና ለ) በጨረታው አሸናፊ ከሆነ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ መሠረት ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገብ ያለበት ሲሆን፣ በጨረታው መሠረት በሚያከናውነው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መሰብሰብ አለበት። 1/ Subject to Sub-Article (2), any price advertised or quoted by a registered person in respect of a taxable supply shall include VAT and this shall be stated in the advertisement or quotation. 2/ A registered person may advertise or quote a price in respect of a taxable supply as exclusive of VAT provided: a) the advertisement or quotation also states the amount of VAT charged on the supply and the price inclusive of VAT; and b) the price inclusive of VAT and the price exclusive of VAT shall be advertised or quoted with equal prominence or impact. 3/ Subject to Sub-Article (4), price tickets on goods supplied by a registered person do not need to state that the price includes VAT if this is stated by way of a notice prominently displayed at all entrances to the premises in which the registered person carries on a taxable activity and at all points in such premises where payments are made by customers. 4/ The Tax Authority may, in the case of any registered person or class of registered persons, approve any other method of displaying prices of goods or services by such persons. 5/ Where a person who is not registered for VAT bids for a tender: a) the person shall quote in the tender a price without VAT; and b) if, as a result of being awarded the tender, the person is liable to be registered under Article 12, the person shall recover VAT on taxable supplies made in relation to the tender.
፩/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ይሆናል፡ሀ) የተመዘገበው ሰው ሲሞት፣ ወይም ክፍያ መፈጸም ያለመቻሉ ወይም መክሰሩ ሲረጋግጥ፤ እና ለ) ከሚከተሉት አንዱ ሲያጋጥም፡- (1) ቀደም ሲል በተመዘገበው ሰው ሲካሄዱ የነበሩ ታክስ የሚከፈልባቸውን እንቅስቃሴዎች የሞተውን፤ ክፍያ መፈጸም ያቋረጠውን ወይም የከሰረውን የተመዘገበ ሰው ሀብት የሚያስተዳድረው ሰው ሲያካሂድ፤ ወይም (2) የተመዘገበውን ሰው ታክስ የሚከፈልበት የሥራ እንቅስቃሴ የሚያቋርጥ ማናቸውም ተግባር ሲፈጸም። ፲፮ሺ፸፯ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የተመዘገበው ሰው ሀብት አስተዳዳሪ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የተመዘገበውን ሰው ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ በማከናወን ተግባር እንደቀጠለ ይቆጠራል። ፫/ ንብረት በመያዣነት የተቀበለ ሰው ቀደም ሲል ንብረቱን በመያዣነት የሰጠውን የተመዘገበ ሰው የመሬት ይዞታ ወይም ሌላ ንብረት የተረከበ እና በመያዣነት የሰጠው ሰው ሲያካሂድ የነበረውን ታክስ የሚከፈልበት የሥራ እንቅስቃሴ ማካሄድ የቀጠለ እንደሆነ ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ ማካሄድ እስከቀጠለበት ጊዜ እና በዚያው መጠን መሬቱን ወይም ንብረቱን በመያዣ እንደሰጠው ሰው ሆኖ ይቆጠራል። Registered Person; and Mortgagee-in- Possession 1/ Sub-Article (2) of this Article shall apply where the following conditions are satisfied: a) a registered person has died or been declared bankrupt or insolvent; and b) either of the following applies: (i) the taxable activity previously carried on by the registered person is carried on by the receiver in relation to the deceased, bankrupt, or insolvent registered person; or (ii) anything is done in connection with the termination of the taxable activity of the registered person. 2/ Where the conditions in Sub-Article (1) of this Article are satisfied, the receiver shall, for the purposes of this Proclamation, be treated as continuing to carry on the taxable activity of the registered person. 3/ Where a mortgagee takes possession of land or other property previously mortgaged by a mortgagor who is a registered person and, while in possession of the land or property, the mortgagee carries on the taxable activity previously carried on by the mortgagor in relation to the land or other property, the mortgagee is, to the extent of, and for the duration that it carries on that taxable activity, treated as the mortgagor.
፩/ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ይሆናል፡ሀ) ታክስ ያለመክፈል ዕቅድ የተዘረጋ ወይም ተግባራዊ የተደረገ ከሆነ፤ ለ) ማናቸውም ሰው ታክስ ያለመክፈሉን ዕቅድ በመጠቀም የታክስ ጥቅም ያገኘ እንደሆነ፤ እና ሐ) ታክስ ያለመክፈሉ ዕቅድ ይዘት ሲመረመር፣ ታክስ ባለመክፈሉ ዕቅድ የተሳተፈ ወይም ተግባራዊ ያደረገው ሰው ወይም ካደረጉት ሰዎች አንዱ ይህንን ድርጊት የፈጸመበት ብቸኛ ዓላማ ወይም ዋነኛ ዓላማ በዚህ አንቀጽ ተራ ፊደል (ለ) የተጠቀሰውን የታክስ ጥቅም ለማግኘት ከሆነ፣ ነው። ፲፮ሺ፸፰ ፪/ በዚህ አዋጅ የተደነገገው ቢኖርም ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ የታክሱ ባለሥልጣን ዕቅዱ ያልተዘረጋ ወይም ተግባራዊ እንዳልሆነ በመቁጠር የተገኘውን የታክስ ጥቅም ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ ያስችላል ብሎ የሚያምንበትን እርምጃ በመውሰድ በተዘረጋው ዕቅድ ታክስ ላለመክፈል የቻለው ሰው እና ከተዘረጋው ዕቅድ ጋር ግንኙነት ያለው ማናቸውም ሰው የሚኖርበትን ተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ ሊወስን ይችላል። ፫/ የታክሱ ባለሥልጣን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት ውሳኔ ሲሰጥ በታክስ አስተዳደር አዋጅ በተደነገገው መሠረት የታክስ ውሳኔ ማሻሻያን ጨምሮ በውሳኔው ምክንያት የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ የተጣለበትን ሰው ወይም ሰዎች ግዴታ የሚገልጽ የውሳኔ ማስታወቂያ እንዲደርስ ማድረግ አለበት። ፬/ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም፣ ‹‹ዕቅድ›› የሚከተሉትን ይጨምራል፡ሀ) በግልጽ የተደረገ ወይም በግልጽ ሳይነገር የተደረገ ቢሆንም ባይሆንም፣ በክርክር ሂደት ሕጋዊ አስገዳጅነት ቢኖረውም ባይኖረውም ስምምነት፣ ማመቻቸት ወይም ቃልኪዳን፤ ወይም ለ) በአንድ ሰው ወይም በሁለት እና ከሁለት በላይ በሆኑ ሰዎች የተፈፀመ ማናቸውም ግዴታ፣ ዕቅድ፣ የውሳኔ ሀሳብ፣ የድርጊት መርሀ ግብር፣ ወይም የድርጊት ስልት፤ እና ፲፮ሺ፸፱ ‹‹የታክስ ጥቅም›› ማለት፡ሀ) አንድ ሰው ሊከፍል የሚገባውን ተጨማሪ እሴት ታክስ መጠን መቀነስ፤ ለ) ሊያገኝ የሚገባውን የግብአት ታክስ ተቀናሽ መጨመር፤ ሐ) ሊያገኝ የሚገባውን ተመላሽ መጨመር፣ መ) ሊከፍል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ማዘግየት፤ ሠ) ሊያገኝ የሚገባውን የግብአት ታክስ ተቀናሽ ማፋጠን፤ ረ) ሊከፍል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ከማዘግየት ወይም ሊያገኝ የሚገባውን የግብአት ታክስ ተቀናሽ ከማፋጠን የሚገኝ ማናቸውም ሌላ ጥቅም፤ ሰ) ታክስ ሊከፈልበት የሚገባው አቅርቦት፣ ወደ ሀገር የሚገባ ዕቃ ወይም በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት፤ እንደሁኔታው፤ ታክስ የማይከፈልበት አቅርቦት፣ ታክስ የማይከፈልበት ወደሀገር የሚገባ ዕቃ ወይም ታክስ የማይከፈልበት በቀጥታ በገዢው ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት እንዲሆን የሚያስችል ማናቸውም ድርጊት፤ ወይም ሸ) ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ከማከናወን ውጪ ባለ ድርጊት ጥቅም ላይ የዋለው ወይም የሚውለው ተቀናሽ የሚሆን ግዢ የግብአት ታክስ ተቀናሽ እንዲገኝበት ማድረግ። 1/ This Article shall apply where all the following conditions are satisfied: a) a scheme has been entered into or carried out; b) a person has obtained a tax benefit in connection with the scheme; c) having regard to the substance of the scheme, it would be concluded that a person, or One of the persons, who entered into or carried out the scheme did so for the sole or dominant purpose of enabling the person to obtain the tax benefit referred to in Paragraph (b) of this Sub-Article. 2/ Despite anything in this Proclamation, where this Article applies, the Tax Authority may determine the VAT liability of the person who obtained the tax benefit, and of any other person related to the scheme, as if the scheme had not been entered into or carried out, or in such manner as, in the circumstances, the Tax Authority considers appropriate for the prevention or reduction of the tax benefit. 3/ Where the Tax Authority has made a determination under Sub-Article (2) of this Article, the Tax Authority shall serve a notice or notices of assessment, including an amended assessment under the Tax Administration Proclamation, to give effect to the determination on the person or persons whose VAT liability is affected by the determination. 4/ In this Article: “Scheme” includes: a) an agreement, arrangement, or promise, whether express or implied, whether or not legally enforceable in legal proceedings; or b) any undertaking, plan, proposal, course of action, or course of conduct whether undertaken unilaterally or by Two or more persons; and “Tax Benefit” means: a) a reduction in the liability of a person to pay VAT; b) an increase in the entitlement of a person to an input tax credit; c) an entitlement to a refund of VAT, d) a postponement of a liability for the payment of VAT; e) an acceleration of an entitlement to an input tax credit; f) any other advantage arising because of a delay in the payment of VAT or an acceleration of the entitlement to an input tax credit; g) anything that causes a taxable supply, taxable import, or reverse charged supply not to be a taxable supply, taxable import, or reverse charged supply, as the case may be; or h) anything that gives rise to an input tax credit entitlement for a creditable acquisition that is used, or is to be used, other than in making taxable supplies.
፩/ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ማናቸውም የገንዘብ መጠን በብር መገለጽ አለበት። ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የገንዘብ መጠን የተገለጸው በብር ሳይሆን በሌላ የገንዘብ ዓይነት የሆነ እንደሆነ፡- ፲፮ሺ፹ ሀ) ወደ ሀገር የገቡ ዕቃዎችን በሚመለከት፣ በዕቃው ላይ ሊከፈል የሚገባውን የጉምሩክ ቀረጥ ለማስላት በጉምሩክ አዋጅ ጥቅም ላይ እንዲውል የተፈቀደውን የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን መሠረት በማድረግ የገንዘቡ መጠን ወደብር እንዲቀየር ይደረጋል፤ ለ) በሌሎች ማናቸውም ሁኔታዎች የገንዘቡ መጠን ወደ ብር የሚለወጠው የገንዘቡ መጠን ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በሒሣብ ስሌት ውስጥ መካተት በሚገባው ቀን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሥራ ላይ ባዋለው በውጭው ሀገር ገንዘብ እና በኢትዮጵያ ብር መካከል ባለው የውጭ ገንዘብ የምንዛሪ ተመን ይሆናል። ፫/ የውጭ ሀገር አቅራቢ የውጭ ሀገር ገንዘብን ወደብር ለመለወጥ ከሚከተሉት አንዱን ዘዴ ሊጠቀም ይችላል፡ሀ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) (ለ) የተመለከተውን አሠራር፤ ለ) አግባብነት ባለው የሒሣብ ጊዜ የመጨረሻ ቀን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጸንቶ የሚሰራበትን በውጭ ሀገር ገንዘብ እና በኢትዮጵያ ብር መካከል ያለውን የምንዛሪ ተመን፤ ወይም ሐ) ከታክሱ ባለሥልጣን ጋር ስምምነት የሚደረስበትን ሌላ ዘዴ። ፬/ የውጭ ሀገር አቅራቢ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) መሠረት የሚመርጠው አሠራር አቅራቢው ለሚፈጽመው አቅርቦት ሁሉ ተፈጻሚ የሚደረግ ሲሆን፣ የታክሱ ባለስልጣን ካልተስማማ በስተቀር አቅራቢው ምርጫውን ከአንድ ዓመት በፊት ሊሰርዝ አይችልም። ፲፮ሺ፹፩ ፭) በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ የውጭ አቅራቢ የታክስ ማስታወቂያውን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን በውጭ ምንዛሬ እንዲፈጽም ሊፈቅድ ይችላል። ፮) ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ‹‹የውጭ ሀገር አቅራቢ›› ማለት፡ሀ) የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፫ (፪) ፊደል ተራ (ሐ) ተፈጻሚ የሚሆንበት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚታዘዝ እቃ አቅራቢ፤ ወይም ለ) የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፬ (፪) ፊደል ተራ (ሐ) ተፈጻሚ የሚሆንበት ከሩቅ የሚሰጥ አገልግሎት አቅራቢ፤ ሐ) የዚ አዋጅ አንቀጽ ፳፫ (፫) እና (፳፭) ተፈጻሚ የሚሆንበት የኤሌክትሮኒክ ማከፋፈያ ገበያ አስተዳዳሪ የሆነ ሰው ነው። 1/ An amount taken into account under this Proclamation shall be expressed in Birr. 2/ Subject to Sub-Article (3) of this Article, if an amount is in a currency other than Birr: a) for an import of goods, the amount shall be translated to Birr at the exchange rate applicable under the Customs Legislation for the purposes of calculating the duty payable on the import; or b) for any other case, the amount shall be translated to Birr at the National Bank of Ethiopia prevailing exchange rate applying between the foreign currency and Birr on the date the amount is taken into account for the purposes of this Proclamation. 3/ A foreign supplier may elect to translate foreign currency amounts to Birr: a) in accordance with Sub-Article (2) Paragraph (b) of this Article; b) at the National Bank of Ethiopia prevailing exchange rate applying between the foreign currency and Birr on the last day of the relevant accounting period; or c) on such other basis as agreed with the Tax Authority. 4/ An election made by a foreign supplier under Sub-Article (3) of this Article shall apply to all supplies made by the supplier and the supplier shall not be able to revoke the election until at least one year after making the election, unless the Tax Authority agrees otherwise. 5) A VAT regulation issued by the Council of Ministers may allow a foreign supplier to carry out a tax notice and VAT in foreign currency. 6/ In this Article, “Foreign Supplier” means a person who is: a) a supplier of remote services to which Article 23 Sub-Article (2) (c) of this Proclamation applies; or b) a service provider from a distance to which Article 24 Sub-Article (2) (c) of this Proclamation applies; c) a person who manages an electronic distribution market to which Article 23 Sub-Article (3) and (25) of this Proclamation applies.
፩/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጨምሮ ለአዋጁ ትክክለኛ አፈጻጸም የሚረዱ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል፡ሀ) የተወሰኑ የአቅርቦት ዓይነቶችን ወይም የግብዓት ታክስ ተቀናሽ አፈቃቀድን፤ ለ) በዚህ አዋጅ ከተደነገገው በተለየ ለአንድ አቅርቦት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተፈፃሚ የሚደረግበትን አግባብ፤ ወይም ሐ) የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎችን የሚመለከቱ ደንቦችን። ፪/ ሚኒስቴሩ ለአዋጁና በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ለሚወጣው ደንብ ትክክለኛ አፈጻጸም የሚያግዙ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል። ፲፮ሺ፹፪ 1/ The Council of Ministers may issue Regulations necessary for the proper implementation of this Proclamation, including in relation to: a) particular types of supplies or the allowance of input tax credits; b) the application of a change, under this Proclamation, in the VAT treatment of a supply; or c) matters regarding transitional provisions. 2/ The Ministry may issue Directives necessary for the proper implementation of this Proclamation and Regulations issued under Sub-Article (1) of this Article.
፩/ ይህ አዋጅ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ወይም ይህ አዋጅ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በወጣ ሕግ ውስጥ ያለ አንድ አቅርቦት ወይም አቅርቦቶች ወይም ወደሀገር የሚገባ ዕቃ ወይም ወደሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ወይም ከውጭ ሀገር የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንደሆኑ ወይም ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ እንደሚደረግላቸው ወይም ዝቅተኛ የተጨማሪ እሴት ታክስ የማስከፈያ መጣኔ የሚጣልባቸው መሆኑን የሚደነግግ አንቀጽ በዚህ አዋጅ ይህ መብት ካልተቋቋመ በስተቀር ተፈጻሚነት አይኖረውም። ፪/ ይህ አዋጅ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ወይም ይህ አዋጅ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ በወጣ ሕግ ውስጥ ያለ አንድ ሰው ወይም ሰዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የተደረጉ መሆኑን የሚደነግግ አንቀጽ በዚህ አዋጅ ይህ መብት ካልተቋቋመ በስተቀር ተፈጻሚነት አይኖረውም። ፫/ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፸፬ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር ፪፻፹፭/፩ሺ፱፻፺፬ ከነማሻሻያዎቹ በዚህ አዋጅ ተሽሯል። ፬/ ማናቸውም ሕግ ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን እስከሆነ ድረስ በዚህ አዋጅ በተደነገጉ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም። 1/ A provision in any other law, whether enacted before or after this Proclamation, specifying that a supply or class of supply, or an import or class of import, is an exempt or Zero-rated supply, exempt import, or subject to a reduced rate of VAT shall have no legal effect unless also provided for in this Proclamation. 2/ A provision in any other law, whether enacted before or after this Proclamation, specifying that a person or class of persons is exempted from paying VAT shall have no legal effect unless also provided for in this Proclamation. 3/ Without prejudice to Article 74 of this Proclamation, the Value Added Tax Proclamation No. 285/2002 is hereby repealed. 4/ No other law may, in so far as it is inconsistent with this Proclamation, be applicable with respect to matters provided for by this Proclamation.
፩/ የተሻረው አዋጅ ይህ አዋጅ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት ስራ ላይ የቆዩ ነባር የሒሣብ ጊዜዎችን በሚመለከት ተፈጻሚነት ይኖረዋል። ፲፮ሺ፹፫ ፪/ በዚህ አዋጅ ነባር የሒሣብ ጊዜዎች በሚል የተጠቀሰው አግባብነት እስካለው ድረስ በተሻረው አዋጅ የነበረውን የሒሣብ ጊዜ ይጨምራል። ፫/ በተሻረው አዋጅ መሠረት የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ እስካልሆነ እና በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብና መመሪያ እስከሚተኩ ድረስ ተፈጻሚነታቸው ይቀጥላል። ፬/ ይህ አዋጅ ከመወጣቱ በፊት በተሰጠ የባንክ ፈቃድ አዋጁ ከጸናበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች በተሻረው አዋጅ መሠረት ይስተናገዳሉ። ፭/ የገቢዎች ሚኒስቴር በዚህ አዋጅ በተደነገገው መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስን የመሰብሰብ ውክልና አሰጣጥን እና የአፈጻጸም ሥርዓቱን እስከሚዘረጋ ድረስ ቀደም ሲል በተሻረው አዋጅ መሠረት ለክልል የታክስ ባለሥልጣናት የሰጠው ውክልና ተፈጻሚነት ይቀጥላል። ፮/ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በመሸጥ ስራ ላይ የተሰማራ እና ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በግንባታ ላይ ላሉ የመኖሪያ ቤቶች በሚውሉ ግብአቶች ላይ የከፈለውን የግብአት ታክስ ያቀናነሰ የተመዘገበ ሰው የሚሸጠው የመኖሪያ ቤት ከታክሱ ነጻ እንዲሆን ለማድረግ የሚቻለው በእነዚህ የግንባታ ዕቃዎች ላይ ያቀናነሰውን የግብዓት ታክስ ለባለሥልጣኑ ተመላሽ ሲያደርግ ነው። ፲፮ሺ፹፬ ፯/ በዚህ አዋጅ የተደነገገው ቢኖርም በቱሪስት አስጎብኚነት የንግድ ስራ ላይ የተሰማራ የተመዘገበ ሰው ይህ አዋጅ ከጸናበት ቀን አንስቶ ለሦስት ዓመታት ያህል የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍለው በሀገር ውስጥ ጥቅል የቱሪዝም አገልግሎት ለመስጠት ከተቀበለው ክፍያ ላይ ለመኝታ፣ ለምግብ እና ለትራንስፖርት የሚያወጣው ወጪ ተቀንሶ በሚቀረው ሂሳብ ወይም በሚከፈለው ኮሚሽን ላይ ይሆናል። ፰/ በዚህ አንቀጽ ‹‹የተሻረው አዋጅ›› ማለት የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር ፪፻፹፭/፩ሺ፱፻፺፬ ከነማሻሻያዎቹ ነው። 1/ The Repealed Law continue to apply to accounting periods prior to the commencement of this Proclamation. 2/ A reference in this Proclamation to a previous accounting period shall include, where the context requires, a reference to an accounting period under the repealed law. 3/ Regulations and Directives issued under the Repealed Law shall continue to apply to the extent that they are not inconsistent with this Proclamation and until such time as they are replaced by Regulations and Directives issued under this Proclamation. 4/ The Repealed Law shall be applicable to goods imported into Ethiopia within Six months from the effective date of this Proclamation using the Letter of Credit issued prior to the issuance of this Proclamation. 5/ The delegation of power granted to Regional tax authorities by the Ministry of Revenue under the Repealed Law shall continue to be applicable until a procedure and a system of delegation is developed in accordance with this Proclamation. 6/ The residential buildings of a registered person engaged in real estate business, who has credited the input tax paid on creditable acquisition used for residential buildings under construction before entry into force of this Proclamation, may only be exempt from VAT upon returning to the Tax Authority the input tax credited. ‹ 7/ Notwithstanding the provisions of this Proclamation, a registered person engaged in tour operation business shall for Three years from the date of effectiveness of this Proclamation pay Value Added Tax on the net amount of the fee received for Inbound tourism product after deducting the cost incurred in Ethiopia for accommodation, meals, transportation and tours or on commission received. 8/In this Article, “Repealed Law” means that Value Added Tax Proclamation No. 285/2002.
ይህ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል። አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ዓ.ም ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ‹ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት 285/2002. ‹ ፲፮ሺ፹፭ አባሪ አንድ (አንቀጽ ፱) ዜሮ የማስከፈያ ልክ ተፈጻሚ የሚሆንባቸው አቅርቦቶች This Proclamation shall enter into force up on the date of its approval by the House of Peoples’ Representatives. Done at Addis Ababa, On this 21th Day of August, 2024 SAHLE WORK ZEWDIE ‹ PRESIDENT OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA
Choose an article to open it.