English
1/ Subject to Sub-Article
(2) of this Article,
this Article shall apply to:
a) a supply, by a telecommunications
service supplier, of a prepaid
telecommunications product, or
[
b) a supply by a person who acts as a
distributor, agent, or
telecommunications intermediary in
relation to the supply of a prepaid
telecommunications product.
2/ Sub-Article
(1) of this Article shall not
apply to a supply by one
telecommunications service supplier to
another telecommunications service
supplier and such a supply is subject to
the normal operation of this
Proclamation.
3/ If a telecommunications service supplier
supplies a prepaid telecommunications
product to a telecommunications
intermediary at a discount from the
intended retail price, the consideration
for the supply shall be calculated as if the
intermediary had paid the intended retail
price.
4/ If a telecommunications intermediary
purchases and on-sells a prepaid
telecommunications product:
a) the acquisition by the intermediary
shall be treated as if it were not an
acquisition, and
b) the supply by the intermediary shall
be treated as if it were not a supply.
5/ Where a telecommunications service
supplier supplies a prepaid
telecommunications product through a
telecommunications intermediary acting
as agent for the telecommunications
supplier, the consideration for the supply
shall not be reduced by the commission
paid to the intermediary.
አማርኛ
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፪) የተመለከተው
እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ
የሚሆነው፡ሀ) የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ
የቅድሚያ ክፍያ በማስከፈል የሚሰጠውን
የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ወይም
ለ) በቅድመ-ክፍያ የሚቀርብን የቴሌኮሙኒኬሽን
አገልግሎት በማቅረብ ረገድ አከፋፋይ፣ ወኪል
ወይም የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አገናኝ
ሆኖ የሚሰራ ሰው የሚያቀርበውን አገልግሎት
በሚመለከት ነው።
[
፲፮ሺ፴፯
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ድንጋጌ አንድ
የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ ለሌላ
የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ
የሚሰጠውን እና በዚህ አዋጅ መሠረት
ከሚከናወን መደበኛ የሥራ እንቅስቃሴ ጋር
የተገናኘን አቅርቦት በሚመለከት ተፈጻሚ
አይሆንም።
፫/ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ በቅድመ
ክፍያ የሚቀርብን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ከችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በታች በሆነ የቅናሽ ዋጋ
ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አገናኝ በሚያቀርብ
ጊዜ የአቅርቦቱ ዋጋ የሚሰላው የቴሌኮሙኒኬሽን
አገልግሎት አገናኙ አቅርቦቱን በችርቻሮ መሸጫ
ዋጋ እንደገዛ ተቆጥሮ ነው።
፬/ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አገናኝ በቅድመ
ክፍያ የሚቀርብን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የሚገዛ እና የሚሸጥ በሚሆንበት ጊዜ፡ሀ) የሚፈጽመው ግዥ እንዳልተፈጸመ፣ እና
ለ) የሚሸጠው አገልግሎት እንዳልቀረበ፣ ተደርጐ
ይቆጠራል።
፭/ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ በቅድመ
ክፍያ የሚቀርብን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ወኪል ሆኖ በሚሠራ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አገናኝ አማካኝነት የሚያቀርብ በሚሆንበት ጊዜ
ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቱ ከሚከፈለው ዋጋ
ላይ ለአገናኙ የሚከፈለው ኮሚሽን ተቀናሽ
አይደረግም።
፲፮ሺ፴፰