Skip to main content
YZlex
Legal Library
AI Assistant
Legal Library
Find Lawyers
About
EN
አማ
Sign In
Loading legal library
Loading document
Library
vat proclamation no 1341 2016 with annex
Article 2
Table of Contents
75
Article 1
Short Title
Article 2
Definition
Article 3
Scope of Application
Article 4
Power to Collect the Tax
Article 5
Consideration
Status requires review
— We have not verified this source's current status.
Structural division:
PART ONE
Article 2 — Definition
vat proclamation no 1341 2016 with annex
Article text
‹‹በእርዳታ የሚሰጡ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች›› ማለት ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን በሚመለከት ለእነዚህ ድርጅቶች በስጦታ የሚቀርቡ ወይም በስጦታ በተገኘ የሚገዙ እና ድርጅቱ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማስፈጸም የሚውሉ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች። ‹‹የትምህርት ፕሮግራም›› በሚከተሉት የሚሰጥ የትምህርት ፕሮግራም ነው፡ሀ) አግባብ ባለው ክልል የትምህርት ቢሮ ፈቃድ የተሰጠው ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ አንደኛ ደረጃ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ ለ) በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር ፩፻፶፪/፪ሺ፲፩ መሠረት በትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና የተሰጠው ዩኒቨርሲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኮሌጅ ወይም ኢንስቲትዩት፣ ሆኖም የትምህርት ፕሮግራሙ ዲግሪ ወይም ተመሳሳይ የብቃት ማስረጃ የሚያስገኝ ከሆነ፤ ሐ) በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና አዋጅ ቁጥር ፱፻፶፬/፪ሺ፰ መሠረት ዕውቅና የተሰጠው የሥልጠና ተቋም፣ ሆኖም የትምህርት ፕሮግራሙ በአዋጁ መሠረት ዕውቅና የተሰጠው የቴክኒክ ወይም የሙያ ሥልጠና ፕሮግራም ከሆነ፤ መ) የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፲፮ሺ፺፩ ‹‹የፋይናንስ አገልግሎት›› ማለት፡ሀ) በአበዳሪው የሚከናወንን ብድር፣ ክሬዲት ወይም የክሬዲት ዋስትናን ማስተዳደርን ጨምሮ ብድር መስጠት፣ መደራደር፣ ወይም በብድር፣ በክሬዲት፣ በክሬዲት ዋስትና ወይም ለገንዘብ በሚሰጥ ዋስትና መነገድ፤ ለ) ዕዳ መሰብሰብን እና ተሰብሳቢ ሒሣብን መሸጥን ሳይጨምር ገንዘብ፣ ተቀማጭ ሒሣብን፤ ቁጠባን እና ሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦችን፣ ክፍያዎችን፣ የገንዘብ ማስተላለፍ ተግባራትን (የፋይናንስ ቴክኖሎጂ አገልግሎትን ሳይጨምር)፣ ዕዳን፣ ቼክን ወይም የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን የሚመለከቱ ተግባራት፤ ሐ) የፋይናንስ ዴሪቬቲቭ ሀብትን የመግዛትና የመሸጥ ውሎች፣ የፋይናንስ ሀብትን ወደፊት በሚውል ቀን ለመግዛት ወይም ለመሸጥ የሚደረግ ስምምነት፣ የፋይናንስ ሰነዶችን ለመግዛት የሚኖር ምርጫን የመግዛትና የመሸጥ ውሎች እና ተመሳሳይ ተግባራትን፣፤ መ) የአደራ አገልግሎት ሳይጨምር በአክሲዩን፣ ድርሻ፣ ቦንድ እና ሌሎች የግዴታ ምስክር ወረቀቶች መገበያየት እና ከእነዚህ ጋር የተያያዘ ማናቸውም ምርጫ ወይም ዋስትና፤ ሠ)የኢንቨስትመንት ፈንድን ማስተዳደር፤ ረ) የረዥም ጊዜ የመድን ውል መስጠት ወይም የባለቤትነት መብት ማስተላለፍ ወይም ለዚህ ዓይነቱ ውል የጠለፋ መድን መስጠት ወይም አነስተኛ የመድህን ውል መስጠት፤ ሰ) የጡረታ ፈንድ፣ የፕሮቪደንት ፈንድን ወይም ሌላ ተመሳሳይ የጥቅም ፈንድ፤ የመድን ጡረታ ፈንድ፤ የጡረታ ሂሳብን ለማስጠበቅ የሚቋቋም ፈንድ ማቋቋም ወይም የባለቤትነት መብትን ማስተላለፍ፤ ሸ) ለዕቃው በሚሰጠው ብድር ላይ የተለየ ክፍያ የሚጠየቅ እና ክፍያው ለዕቃው ተጠቃሚ የተገለጸ እስከሆነ ድረስ በኪራይ ግዥ ስምምነት ወይም በፋይናንስ ሊዝ መሠረት የሚከናወን አቅርቦት፤ ቀ) ብር ወይም የውጭ ምንዛሪ የመግዛት ወይም የመሸጥ ውል፤ በ) ከፊደል ተራ (ሀ) እስከ (ቀ) የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ማመቻቸት፤ ወይም ተ) በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ በሚወሰነው መሠረት የእስልምና ባንክ አገልግሎት መስጠት። ‹‹የእረፍት ጊዜ ወይም የሆቴል መስተንግዶ›› ማለት፡ሀ) በሆቴል፣ በሞቴል፣ በኢን፣ በመኝታ ቤቶች፣ በእንግዳ ማረፊያ፣ በሆስቴል ወይም በተመሳሳይ ሌላ ተቋም በተለምዶ በሚሰጥ መስተንግዶ ለበርካታ ሰዎች በቀን፣ በሣምንት፣ በወር ወይም በሌላ በተወሰነ የጊዜ ልዩነት በሚፈጸም ክፍያ አገልግሎት መስጠት፤ ወይም ለ) በዚህ የትርጉም ክፍል ፊደል ተራ (ሀ) ከተመለከተው የመስተንግዶ አቅርቦት ውጪ በግለሰቦች ለአጭር ጊዜ ለሚደረግ ቆይታ የሚሰጥ መስተንግዶ፣ ፲፮ሺ፺፪ ‹‹የረዥም ጊዜ የመድን ስራ›› የሚለው ሐረግ በመድን ስራዎች አዋጅ ቁጥር ፯፻፵፮/፪ሺ፬ (እንደተሻሻለ) የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል። ‹‹የረዥም ጊዜ የመድን ስራ ውል›› ማለት የረዥም ጊዜ የመድን ስራ በማከናወን ሂደት የሚፈጸም የመድን ስራ ውል ነው። ‹‹የሕክምና አገልግሎት›› ማለት በምግብ፣ መድኃኒትና የጤና እንክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፲፪/፪ሺ፲፪ መሠረት ፈቃድ በተሰጠው የጤና ባለሙያ ወይም የሕክምና ባለሙያ በታወቀ የህክምና ተቋም ውስጥ የሚሰጥ የህክምና ሙያ አገልግሎት ነው። ‹‹አነስተኛ መድህን ውል›› የሚለው ሐረግ በመድን ስራዎች አዋጅ ቁጥር ፯፻፵፮/፪ሺ፬ (እንደተሻሻለ) የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል። ‹‹ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት›› ማለት በፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፱፻፸፱/፪ሺ፰ አንቀጽ ፷፭ ንኡስ አንቀጽ (፩) ፊደል ተራ (ነ) አፈጻጸም ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሆኖ የሚቆጠር አካል ነው። ‹‹በሐኪም የሚታዘዝ መድኃኒት›› ማለት በምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፲፪/፪ሺ፲፩ መሠረት በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ የሚወሰድ መድኃኒት ነው። ‹‹የብዙሐን ትራንስፖርት አገልግሎት›› ማለት ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት በስተቀር ለመንገደኞች እና ለግል መገልገያ ዕቃዎቻቸው እንዲሁም ለጭነት ዕቃዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በመንገድ፣ በባቡር ወይም በጀልባ በክፍያ የሚሰጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ነው፡ሀ) ባለሦስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር፣ አሽከርካሪውን ጨምሮ ከስምንት ሰው በታች የመጫን አቅም ያለው ተሽከርካሪን በመጠቀም የሚሰጥ የትራንስፖርት አገልግሎት፤ ለ) ከነሹፌሩ ቢሆንም ባይሆንም የሚሰጥ የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት፤ እና ሐ) ቱሪስቶችን ማጓጓዝ። ‹‹የታወቀ የህክምና ተቋም›› ማለት በደንቡ የተመለከተው የህክምና ተቋም ነው። “የህክምና ሙያ አገልግሎት›› ማለት በደንቡ የተመለከተው የህክምና አገልግሎት ነው። ‹‹የመኖሪያ ቤት›› ማለት ሆቴልን ወይም የእረፍት ጊዜ መኖሪያን ሳይጨምር ለግል መኖሪያነት በማገልገል ላይ የሚገኝ ወይም የሚያገለግል የማይንቀሳቀስ ንብረት ነው። ‹‹ሽያጭ›› ማለት ከመኖሪያ ሕንጻዎች ጋር በተያያዘ የረጅም ጊዜ የሊዝ ውል መስጠትን ወይም ማስተላለፍን ፲፮ሺ፺፫ አባሪ ሦስት (አንቀጽ ፲፩) ከታክስ ነጻ የሆኑ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ከታክሱ ነጻ ተደርገዋል፡ሀ) በቪዬና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ኮንቬንሽን ሚሲዮኖች፣ ዲፕሎማቶች ወይም የኩንሱላር ጽ/ቤቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እስከሆኑ ድረስ እነዚህ ሚሲዮኖች፣ ዲፕሎማቶች ወይም የኩንሱላር ጽ/ቤቶች ወደ ሀገር የሚያስገቡዋቸው ዕቃዎች፤ ለ) በዓለም አቀፍ ስምምነት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የተደረጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፤ ሐ) በፋይናንስ፣ በቴክኒክ፣ በሰብዓዊ ዕርዳታ ወይም በአስተዳደር ድጋፍ የዓለም አቀፍ ስምምነት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እስከተደረገ ድረስ የውጭ ሀገር መንግሥት ወደ ሀገር የሚያስገባቸው ዕቃዎች፤ መ) በጉምሩክ ደንብ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ እስከተደረገ ድረስ መንገደኛው ይዞት የሚመጣ የግል መገልገያ ዕቃ፤ ሠ) ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከሚወስነው እስካልበለጠ ድረስ ተመላሾች ወደ ሀገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፤ ረ) ወደ ሀገር የሚገባ ለግብርና ሥራ ብቻ የሚውል ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የተባይ ማጥፊያ፣ የአረም ማጥፊያ ወይም የፈንገስ ማጥፊያ፤ ሰ) ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚቀርብ ወደ ሀገር የሚገባ ወርቅ፤ ሸ) የውሃ ማከሚያ፤ አጐበር፣ የሕክምና መገልገያ፣ እና የሕክምና መሣሪያ፤ ቀ) በአባሪ ፪ ትርጉም የተሰጠው ወደ ሀገር የሚገባ በሐኪም የሚታዘዝ መድኃኒት፤ በ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር ፭፻፲፯/፪ሺ፲፬ በተደነገገው መሠረት ኢንቨስተሮች ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር የሚያስገቡት ዕቃ፤ ተ) ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር እንዲገቡ የተፈቀዱ የካፒታል ዕቃዎች፤ ቸ) በጉምሩክ ታሪፍ ደንብ ከጉምሩክ ቀረጥና ከማናቸውም ታክስ ነጻ የሆኑ ያልተመደቡ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች፤ እና ኀ) አምቡላንስ እና የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎችና መሣሪያዎች ወደ ሀገር ፲፮ሺ፺፬
Copy Article
Copy Citation
Share Link
Article navigation
Previous article
Article 1
Next article
Article 3
Article 6
Reverse Charged Supply
Article 7
Taxable Activity
Article 8
Imposition of Value Added Tax
Article 9
Zero-Rated Supply
Article 10
Exempt Supply
Article 11
Exempt Import
Article 12
Compulsory Registration
Article 13
Voluntary Registration
Article 14
Registration
Article 15
Obligations of Registered Person
Article 16
Notification in Case of Registered Person
Article 17
Application for Cancellation of
Article 18
Obligations of Person on Cancellation of
Article 19
Deemed Taxable Supply on Cancellation
Article 20
Mixed Supplies
Article 21
Time of Supply
Article 22
Value of a Supply
Article 23
Supply of Goods in Ethiopia
Article 24
Supply of Services in Ethiopia
Article 25
Supply of Remote Services Through an
Article 26
Time of Import
Article 27
Value of an Import
Article 28
Deferral of VAT on Imported Capital
Article 29
Input Tax Credit Allowed
Article 30
Denial of an Input Tax Credit
Article 31
Input Tax Credit for Newly Registered
Article 32
Self-Supplies
Article 33
Supplies of Second-Hand Goods
Article 34
Gambling Supplies
Article 35
Forfeited Deposits
Article 36
Supplies of Rights, Options, and Vouchers
Article 37
Vouchers for Unspecified Supplies
Article 38
Prepaid Supplies of Telecommunications
Article 39
Employee Benefits
Article 40
General Insurance
Article 41
Supplies Made by or to Agents
Article 42
Supply of Goods of a Debtor
Article 43
Adjustment Event Resulting in VAT
Article 44
Adjustment Event Resulting in VAT
Article 45
Adjustment for Bad Debts
Article 46
፲፮ሺ፶፱
Article 47
Net VAT Payable for an Accounting
Article 48
Carry Forward of Excess Input Tax
Article 49
Refund of Excess Input Tax Credit
Article 50
Interest Payable on Late Payment of
Article 51
Refunds for Diplomatic Missions;
Article 52
Tax Invoices
Article 53
Credit and Debit Notes
Article 54
Requests for VAT Documentation
Article 55
Maintenance of VAT Documentation
Article 56
VAT Documentation for Supplies
Article 57
Application of Tax Administration
Article 58
የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቂያ
Article 59
Due Date for Payment of VAT
Article 60
Collection of VAT on Imports
Article 61
Assessment of Recipient of a Supply
Article 62
VAT Withholding
Article 63
Restriction on Registration of Certain
Article 64
Compliance by Foreign Service Provider
Article 65
Persons Liable for Reverse Charged VAT
Article 66
VAT Penalties
Article 67
Branches and Divisions
Article 68
VAT-Inclusive Pricing
Article 69
Death, Insolvency, or Bankruptcy of
Article 70
VAT Avoidance Schemes
Article 71
Currency Translation
Article 72
Power to Issue Regulations and Directives
Article 73
Repealed and Inapplicable Laws
Article 74
Transitional Provisions
Article 75
Effective Date
Choose an article to open it.