English
The Digital Identification System shall have
the following Objectives: -
1/ To contribute to the protection of human
rights and the improvement of good
governance by ensuring that residents’
right to be easily identified when they
move from place to place in the country;
2/ To establish a Digital Identification
System that allows easy identification of
individuals who want to receive services,
to build trust between service providers
and service recipients, and prevent illegal
activities;
3/ To address duplication of efforts in the
preparation of national policies,
strategies, plans and in undertaking
development activities; thereby reducing
resource wastage and enhancing
inclusiveness;
4/ To collect demographic and biometric
data of residents by establishing a system
that is consistent at the national level,
which is not limited by sector or regional
states and to serve as a source of
identification system for other
governmental and non-governmental
entities; to ensure the transition of
service-oriented identifications to a
Digital Identification System.
አማርኛ
የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚከተሉት
ዓላማዎች ይኖሩታል፡፩/ ነዋሪዎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ሲንቀሳቀሱ
በቀላሉ የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ
በማድረግ ለሰብአዊ መብቶች አከባበር እና ለመልካም
አስተዳደር መሻሻል አስተዋፅኦ ማድረግ፤
፪/ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ግለሠቦችን በቀላሉ
ለመለየት የሚያስችል የዲጂታል መታወቂያ
ሥርአት በመዘርጋት በአገልግሎት ሰጪ እና
አገልግሎት ተቀባይ መካከል እምነት አንዲጎለብት
ማድረግ፣ ሕገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል፤
፫/ ሀገር አቀፍ የዲጂታል መታወቂያ ሥርአት ሀገራዊ
ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች ሲቀረፁ እና
የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን መቅረፍ፤
በዚህም የሃብት ብክነትን መቀነስ እና አካታችነትን
ማጎልበት፤
፲፬ሺ፯፻፳፩
፬/ የዜጎችን የዲሞግራፊክ እና ባዮሜትሪክ መረጃ
ለመሰብሰብ የሚያስችል አንዲሁም፤ በዘርፉም ሆነ
በክልል አደረጃጀት ያልተገደበ በብሔራዊ ደረጃ
ተናባቢ የሆነ ሥርአት በመዘርጋት፤ ለሌሎች
መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት
የመታወቂያ ሥርአት የመረጃ ምንጭ ሆኖ
ማገልገል፤ አገልግሎት ተኮር የሆኑ የመታወቂያ
ሥርአቶች ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርአት
እንዲሸጋገሩ ማጠናከር።