English
1/ The owner of any Personal Data
collected for the Digital Identification
System is the Registrant; Hence any
authentication processes under the
Digital Identification System shall be
done with the consent of the Registrant.
2/ The Institution shall ensure that, the
confidentiality of Personal Data is
maintained in the course of collecting,
registering, authenticating, storing, and
processing of the same.
3/ Data collected in accordance with the
principles set out in Article 6 Sub
Article
(3) of this Proclamation; no
information shall be collected for the
Digital Identification System other than
those necessary to identify Residents
and have direct support to the system.
4/ Any person may not collect, distribute,
print, use, provide data or transfer a copy
to a third party or body or disclose data
collected with Digital Identification
System without the Registrant’s consent.
5/ It is prohibited to disclose, transfer or
modify the Personal Data of any
Registrant, collected under the Digital
Identification System in accordance with
the Rules and Regulations without the
Registrant’s consent.
6/ Notwithstanding the Provisions of Sub
Article
(5) of this Article, the data may be
disclosed or transferred to the relevant
legal entity authorized by law or by court
order.
7/ Summarized demographic reports and
statistical data which will not disclose
Personal Data collected with in digital
identification system may be shared to
legally authorized parties in accordance
with the procedures of the Institution.
8/ Personal Data transmitted to a Relying
አማርኛ
፩/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰበ
ማንኛውም የተመዝጋቢ ግላዊ መረጃ ባለቤት
ተመዝጋቢው በመሆኑ፤ በማንኛውም የዲጂታል
መታወቂያ አሠራር ሥርዓት ውስጥ
አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚደረጉ የማረጋገጥ
ተግባራት በተመዝጋቢው ፈቃድ መደረግ
አለባቸው::
፪/ ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚገቡ
መረጃዎችን በመሰብስብ፣ በመመዝገብ፣
በማረጋገጥ እና ይዞ በማቆየት ሂደት ባሉ
ተግባራት ውስጥ የተመዝጋቢ መረጃዎች
ሚስጢራዊነት የተጠበቀ እንዲሆን ተቋሙ
ማረጋገጥ አለበት::
፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀፅ
(፫) በተቀመጠው መርህ መሠረት ለዲጂታል
መታወቂያ ሥርዓት የሚሰበሰቡ መረጃዎች፤
ነዋሪዎችን በልዩ ሁኔታ ለመለየት የግዴታ
የሚያስፈልጉና ሥርዓቱን በቀጥታ ከሚደግፉ
በስተቀር ሌሎች መረጃዎች ሊሰበሰቡ
አይችሉም::
፬/ ማንኛውም ሰው ተመዝጋቢ ፈቃዱን በግልጽ
ሳይሰጥ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት
የተመዘገቡ የግል መረጃዎችን መውሰድ፣
ማሰራጨት፣ ማተም፣ መጠቀም፣ መረጃውን
መስጠት ወይም ቅጂውን ለሶስተኛ ወገኖች
ወይም አካላት መስጠት ወይም ይፋ ማድረግ
የተከለከለ ነው::
፲፬ሺ፯፻፴፪
፭/ አሠራርና ሕግን ጠብቆ በዲጂታል መታወቂያ
ሥርዓት ለተሰበሰበ የማንኛውም ተመዝጋቢ
ግላዊ መረጃ ያለ ተመዝጋቢው ፈቃድ ለሌላ
ሰው መግለጽ፣ ማስተላለፍም ሆነ እንዲለወጥ
መፍቀድ የተከለከለ ነው::
፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፭) ላይ የተደነገገው
ቢኖርም፣ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው ወይም
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት የግል መረጃው
ለሚመለከተው ሕጋዊ አካል ሊገለጽ ወይም
ሊተላለፍ ይችላል::
፯/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ ግላዊ
መረጃን የማያጋልጡ የተጨመቁ ዲሞግራፊክ
ሪፖርቶች እና የስታትስቲክስ መረጃዎችን በሕግ
ለተፈቀደላቸው አካላት በተቋሙ አሠራር
መሠረት ሊሰጡ ይችላሉ::
፰/ ከዲጂታል መታወቂያ ቋት አሠራሩን ጠብቆ
ለተጠቃሚ አካላት የተላለፈ የተመዝጋቢ መረጃ
የሚያገለግለው ወይም ጥቅም ላይ የሚውለው
ለተፈለገው አገልግሎት ብቻ ሲሆን፤ መጀመሪያ
ከተላለፈበት ዓላማ ባልወጣ መልኩ ተጠቃሚው
አካል ይህንን መረጃ በራሱ ቋት ውስጥ
ማስቀመጥና ለራሱ አገልግሎት ብቻ መጠቀም
ይችላል::
፱/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፯) የተጠቀሰው
እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ተጠቃሚ አካላት
በተመዝጋቢው ፈቃድ ያገኙትን መረጃ፣
መረጃውን ከወሰዱበት ዓላማ ውጪ ለራሳቸው
መጠቀምም ሆነ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ
መስጠት የተከለከለ ተግባር ነው::
፲፬ሺ፯፻፴፫
፲/ በምዝገባ ወቅት በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት
የሚዘጋጅ የተመዝጋቢውን ሙሉ ፈቃድ፣
መብት እና ግዴታዎች የሚገልፅ የፈቃደኝነት
ቅፅ በተመዝጋቢው መሞላትና መፈረም
አለበት።
፲፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፲) ላይ የተጠቀሰው
እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በምዝገባ ወቅት ለተመዝጋቢ
ምስክር ሆኖ ለሚቀርብ ሰው፤ በተቋሙ
የሚዘጋጅ የምስክሩን ሙሉ ፈቃድ፣ መብት እና
ግዴታዎች የሚገልፅ የፈቃደኝነት ቅፅ በምስክር
መሞላትና መፈረም አለበት፤ የምስክሩ ልዩ
ቁጥር ወይም የምዝገባና የማንነት ማረጋገጫ
ሰነዶች በቅጹ ላይ መሞላት እና በዲጂታል
መታወቂያ ሥርዓቱ ተመዝግቦ መያዝ አለበት።
፲፪/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ
መረጃዎች ከተለያዩ የተፈጥሯዊም ሆነ ሰው
ሰራሽ አደጋ፣ የኤሌክትሮኒክ መንገዶችን
በመጠቀም ከሚደርሱ ጥቃቶች፣ ከስርቆት፣
ከመጭበርበር እና መሰል የወንጀል ጥፋቶች
የሚከላከል ደኅንነቱ የተጠበቀ የሕግና
አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት እንዲሁም
ጠንካራ የቴክኒክና የደኅንነት ሥርዓት
መተግበር አለበት።
፲፫/ ለዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ የግል
መረጃዎች፣ ለአጠቃቀም አመቺ በሆነ አኳኋን
በሥርዓት ተደራጅተው ተቋሙ
በሚያስተዳድረው የመረጃ ቋት ውስጥ መቀመጥ
አለባቸው።
፲፬ሺ፯፻፴፬