English
1/Any Relying Party that wants to put Digital
Identification as a mandatory requirement
to provide service shall get approval from
the concerned regulator.
2/ Relying Parties may receive a Registrant's
Personal Data from the Institution or other
Authentication Service Providers
authorized by the Institution, to
authenticat the individual’s identity based
on the consent of the Registrant.
3/ Any Registrant that needs to access
Digital Identification based services, can
get Authentication Services from the
Relying Parties.
4/ Notwithstanding to Sub Article
(2) of this
Article Relying Parties shall obtain
authorization from the Institution before
they start providing service.
5/ Notwithstanding to Sub Article
(2) and
Sub Article
(4) of this Article, if the
Relying Parties can not obtain Data of
the Registrant from the Institution, they
have the right to give service using their
own other method.
6/ The duration of the retention period for
Personal Data by a Relying Party shall be
specified by a Directive of the Digital
Identification Institution.
አማርኛ
፩/ ማንኛውም ተጠቃሚ አካል ለነዋሪው ለሚሰጠው
አገልግሎት የዲጂታል መታወቂያ እንደ
አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ የሚያደርግ አሠራር
ለመዘርጋት ከሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል
ፈቃድ ማግኘት አለበት::
፪/ ተጠቃሚ አካላት በተመዝጋቢው ፈቃድ ላይ
ተመስርተው የግለሰብ ማንነትን ለማረጋገጥ
የሚያስፈልጋቸውን መረጃ ከተቋሙ ወይም
ተቋሙ ከወከለው አረጋጋጭ አካል ማግኘት
ይችላሉ::
፫/ ማንኛውም ተመዝጋቢ፣ በዲጂታል መታወቂያ
ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶችን ማግኘት
ሲፈልግ፣ በተጠቃሚ አካላት በኩል የማረጋገጥ
አገልግሎት ማግኘት ይችላል::
፬/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ
(፪) የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠቃሚ አካላት አገልግሎት
መሥጠት ከመጀመራቸው በፊት ከተቋሙ
ፈቃድ ማግኘት አለባቸው::
፭/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ
(፪) እና ንዑስ
አንቀጽ
(፬) የተጠቀሰው ቢኖርም ተጠቃሚ
አካላት የተመዝጋቢ መረጃን ትክክለኛነት
ከአረጋጋጭ አካል ማግኘት በማይችሉበት
ወቅት፤ የራሳቸውን ሌላ አማራጭ ተጠቅመው
አገልግሎት የመሥጠት መብታቸው የተጠበቀ
ነው::
፲፬ሺ፯፻፴
፮/ ተጠቃሚ አካላት ከዲጂታል መታወቂያ
የማረጋገጥ ሥርዓት ያገኙትን መረጃ ይዘው
ማቆየት የሚችሉበትን የጊዜ ገደብን በተመለከተ
ተቋሙ በመመሪያ ይወስናል።