ይህ አዋጅ “የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፹፬/፪ሺ፲፭” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። This Proclamation may be cited as “Ethiopian Digital Identification Proclamation No. 1284/2023.”
፩/ “መሠረታዊ መታወቂያ” ማለት በአንድ ነዋሪ ልዩ ማንነት ላይ በመመስረት አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል ሕጋዊ መለያ ነው፤ ፪/ “የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት” ማለት የዲሞግራፊክ እና ባዮሜትሪክ መረጃ መዝግቦ በማዕከላዊ ቋት በመያዝና ለእያንዳንዱ ነዋሪ ልዩ ቁጥር በመሥጠት የተደራጀ እና አስተማማኝ መሠረታዊ የመታወቂያ ሥርዓት ነው፤ ፫/ “የዲጂታል መታወቂያ” ማለት በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ውስጥ ለተመዘገበ ነዋሪ የሚሰጥ ልዩ ቁጥር ያለው መለያ ነው፤ ፬/ “የህፃናት ዲጂታል መታወቂያ” ማለት በተቋሙ አሠራር መሠረት የሚወሰንና ለአካለ መጠን ላልደረሰ ህፃን ያለ ባዮሜትሪክ መረጃ የሚሰጥ ልዩ ቁጥር ያለው ጊዜያዊ የዲጂታል መታወቂያ ዓይነት ነው፤ ፭/ “ባዮሜትሪክ መረጃ” ማለት የጣት አሻራ፣ የዐይን ብሌንና የፊት ገፅታ ምስልን በስሌት ለመያዝ የሚቻሉ የአንድ የተፈጥሮ ሰው ልዩ የሰውነት አካላዊ መለያዎች ናቸው፤ ፲፬ሺ፯፻፲፯ ፮/ “የዲሞግራፊክ መረጃ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ የተጠቀሱት ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚገቡ የተመዝጋቢ መረጃዎች ሲሆኑ የባዮሜትሪክ መረጃን አይጨምርም፤ ፯/ “ልዩ ቁጥር” ማለት በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ውስጥ አንድ ነዋሪ ስኬታማ የባዮሜትሪክ እና የዲሞግራፊክ መረጃዎችን ምዝገባን ሲያጠናቅቅ ለተመዝጋቢ የሚሰጥ ልዩ፣ ተደጋጋሚ ያልሆነ ቁጥር ሲሆን፤ በልዩ ሁኔታ ተቋሙ በሚሰጠው ውሳኔ ካልሆነ በስተቀር፤ አንድ ጊዜ ለተመዝጋቢ ከተሰጠ የማይለወጥ ቋሚ ቁጥር ነው፤ ፰/ “ተለዋጭ ቁጥር’’ ማለት ከዲጂታል መታወቂያ ጋር በሚስጥራዊ ሁኔታ የተያያዘ፤ የተመዝጋቢን ግላዊነት ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ ከዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ አንድም ሆነ ከዛ በላይ ሊፈጠር የሚችል ልዩ ቁጥር ነው፤ ፱/ ‘‘ተቋም’’ ማለት የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን የሚያስተገብርና ይህንን አዋጅ የሚያስፈጽም መንግሥታዊ የዲጂታል መታወቂያ ተቋም ወይም እንደአስፈላጊነቱ ለሥራው አግባብነት ያለው መንግሥታዊ ተቋም ውስጥ የሚደራጅ ጽህፈት ቤት ሊሆን ይችላል፤ ፲/ “ነዋሪ” ማለት በፍትሐብሄር ሕጉ አንቀጽ ፩፻፸፬ እና ፩፻፸፭ የተመለከተውን የመኖሪያ ቦታ መስፈርት በሚያሟላ አግባብ በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖር ወይም አግባብ ባለው ሕግ መሠረት በሚመለከተው አካል ፈቃድ አግኝቶ የሚኖር የተፈጥሮ ሰው ነው፤ ፲፬ሺ፯፻፲፰ ፲፩/ “ተመዝጋቢ” ማለት የዲሞግራፊክ እና የባዮሜትሪክ መረጃ በመስጠት፣ ምዝገባ አከናውኖ የዲጂታል መታወቂያ የሚሰጠው ነዋሪ የሆነ ሰው ነው፤ ፲፪/ “መዝጋቢ አካል” ማለት የዲጂታል መታወቂያ ተቋም ወይም በተቋሙ በሚሠጥ ፈቃድ ወይም ውክልና መሠረት የተመዝጋቢን መረጃ የሚሰበስብ ሰው ነው፤ ፲፫/ “ምዝገባ” ማለት ከመዝጋቢ አካል ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ የተላከ የተመዝጋቢ መረጃን ልዩ በሆነ ሁኔታ በማረጋገጥ የመመዝገብ ሂደት ነው፤ ፲፬/ “ተጠቃሚ አካል” ማለት ከዲጂታል መታወቂያ ተቋም እና ከግለሰቡ በተሰጠ ፈቃድ እና መረጃ ላይ ተመሥርቶ የግለሰብ ማንነትን የሚያረጋገጥ ሰው ነው፤ ፲፭/ “ማረጋገጥ’’ ማለት ከዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ማእከላዊ መረጃ ቋት ጋር ቀጥታ በኔትዎርክ ወይም ያለኔትዎርክ በማመሳከር የግለሰብን ማንነት የማጣራትና ማረጋገጫ የመስጠት ሂደት ነው፤ ፲፮/ “አረጋጋጭ አካል’’ ማለት የዲጂታል መታወቂያ መረጃዎች ከተጠቃሚ አካል በሚቀርብ ጥያቄ የማረጋገጥ አገልግሎት የሚሰጥ ሰው ነው፤ ፲፯/ “የግል መረጃ” ማለት በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚሰበሰቡ የባዮሜትሪክ እና በዚህ አዋጅ አንቀፅ ፱ ላይ የተመለከቱት የዲሞግራፊክ መረጃዎች ናቸው፤ ፲፬ሺ፯፻፲፱ ፲፰/ “ጥንቃቄ የሚፈልግ የግል መረጃ” ማለት:- ሀ) ብሔርን፣ ለ) የዘረመልን፣ ሐ) የአካላዊ ወይም የአዕምሯዊ ጤንነት ወይም ሁኔታን፣ መ) የፖለቲካ አመለካከትን፣ ሠ) ሃይማኖትን ወይም ሌላ ሃይማኖት ነክ አስተሳሰብን፣ ረ) የተፈጸመ ወይም ተፈጸመ የተባለ ወንጀልን፤ ሰ) የተፈጸመ ወይም ተፈጸመ የተባለ ወንጀልን አስመልክቶ የተካሄዱ ሂደቶችን፣ እነዚህ ሂደቶች የተጠናቀቁበት መደምደሚያን ወይም በሂደቶቹ ዙሪያ ፍርድ ቤቶች የሰጡት የቅጣት ውሳኔን፣ ሸ) በተቋሙ ወይም ሌሎች ሥልጣን ባላቸው ተቋማት የሚወሰኑ ጥንቃቄ የሚፈልጉ የግል መረጃዎችን ሊጨምር ይችላል:: ፲፱/ “የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ” ማለት ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ወይም ተለዋጭ ቁጥርና የተመዝጋቢ መረጃ የያዘ በቁሳዊ ወይም በዲጂታል አማራጭ የሚዘጋጅ የሰነድ ማስረጃ ነው፤ ፳/ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ መሠረት የተቋቋመ ክልል ሲሆን ለዚህ አዋጅ ዓላማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ይጨምራል፤ ፲፬ሺ፯፻፳ ፳፩/ “መንግሥት” ማለት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ሲሆን ለዚህ አዋጅ ዓላማ የክልሎች አስተዳደሮችንም ያካትታል፤ ፳፪/ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤ ፳፫/ በዚህ አዋጅ ውስጥ በወንድ ፆታ የተገለፀው የሴትንም ፆታ ይጨምራል። Unless the context requires otherwise in this Proclamation: 1/ “Foundational Identification” means a legal identifier that enables Resident to access sesrvices by making use of his unique identity; 2/ “Digital Identification System” means an organized and reliable Foundational Identification system that provides a Unique Number to each Resident by collecting Demographic and Biometric Data in a central database; 3/ “Digital Identification” means a Foundational Identification with a Unique Number that is issued to a resident that is registered on the Digital Identification System; 4/ “Minor Digital Identification” is a type of temporary Digital Identification issued without collecting Biometric Data to a minor as defined per the guidelines of the Institution; 5/ “Biometric Data’’ means physical attributes that can be computed off of a natural person such as fingerprints, iris and facial photo used for unique calculation of a person’s identity; 6/ “Demographic Data’’ means the non- biometric personal attributes of a resident entered into the Digital Identification System, referred in Article 9 of this Proclamation; 7/ “Unique Number” means a special, and non-repeating number issued to a Registrant by the Digital Identification System after a successful registration of Biometric and Demographic Data and once issued, it is permanent unless in exceptional circumstances defined by the Institution; 8/ “Alias Number” is a Unique Number generated one or more times from the Digital Identification System to be securely and privately associated with the unique Digital Identification of the Resident; 9/ “Institution’’ means a Govenmental Digital Identification entity that will implement the Digital Identification System and execute this Proclamation or it may be an office established within a relevant Government body; 10/ “Resident” means a natural person living in Ethiopia fulfilling the requirement of residence place provided in Article 174 and 175 of the Civil Code or living in Ethiopia by obtaining residence permit from relevant authority; 11/ “Registrant” means a resident person who receives a Digital Identification after providing his Demographic and Biometric data; 12/ “Registrar” means the Digital Identification Institution or a person entrusted by the Institution to collect the individuals’ data; 13/ “Registration’’ means the process of enrolling a Registrant, through a unique deduplication process of personal data sent by the Registrar to the Digital Identification System; 14/ “Relying Party” means a person that authenticates an individual's identity, with the knowledge and consent of the Digital Identification Institution and the individual; 15/ “Authentication”means the process of verifying and authenticating, whether online or offline, the identity of an individual against the registered information in the Digital Identification System central database; 16/ “Authentication Service Provider’’ means a person that responds to a request for authentication of Digital Identification Data at the inquiry of a Relying Party; 17/ “Personal Data” means Biometric Data collected with the Digital Identification System and Demographic Data indicated under Article 9 of this Proclamation; 18/ “Sensitive Personal Data” means data on a natural person: a) racial or ethnic origins, b) genetic data, c) physical or mental health or condition, d) political opinion, e) religious beliefs or other beliefs of a similar nature, f) the commission or alleged commission of an offense, g) any proceedings for an offense committed or alleged to have been committed, the disposal of such proceedings or the sentence of any court in the proceedings, h) any other personal data as the Institution or other authorized entities may determine to be sensitive personal data. 19/ “Digital Identification Credential’’ means a physical or Digital documentary evidence containing Personal Data and either the Unique Identification Number or Alias Number; 20/ “Region” means a Region established in accordance with Article 47 of the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and for the purpose of this Proclamation, it includes Addis Ababa City Administration and Dire Dawa City Administration; 21/ “Government” means the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia; and for the purpose of this Proclamation, it includes Regional Administrations; 22/ “Person” means any natural or Juridical person; 23/ In this Proclamation, any phrase expressed with a masculine gender includes the feminine gender.
ይህ አዋጅ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ በማንኛውም ሰው ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። This Proclamation shall be applicable on any person in Ethiopia.
፩/ ነዋሪዎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ሲንቀሳቀሱ በቀላሉ የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ በማድረግ ለሰብአዊ መብቶች አከባበር እና ለመልካም አስተዳደር መሻሻል አስተዋፅኦ ማድረግ፤ ፪/ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ግለሠቦችን በቀላሉ ለመለየት የሚያስችል የዲጂታል መታወቂያ ሥርአት በመዘርጋት በአገልግሎት ሰጪ እና አገልግሎት ተቀባይ መካከል እምነት አንዲጎለብት ማድረግ፣ ሕገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል፤ ፫/ ሀገር አቀፍ የዲጂታል መታወቂያ ሥርአት ሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች ሲቀረፁ እና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን መቅረፍ፤ በዚህም የሃብት ብክነትን መቀነስ እና አካታችነትን ማጎልበት፤ ፲፬ሺ፯፻፳፩ ፬/ የዜጎችን የዲሞግራፊክ እና ባዮሜትሪክ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል አንዲሁም፤ በዘርፉም ሆነ በክልል አደረጃጀት ያልተገደበ በብሔራዊ ደረጃ ተናባቢ የሆነ ሥርአት በመዘርጋት፤ ለሌሎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት የመታወቂያ ሥርአት የመረጃ ምንጭ ሆኖ ማገልገል፤ አገልግሎት ተኮር የሆኑ የመታወቂያ ሥርአቶች ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርአት እንዲሸጋገሩ ማጠናከር። The Digital Identification System shall have the following Objectives: - 1/ To contribute to the protection of human rights and the improvement of good governance by ensuring that residents’ right to be easily identified when they move from place to place in the country; 2/ To establish a Digital Identification System that allows easy identification of individuals who want to receive services, to build trust between service providers and service recipients, and prevent illegal activities; 3/ To address duplication of efforts in the preparation of national policies, strategies, plans and in undertaking development activities; thereby reducing resource wastage and enhancing inclusiveness; 4/ To collect demographic and biometric data of residents by establishing a system that is consistent at the national level, which is not limited by sector or regional states and to serve as a source of identification system for other governmental and non-governmental entities; to ensure the transition of service-oriented identifications to a Digital Identification System.
በዚህ አዋጅ መሠረት የዲጂታል መታወቂያን ሥርዓት በተመለከተ የተደነገጉ ተግባርና ኃላፊነቶችን የሚያስፈፅም ተቋም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሠረት ይቋቋማል ወይም እንደአስፈላጊነቱ ለሥራው አግባብነት ያለው መንግሥታዊ ተቋም ውስጥ ሊደራጅ ይችላል። The Council of Ministers may establish by Regulation an Institution to implement the powers and responsibilities of the Digital Identification System stipulated in this Proclamation or it may be established within a relevant Government body as the case may be.
፩/ አካታችነት፤ ፪/ አስተማማኝነት፤ ፫/ የተመጠነ መረጃ፤ ፬/ የተናባቢነት፤ ፭/ ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት፤ ፮/ ቴክኖሎጂ መር። ፲፬ሺ፯፻፳፪ Digital Identification System shall abide by the following principles: 1/ Inclusiveness; 2/ Infallibly; 3/ Data minimization; 4/ Interoperability; 5/ Transparency and accountability; 6/ Technology lead.
ማንኛውም ዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት የባዮሜትሪክና ዲሞግራፊክ መረጃ በመስጠት የተመዘገበ ነዋሪ ዲጂታል መታወቂያ የማግኘት መብት አለው። Any resident who registered for Digital Identification by giving his biometric and demographic data shall have the right to get Digital Identification.
፩/ ተቋሙ ወይም መዝጋቢው አካል ማንኛውም ነዋሪ ለምዝገባ በሚያመለክትበት ጊዜ ቀደም ሲል አመልካቹ ዲጂታል መታወቂያ ያልተሰጠው መሆኑን የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት፤ ፪/ ተቋሙ ወይም መዝጋቢው አካል የተመዝጋቢው የግል መረጃን ለማረጋገጥ የሚያገለግሉ የመታወቂያ ሰነዶች እና ሌሎች በተቋሙ ተቀባይነት ባላቸው ሰነዶች ወይም የሰው ምስክር ማስረጃዎችን በመጠቀም በማረጋገጥ መመዝገብ ይኖርበታል። ዝርዝሩ ተቋሙ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል። 1/ When any Resident applies for registration, the Institution shall ensure that the applicant has not given Digital Identification before; 2/ The Institution or Registrar entity shall verify and register the personal data of the Registrant using identification documents and other documents acceptable by the Institution or witnesses. The details shall be decided by Directive to be issued by the Institution.
፩/ ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚገባ የግል መረጃ የእያንዳንዱን ተመዝጋቢ የዲሞግራፊክ መረጃ እና ባዮሜትሪክ መረጃን ያካተተ መሆን አለበት፤ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ የተደነገገው ጠቅላላ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚከተሉትን የዲሞግራፊክ መረጃዎች ማካተት አለበት፦ ሀ) ስም፣ የአባት ስም፣ የአያት ስም ወይም በዚህ መልክ የተደራጀ ሕጋዊ ስም ለሌለው ተመዝጋቢ ተቋሙ ተመዝጋቢው በአካባቢው ማህበረሰብ በሚጠራበት ስም ይመዘግበዋል፤ ፲፬ሺ፯፻፳፫ ለ) ዜግነት፤ ሐ) የትውልድ ቀን፣ ወር እና ዓመት፤ መ) ፆታ፤ ሠ) መኖሪያ አድራሻ። ፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ጥንቃቄ የሚፈልግ የግል መረጃን ሳይጨምር የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚከተሉትን መረጃዎች እና ሌሎችም በአማራጭነት ሊይዝ ይችላል፡ሀ) የእናት ሥም፤ ለ) ስልክ ቁጥር፤ ሐ) የኢሜይል አድራሻ፤ መ) ፖስታ አድራሻ። ፬/ አንድ ተመዝጋቢ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ መሠረት የተዘረዘሩ የመታወቂያ ሰነድ ማስረጃዎች ማቅረብ በማይችልበት እና በምስክር በሚመዘገብበት ጊዜ ምስክሩ:- ሀ) ልዩ ቁጥር ያለው፣ ወይም ለ) በዲጂታል መታወቂያ ሥርአት የተመዘገበ መሆን አለበት። ፭/ ስለ ባዮሜትሪክ መረጃ ምዝገባ ሀ) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአካል ጉዳት ወይም በሌላ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ተመዝጋቢው ሌሎች ባዮሜትሪክ መረጃ መስጠት አለመቻሉ በመዝጋቢው አካል ከተረጋገጠ፣ የፊት ገፅታ ፎቶግራፍ ብቻ በመመዝገብ ዲጂታል መታወቂያ ሊሰጥ ይችላል፤ ፲፬ሺ፯፻፳፬ ለ) በዚህ ንዑስ አንቀፅ ፊደል ተራ (ሀ) የተጠቀሰው አንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአካል ጉዳት ምክንያት ተመዝጋቢው ሌሎች ባዮሜትሪክ መረጃ መስጠት አለመቻሉ በተቋሙ ከተረጋገጠ፤ ከፊት ገፅታ ፎቶግራፍ ውጪ ሌላ የባዮሜትሪክ መረጃ አስገዳጅ መሆን አይኖርበትም፤ ሐ) በጤና፣ በዕድሜ ወይም በሌላ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መዝጋቢው አካል ምዝገባ በሚያደርግበት ቦታ መምጣት የማይችሉ ተመዝጋቢዎችን ባሉበት ቦታ ወይም አመቺ በሆነ ቦታ በመገኘት መዝጋቢው አካል ምዝገባ ሊያደርግ ይችላል፤ መ) የግል መረጃ ተቋሙ በሚያወጣው መመሪያ በሚወሰነው የጊዜ ገደብ መሠረት መታደስ ይኖርበታል፤ ሠ) የዚህ ንዑስ አንቀፅ ዝርዝር አፈፃፀም ተቋሙ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል። 1/ Personal Data pushed to the Digital Identification System shall consist of Demographic and Biometric Data of each Registrant; 2/ Without prejudice to Sub Article (1) of this Article, Digital Identification System shall consist of the following Demographic Data: a) First Name, Father’s Name, Grandfather’s Name or when the Registrant does not have such legal name, the Institution may collect the name of the Registrant which is known by the local community; b) Nationality; c) Date of birth, month and year; d) Gender; e) Domicile Address. 3/ Without prejudice Sub-Article (2) of this Article, with the exception of sensitive Personal Data, additional personal data may be collected including, but not limited to: a) Mother's name; b) Phone number; c) Email address; d) Postal Address. 4) Pursuant to Article 8 of this Proclamation; if the Registrant fails to submit the required proof of identity, he may present an individual witness who: a) has a Unique Number, or b) is Registerd in the Digital Identification System. 5) Registration of Biometric Data a) without prejudice to Sub Article (1) of this Article, if it is confirmed by the Registrar that the Registrant can not give Biometric Data because of physical injury or due to a reason beyond capacity, Digital Identification may be provided by registering facial photograph; b) Without prejudice to Pharagraph (a) of this Sub Article, if it is attested by the Institution that the Registrant can not give other Biometric Data due to physical injury, other Biometric data except facial photo shall not be mandatory; c) The Registrar may register Registrants who can not appear at the registration place due to health, age or due to other reason beyond capacity at their place or any other convenient place; d) Personal Data shall be renewed with in time interval decided by Directive to be issued by the Institution; e) The detail implementation of this Sub Article shall be decided by Directive to be issued by the Institution.
በዚህ አዋጅ አንቀፅ ፯ እንዲሁም አንቀፅ ፱ ንኡስ አንቀፅ (፩) ላይ የተደነገገው ቢኖርም፤ ለህፃናት የዲጂታል መታወቂያ ሥርአት ላይ ለመመዝገብ፤ በሥርአቱ ላይ የተመዘገበ ወላጅ፤ አሳዳጊ፤ ሕጋዊ ሞግዚት ወይም ሌላ ማንኛውም ሕጋዊ አካል በኩል የህፃኑን ዲሞግራፊክ መረጃ ብቻ በመመዝገብ ህፃኑ መታወቂያውን መውሰድ ይችላል። ፲፬ሺ፯፻፳፭ Identification for Minors Notwithstanding to Article 7 and Article 9 Sub Article (1) of this Proclamation, minors can be registered upon giving the Demographic Data by a registered parent, caretaker, legal guardian or any legal body who can take responsibility to the minor and such person may take Digital Identification.
፩/ መዝጋቢው አካል በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ የተዘረዘሩትን የተመዝጋቢ መረጃዎች መዝግቦ ወደ ሥርዓቱ ካስገባ በኋላ፣ ተቋሙ አንድ ነዋሪ ከሌላ ነዋሪ በልዩነት እና በአስተማማኝነት ለመለየት የሚያስችል ልዩ ቁጥር ለእያንዳንዱ ተመዝጋቢ መስጠት ይኖርበታል፤ ፪/ ልዩ ቁጥሩ ኤሌክትሮኒክ በሆነ ሥርዓትና በሚስጥራዊ መንገድ የሚመነጭ ሲሆን ከቁጥሩ ጀርባ ያለውን ዝርዝር መረጃ እና ግላዊነት የሚጠብቅ ይሆናል፤ ፫/ አንድ ልዩ ቁጥር ለአንድ ተመዝጋቢ ብቻ የሚሰጥ ሲሆን፤ ይህ ልዩ ቁጥርም በቋሚነት ሳይቀየር ከተመዝጋቢው ጋር ይተሳሰራል፤ ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተጠቀሰው ልዩ ቁጥር እንደተጠበቀ ሆኖ በተቋሙ አሠራር ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች፣ በተለየ መልኩ ወይም በተመዝጋቢው ፍላጎት፣ ከልዩ ቁጥር ጋር በሚስጥራዊ ሁኔታ የተያያዙ፣ የተመዝጋቢን ግላዊነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ፣ የራሳቸው ጊዜ ገደብ ያላቸው፣ ልዩ ቁጥሩን ተክተው መሥራት የሚችሉ ተለዋጭ ቁጥሮች ማመንጨት ይቻላል፤ ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተጠቀሰው ልዩ ቁጥር የማይለወጥ ሲሆን፣ የተመዝጋቢውን የመረጃ ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል በማስረጃ ላይ የሚታተመውና በሌሎች ሁኔታዎች ጥቅም ላይ የሚውለው ቁጥር በተለዋጭ ቁጥር ሊተካ ይችላል፤ ፲፬ሺ፯፻፳፮ ፮/ የዲጂታል መታወቂያ ልዩ ቁጥር የጠፋበት ማንኛውም ሰው ልዩ ቁጥሩ ስለመጥፋቱ ለዲጂታል መታወቂያ ተቋም ወይም ተቋሙ ከወከለው አካል ተገቢውን ክፍያ በመፈፀም በተቋሙ አሠራር መሠረት ቁጥሩን መልሶ ማግኘት ይችላል፤ ፯/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በተቋሙ አሠራር መሰረት የተመዝጋቢው ሞት ከተረጋገጠ፤ ተቋሙ ልዩ ቁጥሩ ሳይቀየር እንደፀና እንዲቆይ እና ለማረጋገጥ አገልግሎት ሥራ ላይ እንዳይውል የማድረግ ሃላፊነት ይኖርበታል፤ ፰/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) ላይ ያለው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በተመዝጋቢው ፍላጎት ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የዲጂታል መታወቂያ ልዩ ቁጥር ሊቆለፍ ወይም ከሥራ ውጪ እንዲሆን ሊደረግ ይቻላል፤ ዝርዝር አፈፃፀሙ ተቋሙ በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ይሆናል። 1/ Upon collection and pushing of Personal Data to the system as described under Article 9 of this Proclamation, the Institution shall issue to each Registrant a Unique Number that uniquely differentiates that person from others; 2/ The Unique Number shall be generated by electronic means in a confidential manner, and shall preserve the security and privacy of the Personal Data behind the number; 3/ One Unique Number shall be given only to one Registrant and shall remain immutable, irrevocable and permanent; 4/ Without prejudice to the Unique Number referred to in Sub-Article (2) of this Article, Alias Numbers for different work sectors, distinctively or based on the need of the Registrant, with a set validity period meant to shield the privacy of the Unique Numbers, allowing the Registrant to receive authentication service similar to what the Unique Number enables may be generated based on the working procedure of the Institution; 5/ The Unique Number described in Sub Article (2) of this Article is immutable, hence for the purpose of protecting the privacy of the Registrant it can be replaced by an Alias Number that may be printed on Digital Identification Credentials or can be used for other purposes; 6/ Any Registrant who has lost his Unique Number may recover from the Institution or from another entity authorized by the Institution up on effecting the necessary payment based on procedures put in place by the Institution; 7) Without prejudice to Sub-Article (4) of this Article, if the death of the Registrant is confirmed by the procedures of the Institution, the Institution shall has the obligation to make the Unique Number remains immutable and ensure that the Unique Number is not used for authentication service; 8) Without prejudice to Sub Article (3) of this Article an individual’s Digital Identification Uniqe number may be locked or disabled as per his request or by a court order. The detailed procedure shall be determined by a Directive to be issued by the Instituion.
፩/ ተቋሙ እና ውክልና በተሰጣቸው አካላት የሚሰጥ ማንኛውም ዓይነት የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ የሚከተሉትን መረጃዎች መያዝ አለበት፦ ሀ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተዘረዘሩት መረጃዎች በሙሉ፤ ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ ንዑስ አንቀጽ (፭) ፊደል ተራ (ለ) ላይ የተጠቀሰውን የፊት ገፅታ ፎቶግራፍ፤ ፲፬ሺ፯፻፳፯ ሐ) ልዩ ወይም ተለዋጭ ቁጥር፤ መ) መታወቂያው የተሰጠበት እና የሚያበቃበት ቀን፤እና ሠ) ሌሎች በአንቀጽ ፱ ውስጥ ከተጠቀሱ መረጃዎች ውስጥ በተቋሙ የሚወሰኑ መረጃዎች። ፪/ የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ ዕድሳት ከባዮሜትሪክ መረጃ የእድሳት ዘመን ጋር አብሮ መሆን ይኖርበታል፤ ሆኖም የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ እስከሚታደስ ድረስ የዲጂታል መታወቂያ ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት አይቻልም፤ ፫/ የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ በተቋሙ ወይም ተቋሙ በወከላቸው አካላት ሊሰጥ ይችላል፤ ፬/ ተቋሙ የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ በሚያድስበት ጊዜ ቀድሞ የተሰበሰቡ መረጃዎች ትክክለኛነታቸውን እና የተመዝጋቢውን ማንነት ትክክለኛነት አረጋግጦ የማደስ ግዴታ አለበት፤ ፭/ ዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ የጠፋበት ወይም የተበላሸበት ማንኛውም ነዋሪ፤ መታወቂያው ስለመጥፋቱ የሚገልጽ ማስረጃ ወይም የተበላሸውን መታወቂያ በማያያዝ፤ በምትኩ ዲጂታል መታወቂያ እንዲሰጠው ለተቋሙ በማመልከት የተቋሙን አሠራር ተከትሎ መውሰድ ይችላል፤ ፲፬ሺ፯፻፳፰ ፮/ የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ ወድቆ ያገኘ ማንኛውም ሰው መታወቂያውን ወዲያውኑ ለተቋሙ ወይም በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ማስረከብ አለበት። 1/The Digital Identification Credential issued by the Institution and by other authorized entities shall contain the following personal data: a) All the Data listed under Article 9 Sub Article (2) of this Proclamation; b) facial Photograph referred to in Article 9 Sub Article (5) Paragraph (b) of this Proclamation; c) Unique or Alias Number; d) Date of issuance and date of expiry of the Digital Identification Credential; and e) Other Data provided under Article 9 of this Proclamation subject to the decision of the Institution; 2/ The Digital Identification Credential must be renewed upon the recapture of biometric data; however, if the Digital Identification Credential has expired, it shall not be used for authentication services; 3/ Digital Identification Credentials may be issued by the Institution or by other bodies mandated by the Institution; 4/ The Institution shall has the obligation to renew the Digital Identification Credential after verifying the Registrant’s Personal Data collected before; 5/ A Registrant whose Digital Identification Credential is lost or damaged can apply for a replacement and obtain a new credential upon presenting proof of loss or attaching the damaged credentials as per the procedures put in place by the Institution; 6/ Any person who finds a lost physical Digital Identification Credential shall return it to the Institution or to a nearby police station.
፩/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚመዘገቡ እና በዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ ላይ የሚገለፁ የግል መረጃዎች በፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ፣ ምዝገባ በሚካሄድበት ክልል የሥራ ቋንቋ እና በእንግሊዘኛ ይሆናል፤ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚመዘገብም ሆነ በዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ ላይ የሚወጣ መረጃ ተቋሙ በሚያወጣው መመሪያ በሚወሰነው መሰረት በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ቋንቋ ሊመዘገብ ይችላል። 1/ Personal Data collected into the Digital Identification System and displayed on Digital Identification Credentials shall be in the working languages of the Federal Government, in the working language of the Regional Government where registration is took place and in English; 2/ Without prejudice Sub Article (1) of this Article, Personal Data may be recorded and Digital Identification Credential printed in additional local language as per a Directive to be issued by the Institution. [
፩/ ማንኛውም ተመዝጋቢ ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በገቡ የግል መረጃዎች ላይ ለውጥ ሲኖር የዲጂታል መታወቂያ ለሚሰጠው አካል ማሳወቅ አለበት። ፪/ ተቋሙ ወይም መዝጋቢው አካል በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ መረጃዎች በተለያዩ ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋ ምክንያት ከጠፉ ወይም ከተበላሹ ለተመዝጋቢው ማሳወቅ እና መረጃዎቹ እንደገና እንዲሟሉ ማድረግ አለበት። [ ፲፬ሺ፯፻፳፱ Identification 1/ Any Registrant shall notify to the Institution of the changes to his Personal Data collected to the Digital Identification System after Registration. 2/ The Institution or Registrar shall notify to the Registrant and let the Registrar updtated Data collected by Digital Identification System if the Data collected are misplaced or destroyed by any natural or man made disasters.
፩/ ማንኛውም ተጠቃሚ አካል ለነዋሪው ለሚሰጠው አገልግሎት የዲጂታል መታወቂያ እንደ አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ የሚያደርግ አሠራር ለመዘርጋት ከሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል ፈቃድ ማግኘት አለበት:: ፪/ ተጠቃሚ አካላት በተመዝጋቢው ፈቃድ ላይ ተመስርተው የግለሰብ ማንነትን ለማረጋገጥ የሚያስፈልጋቸውን መረጃ ከተቋሙ ወይም ተቋሙ ከወከለው አረጋጋጭ አካል ማግኘት ይችላሉ:: ፫/ ማንኛውም ተመዝጋቢ፣ በዲጂታል መታወቂያ ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶችን ማግኘት ሲፈልግ፣ በተጠቃሚ አካላት በኩል የማረጋገጥ አገልግሎት ማግኘት ይችላል:: ፬/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፪) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠቃሚ አካላት አገልግሎት መሥጠት ከመጀመራቸው በፊት ከተቋሙ ፈቃድ ማግኘት አለባቸው:: ፭/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና ንዑስ አንቀጽ (፬) የተጠቀሰው ቢኖርም ተጠቃሚ አካላት የተመዝጋቢ መረጃን ትክክለኛነት ከአረጋጋጭ አካል ማግኘት በማይችሉበት ወቅት፤ የራሳቸውን ሌላ አማራጭ ተጠቅመው አገልግሎት የመሥጠት መብታቸው የተጠበቀ ነው:: ፲፬ሺ፯፻፴ ፮/ ተጠቃሚ አካላት ከዲጂታል መታወቂያ የማረጋገጥ ሥርዓት ያገኙትን መረጃ ይዘው ማቆየት የሚችሉበትን የጊዜ ገደብን በተመለከተ ተቋሙ በመመሪያ ይወስናል። 1/Any Relying Party that wants to put Digital Identification as a mandatory requirement to provide service shall get approval from the concerned regulator. 2/ Relying Parties may receive a Registrant's Personal Data from the Institution or other Authentication Service Providers authorized by the Institution, to authenticat the individual’s identity based on the consent of the Registrant. 3/ Any Registrant that needs to access Digital Identification based services, can get Authentication Services from the Relying Parties. 4/ Notwithstanding to Sub Article (2) of this Article Relying Parties shall obtain authorization from the Institution before they start providing service. 5/ Notwithstanding to Sub Article (2) and Sub Article (4) of this Article, if the Relying Parties can not obtain Data of the Registrant from the Institution, they have the right to give service using their own other method. 6/ The duration of the retention period for Personal Data by a Relying Party shall be specified by a Directive of the Digital Identification Institution.
፩/ የዲጂታል መታወቂያ የአንድን ነዋሪ ማንነትን ለማስረዳት ወይም ለማረጋገጥ እንደ ህጋዊ እና በቂ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ፪/ የዲጂታል መታወቂያ ተቋሙ አንዱ አረጋጋጭ አካል ቢሆንም፤ ተቋሙ በሚሰጠው ውክልና ተጨማሪ አረጋጋጭ አካላትን መሰየም ይችላል። ፫/ ማንኛውም ተመዝጋቢ የዲጂታል መታወቂያ ላይ የተመሠረተ የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት ልዩ ቁጥር ወይም ልዩ ቁጥሩን የያዘ የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ ማቅረብ አለበት። ፬/ አረጋጋጭ አካላት የግል መረጃን ለተጠቃሚ አካላት በሚያረጋግጡበት ወቅት የአገልግሎት ፍላጎትን መነሻ በማድረግ፣ ተቋሙ በሚሰጠው ፈቃድ መሠረት፣ ዝቅተኛ ተፈላጊ የግል መረጃዎችን ብቻ መስጠት ይኖርባቸዋል። ፭/ አረጋጋጭ አካላትም ሆኑ ተጠቃሚ አካላት ከዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ላገኙት የግል መረጃ ተገቢ ጥበቃና ደኅንነት የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው። ፲፬ሺ፯፻፴፩ Usage 1/ Digital Identification may be taken as a legal and sufficient evidence to proof or authenticate a Resident’s identity. 2/ Though the Institution is one of the authentication service providers, It may authorize an additional authentication service providers. 3/ Any Registrant that wants to receive Digital Identification based Authentication Service shall present Unique Number or a Digital Identification Credential with its Unique Number. 4/ When the Authentication Service Providers authenticat personal data, they shall provide only minimal necessary level of personal data based on the needs of the Relying party as authorized by the Institution; 5/ Authentication Service Providers as well as Relying Parties shall ensure the safety and security of the Personal Data they received from the Digital Identification System.
፩/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰበ ማንኛውም የተመዝጋቢ ግላዊ መረጃ ባለቤት ተመዝጋቢው በመሆኑ፤ በማንኛውም የዲጂታል መታወቂያ አሠራር ሥርዓት ውስጥ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚደረጉ የማረጋገጥ ተግባራት በተመዝጋቢው ፈቃድ መደረግ አለባቸው:: ፪/ ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚገቡ መረጃዎችን በመሰብስብ፣ በመመዝገብ፣ በማረጋገጥ እና ይዞ በማቆየት ሂደት ባሉ ተግባራት ውስጥ የተመዝጋቢ መረጃዎች ሚስጢራዊነት የተጠበቀ እንዲሆን ተቋሙ ማረጋገጥ አለበት:: ፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀፅ (፫) በተቀመጠው መርህ መሠረት ለዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚሰበሰቡ መረጃዎች፤ ነዋሪዎችን በልዩ ሁኔታ ለመለየት የግዴታ የሚያስፈልጉና ሥርዓቱን በቀጥታ ከሚደግፉ በስተቀር ሌሎች መረጃዎች ሊሰበሰቡ አይችሉም:: ፬/ ማንኛውም ሰው ተመዝጋቢ ፈቃዱን በግልጽ ሳይሰጥ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተመዘገቡ የግል መረጃዎችን መውሰድ፣ ማሰራጨት፣ ማተም፣ መጠቀም፣ መረጃውን መስጠት ወይም ቅጂውን ለሶስተኛ ወገኖች ወይም አካላት መስጠት ወይም ይፋ ማድረግ የተከለከለ ነው:: ፲፬ሺ፯፻፴፪ ፭/ አሠራርና ሕግን ጠብቆ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ለተሰበሰበ የማንኛውም ተመዝጋቢ ግላዊ መረጃ ያለ ተመዝጋቢው ፈቃድ ለሌላ ሰው መግለጽ፣ ማስተላለፍም ሆነ እንዲለወጥ መፍቀድ የተከለከለ ነው:: ፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) ላይ የተደነገገው ቢኖርም፣ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት የግል መረጃው ለሚመለከተው ሕጋዊ አካል ሊገለጽ ወይም ሊተላለፍ ይችላል:: ፯/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ ግላዊ መረጃን የማያጋልጡ የተጨመቁ ዲሞግራፊክ ሪፖርቶች እና የስታትስቲክስ መረጃዎችን በሕግ ለተፈቀደላቸው አካላት በተቋሙ አሠራር መሠረት ሊሰጡ ይችላሉ:: ፰/ ከዲጂታል መታወቂያ ቋት አሠራሩን ጠብቆ ለተጠቃሚ አካላት የተላለፈ የተመዝጋቢ መረጃ የሚያገለግለው ወይም ጥቅም ላይ የሚውለው ለተፈለገው አገልግሎት ብቻ ሲሆን፤ መጀመሪያ ከተላለፈበት ዓላማ ባልወጣ መልኩ ተጠቃሚው አካል ይህንን መረጃ በራሱ ቋት ውስጥ ማስቀመጥና ለራሱ አገልግሎት ብቻ መጠቀም ይችላል:: ፱/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፯) የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ተጠቃሚ አካላት በተመዝጋቢው ፈቃድ ያገኙትን መረጃ፣ መረጃውን ከወሰዱበት ዓላማ ውጪ ለራሳቸው መጠቀምም ሆነ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት የተከለከለ ተግባር ነው:: ፲፬ሺ፯፻፴፫ ፲/ በምዝገባ ወቅት በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚዘጋጅ የተመዝጋቢውን ሙሉ ፈቃድ፣ መብት እና ግዴታዎች የሚገልፅ የፈቃደኝነት ቅፅ በተመዝጋቢው መሞላትና መፈረም አለበት። ፲፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፲) ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በምዝገባ ወቅት ለተመዝጋቢ ምስክር ሆኖ ለሚቀርብ ሰው፤ በተቋሙ የሚዘጋጅ የምስክሩን ሙሉ ፈቃድ፣ መብት እና ግዴታዎች የሚገልፅ የፈቃደኝነት ቅፅ በምስክር መሞላትና መፈረም አለበት፤ የምስክሩ ልዩ ቁጥር ወይም የምዝገባና የማንነት ማረጋገጫ ሰነዶች በቅጹ ላይ መሞላት እና በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ ተመዝግቦ መያዝ አለበት። ፲፪/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ መረጃዎች ከተለያዩ የተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋ፣ የኤሌክትሮኒክ መንገዶችን በመጠቀም ከሚደርሱ ጥቃቶች፣ ከስርቆት፣ ከመጭበርበር እና መሰል የወንጀል ጥፋቶች የሚከላከል ደኅንነቱ የተጠበቀ የሕግና አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት እንዲሁም ጠንካራ የቴክኒክና የደኅንነት ሥርዓት መተግበር አለበት። ፲፫/ ለዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ የግል መረጃዎች፣ ለአጠቃቀም አመቺ በሆነ አኳኋን በሥርዓት ተደራጅተው ተቋሙ በሚያስተዳድረው የመረጃ ቋት ውስጥ መቀመጥ አለባቸው። ፲፬ሺ፯፻፴፬ 1/ The owner of any Personal Data collected for the Digital Identification System is the Registrant; Hence any authentication processes under the Digital Identification System shall be done with the consent of the Registrant. 2/ The Institution shall ensure that, the confidentiality of Personal Data is maintained in the course of collecting, registering, authenticating, storing, and processing of the same. 3/ Data collected in accordance with the principles set out in Article 6 Sub Article (3) of this Proclamation; no information shall be collected for the Digital Identification System other than those necessary to identify Residents and have direct support to the system. 4/ Any person may not collect, distribute, print, use, provide data or transfer a copy to a third party or body or disclose data collected with Digital Identification System without the Registrant’s consent. 5/ It is prohibited to disclose, transfer or modify the Personal Data of any Registrant, collected under the Digital Identification System in accordance with the Rules and Regulations without the Registrant’s consent. 6/ Notwithstanding the Provisions of Sub Article (5) of this Article, the data may be disclosed or transferred to the relevant legal entity authorized by law or by court order. 7/ Summarized demographic reports and statistical data which will not disclose Personal Data collected with in digital identification system may be shared to legally authorized parties in accordance with the procedures of the Institution. 8/ Personal Data transmitted to a Relying
፩/ የአንድ ነዋሪ ዲጂታል መታወቂያ የተጭበረበረ መሆኑ ከተረጋገጠ፤ ተቋሙ ዲጂታል መታወቂያውን ሊቆልፍ፣ መረጃውን ሊያስተካክል፣ ወይም የተጭበረበረው መረጃ ለሌላ አገልግሎት እንዳይውል ለማድረግ የሚያስችሉ ሕጋዊ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ሊወስድ ወይም ክስ ሊመሰርት ይችላል። ፪/ ተቋሙ የተሳሳተ መረጃ መኖሩን ሲያረጋግጥ ልዩ ቁጥሩ ሳይቀየር መረጃውን የማስተካከል ኃላፊነት አለበት። 1/ When the Digital Identification of a Resident is confirmed to be fraudulent, the Institution may lock the Digital Identification, update the data or take other legal precautionary measures to to block the fraudulent data from further use or may initiate suit or charge. 2/ Whenever the Institution verifies that there is erroneous Personal Data it has the responsibility to rectify the error, with out changing the Unique Number.
፩/ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተመዝጋቢ መረጃን በአስተማማኝነት የሚይዝ ጠንካራ መረጃ አስተዳደር ሥርዓት መሆን አለበት። ፪/ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በጊዜ ሂደት የሚለዋወጡ የዲጂታል መታወቂያ መረጃዎችን የማዘመን፣ እንደገና የማረጋገጥ፣ የማደስ፣ በጊዜያዊነት የመቆለፍ ወይም የመሻር ሥራዎችን ይሠራል። 1/ The Digital Identification System shall be a reliable and robust system to securely and safely administer Personal Data. 2/ The Digital Identification System is tasked with maintaining Personal Data quality over time, including the responsibility of updating, re-verifying, renewing, temporarily locking or revoking Digital Identification Information.
፩/ ተቋሙ የቅሬታ ማስተናገጃ ክፍል ማቋቋም እና ይህንኑ ለተገልጋዮች ይፋ ማድረግ አለበት:: ፪/ ማንኛውም ሰዉ በተቀበለው የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎትና በተላለፈበት ውሳኔ ላይ ካልተስማማ ለተቋሙ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው:: ፲፬ሺ፯፻፴፭ ፫/ በተቋሙ የአሠራር ሥርዓት ሂደት የሚያጋጥሙ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች አቀራረብና አፈታት ሂደት፤ ተቋሙ በሚዘረጋው የቅሬታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ መሠረት ይፈታል:: ፬/ በተቋሙ ውሳኔዎች ቅር የተሰኘ አካል ቅሬታውን ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል:: 1/ The Institution shall establish a complaint handling department and notify such establishments to its customers. 2/ Any person against whom Digital Identification service is provided and a decision is made has the right to lodge a complaint to the Institution. 3/ Any complaints and grievances that may be encountered in the course of service provision of the Institution shall be solved in accordance with the grievance filing and redressal Directive of the Institution. 4/ A party who is dissatisfied with the decisions of the Institution may file a complaint to the pertinent court.
ግዴታ የተላለፈ ማንኛውም ሰው ከ፲ሺ (አስር ሺህ) ብር እስከ ፩፻ሺ (አንድ መቶ ሺህ) ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል:: (100,000). ፲፬ሺ፯፻፴፮ ፪/ በዚህ አዋጅ አንቀፅ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ ፫፣ ፬ ወይም ፭ ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ መታወቂያ ለማግኘት አስፈላጊ ከሆኑት መረጃዎች ውጪ ሌሎች መረጃዎችን የሰበሰበ ማንኛውም መዝጋቢ አካል ከ፲ሺ (አስር ሺህ) ብር እስከ ፩፻ሺ (አንድ መቶ ሺህ) ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል:: ፫/ በዚህ አዋጅ አንቀፅ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ (፱) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት የተሰበሰቡ መረጃዎችን ሆነ ብሎ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም ሰው ከ፩(አንድ) ዓመት እስከ ፭(አምስት) ዓመት ወይም እንደነገሩ ክብደት እስከ ፰(ስምንት) ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል:: ፬/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) እና (፪) ላይ የተመለከተው ጥፋት የተፈፀመው የሕግ የሰውነት መብት በተሰጠው አካል ከሆነ ከ ፫፻ሺ (ሶስት መቶ ሺህ) ብር እስከ ፰፻ሺ (ስምንት መቶ ሺህ) ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል:: ፭/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፫) ስር የተመለከተው ድርጊት የተፈፀመው በቸልተኝነት ከሆነ ቅጣቱ ከ ፮ (ስድስት) ወር እስከ ፩ (አንድ) ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከ ፲ሺ (አስር ሺህ) ብር እስከ ፸ሺ (ሰባ ሺህ) ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይሆናል:: ፮/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፫) ላይ የተመለከቱት ጥፋቶች የተፈፀሙት የሕግ የሰውነት መብት በተሰጠው አካል ከሆነ ከ ፩፻ሺ (አንድ መቶ ሺህ) ብር እስከ ፭፻ሺ (አምስት መቶ ሺህ) ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል። ፲፬ሺ፯፻፴፯ Any person when requested by concerned organ to render the necessary cooperation for the effective implementaion of objectives and activities indicated in this Proclamation shall has the obligation to cooperate.
፩/ በዚህ አዋጅ እና ይህን አዋጅ ተከትለው በሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎች መሠረት ሥልጣን ባለው አካል የተሠጠን ዲጂታል መታወቂያን እንደ ሕጋዊ መታወቂያ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነ ወይም ማንነትን ብቻ በማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆነ ወይም በዚህ አዋጅ 1/ Any person who refuses to receive digital identification as a legal identification or refuse to provide services with Digital Identification issued upon verification of identity by the relevant authority based on this Proclamation, Regulation and Directives to be issued following this Proclamation or violates duty to cooprate under Article 21 of this Proclamation shall be punished with a fine from Birr Ten Thousand (10,000) to Birr One Hundred Thousand (100,000). 2/Any Registrar who collected more data than needed to get digital Identification in violation of Article 17 Sub Article (3), (4) or (5) of this Proclamation shall be punished with fine from Birr Ten Thousand (10,000) to Birr One hundred Thousand (100,000). 3/ Any person who intentionaly transfer data collected to receive Digital Identification to a third party in violation of Article 17 Sub Article (9) of this Proclamation shall be punished from 1(One) year to 5(Five) years or in accordance with the circumstance of the case up to 8(Eight) years rigorous imprisonment. 4/ If the crime provided under Sub Article (1) and (2) of this Article is committed by juridical person, it shall be punishable with fine from Birr Three Hundred Thousand (300,000) to Birr Eight Hundred Thousand (800,000). 5/ If the crime provided under Sub Article (3) of this Article is committed negligently the punishment shall be punishable from 6(Six) month to 1(One) year simple imprisonment or with fine from Birr Ten Thousand (10,000) to Birr Seventy Thousand (70,000). 6/ If the crime provided under Sub Article (3) of this Article is committed by a juridical person, it shall be punishable with fine from Birr One Hundred Thousand (100,000) to Birr Five Hundred Thousand (500,000). ‹
የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች የሚቃረን ማንኛውም ሕግ ወይም የአሠራር ልማድ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ተፈፃሚነት አይኖረውም። No law or customary practice, inconsistent with the provisions of this Proclamation shall be applicable with respect to matters provided for by this Proclamation.
የዚህ አዋጅ አንቀፅ ፳፫ ድንጋጌ ቢኖርም ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በተቋሙ የተሰጠ የዲጂታል መታወቂያ በዚህ አዋጅ መሠረት እንደተሰጠ መታወቂያ ተቆጥሮ ሕጋዊነት ይኖረዋል። Notwithstanding Article 23 of this Proclamation, Digital Identification issued before the adoption of this Proclamation, shall be considered as issued based on this Proclamation and remain legal.
፩/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልግ ደንብ ሊያወጣ ይችላል:: ፪/ ተቋሙ ይህን አዋጅ እና ይህን አዋጅ ተከትሎ የሚወጡ ደንቦችን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል። 1/ The Council of Ministers may issue Regulation necessary to enforce this Proclamation. 2/ The Institution may issue necessary Directives to implement this Proclamation and Regulations issued following this Proclamation.
ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል። አዲስ አበባ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም ‹ ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ‹ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፲፬ሺ፯፻፴፰ This Proclamation shall enter into force on the date of its publication in the Federal Negarit Gazeta. Done at Addis Ababa, On this 18th Day of April, 2023. SAHLEWORK ZEWDIE‹ PRESIDENT OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA
Choose an article to open it.