ንብረት በሐራጅ ስለሚሸጥበት የህግ አአግባብ የመ/ቁ. 15672 (አአቶ ታደለ ገለቻ እእና አአቶ ውድመጣስ ኑሮ)
No summary available.
መ/ቁ.14699 ዳኞች፡-
¾T>¨×” ¨Ü uƒ¡¡K— c’É ”Ç=[ÒÑØ QÑ< eKT>ÁekUÖ¨< G<’@ - ¾Ñu= Ów Å”w lØ 258/55 ›”kê 29 ›SM"‹ Ñu= KSõÖ ¨Ü ÁÅ[Ñ<ƒ Ñ”²w u¨Ü’ƒ dÃÁ´ Ów ”Ç=ŸõK<uƒ ¾}¨c’ uSJ’< ä¨< Ñ”²w u¨Ü’ƒ ”Ç=Á´L†¨< ¾Ö¾l c=J” ¾Ów ÃÓv˜ cT> Ñ<v›?¨<U ¨Ü KS¨<×~ Te[Í ¾k[u uSJ’<
u¨Ü’ƒ K=Á´L†¨< ÃÑvM uTKƒ c=¨e” Ñ<ÇÄ” uÃÓv˜ Á¾¨< ¾ôÈ^M
Ÿõ}— õÉ u?ƒU ÃI”’< ¨<d’@ Á쓨< u=J”U ¾ôÈ^M ÖpLà õÉ u?ƒ
Ó” ¾k[u<ƒ Te[Í‹ uÓw QÑ< u}Å’ÑѨ< SW[ƒ ƒ¡¡K— c’Ê‹ eLMJ’< u¨ß’ƒ K=Á²< eKTÃÑv Ów ßðMv†¨< uTKƒ ¨<d’@ uSYÖ~ ¾k[u
›u?~::
ዉሳኔ፡- ¾ôÈራል ÖpLà õ`É u?ƒ ¾cÖ¨< ¨<d’@ }ibM:: Å”w lØ 258/55 ›”kê 29 #ƒ¡¡K—$ c’Ê‹ ”Ç=ku< ¾ðKÑuƒ ª’— U¡”Áƒ ¨Ü‹ ukØ Ñu=” KSðÖ eKS¨<׆¨< uum
G<’@ KT[ÒÑØ “ Ów Ÿó¿ Hc}— c’É uTp[w ¾Ów ÓȨ<”
”ÇÃgi KSq×Ö ”Í= ¾c’Ê‹” ›²ÑÍ˃ Y’-Y¯ƒ STELƒ
›KSTELƒ KSq×Ö` ›ÃÅKU::ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ሲሆን አመልካች በይግባኝ አቤቱታቸው ገቢ ለመፍጠር ወጪ ያደረጉት ገንዘብ በወጪነት ሳይያዝ ግብር እንዲከፍሉበት የተወሰነ በመሆኑ ይኸው ገንዘብ በወጪነት እንዲያዝላቸው የጠየቁ ሲሆን ጉባኤውም ወጪ ለመውጣቱ ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ በወጪነት ላያዝላቸው ይገባል በማለት ወስኗል። ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ውሣኔ ያፀናው ቢሆንም የፍ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ግን ለድርጅቱ ወጥተዋል የተባሉት ወጪዎችን ለማረጋገጥ የቀረቡት ማስረጃዎች በግብር ሕጉ በተደነገገው መሰረት ትክክለኛ የሆኑ ሰነዶች ስላልሆኑ በወጪነት ላያዙ ስለማይገባ ግብር ይከፈልባቸው በማለት ውሣኔ ሰጥተዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታም የቀረቡት ሰነዶች ወጪዎቹ ገቢን ለመፍጠር የወጡ ወጪዎች ለመሆናቸው ለማረጋገጥ ብቃት ያላቸው ሰነዶች በመሆናቸው በወጪዎቹ ላይ ግብር እንዲከፈል መደረጉ የህግ ስህተት ነው የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ ደረሰኞቹ በግብር ሕጉ መሰረት የተሰሩ ትክክለኛ ሰነዶች ስላልሆኑ ተቀባይነት ላያገኙ አይገባም በማለት ተከራክሯል።
ከላይ ከተመለከተው የግራ ቀኙ ክርክር ሲሆን ይህ ችሎት አመልካች ግብር እንዲከፈሉ የተሰጠው ውሣኔ የገቢ ግብርን ለማስከፈል የወጣውን አዋጅ መሰረት ያደረገ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
በገቢ ግብር አዋጁ መሰረት ግብር የተጣለበትን ገቢ የሚሰበስብ ማንኛውም ሰው በአዋጁ በተመለከተው መሰረት ከጠቅላላው ገቢ ላይ ገቢውን ለመፍጠር የወጡ ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ በሚገኘው የተጣራ ትርፍ ላይ ግብር የመክፈል ሃላፊነትና ግድታ አለበት። በመሆኑም ግብር ከፋይ ገቢን ለመፍጠር ያወጣውን ወጪ ትክክለኛነት ተቀባይነት ላያገኙ የሚገባቸው ሰነዶች በማቅረብ ወጪዎቹን የማስረዳት ሸክም አለበት። የግብር ሰብሳቢው ባለስልጣንም የሚቀርቡለትን ሰነዶች ወጪዎች በትክክል ገቢን ለመፍጠር የወጡ ለመሆናቸው የሚያስረዱ ትክክለኛ ሰነዶች ስለመሆናቸው የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት። የቀረቡለት ሰነዶች ትክክለኛነት የማረጋገጥ ሃላፊነት የግብር ሰብሳቢው መ/ቤት እንደመሆኑ መጠን መ/ቤቱ የሰነዶቹን ትክክለኛነት ላያረጋግጥ የሚገባው እንድት ነው የሚለው በቀጣይነት መታየት ይኖርበታል። የገቢ ግብር አዋጅ የወጣው ግብር ከፋዩ ግብር በተጣለበት ገቢ ላይ የሚፈለገውን ትክክለኛ ግብር እንዲከፍል ለማድረግ ነው። ከላይ እንደተገለፀውም ግብር የሚከፈልበት ገቢ ገቢውን ለመፍጠር የወጣው ወጪ ከጠቅላላ ገቢው ላይ ከተቀነሰ በኋላ በሚገኘው ትርፍ ላይ ብቻ በመሆኑ ገቢን ለመፍጠር የወጡ ወጪዎች ሳይቀነሱ በጠቅላላው ገቢ ላይ ግብር እንዲከፈል ማድረጉ የአዋጁን አላማ የሚንድ ይሆናል። በልላ በኩል የቀረቡትን ሰነዶች በሙሉ መቀበሉም ግብር ላከፈልበት የሚገባው ገቢ እንዲቀንስ የሚረዳ ስለሚሆን የሚቀርቡ ሰነዶች ትክክለኛነት በጥንቃቄ መረጋገጥ ይኖርባቸዋል። በዚህም ምክንያት የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 258/55 አንቀጽ 29 ለባለስልጣኑ የሚቀርቡ የሂሣብ መዛግብት እና ሰነዶች ውስጥ የሚሰፍሩ ሂሳቦች ትክክለኛ በሆኑ ሰነዶች /ቫውቸሮች/ መደገፍ እንዳለባቸው ያዛል። ይህ የአዋጁ ድንጋጌ ትክክለኛ ሰነዶች እንዲቀርቡ የፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ወጪዎቹ በቀጥታ ገቢን ለመፍጠር ስለመውጣታቸው በበቂ ሁናቴ ለማረጋገጥ እና ግብር ከፋዩ ሃሰተኛ ሰነድ በማቅረብ የግብር ግድታውን እንዳይሸሽ ለመቆጣጠር እንጂ የሰነዶቹን አዘገጃጀት ሥነ - ሥርዓት መሟላት አለመሟላቱን ለመቆጣጠር ባለመሆኑ የሰነዶቹ ይዘት ላታይ የሚገባው ከዚሁ የአዋጁ አላማ አንፃር ላሆን ይገባል። በመሆኑም ለመ/ቤቱ የቀረቡት ሰነዶች ወጪ ለመውጣቱ የሚያሳዩ በቂ ሁኔታዎችን እስከያዙ ድረስ መ/ቤቱ ሰነዶቹ ሲዘጋጁ ላሟሉ ያስፈልጋል የሚላቸው ስርዓቶች /ፎርማላቲዎች/ በሙሉ ባለመሟላታቸው ብቻ ሰነዶቹን ውድቅ ማድረግ ተገቢ አይሆንም። በእርግጥ የሥርዓቶቹ መሟላት ወጪው መውጣቱን ለማረጋገጥ የተሻሉ ማስረጃዎች ላያደርጋቸው ይችል ይሆናል። ሆኖም ሰነዶቹ መ/ቤቱ እንዲሟሉ የሚፈልጋቸው ሥርዓቶች ባያሟሉ እንኳን ወጪ ለመውጣቱ ላያረጋግጡ የሚችሉ በቂ ሁኔታዎችን እስካሳዩ ድረስ ተቀባይነት ላያገኙ የማይችሉበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም።
ወደ ተያዘውም ጉዳይ ስንመለስ አመልካቹ የህንፃ ተቋራጭ ሲሆኑ ግብር የተጠየቁትም ለሚሰሩት የግንባታ ሥራ እንደሆነ ከመዝገቡ ተረድተናል። ግብር 110 111 የተጣለባቸው ይህንኑ ሥራ አከናውነው ገቢ አግኝተዋል በማለት ከሆነ አመልካች ግንባታውን ማከናወናቸው የተረጋገጠ ጉዳይ ለመሆኑ መረዳት ይቻላል። ይህን የሥራ ዘርፍ ለማከናወን ደግሞ አሸዋ፣ ድንጋይ የመሳሰሉት ጥሬ እቃዎች መጠቀማቸው እንደማይቀር አከራካሪ አይሆንም። አከራካሪ ላሆን የሚችለው ግብር የተጣለበትን የግንባታ ሥራ ለመስራት እነዚህ ጥሬ እቃዎች መገዛት አለመገዛታቸው ሳይሆን ግንባታውን ለመስራት ጥቅም ላይ የዋሉት ጥሬ እቃዎች መጠን እና ዋጋቸው ነው።
አመልካች ሥራቸውን ለማከናወን ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ጥሬ እቃዎች የገዙት ከገጠር የአገሪቱ ክፍል ለመሆኑ የገለፁትን እውነታ ተጠሪ ክርክር እንዳላቀረበበት ከመዝገቡ ተመልክተናል። በገጠር የሃገሪቱ ክፍል ለሚደረግ ሽያጭ ደግሞ ማህተም ያለው ደረሰኝ ማግኘት ከባድ በመሆኑ የወጣውን ወጪ ለማረጋገጥ የቀረበው ሰነድ ነጭ ወረቀት መሆኑን አመልካቹ ገልፀዋል። ግብር ሰብሳቢው መ/ቤትም የቀረበለትን ሰነድ ውድቅ ያደረገውም ሰነዱ ማህተም ያልተደረገበት ነው በሚል ብቻ እንጂ ግብር የተጣለበትን ገቢ ለመፍጠር እነዚህ ጥሬ እቃዎች አልተገዙም ወይም ወጪው የተጋነነ ነው በማለት አለመሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል። ተጠሪ በዚህ በኩል ያቀረበው ክርክር ቢኖር ኖሮ ከፍ ሲል እንደተባለው ጉዳዩ አከራካሪ ላሆን ይችል ነበር። በተጠሪ በኩል ግን እንደዚህ አይነት ክርክር አልቀረበም። በእቃዎቹ ዋጋና መጠን ላይ ክርክር ሳይቀርብ ወጪ መውጣቱ በተረጋገጠ ጉዳይ ላይ ሰነዱ ማህተም የለውም በሚል ብቻ ሰነዱን ውድቅ ማድረጉ ደግሞ በወጣ ወጪ ላይ ግብር እንዲከፈል የማድረግ ውጤት ስለሚኖረው አዋጁን የሚቃረን አፈፃፀም ይሆናል።
በተመሳሳይ ለመኪና የሰልዳ ቁጥር ከመስጠቱ በፊት የሻንሲ ቁጥር እየተመዘገበ ጥገና ሲደረግ የነበረ በመሆኑ የቀረበው የታርጋ ቁጥሩ ያልተመዘገበበት ደረሰኝ መሆኑን መዝገብ ያመለክታል። በዚህ ደረሰኝ ላይ የሰፈረው የሻንሲ ቁጥር የአመልካች መኪና ለመሆኑ ማረጋገጡን ግብር ሰብሳቢው መ/ቤትም አይከራከርም።
መታየት ያለበት ደግሞ የቀረበው ሰነድ ለአመልካች መኪና ጥገና የተደረገ መሆኑን ማረጋገጡ እንጂ የግድ የመኪናው ሰልዳ ቁጥር መፃፉ ላሆን አይገባም። የሻንሲ ቁጥሩም ቢሆን ከታርጋ ቁጥሩ የበለጠ መኪናው የአመልካች መኪና ለመሆኑ የማረጋገጥ ብቃት አለው። በመሆኑም ደረሰኙ ጥገና የተደረገለት መኪና የትኛው መኪና ለመሆኑ ማረጋገጥ እየቻለ የታርጋ ቁጥሩ ባለመግለጹ ብቻ ገቢን ለመፍጠር የወጣው ወጪ ላይ ግብር እንዲከፈል ማድረጉ የሕግ ስህተት ነው። ለነዳጁ የወጣውን ወጪ በተመለከተም ከዚህ የተለየ አይደለም። ነዳጅ ለመቀዳቱ በተሰጠው ደረሰኝ ላይ የተመዘገበው የመኪናው ታርጋ ቁጥር የአመልካች መኪና ታርጋ ቁጥር ላለመሆኑ የቀረበ ክርክር ሳይኖር የባለቤቱ ስም ባለመፃፉ ብቻ ሰነዱ ወድቅ ላደረግ የሚገባባት ምክንያት የለም።
በአጠቃላይ ገቢን ለመፍጠር የሚወጣን ወጪ በትክክለኛ ሰነድ እንዲረጋገጥ ሕጉ የሚያዘው ግብር ከፋዩ የተጣለበትን ግብር የመክፈል ግድታውን ሳይወጣ እንዳይቀር ለመቆጣጠር በመሆኑ ሰነዶቹ በበቂ ሁኔታ ወጪ መውጣቱን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ነገሮች ከያዙ በሰነድ አዘጋጃጀት ላይ የተለያዩ ፎርማላቲዎች ባለመሟላታቸው ብቻ ሰነዱን ውድቅ ማድረጉ፣ ከፍ ሲል እንደተገለፀው፣ ውጤቱ ከግብር ሕጉ በመውጣት ግብር እንዲከፈልበት ባልተጠየቀ ገንዘብ ላይ ግብር እንዲከፈል ማድረግ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የቀረቡትን ሰነዶች የተለያዩ ስርዓቶች /ፎርማላቲዎች/ ባለማሟላታቸው ብቻ ውድቅ ማድረጉ የሕግ ስህተት ነው።
ው ሣ ኔ የጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13065 በጥር 26 ቀን 1996 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ.7813 በሐምል 16 ቀን 1995 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ እና የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በግ/ይ/መ/ቁ. ወ-17 በየካቲት 8 ቀን 1992 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ግራ ቀኙ ወጪ እና ኪሣራ ይቻቻሉ።
No topics extracted.