የወራሽነት ጥያቄን ለማቅረብ ስለተወሰነ ጊዜ የመ/31 (እእነ የሻረግ መንግሥት እእና እእማሆይ የሻረግ ፈረደ)
No summary available.
ታህሣስ 27 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡-
ውሳኔ፡- የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጉዳዩ የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 442 ላይ ንብረተ ለምን ያህል ጊዜ በድጋሚ እንዲሸጥ በፍ/ቤቱ እንደሚታዘዝ ሳይደነግግም ንብረቱ ገዢ አያገኝም ወደሚል መደምደሚያ አያደርስም።
ሁለት ጊዜ ሐራጅ ሽያጭ ወጥቶ አሸናፊዎች ካልከፈሉ ለ3ኛ ጊዜ ሐራጅ ወጥቶ ቤቱ ላሸጥ ይገባል።
84 85
27/04 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡-
ተጠሪ፡- አቶ ውድመጣስ ኑሮ - አልቀረበም።
ው ሣ ኔ ይህ የአፈፃፀም ክርክር ለዚህ ሰበር ችሎት ላቀርብ የቻለው የፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፍትሐብሕር ቀጥታ ክስ ችሎት መጋቢት 29 ቀን 1996 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ አመልካች ቅር በመሰኘታቸው ነው።
ለጉዳዩም መነሻ በሆነው በአመልካችና በተጠሪ መካከል በነበረው የአፈፃፀም ክርክር ተጠሪ (የፍርድ ባለመብት) የነበሩ ሲሆን አመልካች ደግሞ የፍርድ ባለእዳ ነበሩ አመልካች የሚሉትም የእኔ ባለቤት ከወ/ሮ ይችዓለም ለገሰ ገዝታው ስሙ ያልተዛወረ «ሰላም የህፃናት ልብስ መደብር» የተባለው ድርጅት ተሽጦ ለእዳዬ መክፈያ እንዲውል የፍ/ከ/ፍ/ቤት ውሣኔ ሰጥቶ የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ ድርጅቱን አስገምቶ ፍ/ቤቱም ድርጅቱን ለሐራጅ ጨረታ እንዲቀርብ አድርጓል ሆኖም ግን ሁለት ተጫራቾች በተለያየ ጊዜ ተጫርተው ያሸነፉ ቢሆንም ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ላያደርጉ አልቻሉም በዚህም መሰረት የከ/ፍ/ቤት ቀጥታ ክስ ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 442 መሰረት ንብረቱ በጨረታ እንዲሸጥ ትእዛዝ የሚሰጠው ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ የተገለፀ ነገር የለም፣ ነገር ግን አፈፃፀሙ ተግባራዊ መሆን ስላለበት ላልተወሰነ ጊዜ ትእዛዝ ሲሰጥ መቆየት የለበትም፣ በመሆኑም ንብረቱ ለሁለተኛ ጊዜ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት የባለእዳውን ንብረት ባለገንዘቡ እንደሚረከበው ሁሉ ድርጅቱን ባለመብቱ በንብረቱ ግምት መሰረት ይረከቡት የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል።
አመልካችም በዚህ ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ለፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ የጠየቁ ሲሆን ፍ/ቤቱም ጉዳዩን አይቶ የከ/ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ ጉድለት የልለው ነው በማለት ወስኗል።
ከዚህ በኋላ አመልካች የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ለዚህ ሰበር ችሎት ይግባኛቸውን አቅርበዋል።፡ የይግባኛቸውም መሰረታዊ ነጥብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 442 ፍ/ቤቱ ንብረቱ እንደገና እንዲሸጥ ትእዛዝ ይሰጣል ይባል እንጅ በመነሻው ግምት የፍርድ ባለመብቱ (ተጠሪ) ይረከበዋል አይልም የሚል ሲሆን ተጠሪም በዚሁ መሰረት መልሱን ይዞ የቀረበ ሲሆን አመልካችም የበኩሉን የመልስ መልስ አቅርቦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
ይህ የፍድራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ጉዳዩን ከተገቢው የሕግ ድንጋጌ ጋር መርምሯል። እንደመረመረውም ክርክሩ የቀረበበትን ድርጅት ለመሸጥ ሁለት ጊዜ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ፣ በሁለቱም ሐራጅ የሐራጁ አሸናፊዎች ሐራጁ በተደረገ በ15 ቀኖች ውስጥ የንብረቱን ዋጋ በሙሉ አልከፈሉም ተብሎ የፍርድ ባለመብቱ ማለትም ተጠሪ ንብረቱን በግምቱ እንዲረከብ መባሉ አግባብ መሆን አለመሆኑን አይቷል። በዚህም መሰረት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 442 ላይ እንደተመለከተው የጨረታ አሸናፊ የሆነው ሰው በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ የንብርቱን ዋጋ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ፍ/ቤቱ ንብረቱን እንደገና እንዲሸጥ ትእዛዝ ይሰጣል የሚል ተመልክቷል። ምንም እንኳን እዚህ ላይ በሕጉ ውስጥ ይህ አይነት ሁኔታ የተከሰተበት ንብረት ለምን ያህል ጊዜ በድጋሚ እንዲሸጥ በፍ/ቤቱ እንደሚታዘዝ ያልተመለከተ ቢሆንም ንብረቱ ከነአካቴው ገዥ አያገኝም ወደሚል መደምደሚያ የሚያስደርስ አይሆንም። ስለሆነም በተያዘው ጉዳይ ላይ የጨረታው አሸናፊዎች ገንዘቡን አልከፈሉም ማለት ልላ ገዥ የለም ማለት አይደለም። በዚህም መሰረት የከ/ፍ/ቤት ክርክር የተነሣበትን ድርጅት ባለመብቱ በንብረቱ ግምት መሰረት እንዲረከቡት በማለት የሰጠው ትእዛዝና የጠ/ፍ/ቤቱም የሰጠው ይህንኑ የሚያፀና ውሳኔ አግባብ አይደለም በማለት ሽረን ክርክር የተነሣበት ድርጀት በሐራጅ ይሸጥ ሲል ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት ወስኗል። ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ መዝገቡ ስላለቀ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.