በመኪና ግጭት ጉዳት የደረሰበት ሰው ጉዳት ካሳ ለማግኘት የመኪናው ባለቤት ጥፋት እእንዳለበት ማስረዳት የማይኖርበት ስለመሆኑ - የመ/7A (አአዋሳ እእርሻ ልማት ድርጅት እእና አአቶ መሐሪ መታ)
No summary available.
ህዳር 19 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ አብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ዳኜ መላኩ መስፍን እቁበዮናስ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ነገረፈጁ አቶ አብርሃም ፀጋዬ ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አረጋሽ ከበደ አልቀረበችም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ ላሆን የቻለው የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ነው።
ይኼው ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ.304/92 በቀረበለት ካሳ ጉዳይ ላይ የአሁኑ አመልካች በጣልቃ ገብነት የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን አድርጐ ጣልቃ ገቡ በፍትሐብሕር ህግ ቁ.2143/1/ መሰረት ያቀረበውን የይርጋ ክርክር በብይን ውድቅ ካደረገ በኋላ ግንቦት 21 ቀን 1995 ዓ.ም በዋለው ችሎት በከሣሽ በኩል የቀረበውን ክሥና በግራ ቀኙ መካከል የተደረጉትን የፍሬ ነገር ክርክሮች መርምሮ ከሣሽዋ ወ/ሮ አረጋሽ ከበደ ባለቤቷ አቶ ሀ/ሚካኤል መርጊያ ንብረትነቱ የአንደኛ ተከሣሽ በሆነው የሰልዳ ቁጥር 3-17155 መኪና ተገጭቶ በመሞቱ ምክንያት በሚስቱና በሁለቱ ህፃናት ልጆቹ ላይ በቀለብ ረገድ ለደረሰው ጉዳት የመኪናው ባለቤት አንደኛው ተከሣሽ እና መኪናውን ሲያሽከረክር አደጋውን ያደረሰው ሁለተኛው ተከሣሽ በሕግ ኃላፊ ስለሚሆኑ ካሣ ብር 60,000 ላከፍሉ ይገባል። ጣልቃ ገብ የሆነው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በበኩሉ ግጭቱን ላደረሰው መኪና በገባው የመድን ዋስትና መጠን ካሣውን መክፈል አለበት የሚል ውሣኔ ሰጥቷል።
ጣልቃ ገብነት የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን የተደረገው የአሁኑ አመልካች የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ባለመስማማትና ክሱም በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል ምክንያት በፍ/ይ/መ/ቁ.03564 ለOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን ላያቀርብ የቻለ ቢሆንም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ መጋቢት 14 ቀን 1996 ዓ.ም መርምሮ በሰጠው ትእዛዝ ከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.337 መሰረት ይግባኙን በመሰረዝ አሰናብቶታል።
በዚህ መዝገብ ለሰበር አቤቱታ የቀረበውም ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔም ሆነ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ ደረጃ ጉዳዩን ተመልክቶ የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በሚል ሲሆን አመልካች በተነሣው የይርጋ ክርክር ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት የሚልበትን ምክንያት ሰኔ 11 ቀን 1996 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ አብራርቶ አቅርቧል።
ጉዳዩ ተመርምሮ የይርጋው ጥያቄ ከሕጉ አኳያ ተጣርቶ መወሰን የሚያስፈልገው ሆኖ በመታየቱ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን በአመልካች በኩል የቀረበው ማመልከቻም ለአሁኗ ተጠሪ ተልኮ ቀርባ መልስ እንድትሰጥበት ታዞ በ15/4/97 ዓ.ም የተፃፈ መለስ አቅርባለች። በጽሑፍ ያቀረበችው መልስ ሲታይ ተጠሪ ባለቤቴ በመኪና ተገጭቶ በመሞቱ ምክንያት በክሱ የተጠየቀው የጉዳት ካሣ እንዲከፈል ሣይሆን በቀለብና መተዳደሪያ ረገድ ታስቦ ላከፈለን የሚገባ ገንዘብ ነው። ክሱ በጉዳት ካሣ ጥያቄ ላይ ያልተመሰረተ ከሆነ ደግሞ አመልካች የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2143/1/ በመጥቀስ የሚያቀርበው የይርጋ ክርክር ላኖር አይችልም። ስለዚህ ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት ምክንያት የለም። ከዚህ ልላ በሚስትነት ጉዳይ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች በክርክር ላይ ቆይቼ የመጨረሻ ውሤኔ የተሰጠው በ07/07/90 ስለሆነ ክሥ የማቅረብ መብት ያገኘሁት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሲታሰብ ደግሞ በ4/1/92 ያቀረብኩት ክሥ ከይርጋ ነፃ ነው የሚሉትን ክርክሮች ያቀፈ ነው።
የአሁኑ አመልካች ደግሞ ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል በማለት አጥብቆ የሚከራከረው ተጠሪ ክሥ ያቀረበችው አደጋው ወይም ጉዳቱ ከደረሰ ከሰባት አመት ቆይታ በኋላ ነው። የይርጋ ጊዜ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2143/2/ መሰረት ለወንጀሉ ጉዳይ የተወሰነው የይርጋ ዘመን ልክ ይሆናል ከተባለም አደጋውን ያደረሰው ሹፍር የወ/መ/ሕ/ቁ.526/1/ ተጠቅሶ ክሥ ቀርቦበት በብር 1000 የተቀጣ መሆኑ በማሥረጃ ስለተረጋገጠ ለዚህ ወንጀል የተወሰነው የይርጋ ጊዜ ሶስት አመት ብቻ ነው በሚል ምክንያት ነው።
ችሎቱም በቀረበው ጉዳይ በዋናነት ላመረመር የሚገባው ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል አይሆንም? ጉዳቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ ከተገኘ የይርጋው ዘመን ልክ ምን ያህል ነው የሚለው የይርጋ ጥያቄ መሆኑን ተገንዝቧል።
ከፍተኛው ፍ/ቤት ከሰጠው ውሣኔ ለመረዳት እንደተቻለው ከሣሽ የሆነችው የአሁኗ ተጠሪ ሁለተኛ ተከሣሽ የሆነው ከበደ ኃይሉ ንብረትነቱ የአንደኛው ተከሣሽ አላ መሐመድ የሆነ የሰልዳ ቁጥሩ 3-17155 መኪና እያሽከረከረ ሲጓዝ ሰኔ 5 ቀን 1984 74 75 ዓ.ም ባለቤቴ አቶ ሀ/ሚካኤል መርጊያን ጥፋት በሆነ ቸልተኝነት ገጭቶ ገድሎታል በማለት በባለቤቷ መሞት ምክንያት እርሷ እና ሁለት ህፃናት ልጆቹ ቀርቆብናል ወይም አጥተናል የምትለውን ገንዘብ በመግለጽ አስልታ በጠቅላላው ብር 222,000 ተከሣሾች በአንድነት በነጠላ እንዲከፍሐት በ4/1/92 ዓ.ም ተጽፎ እንዲቀርብ ባደረገችው ክሥ ጠይቃለች። የአሁኑ አመልካች የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በቀጥታ የቀረበበት ክሥ ባይኖርም አደጋውን ላደረሰው መኪና የመድን ዋስትና ሰጥቷል በመባሉ ምክንያት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.43/1/ መሰረት የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን አመልካችም አደጋውን ላደረሰው መኪና የመድን ዋስትና በተገባለት መጠን ካሣ የመክፈል ኃላፊነት እንዳለበት አምኖ ክሱን በማስመልከት የበኩሉን መልስ ሲሰጥ የይርጋ ክርክር አንስቷል። በኢንሹራንስ ምክንያት ካሣ እንዲከፍል የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን ከተደረገ ኢንሹራንስ ገቢው ጉዳት ደርሳብኛል ብሎ በከሰሰው ሰው ላይ ላያቀርብ የሚችላቸውን የሕግ ክርክሮች ማቅረብ ይችላል።
አመልካች ሦስተኛ ወገን ሆኖ የክርክር ተካፋይ በሆነበት ጉዳይ ክሱን በመቃወም የይርጋ ክርክር ላያቀርብ የቻለው በዚሁ ሁኔታ በመጠቀም ነው።
የቀረበውን የይርጋ ክርክር በተመለከተም ጉዳዩ ከውል ውጭ የሆነ ኃላፊነትን የሚመለከት ስለሆነ ክሱ በይርጋ ቀሪ መሆን አለመሆኑ ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2143 አኳያ የሚመረመር ነው። የአሁኑ አመልካች ለይርጋው ክርክር መነሻ ያደረገው ይኼው ከውል ከውል ውጭ ስለሚመለከት ካሣ ጉዳይ ክሥ የይርጋ ዘመን የሚወሰነውን ድንጋጌ ነው። የክሱ ፍሬ ነገር ጉዳዩ ከውል ውጭ የሆነ ኃላፊነት የሚመለከት መሆኑን እያረጋገጠ ተጠሪዋ በአመልካች በኩል ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መልስ ስትሰጥ ጉዳዩ ሟች በመኪና ተገጭቶ ከመሞቱ ጋር የተያያዘ ቢሆንም ክሱ የተመሰረተው በቀለብ ጥያቄ ላይ እንጅ በጉዳት ካሣ ላይ ስላልሆነ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2143 ላይ የተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ ተፈፃሚ ላሆን አይችልም በሚል ያቀረችው ክርክር ተቀባይነት የለውም። ተጐጂው በመሞቱ ምክንያት ሚስት ወይም ልጆች በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2095 መሰረት በቀለብ መተዳደሪያ ረገድ የሚያቀርቡት የካሣ ጥያቄም ቢሆን ከውል ውጭ የሆነ ኃላፊነትን የሚመለከት እንጂ በልላ የተለየ ግንኙነት ላይ ወይም በልላ የሕግ ምክንያት ላይ የተመሰረተ አይደለም።
በዚሁ በተጠቀሰው የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2143 ላይ የተመለከተው የይርጋ ዘመን ሲታይ የመጀመሪያው ንኡስ ቁጥር «1» ተበዳዩ ክሥ ማቅረብ የሚችለው ካሣ የሚጠየቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት አመት ድረስ መሆኑን የሚደነግግ ሲሆን ንኡስ ቁጥር 2 ደግሞ ጉዳቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ የይርጋ ዘመኑ ርዝመት የበለጠ እንደሆነ የካሣው ጉዳይ ክሥ የይርጋ ዘመኑ ርዝመት እንደሚሆን ይገልፃል።
የቀረበው ጉዳይ ከዚሁ የይርጋ ድንጋጌ አንፃር ሲመረመር የአሁኗ ተጠሪ ካሣ የተጠየቀበት ጉዳት ሰኔ 5 ቀን 1984 ዓ.ም ደርሶ የካሣውን ጉዳይ ክሥ ያቀረበችው
No topics extracted.