ለተወሰነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ የስራ ውል ስለማድረግ - የመ/24 (የኢትዮጵያ ቴልኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን እእና ወ/ት ትእግሥት ወርቁ
No summary available.
ታህሣስ 17 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡-
Ò - ¾¨^i’ƒ ØÁo” KTp[w eK}¨c’¨< Ñ>²? - ¾ÃÒ ØÁo
uõÉ u?ƒ }kvÃ’ƒ ¾TÕuƒ G<’@ - የõ/w/I/l 10001/2/' 1168'
1845' 1853
¾›T^ wN?^© ¡ML© S”ÓYƒ ÖpLà õÉ u?ƒ ¾›G<” ›SM"Œ‹ }Ö]ª ¾TE‹ ›v‹” ¾›„ S”ÓY~ ²¨MÈ” u?ƒ K=Áe[¡u<” ÃÑvM uTKƒ Ák[u<ƒ” ¡e SUa ¾cT@” ԔŠŸõ}— õÉ u?ƒ ¾cÖ¨<” ¨<d’@
uSh ¾Ô”Å ¨[Ç õÉ u?ƒ ¡c< uÃÒ k] J“EM uTKƒ Á쓨<” ¨<d’@
uSn¨U ¾k[u ›u?~።ዉሳኔ፡- u¡MK< ÖpLÃ õ`É u?ƒ ¾}cÖ¨< ¨<d’@ ì”…M::
Ñ<U ¾T>cÖ¨< ¾¨<M c’É dÕ uõ/w/I/l.1845” u}SKŸ} ¾T>cØ ¨<d’@ ¾Kኡ።
ታህሣስ 17 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡-
በዚህ መዝገብ ለሰበር ለቀረበው አቤቱታ መነሻ የሆነው የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 364 በይግባኝ ደረጃ ቀርቦለት በነበረው ጉዳይ ሲያከራከር ቆይቶ የካቲት 16 ቀን 1996 ዓ/ም መረምሮ የሰሜን ጐንደር ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የአሁኑ አመልካቾች ተጠሪዋ የሟች አባታችን የአቶ መንግሥቱ ዘወልድን ቤት ላያስረክቡን ይገባል በማለት ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል የሰጠው ውሣኔ ነው። የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዚህ ውሣኔው ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የጐንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ክሱ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1000 /1/2/ እና 1845 መሰረት በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል የወሰነው በሕጉ አግባብ ነው በማለት አጽንቶታል።
አመልካቾች አባታችን አቶ መንግሥቱ ዘወልድ ከሞቱ በኋላ በውርስ ላተላለፍልን የሚገባውን ቤት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም በተደረገ ስምምነት ተረክበን ተጠሪዋ ባይወልዱንም እናታችን ናቸው ብለን በማሰብ እንዲቀመጡበት ያደረግነውንና በአክብሮት ሣንጠይቃቸው የቆይነውን ንብረት እንዲያስረክቡን በማለት ያቀረብነው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል 62 63 በሚል ለሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። አመልካቾች ንብረቱን ሣንጠይቅ የቆየነው በቤተዘመድ ግንኙነት ምክንያት ተጠሪዋን በመፍራትና በማክበር ስለሆነ ፍ/ቤቱ የይርጋውን ክርክር በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1853/1/ መሰረት ላቀበለው አይገባም ባዮች ናቸው።
አቤቱታው ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በመወሰኑ በአመልካቾች በኩል የቀረበው ማመልከቻ ለአሁኗ ተጠሪ እንዲደርሳቸው ተደርጐ ሐምል 18 ቀን 1996 ዓ/ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካቾች በበኩላቸው የመልስ መልስ ሰጥተውበት ተከራክረዋል።
በተጠሪዋ በኩል የቀረበው ክርክር ሲታይ አመለካቾች እኔን የእንጀራ እናታቸውን በማክበርም ሆነ በመፍራት መብታቸውን ሣይጠይቁ ቆይተዋል ላባል ስለማይችል ፍ/ቤት ይርጋ አልቀበልም የሚልበት ምክንያት የለም የሚል ይዘት ያለው ነው።
ችሎቱም የአሁኑ አመልካቾች ከ1962 ዓ/ም በፊት የሞቱትን የአባታችንን ቤት ይዘው የሚገኙት የአሁኗ ተጠሪ ላያስረክቡን ይገባል በሚል ያቀረቡት ክሥ በይርጋ ቀሪ ሆኗል አልሆነም፣ ፍ/ቤት ይርጋ አልቀበልም የሚልበት የሕግ ምክንያት አለ ወይንስ የለም የሚለውን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የጐንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤትም ሆነ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካቾች ከአባታችን በውርስ ላተላለፍልን የሚገባውን ቤት የአሁኗ ተጠሪ ምንም አይነት መብት ሣይኖራቸው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆን ይዘው ስለሚገኙ ላያስረክቡን ይገባል በሚል ያቀረቡትን ክስ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1845 መሰረት በአሥር አመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ላወሰኑ የቻሉት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም ተደርጓል የተባለውን ውል መነሻ በማድረግ ነው። ከሰነዱ እንደሚታየው ግን ቤቱን የአሁኗ ተጠሪ ለቀው ለሟቹ ለአቶ መንግሥቱ ዘውልድ ወራሾች ማሥረከባቸው እና ልሎችን ንብረቶችም ስለመከፋፈላቸው ከመገለጹ በቀር የሟቹ የአባታቸው ሚስት በቤቱ እየተጠቀሙበት ይቆዩ ወይም ይኑሩበት የሚል ነገር የለውም። ከዚህ ልላ ቤቱ በሟች ሚስት ይዞታ ሥር ቆይቶ ወደፊት በዚህ ጊዜ ለወራሾች ያስረክባሉ የሚል የውል ቃል የለውም። በሰነዱ ላይ የሰፈረው በሕግ የውል ትርጉም የሚሰጠው አይደለም። ውል ማለት ደግሞ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1675 ላይ እንደተመለከተው ንብረታቸውን የሚመለከቱ ግድታቸውን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸው ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መካከል የሚደረግ ሥምምነት ስለሆነ በዚሁ መሰረት የውል ትርጉም የሚሰጠው ነገር ሣይኖር ውል አለ የሚል መነሻ በመያዝ ይርጋን በሚመለከት ተፈፃሚ የሚሆነው ስለውሎች በጠቅላላው በሚለው የፍትሐብሕር ሕጉ ክፍል ተጽፎ የሚገኘው በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1845 ላይ የተመለከተው የአሥር አመት ጊዜ ነው ብሎ መወሰን ትክክል አይደለም። በአሁኑ አመልካቾች በኩል የቀረበው የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም የተፃፈው ሰነድ ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1845 ጋራ በተያያዘ የሚያስነሣው የይርጋ ጥያቄ ስለልለ በዚህ ጉዳይ የተጠቀሰው የይርጋ ሕግ አግባብነት የለውም።
በልላም በኩል የአሁኗ ተጠሪ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ሲከራከሩ የነበሩት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም ተፃፈ የተባለውን ሰነድ መነሸ በማድረግ ብቻ ሣይሆን ቤቱ ከ1943 ዓ/ም ጀምሮ ባለማቋረጥ ግብር እየከፈልኩበት ንብረቴ ሆኗል፣ ከሃያ ሰባት አመት በላይ በስሜ ስገብርበት ቆይቼ የቤቱ የቦታ ይዞታም ሆነ የቤቱ ባለቤትነት ሥም በሥሜ ላሆን ችሐል በሚል ምክንያት ጭምር ሲሆን እነዚህ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች መሆናቸውን ከመዝገቡ ለመረዳት ተችሐል። ከእነዚህ ፍሬ ነገሮች በመነሣት በሕጉ በኩል ያለው ሲታይ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1168/1/ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለእጅ /ባለይዞታ/ የሆነ ሰው የዚሁኑ ንብረት ግብር ባለማቋረጥ 15 ዓመት በሥሙ ከከፈለ የዚሁ ሀብት ባለቤት ይሆናል በሚል ደንግጐ ይገኛል። ሕጉ 64 65 ይርጋ አዘል ስለሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለእጅ /ባለይዞታ/ የሆነው ሰው የዚህን ንብረት ግብር ባለማቋረጥ ለ15 ዓመት በሥሙ ከከፈለ ልላ ይገባኛል የሚል ሰው እንዲሰጠው ላጠይቀው አይችልም። በሕጉ ለባለይዞታው መብቱ ይረጋለታል። የአሁኗ ተጠሪም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት ባለይዞታ በመሆን የዚሁኑ ንብረት ግብር ባለማቋረጥ ከ15 ዓመት በላይ በሥማቸው ሲከፍሉ ስለቆዩ በሕጉ የዚሁ ሀብት ባለቤት ሆነዋል። የአሁኑ አመልካቾች አባት ከ1962 ዓ/ም በፊት የሞቱ ስለሆነ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በተጠሪዋ ይዞታ ሥር የቆየውን ቤት ከሃያ ስምንት አመት በኋላ እንዲያስረክቧቸው ያቀረቡት ክሥ በይርጋ ቀሪ አይሆንም በሚል የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
አመልካቾች ክስ ሣናቀርብ የቆየነው ተጠሪዋ የሟቹ አባታችን ሚስት በመሆናቸው በመፍራትና በማክበር በመሆኑ ፍ/ቤት ይርጋውን ላቀበለው አይገባም በሚል ያነሱትን ክርክር በተመለከተም በእርግጥ ፍ/ቤት ይርጋን አልቀበልም የሚልባቸው ምክንያቶች አሉ። እነዚህ ምክንያቶች በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1853 የተዘረዘሩት ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል ባለገንዘቡ የሚፈልገውን ያልጠየቀበት ምክንያት ባለእዳውን የመፍራትና የማክበር ስሜት መኖር አንዱ ነው። አመልከቾች ከሃያ ስምንት አመት በላይ ተጠሪዋ ቤቱን እንዲያስረክቡን ሣንጠይቅ የቆየነው የአማታችን ሚስት ስለሆኑ እንደ እናት ስለምናያቸው የመፍራትና የማክበር ስሜት አድሮብን ነው ይበሉ እንጅ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት አመለካቾች አባታቸው ከሞቱ በኋላ የአባታችንን ንብረት አካፍይን ወይም አስረክቢን የሚል ጥያቄ አንስተው ሽማግልዎች ሰብስበው የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም በተፃፈ ሰነድ በተደረገ እርቅ ንብረት መከፋፈላቸው መገለጹና በዚሁ ሰነድ አማካኝነት ቤቱን ተረክበን ነበር ማለታቸው ሲታይ ከዚህ በኋላ ሣይጠይቁ የቆዩት ተጠሪዋን በመፍራትና በማክበር ምክንያት ነው ለማለት አይቻልም በሚል ሣይቀበላቸው ቀርቷል። በአመልካቾች በኩል ተጠሪዋን የመፍራትና የማክበር ስሜት ነበረ አልነበረም ለሚለው ፍ/ቤት መፍራትም ሆነ ማክበር አልነበረም የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረሰ ወደ ፍሬ ነገር ጥያቄ ስለሚያመዝን በሰበር ደረጃ ላመረመር አይችልም። በሰበር ደረጃ ላታይ የሚችለው የሥር ፍ/ቤት የመፍራትና የማክበር ስሜት መኖሩን አረጋግጦ ይርጋን አልቀበልም ለማለት የሚያስችል የሕግ ምክንያት አይደለም በሚል ወስኖ ቢገኝ ነው። ስለዚህ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በይርጋ ሕግ ቀሪ መሆኑ ቢረጋገጥም ፍ/ቤት ይርጋውን አልቀበልም የሚልበት የሕግ ምክንያት አለ በሚል ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
ከፍ ሲል እንደተገለፀው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት
No topics extracted.