የስራ ውሉ በህገ ወጥ መንገድ የተቋረጠ የስራ መሪ ስለሚያገኘው መፍትሕ የመ/15/ (አአርሲ እእርሻ ልማት ድርጅት እእና አአቶ ሰለሞን አአበበ/
No summary available.
የመ/ቁ.16648 ታህሣስ 20 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡-
ውሳኔ፡- የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዩ ወሳኝ ቦርድ የሰጠውና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያጸናው ውሳኔ ተሽሯል።
በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 162 /3/ መሰረት የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓትና የልሎች ክፍያዎች ጥያቄ ላጠየቅ ይገባው ነበር ከሚሰኝበት ጊዜ ጀምሮ የስራ ውሉ ተቋርጦ ቢሆን እንኳን ይህን ከግምት ሳያስገባ እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል።
የሰራተኛው ወይም የአሰሪው ጥያቄ በተተኪዎቻቸው ወይም በወራሾቻቸው በሚቀርብበት ጊዜ በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 162/3/ እና 162/3/ በተደረጉ የይርጋ ድንጋጌዎች ይመራል።
የሰራተኛው ወይም የአሰሪው ተተኪዎች ወይም ወራሾች የሰራተኛውን ወይም የአሰሪውን ሳይሆን የራሳቸውን መብት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡት ጥያቄ በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 162/3/ እና 162/4/ በተደነገጉት ሳይሆን በአንቀጽ 162/1/ በተደነገገው የይርጋ ድንጋጌ ይመራል።
በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 164/1/ መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚቋረጠው ክሱ በአዋጅ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን በተሰጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ወይም በፍርድ ቤቶች በተቋቋሙ የስራ ክርክር ችሎቶች የቀረበ እንደሆነ ነው።
ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ባልተሰጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ወይም በስራ ክርክር ችሎት የቀረበ ክስ በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 164/1/ መሰረት የይርጋ ጊዜን መቆጠር አያቋርጥም።
በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 164/2/ መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚቋረጠው አቤቱታው የቀረበው ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀረበ እንደሆን ብቻ ነው።
ለአሰሪ የቀረበ አቤቱታ በአዋጅ ቁ.42/85 (377/96) አንቀጽ 164(2) መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠርን አያቋርጥም።
በአዋጅ ቁ.42/85 (377/96) አንቀጽ 166(1) ከፍትሐ-ብሄር ህግ ቁጥር 1793 ጋር ተገናዝቦ መታየት አለበት።
ሰራተኛ ወይም አሰሪ በአዋጅ ቁ.42/85 (377/96) አንቀጽ 166(1) ለመጠቀም በድንጋጌው የተመለከቱት ሁኔታዎች መከሰታቸውን እና ክሱ በይርጋ የሚታገድበት ከመድረሱ በፊት ያልቀረበው በድንጋጌው ከተመለከቱት ሁኔዎች ቢያንስ በአንዱ መከሰት ምክንያት መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጥ አለበት።
10 11 የመ.ቁ. 16648 ታህሣስ 20 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ ወ/ሮ ሆሳእና ነጋሽ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን - አልቀረበም።
ተጠሪዎች፡- እነ አቶ አንለይ ያየህ /27 ሰዎች/ - ጠበቃ ብዙአለም መርሻ ቀረበ
ይህ ክርክር አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ዘንድ የተጀመረ ነው።
ተጠሪዎች ለቦርዱ ነሐሴ 15 ቀን 1993 ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ ያቀረቡት ክስ ተከሣሽ /አመልካች/ በጌዶ፣ ነቀምት እና ጊምቢ በአከናወነው የትራስሚሽን መስመር መዘርጋት ሥራ ላይ በተለያየ የሥራ መደብ አገልግሎት ሰጥተናል። ይሁን እንጂ አመልካች በዚህ ሥራ ላይ ለተሳተፉት ሰራተኞች በመሉ በመንግስት ትእዛዝ መሰረት ከመጋቢት 15 ቀን 1992 ዓ.ም. ጀምሮ የሁለት እርከን ጭማሪ ሲያደርግ እኛን ግን ከልክሎናልና ለእኛም ይህን ጭማሪ ከሞራል ካሣ እና ከወጭና ኪሣራችን ጋር ላከፍለን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።
አመልካችም ለቀረበበት ክስ የተጠየቀው የእርከን ጭማሪ ክፍያ ለልሎች ሰራተኞች ከተፈፀመበት ከመጋቢት 15 ቀን 1992 ዓ.ም. ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት እስከ ነሐሴ 15 ቀን 1993 ዓ.ም. ድረስ ያለው ጊዜ ከአስራ ሰባት ወር በላይ በመሆኑ ክሱ በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162/1-3/ መሰረት በይርጋ ላታገድ ይገባዋል ሲል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወማያ አቅርቧል። በአማራጭም መልሱን ሰጥቶ ተከራክሯል።
ክርክሩ የቀረበለት ቦርድም " …. የከሣሽና የተከሣሽ የሥራ ግንኙነት ቀጣይነት ያለው በመሆኑ …." በክሱ የቀረበው ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ አይደለም በማለት የአመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ አድርጎታል። ወደ ጉዳዩ ፍሬ ነገር በመግባትም ከከሣሾቹ ውስጥ ከፊሎቹ ብቻ የአንድ እርከን ጭማሪ እንዲሰጣቸው እና ይኸውም ከመጋቢት 15 ቀን 1992 ዓ.ም. ጀምሮ ተስተካክሎ እንዲከፈላቸው ወስኗል።
ከዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ፍርዱ ጉድለት የለበትም በማለት የይግባኙን መዝገብ ዘግቶታል።
በመቀጠል አመልካች ከአስራ ሰባት ወራት በኋላ የቀረበው የተጠሪዎች ክስ በይርጋ አይታገድም በሚል በመወሰኑ ሕግ ተጥሷል፤ እንዲሁም በዋናው ጉዳይ የተሰጠው ውሣኔ የተሳሳተ ፍሬ ነገርን መሰረት ያደረገ ስለሆነ ላሻርልን ይገባል ሲል አቤቱታውን ለዚህ ችሎት አቅርቧል። ተጠሪዎችም በጠበቃቸው አማካኝነት በአቀረቡት መልስ መጋቢት 15 ቀን 1992 ዓ.ም. የእርከኑ ጭማሪ እንደሚሰጥ ውሣኔው ለሰራተኞቹ ይፋ የሆነበት ቀን እንጁ ክፍያው የተፈፀመበት ቀን አይደለም። ይሁን እንጂ ልሎቹ ሰራተኞች የካቲት 8 ቀን 1993 ዓ.ም. የእርከኑ ጭማሪ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ሲገለጽላቸው ይህ ለተጠሪዎቹ ሳይደረግ በመቅረቱ ተጠሪዎቹ ይህን እንደአወቁ የካቲት 27 ቀን 1993 ዓ.ም. አቤቱታቸውን ለኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቅርበዋል። ለዚህ አቤቱታ በፅሁፍ ምላሽ ያላገኙ ስለሆነም የይርጋው ጊዜ ተቋርጧል የሚልና በጥቅሉም ፍርዱ እንዲፀና የሚጠይቅ መልስ አቅርበዋል።
ችሎቱም በዚህ ጉዳይ ላታይ የሚገባው ነጥብ በተጠሪዎች የቀረበው ክስ በይርጋ ላታገድ ይገባዋል? ወይስ አይገባውም? የሚለው ሆኖ አግኝቶታል።
ሕግ የተለያዩ ጉዳዮች እንደየሁኔታው አግባብነት ላለው አካል ቀርበው የሚታዩበትን የተለያየ የጊዜ ገደብ አስቀምጦ ይገኛል። በዚህም 12 13 ምክንያት አንድን ጉዳይ ለአንድ አካል አቅርቦ እንዲታይ ለማድረግ ጉዳዩ በሕግ የተፈቀደለትን የጊዜ ገደብ ጠብቆ የቀረበ እንዲሆን ያስፈልጋል። በሕግ የተወሰነለትን ጊዜ አሳልፎ የቀረበ ጉዳይ ወደ ፍሬ ነገሩ ተገብቶ የመታየትን እድል ሳያገኝ ከወዲሁ ውድቅ ላደረግ ወይም በይርጋ ላታገድ ይችላል።
ከላይ እንደተጠቀሰው በግራ ቀኙ የቀረበው ሙግት የሥራ ክርክርን የሚመለከት ነው። ለክርክሩ አግባብነት ያለው ሕግም የአዋጅ ቁጥር 42/85 ነው።
ይህ የአዋጅ ቁ. 42/85 በክፍል አስር ምእራፍ አንድ ከአንቀጽ 162 – 166 በሚገኙት ሕጎች ስር ስለ ይርጋ ደንብ ደንግጓል። የአዋጅ ቁ. 42/85ን የሻረው የአዋጅ ቁ. 377/1996ም በተመሳሳይ የሕጉ ክፍል፣ በተመሳሳይ የሕጉ ምእራፍ እና በይዘታቸው ጭምር አንድ አይነት በሆኑ አንቀጾች ስር የይርጋ ደንብን አስቀምጧል።
በእርግጥ ለዚህ ለያዝነው ጉዳይ ተፈፃሚነት ያለው የአዋጅ ቁ. 42/85 ነውና ለጭብጣችን ምላሽ ለመስጠት እንድንችል በዚህ ውሣኔያችን ውስጥ እንደአግባብነታቸው ይህ አዋጅ ያስቀመጣቸው የይርጋ ደንቦች በዋነኛነት የሚጠቀሱ ይሆናል። ይሁን እንጂ እነዚህ ሁለት ሕጎች አንድ አይነት አንቀጾች የያዙ በመሆናቸው በዚህ ውሣኔ ውስጥ ለአዋጅ ቁ. 42/85 የይርጋ ደንብ ድንጋጌዎች የሚሰጠው ትርጓሜ በአዋጅ ቁ. 377/1996 ለሚገኙትም ተፈፃሚነት ይኖረዋል።
የአዋጅ ቁ. 42/85 የመብት ጥያቄዎች ስለሚቀርቡበት የጊዜ ገደብ በአንቀጽ 162 ላይ ደንግጓል። ከመነሻው የተጠቀሰው አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ /1/ በዚህም ሆነ በልላ ሕግ በተለየ ሁኔታ ከአልተወሰነ በስተቀር ጉዳዩን ማቅረብ ከሚቻልበት ቀን አንስቶ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ከአልቀረበ የመብቱ ጥያቄ በይርጋ እንደሚታገድ አመልክቷል። ይህ ድንጋጌ የጉዳዩ የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ጉዳዩን ለማቅረብ ከሚቻልበት ጊዜ አንስቶ መሆኑን ይጠቅሳል። እንዲሁም በሕግ የተለየ የጊዜ ገደብ ያልተደረለት ጉዳይ ሁሉ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ላቀርብ እንደሚገባው በመደንገግ አጠቃላይ የሆነ የጊዜ ወሰን አስቀምጧል። በተጨማሪም ይኸው የአዋጅ ቁ.
42/85 አንቀጽ 162 በንኡስ አንቀጽ /2/፣ /3/ እና /4/ ላይ ሕጉ የተለየ የይርጋ ጊዜ የወሰነላቸውን የአቤቱታ አይነቶች ለይቶ አመላክቷል።
የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162 የተለየ የይርጋ ጊዜ ከወሰነላቸው የመብት ጥያቄዎች ውስጥ የመጀመሪያው የሆነው አንቀጽ 162/2/ "ሰራተኛው የሥራ ውሉ ከሕግ ውጭ ተቋርጦብኛል በማለት ወደ ሥራው ለመመለስ የሚያቀርበው ክስ ውሉ በተቋረጠ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል" በማለት ደንግጓል። በልላ በኩልም የሥራ ውልን መቋረጥ ምክንያት አድርጎ ሰራተኛው በአሰሪው ላይ አላያም አሰሪው በሰራተኛው ላይ የሚያነሳው የክፍያ ጥያቄ የሥራ ውሉ በተቋረጠ በስድስት ወር ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ እንደሚታገድ በዚሁ አንቀጽ 162/4/ ላይ ተደንግጓል።
በግልጽ እንደሚታየው የመጀመሪያው ድንጋጌ የሥራ ውሉን መቋረጥ ሕጋዊነት በመቃወም ወደ ሥራዬ ልመለስ ይገባል የሚል ሰራተኛ ይህን ጥያቄውን ለማቅረብ የሦስት ወር ጊዜ ብቻ እንዳለው ያስገነዝባል። ሁለተኛው ድንጋጌ ደግሞ የሥራ ውልን መቋረጥ መነሻ አድርገው የሚቀርቡ ማናቸውም አይነት የክፈያ ጥያቄዎች በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተገደቡ መሆናቸውን ያመላክታል። በተጨማሪም ከእነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች አቤቱታ አቅራቢው የሥራ ውሉ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ በመብቱ መጠቀም የሚችል መሆኑን መረዳት ይቻላል።
እንደሚታወቀው ወደ ሥራ ልመለስ ይገባል የሚል ክስ በሰራተኛው በእራሱ እንጂ በተተኪዎቹ ወይም በወራሾቹ ላመሰረት የሚችል አይደለም። ይሁን እንጂ ከሥራ ውል መቋረጥ በኋላ ሰራተኛውም ሆነ አሰሪው አንዱ ከልላው ወገን ላጠይቋቸው የሚችሐቸው የክፍያ አይነቶች በተተኪዎቻቸው ወይም በወራሾቻቸው ላጠየቁ የሚችሉበት ሁኔታ ላኖር እንደሚችል የሚታመን ነው።
14 15 እንዲህ በሚሆን ጊዜ ተተኪዎቹ ወይም ወራሾቹ መሰረት አድርገው የሚቀርቡት የእራሳቸውን ሳይሆን የአውራሻቸውን ሰራተኛ ወይም አሰሪ መብት ነውና በይርጋው ጊዜ አቆጣጠር ላይ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። ስለሆነም የሰራተኛውን ወይም የአሰሪውን መብት ተክተው በወራሾቻቸው ወይም በተተኪዎቻቸው የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄዎች የሥራ ውሉ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ በስድስት ወራት ውስጥ ካልቀረቡ በይርጋ ላታገዱ ይገባል።
ልላው የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162 የተለየ የይርጋ ጊዜ የወሰነለት የአቤቱታ አይነት በአንቀጽ ንኡስ አንቀጽ /3/ ላይ ተመልክቷል። ይኸውም " ሰራተኛው የሚያቀርበው የደመወዝ የትርፍ ሰዓትና የልሎች ክፍያዎች ጥያቄ መጠየቅ ከሚገባው ጊዜ ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ…" መቅረብ እንደሚገባውና ይኸ ካልሆነ በይርጋ እንደሚታገድ ተደንግጓል። ከድንጋጌው መረዳት እንደሚቻለው ይህን አንቀጽ ተመስርቶ የሚቀርብ የመብት ጥያቄ በአሰሪውና በሰራተኛው መካከል የተፈፀመው የሥራ ውል ፀንቶ በአለበት ሁኔታ ሰራተኛው ከአሰሪው የሚጠይቀውን ክፍያ የሚመለከት እንጂ የግድ የሥራ ውሉን መቋረጥ ተከትሎ የሚነሳ አይደለም። በተጨማሪም የስድስት ወሩ የይርጋ ጊዜ እንደሁኔታው ክፍያው ላጠየቅ ይገባ ነበር የሚሰኝበትን እለት ተመስርቶ መቆጠር የሚጀምር እንጂ ውስን የመነሻ ጊዜ የተቀመጠለት አይደለም።
ይኸ አንቀጽ 162/3/ ሰራተኛው አሰሪውን ደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓትና ልሎችም ክፍያዎችን ላጠይቅ የሚችልበትን ውስን ጊዜ ያስቀመጠ ቢሆንም የሥራ ውልን መቋረጥ ለይርጋው ጊዜ አቆጣጠር እንደመነሻ ባለመውሰዱ ከአንቀጽ/2/ እና /4/ ይለያል። ይርጋውም ሰራተኛው የተጠቀሱትን ክፍያዎች ላጠይቅ ይገባው ነበር ከሚሰኝበት ጊዜ ይነሳና ምናልባትም የሥራ ውሉ ተቋርጦ እንኳ ቢሆን ይኸን ከግምት ውስጥ ሳያስገባ እስከ ስድስት ወር ድረስ መቆጠሩ ይቀጥላል። እንዲሁም እነዚህ ክፍያዎች በሰራተኛው ሳይሆን በተተኪዎቹ ወይም በወራሾቹ ላቀርብ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል። እንዲህ በሚሆን ጊዜም ጥያቄው የሰራተኛውን መብት ተመስርቶ የሚቀርብ ነውና ልክ እንደቀድሞው ሁሉ በይርጋው ጊዜ አቆጣጠር ላይ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። ስለሆነም ተተኪዎች ወይም ወራሾች የተጠቀሱትን ክፍያዎች ሰራተኛው ላጠይቅ ይገባው ነበር ከሚባልበት ጊዜ አንስቶ እስከ ስድስት ወር ድረስ ካልጠየቁ በቀር ክሳቸው በይርጋ የሚታገድ ይሆናል።
እንግዲህ በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162 መሰረት አንድ የሥራ ክርክር ጉዳይ የተለየ የይርጋ ጊዜ የተቀመጠላቸውን የመብት ጥያቄዎች የሚመለከት ከሆነ ከንኡስ አንቀጽ/2/ እስከ /4/ የተጠቀሱትን የሦስት ወይም የስድስት ወራት የጊዜ ገደብ አክብሮ የቀረበ ላሆን ይገባዋል። በእነዚህ ድንጋጌዎች ሥር የማይሸፈን ከሆነ ደግሞ በንኡስ አንቀጽ /1/ በተመለከተውና በአንፃሩም ሰፊ በሆነው የአንድ ዓመት የጊዜ ወሰን ውስጥ እንዲቀርብ ያስፈልጋል።
በልላ በኩል ደግሞ ይህ የይርጋ ጊዜ የተወሰነበት የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162 ሰራተኛውና አሰሪው አንዱ ከልላቸው የመብት ጥያቄዎችን የሚያቀርቡበትን ሁኔታ ብቻ በመጥቀስ የተደነገገ መሆኑን ከአንቀጾቹ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጂ የሰራተኛው ወይም የአሰሪው ጥያቄ በተተኪዎቻቸው ወይም በወራሾቻቸው በሚቀርብበት ጊዜም የይርጋው አቆጣጠር ላለወጥ እንደማይገባ ከላይ ተመልክቷል። በእርግጥ የሰራተኛውም ሆነ የአሰሪው ተተኪዎች ወይም ወራሾች የሰራተኛውን ወይም የአሰሪውን ሳይሆን የእራሳቸውን መብት መሰረት አድርገው አንዳቸው ከልላቸው ክፍያ ላጠይቁ የሚችሉበት ሁኔታ ይኖራል።
እንዲህ በሚሆን ጊዜ ግን የይርጋው አቆጣጠር ከአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162/3/ ወይም /4/ አኳያ ሳይሆን አጠቃላይ የይርጋ ደንብ ድንጋጌ ከሆነው ከአንቀጽ 162/1/ አግባብ መታየት ይገባዋል። ስለሆነም የተጠቀሱት ሰዎች 16 17 በእራሳቸው መብት ላይ ተመስርተው የሚያቀርቡት ክስ በልላ ሕግ ላይ በልላ የይርጋ ደንብ ካልተሸፈነ በቀር በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162/1/ መሰረት የመብታቸውን ጥያቄ ላያቀርቡ ከሚችሉበት ጊዜ አንስቶ እስከ አንድ አመት ድረስ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል።
ከፍ ሲል እንደተመለከተው የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162 አንድ የሥራ ክርክር ጉዳይ ላቀርብ የሚችልበትን የጊዜ ወሰን አስቀምጧል። በልላ በኩል ደግሞ አንድ ጉዳይ በሕግ የተወሰነለትን የጊዜ ወሰን ጠብቆ ባይቀርብም እንኳን ላታይ የሚችልባቸው ሦስት ሁኔታዎች እንዳሉ ደንግጓል። እነዚህም ሁኔታዎች ከአንቀጽ 164 እስከ አንቀጽ 166 ባሉት ድንጋጌዎች ላይ ተጠቅሰው የሚገኙ ሲሆን እነርሱም፡የይርጋ ጊዜ መቋረጥ፣ የይርጋ መብትን መተው እና ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ጊዜው ያለፈበትን ክስ መቀበል መሆናቸው በእነዚሁ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል።
ስለ ይርጋ ጊዜ መቋረጥ ከፍ ሲል እንደተመለከተው የመጀመሪያው ሁኔታ የይርጋ ጌዜ መቋረጥን ይመለከታል። ይህ ሁኔታ የተደነገገበት የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 164 የይርጋ ጊዜ፡
በመሰረቱ አንድ ወገን ተከራካሪ በልላው ላይ ክስ መስርቶ የመገኘቱ ጉዳይ ተጀምሮ የነበረን የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር እንደሚያቋርጠው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1851/ለ/ ላይ ተመልክቷል። ለሥራ ክርክር ጉዳይ ተፈፃሚነት ያለው የአዋጅ ቁ. 42/85ም ከዚህ የፍትሐብሕር ሕግ ጋር በተስማማ ሁኔታ ክስ አቅርቦ የመገኘት ነገር የይርጋን ጊዜ አቆጣጠር እንደሚያቋርጥ በአንቀጽ 164/1/ ላይ ጠቅሶታል። የይርጋውን አቆጣጠር የሚያቋርጠው ክስ የተመሰረተውም የሥራ ክርክርን ከሚወስን ባለስልጣን ዘንድ ላሆን እንደሚገባ በንኡስ አንቀጹ በግልጽ ተደንግጓል። ይሁን እንጂ ይህ ድንጋጌ የሥራ ክርክርን እንዲወስን ኃላፊነት ለተሰጠው ባለስልጣን ሲል ማንን ለማለት ነው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ስለማይሰጥ ይህን ነጥብ ለመፍታት ይተረጎም ዘንድ ያስፈልጋል። ከአዋጅ ቁ. 42/85 አግባብ የሥራ ክርክር የሚወሰን ባለሥልጣን ላሰኝ የሚችለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በቅድሚያ " ውሣኔ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ ማየቱ ይጠቅማል። ይህ "ውሣኔ" የሚለው ቃል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 3 ላይ አንድን ክርክር የያዘ ፍርድ ቤት "… ተከራካሪዎቹ ወገኖች ያቀረቡትን ክስና መልስ እንዲሁም ማስረጃዎቹን መርምሮ …." የሚሰጠው ውሣኔ ማለት እንደሆነ ተተርጉሟል። ስለሆነም ጉዳዩ ከዚህ ትርጓሜ አኳያ ሲታይ አንድን አካል የሥራ ክርክርን የሚወስን ባለስልጣን ነው በሚል ለመፈረጅ ተቋሙ በሥራ ክርክር ጉዳይ ላይ ግራ ቀኝ ወገንን አከራክሮ ውሣኔ ለመስጠት በአዋጁ ስልጣን የአገኘ ላሆን ይገባዋል።
እንደሚታወቀው በአዋጁ መሰረት አንድም ፍርድ ቤቶች በስራቸው በተቋቋሙ የሥራ ክርክር ችሎቶች አማካኝነት፤ ልላም በየክልላዊ መስተዳድሩ የተቋቋመ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በሥራ ክርክር ጉዳይ ላይ ውሣኔ ይሰጡ ዘንድ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። ይኸንንም ከአዋጁ አንቀጽ 137-140 እንዲሁም ከ147-156 ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ላይ መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም እነዚህን ሁለት ዳኝነት 18 19 ሰጭ አካላት የሥራ ክርክርን ለመወሰን ስልጣን የተሰጣቸው አካላት ናቸው ልንላቸው እና የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 164/1/ የሥራ ክርክርን ለሚወስን ባለስልጣን ሲል አንድም ፍርድ ቤትን ልላም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድን ማለቱ ነው።
በሚል ልንተረጉመው ይገባል።
በተጨማሪም የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 164/1/ የሥራ ክርክርን ለሚወስን ባለስልጣን ክስ ማቅረብ የይርጋን ጊዜ እንደሚያቋርጥ ከሚደነግግ በቅር ክሱ ክርክሩን ለመዳኘት ስልጣን ለልለው አካል ቢቀርብ የይርጋው አቆጣጠር ምን ላሆን እንደሚገባ አላመለከተም። ለምሳል ፍርድ ቤት እና የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ሁለቱም የሥራ ክርክርን ለመዳኘት ስልጣን የተሰጣቸው አካላት ቢሆኑም ፍርድ ቤት የወል የሥራ ክርክርን፤ ቦርድ ደግሞ የግል የሥራ ክርክርን የሚመለከቱ ክሶች ይዳኙ ዘንድ በአዋጁ ስልጣን አልተሰጣቸውም። ስለሆነም እነዚህ አካላት ዘንድ የቀረበው ክስ በስልጣናቸው ላሸፈን የማይችል የሥራ ክርክር ሆኖ ቢገኝ የይርጋው አቆጣጠር ይቋረጣል? ለሚለው ጥያቄ ድንጋጌው ግልጽ ምላሽ ስለማይሰጥ ነጥቡን ለማጥራት ይቻል ዘንድ ድንጋጌው ከልላ ተዛማጅነት ካለው ሕግ ጋር ተገናዝቦ እንዲተረጎም ያስፈልጋል። በዚህ ችሎት እምነትም ለዚህ ጉዳይ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 278/3/ አግባብነት ይኖረዋል።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 278/3/ በፍርድ ቤት ፈቃድ እንደገና ስለሚቀርቡ ክሶች የይርጋ አቆጣጠር የሚደነግግ ነው። ይኸውም አንድ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ክስ በከፊልም ሆነ በሙሉ አንስቶ ከሣሹ ክሱን እንደገና እንዲያቀርብ ሲፈቅድ የይርጋው ዘመን የመጀመሪያው ክስ እንዳልቀረበ ተቆጥሮ በአዲሱ ክስ መሰረት እንደሚታሰብ ይጠቅሳል ይኸም ሁለተኛው ክስ የቀረበው የፍርድ ቤትን ፈቃድ ተመስርቶ ቢሆንም እንኳ የቀደመው ክስ የኋለኛውን ክስ የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር እንደማያቋርጠው ያስረዳናል። ሕጉ ይህን ከአልፈቀደ ደግሞ ከሣሽ ክርክሩን ለመዳኘት ከስልጣኑ ውጭ ለሆነ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ በሁለተኛ ደረጃ የመሰረተውን ክስ የይርጋ አቆጣጠር ያቋርጠዋል ማለቱ አሳማኝነት የልለው ይሆናል። የያዝነው ጉደይ ከዚህ ሕግ አግባብ ሲታይ ደግሞ አንድ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ክስ የሥራ ክርክርን ለሚወስን ባለስልጣን ቀርቦ መገኘቱ ብቻውን የይርጋውን ዘመን አቆጣጠር የሚያቋርጠው አይሆንም። ክሱ የይርጋውን ጊዜ አቆጣጠር ያቋርጠዋል ይሰኝ ዘነድ ለፍርድ ቤት ወይም ለቦርድ መቅረቡ ብቻ ሳይሆን የቀረበው የሥራ ክርክሩን ጉዳይ ለመዳኘት በሕጉ ስልጣን ላለው አካል እንዲሆን ያስፈልጋል።
ልላው የይርጋን ዘመን አቆጣጠር የሚያቆርጠው የአዋጅ ቁ. 42/85ን እንዲያስፈፅም ስልጣን ለተሰጠው አካል አቤቱታ አቅርቦ መገኘት መሆኑ በአንቀጽ 164/2/ ላይ ተመልክቷል። ይህ አካል የመጨረሻ ውሣኔ በጽሁፍ እስከሚሰጥ ድረስ ይርጋው ላቋረጥ እንደሚገባም በድንጋጌው ተመልክቷል። ይሁን እንጂ አዋጁን እንዲያስፈጽም ስልጣን የተሰጠው አካል ማን ነው? በዚህ አካል የሚተላለፈው ውሣኔስ በሕጉ አግባብ ውሣኔ ላሰኝ ይገባዋል? ለሚለው ነጥብ ምላሽ ለማግኘት ድንጋጌውን መተርጎም ይገባናል።
በቅድሚያ ሁለተኛውን ጥያቄ እናያለን። በመሰረቱ ከሕግ አግባብ "ውሣኔ" ላባል የሚገባው ምን ዓይነት ውሣኔ እንደሆነ ከፍ ሲል ተገልጿል። "ውሣኔ" ላሰጡ የሚችሉት የሥራ ክርክርን ለመዳኘት ስልጣን ያላቸው አካላት ብቻ መሆናቸውንም በችሎት ከተሰጠው ትርጓሜ መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም አዋጁን ለማስፈፀም ስልጣን በአለው አካል የሚሰጥ ውሣኔ የአስተዳደር ውሣኔ ላባል ከሚችል በቀር በሕጉ አግባብ በዳኝነቱ አካል እንደተሰጠ ውሣኔ የሚቆጠር አይደለም።
ወደ መጀመሪያው ጥያቄ ስንመለስ ጉዳዩን የሰራተኛና የማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም የክልሎች የሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሕጉ ከተሰጠው ስልጣን አኳያ መመርመሩ ተገቢነት ይኖረዋል። ይህ ሚኒስቴር በርካታ ተግባሮችን እንዲያከናውን በአዋጅ ቁ. 42/85 ስልጣን የተሰጠው ሲሆን ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ተጠቅሰዋል። ከአዋጁ አንቀጽ 119 ብንጀምር ይህ ሚኒስቴር በዚህ ድንጋጌ መሰረት 20 21 የማሕበራትን ምዝገባ ላከለክል ይችላል፤ በአንቀጽ 120 እና 122 መሰረት የማሕበራትን የመመዝገቢያ የምስክር ወረቀት በመሰረዝ ለፍርድ ቤት ይግባኝ ላቀርብበት የሚችል ውሣኔ ላያሳልፍ ይችላል፤ በአንቀጽ 20 መሰረት ሰራተኛን ከሥራ ለማገድ የተሰጠ ምክንያት በቂ በመሆን አለመሆኑ ጉዳይ ላይ ውሣኔ ይሰጣል፤ ከዚህ የሚኒስቴሩ ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለፍርድ ቤት ላቀርብ እንደሚችል ደግሞ በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 20/3/ ላይ ተመልክቷል፤ በተጨማሪም ሚኒስቴሩ በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 137/2/ መሰረት ፍርድ ቤት ዘንድ ተገቢ ብዛት ያላቸው የሥራ ክርክር ችሎቶች ይቋቋሙ ዘንድ ለተገቢው አካል ጥያቄ ለማቅረብ ይችላል፤
በአሰሪውና በሰራተኛው መካከል የወል የሥራ ክርክር ሲነሳ በንቀጽ 141 መሰረት ጉዳዩን በማስማማት ለመጨረስ አስማሚ ይመድባል፤ እንደዚሁም በአንቀጽ 178 መሰረት ስለ ሥራ ሁኔታ ቁጥጥር የሚያደርጉ የሥራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎችን ይመድባል። እነዚህ ከሞላ ጎደል የተጠቀሱት በሕጉ የተፈቀዱት የሚኒስቴሩ ተግባራት ሚኒስቴሩ በአሰሪና ሰራተኛው ግንኙነት ላይ ከፍተኛ የሆነ የአፈፃፀም ኃላፊነት እንዳለበት ያረጋግጡልናል። ልላ ከሚኒስቴሩ የተስተካከለ የአስፈፃሚነት ኃላፊነት የተሰጠው አካል አለመኖሩንም ከአዋጁ መረዳት ይቻላል። ይልቁንም ሚኒስቴሩ በአዋጁ አንቀጽ 170/1/ ላይ ሕጉን ለማስፈፀም ይችል ዘንድ በበርካታ ጉዳዮች ላይ መመሪያ የማውጣት ስልጣን እንደተሰጠው ተመልክቷል። ይህም ሚኒስቴሩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ሕግን በሥራ ላይ ለማዋልና ለማስፈጸም በአዋጁ ስልጣን የተሰጠው ብቸኛ አካል መሆኑን ያስገነዝበናል። ለዚህ አካል /በስሩ እንዲመድባቸው ስልጣን ለተሰጠው ተቋማት ጭምር/ በአዋጁ እንዲያከናውናቸው ስልጣን በአገኘበት ተግባራት ረገድ አቤቱታ አቅርቦ መገኘትም በአንቀጽ 164/2/ መሰረት የይርጋውን ዘመን አቆጣጠር የሚያቋርጠው ይሆናል።
የመጨረሻው ለይርጋ ጊዜ መቋረጥ ምክንያት የሚሆነው በአንቀጽ 164/3/ ላይ እንደተመለከተው በይርጋው ጊዜ ማለፍ ተጠቃሚ የሆነው ወገን ያልሆነውን ወገን መብት በቃል ሳይሆን በጽሁፍ ሲያውቅለት አላያም መብቱን በከፊል ፈጽሞለት ሲገኝ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ምክንያት የይርጋውን አቆጣጠር ከሦስት ጊዜ በላይ ላያቋርጠው እንደማይችል በዚሁ ድንጋጌ ላይ የተመለከተ ነው።
በእርግጥ የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 164 ሦስት አይነት የይርጋ ማቋረጫ ምክንያቶች ያስቀመጠ ቢሆንም የይርጋው መቋረጥ በይርጋ ዘመኑ አቆጣጠር ላይ ያለውን ውጤት ግን አላመለከተም። በመሆኑም የይርጋ ጊዜ መቋረጥ ምን ውጤት እንደሚያስከትል ለማወቅ አግባብነት ያለውን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1852/1/ን ከጉዳዩ ጋር አገናዝቦ መመልከት ያስፈልጋል። ይህ አንቀጽ አንድ የይርጋ ዘመን ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ "… እንደገና አዲስ የይርጋ ዘመን …" ላቆጠር እንደሚገባ ደንግጓል። ይህም ይርጋው ከመቋረጡ በፊት ተቆጥረው የነበሩት ቀናት እንዳለ ቀሪ እንደሚሆኑና የይርጋው ጊዜ እንደገና እንደ አዲስ ተብሎ ላቆጠር እንደሚገባ ያስገነዝበናል።
በመሆኑም በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 164 በተመለከቱት ሁኔታዎች ሳቢያ አንድ የይርጋ ጊዜ መቋረጡ ቢረጋገጥ ቀጣዩ የይርጋ ዘመን ይኸን ከፍ ሲል የተጠቀሰውን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1852/1/ የተመለከተውን አቆጣጠር ይከተል ዘንድ ያስፈልጋል።
በመሰረቱ አንድ የሥራ ክርክር ክስ የቀረበበት ወገን ክሱ የይርጋ ጊዜው ያለፈበት ነው ሲል ቢቃወም በእርግጥ ክሱ ጊዜው ያለፈበት ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ የጉዳዩ ጭብጥ ሆኖ እንደሚያዝ ይታመናል። ለዚህ ጭብጥ መመስረት ምክንያት የሆነው ክርክር የቀረበው በተከሣሹ በመሆኑም የይርጋውን ጊዜ ማለፍ ያስረዳ ዘንድ ይገባዋል። በልላ በኩል ደግሞ ክሱን ያቀረበው ወገን የይርጋው ጊዜ ተቋርጧል የሚል 22 23 ክርክር የሚያነሳ ቢሆን ይህን ሙግቱን በቅድሚያ ያስረዳ ዘንድ ይጠበቅበታል።
በተጨማሪም የሥራ ክርክር ጉዳይ የቀረበለት ፍርድ ቤት ከሣሹ አስቀድሞ በአዋጅ ቁ. 42/85 መሰረት ጉዳዩን ለመዳኘት ስልጣን ለተሰጠው ፍርድ ቤት ወይም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ማቅረቡን ከአረጋገጠ በአዋጁ አንቀጽ 164/1/ መሰረት የይርጋውን ዘመን መቋረጥ ላቀበለው ይገባል። ከተጠቀሰው የሕጉ መስፈርት ውጭ የሆኑ ምክንያቶችን ለውሣኔው መሰረት ላያደርግ አይችልም።
ለምሳል ያህል ክሱ ላቀርብ የሚገባው ለሥራ ክርክር ችሎቱ ነበር በሚልና በመሳሰለ ምክንያት የይርጋውን አቆጣጠር መቋረጥ አልቀበልም ላል አይችልም።
በልላ በኩል ደግሞ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን ለማስፈፀም ስልጣን የተሰጠው ሚኒስቴሩ ብቻ መሆኑ ከላይ ተመልክቷል። ስለሆነም ክርክሩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ከሣሹ ለዚህ ሚኒስቴር /በስሩ ለሚመድባቸው ተቋማት ጨምሮ/በስልጣኑ ክልል አቤቱታ አቅርቦ እንደነበር ከአረጋገጠ የይርጋውን ዘመን በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 164/2/ መሰረት ላያቋርጠው ይገባል። ከዚህ ውጭ ለሆነ አካል አቤቱታ መቅረቡ መረጋገጡ ግን የይርጋውን ጊዜ አቆጣጠር የሚያቋርጠው አይሆንም። ለምሳል ያህል አንድ ከሣሽ ሰራተኛ ለአሰሪው መ/ቤት አቤቱታ አቅርቤ ውጤቱን ስጠባበቅ ነበር ሲል መከራከሩንና ይህንንም ማረጋገጡን ፍርድ ቤቱ ለይርጋው ዘመን አቆጣጠር ማቋረጫ አድርጎ ላወስድለት አይችልም።
የይርጋ መብትን ስለመተው እንደሚታወቀው በአዋጅ ቁ. 42/85 ውስጥ የተመለከተው የይርጋ ሕግ በፍሬ ነገር ሕግ /Substantive law/ ላይ እንጂ በሥነ ሥርዓት ሕግ /Procedural law/ ላይ የተቀመጠ የይርጋ ደንብ አይደለም። በፍሬ ነገር ሕግ /Substantive law/ ላይ የሚገኝ የይርጋ ደንብ ደግሞ በተከሣሹ ወገን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ላቀርብ የሚገባው ነው።
ተከሣሹ በመቃወሚያነት አንስቶ ከአልተከራከረበት በቀር ፍርድ ቤት በእራሱ አነሳሽነት ጉዳዩ የይርጋ ጊዜ ያለፈበት መሆን አለመሆኑን አጣርቶ እና ሕጉን ጠቅሶ ፍርድ ላሰጥበት አይችልም። ስለሆነም አንድ የሥራ ክርክር ክስ የተመሰረተበት ተከሣሽ የይርጋውን ክርክር በመቀወሚያነት ካላነሳው በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 165 አግባብ በዚህ ረገድ የመከራከር መብቱን እንደተወው ይቆጠራል። በውጤቱም በሕግ የተወሰነለትን ጊዜ አሳልፎ የቀረበው ክስ በይርጋ ምክንያት ውድቅ ሳይደረግ ወደ ጉዳዩ ፍሬ ነገር ተገብቶ የመዳኘት እድልን ያገኛል።
ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት አንድ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ክስ የይርጋ ጊዜውን አሳልፎ ቢቀርብ እና ይህ የሆነው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑ በውሣኔ ሰጭው አካል ቢረጋገጥ ምንም እንኳን ክሱ ጊዜው ያለፈበት ቢሆንም ላታይ እንደሚገባ በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 166 ላይ ተደንግጓል። የተጠቀሰው ምክንያት በተወገደ በአስር ቀን ውስጥ ያልቀረበ ክስ ግን ተቀባይነት እንደማያገኝ በዚሁ ድንጋጌ ላይ ተመልክቷል።
በግልጽ እንደሚታየው ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከፍ ሲል በተጠቀሰው ድንጋጌ አልተተረጎመም። ስለዚህም ጉዳዩን ይህን ሐሳብ ከሚተረጉመው የፍትሐብሕር ሕግ አንቀጽ 1792 ጋር አገናዝቦ መመልከት ያስፈልጋል። በዚህ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1792 እንደተደነገገው ከዓቅም በላይ የሆነ ላመልሱት የማይቻል ኃይል ደርሷል የሚባለው አንድ ባለእዳ ባላሰበው ነገር ድንገት ደራሽ ሆኖበት ግድታውን እንዳይፈጽም ፍጹም መሰናክል በሆነ ዓይነት የሚያግደው ነገር ባጋጠመው ጊዜ ነው።
ጉዳዩ ከዚህ ትርጉም አኳያ ሲታይ አንድን የሥራ ክርክር ክስ ጊዜው ላያልፍበት የቻለው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በሚል 24 25 ለመፈረጅ ክሱ ቀድሞ ላታሰብ በማይችል እና ከሣሹም ፍጽም የሆነ መሰናክል የገጠመው በመሆኑ ምክንያት ብቻ በጊዜው ሳይመሰረት መቅረቱ ሲረጋገጥ ነው።
ይሁን እንጅ ይህ ትርጓሜ እነዚህ ምክንያቶች ምን አይነት ምክንያቶችን ይመለከታል? የሚለውን ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀሬ ይሆናል። የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 166 ከአቅም በላይ ላሰኙ የሚችሉ ምክንያቶችን ያላመላከተን በመሆኑም ለዚህ ጉዳይ እንደገና ወደ ፍትሐብሕር ሕጉ ድንጋጌዎች መመለስ ያስፈልገናል።
የፍትሐብሕር ሕጉ በቁጥር 1793 ላይ ከአቅም በላይ ላሰኙ የሚችሉ ምክንያቶችን በመዘርዘር አስቀምጧል። እነርሱም፡ሀ/ ባለእዳው አላፊ የማይሆንበት ያልታሰቡና በልላ ሰው ላይ የሚመጡ ድንገት ደራሽ ነገሮች፣ ለ/ ውሉ እንዳይፈጸም በመንግሥት የሚደረግ ክልከላ፣ ሐ/ እንደ መሬት መናወጽ፣ መብረቅ፣ ማእበል ይህን የመሳሰለ ፍጥረታዊ መቅሰፍት፣ መ/ የጠላት የውጭ አገር ጦርነትና የአገር ውስጥ ጦርነት፣ ሰ/ የባለእዳው መሞት ወይም ባልታሰበ ሁኔታ የሚደርስበት ከባድ አደጋ ወይም ጽኑ ሕመም /መሆናቸው ተመልክቷል/።
እንግዲህ ከሣሽ ክሱን በጊዜው ያልመሰረተበት ምክንያት ከፍ ሲል በተጠቀሰው ድንጋጌ በተመከቱት ምክንያቶች ስር የሚሸፈን ከሆነ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ገጥሞታል የሚሰኝ ይሆናል። ዳኝነት ሰጭው አካልም ይህንን ከአረጋገጠ ጊዜው ያለፈበትን ክስ ተቀብሎ ወደ ፍሬ ጉዳዩ በመግባት ፍርድ ይሰጥበት ዘንድ ይገደዳል።
ከላይ እንደተገለፀው የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 166 " ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት "ማለት ምን ማለት እንደሆነ አልተረጎመም። እነዚህ ምክንያቶች ምን አይነት ላሆኑ እንደሚገባም አላመለከተም። ነገር ግን በይርጋ የታገደን ክስ ለመቀበል" በቂ ምክንያት" ተደርገው የሚወሰዱ ምክንያቶችን አመላክቷል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው።
ሀ/ የሰራተኛ መታመም፣ ለ/ የሰራተኛው በትእዛዝ ከመደበኛ የመኖሪያ ሥፍራ ውጭ መዛወር ሐ/ የሰራተኛው ከብሕራዊ ጥሪ ላይ መገኘት እነዚህ በድንጋጌው የተመለከቱት ውስን ምክንያቶች በሰራተኛው የቀረበው ክስ በይርጋ የታገደ መሆኑ ቢታይም ተቀባይነት ያገኝለት ዘንድ የሚፈቅዱ ናቸው። እንዲሁም እነዚህ እክሎች የገጠሙት ሰራተኛ ጉዳይ በዳኝነት አካል ሳይታይለት እንዳይቀር ልዩ የሆነ ጥበቃ የማድረግን ነገር አላማ ማድረጋቸውን ከድንጋጌው መረዳት የሚቻል ነው።
በእርግጥ እነዚህ ምክንያቶች በሰራተኛው ክስ ተጠቅሰው መገኘታቸው ብቻውን ጊዜው ያለፈበትን ጉዳይ ለመቀበል የሚበቃ አይሆንም። ይህን ማድረግም ከድንጋጌው አላማ ጋር የተጣጣመ መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ አይረዳንም። ስለሆነም ሰራተኛው ጊዜው ያልፈበትን ክስ ቢያቀርብ እና ጉዳዩ ከዚህ ድንጋጌ አግባብ እንዲታይለት ቢጠይቅ መታመሙን ወይም በትእዛዝ ከመኖሪያ ሥፍራው መዛወሩን ወይም በብሕራዊ ጥሪ ላይ የነበረ መሆኑን የሚያሳይለትን ማስረጃ በማቅረብ በቅድሚያ ክርክሩን ያስረዳ ዘንድ ያስፈልጋል። ጉዳይ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የምክንያቱን ተገቢነት በግራ ቀኙ ከቀረበለትም ሆነ በእራሱ አነሳሽነት ከአስመጣው ማስረጃ አኳያ ላመረምረው ይገባል ፍርድ ቤቱ ይህን ሲያደርግም እነዚህ ምክንያቶች ሰራተኛው ክሱን እንዳይመሰርት መስናክል የሆኑበትን መጠን ጭምር ከግምት እንዲያስገባ ያስፈልጋል። በውጤቱም ፍርድ ቤቱ እነዚህ ምክንያቶች ከሣሹ ክሱን ላመሰርት በማይችልበት ደረጃ ላይ አድርሰውት ነበር ሲል የሚያምንበት ላሆን ይገባዋል። ይህ ካልሆነ ግን ፍርድ ቤቱ በይርጋ የታገደውን ክስ ከወዲሁ ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል።
26 27 አሁን በዚህ መዝገብ ወደተያዘው ክርክር እንመለሳለን። በዚህ ውሣኔ መግቢያ ላይ እንደተመለከተው ተጠሪዎች ለቦርድ አቅርበውት የነበረው ክስ ለልሎች ሰራተኞች የተደረገው የሁለት እርከን ጭማሪ ለእኛም ላሰጠን ይገባል የሚል ሲሆን አመልካችም ክሱ በይርጋ ላታገድ ይገባዋል በማለት ተቃውሞውን አቅርቦ የተከራከረበት ነው።
በመሰረቱ ይህ የተጠሪዎቹ ጥያቅ የክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ነው።
እንዲሁም የክፍያ ጥያቄው በመካከላቸው ያለው የሥራ ውል ፀንቶ በአለበት ጊዜ የተነሳ እንጂ የሥራ ውል መቋረጥን ተከትሎ የቀረበ አይደለም። በእነዚህ ምክንያቶች የይርጋው አቆጣጠር ጉዳይ በተለይ ከተደነገገው የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162/3/ አግባብ ላታይ የሚገባው ነው።
በዚህ የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162/3/ መሰረት የተጠቀሰው የክፍያ ጥያቄ ላጠየቅ ከሚገባው ጊዜ ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ ካልተጠየቀ በይርጋ ላታገድ የሚገባው ነው። ተጠሪዎች ይህ የሁለት እርከን ጭማሪ ለልሎች ሰራተኞች ተደርጓል የሚሉት መጋቢት 15 ቀን 1992 ዓ.ም. እንደነበር ከስር ውሣኔ ላይ መረዳት የሚቻል ነው። ክሳቸውን ለቦርድ ያቀረቡት ደግሞ ነሐሴ 15 ቀን 1993 ዓ.ም. መሆኑ በስር ውሣኔ የተመለከተ ነው። በዚህ ችሎት እምነት አመልካች ለልሎቹ ሰራተኞች ጭማሪውን አድርጓል መባሉ በስር ክርክር በተጠሪዎች ጭምር የታመነበት መጋቢት 15 ቀን 1992 ዓ.ም. ክፍያው በተጠሪዎች ላጠየቅ የሚገባበት ጊዜ እንደሆነ ተደርጎ ላወሰድ የሚገባው ነው። የተጠሪዎቹ ክስ የቀረበው ከዚህ ጊዜ በኋላ ከአንድ ዓመት በላይ ቆይቶ በመሆኑም ከፍ ሲል በተጠቀሰው ድንጋጌ መሰረት በስድስት ወሩ ይርጋ ላታገድ የሚገባው መሆኑ የማያከራክር ነው።
በእርግጥ ተጠሪዎች የእርከን ጭማሪው ለልሎቹ ሰራተኞች የተደረገው መጋቢት 15 ቀን 1992 ዓ.ም. አይደለም። ይኸ ቀን ጭማሪ መደረጉ ለሰራተኞች ይፋ የተደረገበት ቀን ነው። ይሁን እንጂ የካቲት 8 ቀን 1993 ዓ.ም. ለልሎቹ ሰራተኞች ተጠቃሚ መሆናቸው ሲፃፍላቸው ለተጠሪዎች ግን ይኸ ባለመደረጉ የካቲት 27 ቀን 1993 ዓ.ም. ለኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቤቱታ በማቅረባችን የይርጋው አቆጣጠር ተቋርጧል በማለት በስር ፍርድ ቤቶች ያላነሱትን ክርክር ለዚህ ችሎት አቅርበዋል። በመሰረቱ ይኸ የተጠሪዎቹ ክርክር በዚህ ችሎት የቀረበ አዲስ የክርክር ነጥብ በመሆኑ ዳኝነት ላሰጥበት የሚገባ አልነበረም። ይኸ ቢታለፍ ደግሞ አሁንም ተጠሪዎቹ ልሎቹ ሰራተኞች የእርከን ጭማሪው ተጠቃሚ መሆናቸው ሲፃፍላቸው ለእኛ ይህ ሳይደረግ ቀርቷል ከሚሉበት ከየካቲት 8 ቀን 1993 ዓ.ም. ጀምሮ በስድስት ወራት ውስጥ ማለትም እስከ ነሐሴ 8 ቀን 1993 ዓ.ም. ክሱን ላመሰርቱ ሲገባ ይህን አድርገው ባለመገኘታቸው ይህም ክርክራቸው የይርጋውን ጊዜ ማለፍ የሚያረጋግጥባቸው ነው። እንዲሁም ይህ ችሎት ለአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 164/2/ ከሰጠው ትርጓሜ አግባብ የአመልካች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቤቱታ ማቅረብ አዋጁን እንዲያስፈጽም ስልጣን ለተሰጠው አካል አቤቱታ እንደማቅረብ ስለማይቆጠር ይኸ ተጠሪዎቹ ፈጽመነዋል ያሉት ድርጊትም የይርጋውን ጊዜ አቆጣጠር የሚያቋርጠው ሆኖ አልተገኘም።
ው ሣ ኔ 1ኛ/ ተጠሪዎች በአመልካቹ ላይ የመሰረቱት ክስ በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 162/3/ መሰረት በይርጋ ላታገድ ይገባል።
2ኛ/ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ እና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደቅደም ተከተላቸው በመ.ቁ. 171/02/93 እና በመ.ቁ.28793 የአመልካችን የይርጋ ክርክር ውድቅ አድርገው የአንድ እርከን ጭማሪ ለተጠሪዎች እንዲከፍል የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
No topics extracted.