የሰበር መ/07 /ንብ ትራንስፖርት A.ማ እእና አአቶ ተገኑ መሸሻ/ በድርጅት ውስጥ የስራ መሪ የሆነ የሰራተኛ ከአሰሪው ጋር ያለው የስራ ክርክር በፍትሐብሕር ህጉ የስራ አአገልግሎት መስጠትን ስለማመለከቱ ውሎች ክፍል የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ሲሆን የስራ ውሉ ተቋርጦ የስራ መሪው ስራ ላልሰራበት ጊዜ ደመወዝ የሚያገኝበት የህግ ምክንያት ስላለመኖሩ/ ............................................ 141 የሰበር
No summary available.
ጥቅምት 25 ቀን 1998 ዳኞች፡
በድርጅት ሥራ መሪና በድርጅቱ መካከል ያለ የስራ ክርክር የሚዳኘው በፍትሐብሕር ህጉ የስራ አገልግሎትን መስጠት ስለማመለከቱ ውሎች ከቁጥር 2512 እና ተከታታዮቹ በተደነገጉት ህጐች መሰረት ነው።
የስራ መሪ ደመወዝ ለተሰራ ስራ ብቻ የሚከፈል እንጂ ላልተሰራ ስራ የሚከፈል አይደለም።
የስራ መሪው አንድም የስራ አገልግሎት ባይሰጥም እንኳን ይኸው ሁኔታ አሰሪው ስራ ሳይሰጠው በመቅረቱ ወይም እንዳይሰራ በመከልከሉ የተነሳ እንደሆነ ደመወዙን ለማግኘት መብት የለው ውሉ ባልታገደበት ወይም ባልተቋረጠበት ጊዜ ሰራተኛው /የስራ መሪው/ ስራ ላይ ሆኖ ነገር ግን አሰሪው ሥራ ሳይሰጠው ወይም እንዳይሰራ በከለከለው ጊዜ እንጂ ሰራተኛው ከስራና ከደመወዝ ታግዶ የስራ አገልግሎት ላልሰጠባቸው ጊዜያት አይደለም።
143 144
ጥቅምት 25 ቀን 1998 ዳኞች፡
በሥር ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ከሣሽ ሲሆን አመልካቹ ተከሣሽ ነበር።
የተሰጠው የሥራ ክስ በድርጅቱ ውስጥ የቴክኒክ ዋና ክፍል ሀላፊ ሆኜ ስሰራ ከታህሣሥ 23/94 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ ታግጄ ከቆየሁ በኋላ ሰኔ 5/95 የተፃፈ የስንብት ደብዳቤ ተሰጥቶኛል ስለዚህ ከታገድኩበት ጊዜ አንስቶ እስከተሰናበትኩበት ጊዜ ድረስ ያለው የ17 ወር ከ15 ቀን የተጣራ ደመወዜ 23.500 (ሃያ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ወጪና ኪሣራ ተጨምሮ ይከፈለኝ የሚል ነው።
የሥር ተከሳሽ ማለትም ተጠሪው ቀርቦ የይርጋ መቃወሚያ አንስቶ በብይን ውድቅ የተደረገበት ቢሆንም ፍሬ ጉዳዩን በተመለከተ ከሣሽ ከሥራ የተሰናበተው ድርጅቱን የሚጐዳ ተግባር የፈፀመ መሆኑን በመግለጽ ሥራ ላልሰራበት ጊዜ ደመወዜ ላከፈለው እንደማይገባ ይከፈለው ቢባል እንኳ ከ3 ወር ደመወዝ ላበልጥ እንደማይችል በመግለጽ ተከራክሯል።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ከሣሽ የሥራ መሪ እንደመሆኑ በፍ/ህጉ ላይ የሥራ መሪን ከሥራ ስለማገድ የተደነገገ ድንጋጌ የለም፣ በድርጅቱ የውስጥ ደንብ ስለመኖሩና በውስጥ ደንቡ መሰረት ስለማገዱ አላስረዳም በመልስ የዘረዘራቸውን ተግባራት ከሣሽ ፈጽመዋል ቢባል እንኳ ከሥራና ከደመወዝ ለማገድ በቂ ምክንያቶች አይደሉም በፍ/ሕ/ቁጥር 2574/1 ሰራተኛው አገልግሎት ባይሰጥም ይህ የሆነው በአሰሪው ምክንያት ከሆነ ደመወዝ የመክፈል ግድታ አለበት፣ የ3 ወር 145 146 ደመወዝ ብቻ ላከፈላቸው ይገባል የሚለው የተከሣሽ ክርክር በፍ/ሕ/ቁጥር 2574/2/ የተመለከተው የ3 ወር ደመወዝ ክፍያ የሥራ ውሉ ለተቋረጠበት እንጂ የሥራ ውሉ ለታገደበት ጊዜ የሚመለከት አይደለም በማለት ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ተከሣሽ ለከሣሽ እንዲከፍል ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካቹ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርብም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙ ተሰርዞበታል።
አመልካቹ የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት ይታረምልኝ ሲል በ14/5/97 የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።
የአቤቱታው ፍሬ ቃል ተጠሪው በ5/10/95 እና በ5/2/95 ተጽፎ የተሰጣቸው ደብዳቤ የሥራ ስንብት ሣይሆን የሥራ ልምድ የምስክር ወረቀት መሆኑን የሥር ፍ/ቤት በአግባቡ አልመረመረም።
አመልካች ተጠሪን ከሥራ ለማገድ ምክንያት ያደረገው በድርጅቱ ሥራና ገንዘብ ላይ በተለያዩ ጊዜያት ጉዳት ማድረሣቸውን የሚያመለክቱ ናቸው። ፍ/ቤቱ የፍ/ሕ/ቁጥር 2575 ስለ ሥራ ውል መቋረጥ እንጂ ስለ ሥራ ውል ማገድ የሚመለከት አይደለም ያለው ያለአግባብ ነው፣ ተጠሪው በእገዳ ላይ ለቆዩበት ጊዜ ሥራ እንዳይሰሩ የከለከላቸው ድርጅቱ ነው ተብሎ ደመወዙ ይከፈለው መባሉ ስህተት ነው ምክንያቱም የፍ/ሕ/ቁጥር 2540 ሥራ ላልተሰራባቸው ቀኖች ሰራተኛው ደመወዝ ለማግኘት መብት የለውም የሚለውን የሚቃረን ነው። የፍ/ህግ ቁጥር 2574/2/ ከ3 ወር የማይበልጥ ክፍያ እንዲከፈል የደነገገው የሥራ ውል ሲቋረጥ ብቻ ነው ተብሎ የተሰጠው ትርጉም ስህተት ነው በአጠቃላይ የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ሥህተት ያለበት ስለሆነ ውሣኔዎቹ ተሽረው ወጪና ኪሣራ ተከፍሎን እንሰናበት የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታ ማመልከቻው ለተጠሪው ደርሶ ሚያዝያ 19/1997 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ የአመልካች የሰበር አቤቱታ የሕግ ስህተት መፈፀሙን አይገልጽም፣ የ6 ወር የጊዜ ገደብ የከሣሽን የጥቅም ጥያቄ በይርጋ አያግደውም፣ ተጠሪው በጥፊት ተከስሼ አላውቅም፣ ባልተቀጣሁበት ጉዳይ ጥፋት ነው ተብሎ ለሰበር አቤቱታ መቅረቡ 147 148 ያለአግባብ ነው፣ ተጠሪ በ5/10/95 እና በ5/2/95 የተፃፈው የሥራ የምስክር ወረቀት እንጂ የሥራ ስንብት ደብዳቤ አይደለም ያሉት የፍሬ ነገር ክርክር እንጂ የህግ ስህተት መሆኑን አያመለክትም፣ አመልካች መ/ቤት ከሥራና ከደመወዝ ያለበቂ ምክንያት አግደውና አሰናብተው ስለአጉላሉኝ በደሉ ታይቶ የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት ሳይሆን የፍሬ ነገር ክርክር ነው፣ በፍ/ሕግ ቁጥር 2540 ሥራ ላልሰራባቸው ቀኖች ደመወዝ ላከፈለው አይገባም ለተባለው ተጠቃሹ ህግ ሰራተኛው ሥራውን በራሱ ፍላጐት ሣይሰራ ሲቀር እንጂ አሰሪው ሥራ ሲከለክለው የሚጠቀስ አይደለም፣ የፍ/ሕግ ቁጥር 2574/2/ ለኪሣራ እንጂ ውዝፍ ደመወዝን የሚመለከት አይደለም፣ ከዚህ ጉዳይ ጋርም ግንኙነት የለውም ስለሆነም ጥያቄው ከበቂ ኪሣራ ጋር ተሰርዞ እንድሰናበት በማለት ሲከራከር አመልካቹ አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን አቅርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የቀረበው ክርክር ከፍ ብሎ በዝርዝር የተመለከተው ሲሆን፣ በኛ በኩል ተጠሪው ከሥራ ታግዶ ለቆየበት ጊዜ ደመወዙ ይከፈለው መባሉ ተገቢ መሆን አለመሆኑን አግባብ ካላቸው ሕጐች ጋር በማገናዘብ መርምረናል። ተጠሪው በአመልካቹ ድርጅት ውስጥ የሥራ መሪ ሆኖ ሲሰራ የነበረ በመሆኑ የአመልካችና የተጠሪው የሥራ ክርክር የሚዳኘው በፍትሐብሕር ሕጉ በአንቀጽ 16 የሥራ አገልግሎትን መስጠት ስለሚመለከቱ ውሎች ከቁጥር 2512 እና ተከታታይዎቹ በተደነገጉት ሕጐች መሰረት ነው።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሰሪን የሥራ ውል ስለማቋረጥ እንጂ አሰሪን ከሥራ ስለማገድ በፍ/ብሕር ሕጉ የተቀመጠ ድንጋጌ የለም ካለ በኋላ በፍ/ሕግ ቁጥር 2541/1/ መሰረት አመልካቹ ተጠሪውን ከሥራና ከደመወዝ አግዶ ለቆመባቸው ወራቶች ደመወዙን ይክፈለው ሲል ወስኗል።
በመሰረቱ ከፍ/ሕግ ቁጥር 2534 ድንጋጌ በግልጽ መረዳት የሚቻለው ደመወዝ ለተሰራ ሥራ ብቻ የሚከፈል እንጂ ላልተሰራ ሥራ የሚከፈል አይደለም።
የፍ/ብሕር ሕግ ቁጥር 2540 ይህንኑ የሕጉን መርህ በመከተል ሥራ ላልተሰራባቸው ጊዜያት ወይም ቀናት ሰራተኛው ደመወዝ ለማግኘት መብት የለውም በማለት ግልጽ ድንጋጌ አስፍሮ ይገኛል።
149 150 ይሁንና የፍ/ሕግ ቁጥር 2541/1/ ሰራተኛው አንድም የሥራ አገልግሎት ባይሰጥም እንኳን ይኸው ሁኔታ አሰሪው የሥራ ሣይሰጠው በመቅረቡ ወይም እንዳይሰራ በመከልከሉ የተነሣ የሆነ እንደሆነ ደመወዙን ለማግኘት መብት አለው ሲል ሰራተኛው የሥራ ውሉ ባልታገደበት ወይም ባልተቋረጠበት ጊዜ ሥራ ላይ ሆኖ ነገር ግን አሰሪው ሥራ ሣይሰጠው ወይም እንዳይሰራ በከለከለው ጊዜ የሚያገለግል እንጂ ሰራተኛው ከሥራና ከደመወዝ ታግዶ የሥራ አገልግሎት ላልሰጣባቸው ጊዜያት ደመወዝ እንዲከፈለው የሚፈቅድ ድንጋጌ አይደለም።
ስለሆነ የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ብቻ ብለው በተመለከቱት የፍ/ብሄር ድንጋጌዎች አተረጓጐም ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመባቸው በመሆኑ ላሻሩ ይገባል ብለናል።
ውሣኔ የፍ/ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ በ5/5/97 የሰጠው ውሣኔ እና የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 1119 በ1-2-97 የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት የተሻሩ ስለሆነ የውሣኔው ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረሳቸው መዝገቡ ተዘግቷል
No topics extracted.