የሰበር መ/12 የአዲስ አአበባ ከተማ አአስተዳደር ጽ/ቤት እእና የወ/ሮ ሳዲያ እእስማኤል ወራሾች/ - /በተሰረዘ የባለሀብትነት ምስክር ወረቀት የሚገኝ የባለሀብትነት መብት ስላለመኖሩ/
No summary available.
ጥቅምት 16 ቀን 1998 ዳኞች፡
ው ሣ ኔ፡ - የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያጸናው ብይን በአብላጫ ድምፅ ተሽሯል።
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን በማወቅ በአስተዳደር ክፍል ለአንድ ሰው የተሰጠ የባለሀብትነትን የምስክር ወረቀት ማስረጃ የተሰጠው ሰው የዚሁ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት እንደሆነ ይቆጠራል።
ማስረጃው የተሰጠው ከደንብ ውጭ በሆነ አሰራር መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ከፍ/ብ/ህ/ቁ.1195 የተመለከተው የሕላና ግምት ፈራሽ ይሆናል።
በተሰረዘ የባለሀብትነት ምስክር ወረቀት የሚገኝ የባለሀብትነት መብት አይኖርም።
133 134
ጥቅምት 16 ቀን 1998 ዳኞች፡
በሰበር ችሎቱ ለቀረበው ክስ መነሻ የሆነው ጉዳይ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች በስር በመቃወም አመልካች በመሆን የሥር ፍ/ቤት ታህሣሥ 6 ቀን 1995 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ውሣኔ ላይ የተቃውሞ አቤቱታ በማቅረቡ ነው። ይዘቱም ተቃውሞ በቀረበበት ፍርድ ተከሣሽ የሆኑት አቶ አማን መሐመድ ከመቃወም አመልካች በውል ተከራይተው የሚነግድበትን በወ.5 ቀበል 9 የቤት ቁ. 797 እና 798 የሆኑትን ንግድ ቤቶች ተቃውሞ በቀረበበት ፍርድ ከሣሽ የሆኑት ወ/ሮ ሳዲያ የግል ንብረቶች ናቸው በሚል ተከሣሽ ቤቶቹን ለቀው ለከሣሽ እንዲያስረክቡ እንዲሁም ከየካቲት 7 ቀን 1994 ጀምሮ ያለውን ኪራይ እንዲከፍል በማለት ውሣኔ በመስጠቱ ነው። በመቃወም አመልካች ቤቶቹ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሱ ላለፉት 28 አመታት ለአቶ አማን መሐመድ አከራይቶ ሲጠቀም መቆየቱንና ለከሣሽ ተሰጥቶ የነበረው 6 የሆነ የባለቤትነት ደብተር በአ/አበባ አስተዳደር ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ የቤቶች ጉዳይ መምሪያ የተሰረዘ መሆኑን በመግለጽ ተከራክሮ የቆየ ቢሆንም ፍ/ቤቶቹ ስለ መወረሳቸው የሚያረጋግጥ የመረካከቢያ ቅጽ አልቀረበም በማለት የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አድርጐታል።
ጉዳዩ በይግባኝ በፍ/ከ/ፍ/ቤት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም በተመሣሣይ ሁኔታ የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል።
135 136 የአሁን አመልካች በሰበር አቤቱታው የፍ/ከ/ፍ/ቤት በተሰረዘና ተቀባይነት በልለው ማስረጃ ላይ ተንተርሶ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብሎ ያቀረበው ማመልከቻ የሕግ ትርጉም የሚያስነሳ ነጥብ ያለው መሆኑን በማመን ጉዳዩ ለሰበር እንዲቀርብ ተደርጓል። የተጠሪ መልስና የአመልካች የመልስ መልስ እንዲቀርብ ተደርጓል።
ይህ የሰበር ችሎት ጉዳዩን መርምሯል። በዚህ ጉዳይ የሕግ ትርጉም የሚያስፈልገው ነጥብ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን በማወቅ በአስተዳደር ክፍል የተሰጠ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት በተሰረዘ ጊዜ ውጤቱ ምን ይሆናል? የሚለው ነው።
በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1195 ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባሀብትነትን በማወቅ በአስተዳደር ክፍል ለአንድ ሰው የተሰጠ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ ለተሰጠው ሰው ለዚሁ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት እንደሆነ እንደሚያስቆጥረው ተመልክቷል። በአንፃሩ ማስረጃው የተሰጠው ከደንብ ውጭ በሆነ አሰራር መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ከፍ ብሎ በፍትሐብሕር ቁጥር 1195 ላይ የተመለከተው የሕላና ግምት ፈራሽ እንደሚሆን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1196/1/ ይደነግጋል። በያዝነው ጉዳይ በሕግ አግባብ ሥልጣን ተሰጥቶት ይህን መሰሉን የባለሀብትነት ማስረጃ የሚሰጠው ክፍል 6 የሆነውን የባለቤትነት ደብተር የሰረዘው መሆኑ ተረጋግጧል። በተሰረዘ የባለሀብትነት ምስክር ወረቀት ደግሞ የሚገኝ የባለሀብትነት መብት አይኖርም። የተጠሪ ወራሾችም አውራሻቸው ያልነበራቸውን መብት ላወርሱ አይችሉም። የሥር ፍ/ቤት ከፍ ሲል በተጠቀሱት የሕግ ቁጥሮች መሰረት የባለሀብትነት የምስክረ ወረቀቱ የተሰረዘ መሆኑን የተረዳው ቢሆንም የባለቤትነት ደብተሩ መሰረዝ ለአሁኑ አመልካች የሚሰጠው መብት የለም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው በማለት ይህን ፍርድ በድምጽ ብልጫ ሰጥተዋል።
ውሣኔ
137 138
የሐሳብ ልዩነት በአንድ ክርክር ውስጥ ተካፋይ መሆን የሚገባው ወይም በክርክሩ ለመግባት የሚችል እና በክርክሩ ሳይካፈልበት የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካበት ማናቸውም ሰው ፍርዱ ከመፈፀሙ በፊት መቃወሚያ ላያቀርብበት እንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 ላይ ተደንግጓል። ከዚህ ድንጋጌ አግባብ አንድ አመልካች ፍርድ ከመስጠቱ በፊት በነበረው ክርክር ተካፋይ ላደረግ ይገባው ነበር፤ አላያም ሳይሟገትበት የተሰጠው ፍርድ የእርሱን መብት የሚጎዳ ሆኖ ተገኝቷል ይሰኝለት ዘንድ ለአብቱታው የአቀረበው ማስረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጠለት እንዲሆን ያስፈልጋል።
በዚህ በተያዘው ጉዳይ አመልካች በወረዳ 5 ቀበል 19 ውስጥ የሚገኙትን ቁጥር 797 አና 798 የሆኑ የንግድ ቤቶች የተጠሪዎች አውራሽ እንድትረከብ በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠው ፍርድ መብቴን የሚጎዳው ነውና ገብቼ ተከራክሬ ፍርዱን እንዳሽር ይፈቀድልኝ ሲል ይህን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 በመጥቀስ አቤቱታው ለተጠቀሰው ፍ/ቤት አቅርቧል። በቤቶቹ ላይ መብት አለኝ የሚለው ደግሞ በመንግሥት የተወረሱ ናቸው በሚል መሆኑን መዝገቡ ያስረዳል። ይሁን እንጂ ቤቶቹ በመንግሥት የተወረሱ መሆናቸውን የማያሳይለት ማስረጃ አላቀረበም።
የአቀረበው ሙግትም ይህ ማስረጃ አለኝ ወይም ነበረኝ በሚል አይነት ፍሬ ነገር ላይ የተመሰረተ አይደለም። በልላም በኩል ንብረቱ ባለቤት የልለው ጠፍ የሆነ ንብረት ነው የሚል ክርክርና ማስረጃ የልለው በመሆኑ ጉዳዩ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1194 አግባብ ላታይና የቤቶቹ ባለቤት መንግሥት ነው ላባል የሚችል አይደለም። ለተጠሪዎች አውራሽ ተሰጥቶ የነበረው የባለቤትነት ደብተር ተሰርዟል ማለቱ ብቻውንም ለእርሱ መብት የሚሰጠውና አቤቱታውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 አግባብ እንዲስተናገድለት ለማድረግ የሚያስችል አይደለም።
በኔ እምነት የስር ፍርድ ቤቶች ወደ ዋናው ጉዳይ ተመልሰው ክርክሩን እንደገና መመርመር ሳያስፈልጋቸው አመልካቹን ወደ ክርክሩ ለመግባት የሚያስችልህ መብት መኖሩን አላስረዳህም በሚል ከወዲሁ 139 140 ጥያቄውን ውድቅ በማድረጋቸው የፈፀሙት የሕግ ስህተት የለም።
ስለሆነም ውሣኔያቸው ላፀና የሚገባው ነው በማለት ስሜ በሦስተኛ ተራ የተጠቀሰው ዳኛ አብዛኛው ድምጽ በተሰጠው ውሣኔ ባለመስማማት በሐሳብ ተለይቻለሁ።
No topics extracted.