የሰበር መ/33/የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስስልጣን እእና ሙሉ አአብርሃ/ የጉምሩክ ባለስልጣን በህጉ መሰረት የጉምሩክ ስነ ስርአት የልተፈጸመበት እእቃ ከጉምሩክ መጋዘን እእንዳይወጣ በማድረግ ወይም ድክላራሲዮን ባመስጠቱ በእቃው ባለቤት ላይ በሚደርስ ጉዳት ኃላፊ ስላለመሆኑ/
No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 1998 ዳኞች፡
የጉምሩክ ባለስልጣን በህጉ መሰረት ከጉምሩክ መጋዘን እንዳይወጣ ላደረገው እዳ ያስከፈለውን የመጋዘን ኪራይ የሚመለስበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
የጉምሩክ ባለሥልጣን ድክላራሲዮን መስጠት የሚችለው በህጉ መሰረት የጉምሩክ ስነ ስርአት ለተፈጸመበት እቃ ብቻ ነው። የጉምሩክ ስነ ስርአት ላልተፈጸመበት እቃ ድክላራሲዮን ባለመስጠቱ በእቃው ባለቤት ለሚደርስ ጉዳት የጉምሩክ ባለስልጣን አይጠየቅም።
ጥቅምት 18 ቀን 1998 ዳኞች፡
መልስ ሰጪ፡ - አቶ ሙሉ አብርሃ ቀርቧል።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ መዝገብ ተከፍቶ ለሰበር ችሎት ላቀርብ የቻለው የአሁኑ አመልካች ክርክሩን በመጀመሪያ ያየው የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ሆነ ጉዳዮን በይግባኝ የተመለከተው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተመሣሣይ መንገድ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት 117 118 መሆኑን በመግለጽ ጥቅምጽ 29 ቀን 1997 ዓ.ም ተጽፎ እንዲቀርብ ባደረገው አቤቱታ መነሻ ነው።
በአሁኑ ተጠሪ ከሣሽነት የተጀመረውን ክርክር በመጀመሪያው በፍ/መ/ቁ.34187 ያየው የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ ከውጭ አገር በሕጋዊ መንገድ በማስመጣት ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባሁትን 1600 ካርቶን የፎቶ ኮፒ ወረቀት ተከሣሹ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ያለአግባብ ይዞ በማቆየት ለመጋዘን ኪራይ ያስከፈለኝ ብር 11.793.10በ ተመላሽ እንዲያደርግልኝ፣ ተከሣሽ በመጨረሻ እቃውን ሲለቅ አብሮ መስጠት የሚገባውን ዲክላራሲዮን ለመስጠት ፈቃደኛ ሣይሆን በመቅረቱና በዚሁ ምክንያት እቃውን በሀገር ውስጥ ለገበያ በማቅረብ ለመሸጥ ባለመቻል ለመጋዘን ኪራይ ያወጣሁትን ብር 96.600 እንዲከፍለኝ፣ የእቃውን ዲክላራሲዮንም እንዲሰጠኝ በሚል ባቀረበው ክስ ላይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን መልስ እንዲሰጥበት አድርጐ ካከራከረ በኋላ ሰኔ 14 ቀን 1996 ዓ.ም.
በዋለው ችሎት መርምሮ በሰጠው ውሣኔ ተከሣሹ ከጉምሩክ ሕግ ጋር በተያያዘ ያነሣቸውን ክርክሮች ውድቅ በማድረግ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ብር 112.069.95 ከሕጋዊ ወለድ እና ክርክሩ ካስከተላቸው ልዩ ልዩ ወጪዎች ጭምር ለከሣሹ እንዲከፍል፣ የእቃውን ዲክላራሲዮንም ተከሣሹ እንዲበትን ወስኗል።
የአሁኑ አመልካች ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ.32978 የይግባኝ አቤቱታ ላያቀርብ የቻለ ቢሆንም ጥቅምት 16 ቀን 1997 ዓ.ም. በሰጠው ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.337 መሰረት ይግባኙን ሰርዞበታል።
ቀጥሎም በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። አመልካች የአሁን ተጠሪ እቃው በጉምሩክ መጋዘን ለቆየበት የከፈለው ኪራይ በሕጉ ላመለስለት አይችልም። የጉምሩክ ባለሥልጣን እቃው በመጋዘን ለሚቆይበት ጊዜ ኪራይ የማስከፈል ስልጣን አለው። እቃው ተይዞ ላቆይ የቻለው በቅድመ ጭነት ምርመራ ሪፖርት ላይ አንድ ካርቶን የያዘው አንድ ፓኬት የፎቶ ኮፒ ወረቀት ነው ተብሎ ቢገለጽም ሲፈተሽ አንዱ ካርቶን 5 ፓኬት የያዘ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ተጠሪው ከውጭ አገር ያስመጣው 1600 ካርቶን በአጠቃላይ 6400 ተጨማሪ ፓኬቶች የያዘ መሆኑ በተደረገው ፍተሻና ምርመራ ስለተረጋገጠ እቃውን 119 120 የመያዝ ሥልጣን አለው። በእቃው ላይ ተገቢው ቀረጥ ሣይከፈልበት አመልካች ዲክላራሲዮን ለመስጠት አይገደድም። ተጠሪው እቃውን ከተረከበ በኋላ ለመጋዘን ኪራይ ከፍያለው የሚለውን ገንዘብ የምከፍልበት ምክንያት የለም ባይ መሆኑን በጽሁፍ እንዲቀርብ ያደረገው ማመልከቻ ያስረዳል።
ጉዳዩ ለሰበር ችሎት የሚያስቀርብ ነው ተብሎ በአመልካች በኩል የቀረበው ማመልከቻ ለተጠሪው እንዲደርሰው ተደርጐ የካቲት 7 ቀን 1997 ዓ.ም የተፃፈ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል። በተጠሪው በኩል የቀረበው ክርክር፡ - ተጠሪ የእቃውን መጠንና ብዛት በተመለከተ የሰጠው መግለጫ ትክክለኛ መሆኑ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር በአሁኑ አመልካች የተካደ ፍሬ ነገር ስላልሆነ ለሰበር ባቀረበው አቤቱታ ተጠሪው ስለእቃው ብዛት አሳስቶ አቅርቧል በሚል የገለፀው ተቀባይነት የለውም። የቅድመ ጭነት ምርመራ እንዲያደርግ ኃላፊነትና ሥልጣን የተሰጠው ኤስ.ጂ.ኤስ ኩባንያ ሪፖርት ሲያደርግ በእቃው ብዛትም ሆነ ክብደት ረገድ ስህተት በማድረግ በቀረጥና ታክስ ታሪፍ አመዳደብ ላይ በመንግሥት ገቢና ጥቅም ላይ ላስከተለው ጉዳትም ሆነ ጥፋት ራሱ ኩባንያው ኃላፊነት ወስዶ ላከፍል የሚገባው እንጂ እቃ አስመጪው የሚጠየቅበት ምክንያት የለም። ተጠሪው የፈፀመው ጥፋትም ሆነ ስህተት እንደልለ ታምኗል። አመልካችም በተጠሪው በኩል የተፈፀመ ጥፋት እንደልለ እያወቀ እቃው በጉምሩክ መጋዘን እንዲራገፍ በማድረግ ሲጠየቅ ባለማስረከብ በመጋዘን እንዲቆይ ያደረገው ያለአግባብ ነው።
ዲክላራሲዮኑንም የመስጠት ግድታ አለበት የሚል ይዘት ያለው ሲሆን አመልካች በበኩሉ በተጠሪው በኩል የተሰጠው መልስ ተቀባይነት የለውም የሚልባቸውን ምክንየቶች በመግለጽ ተከራክሯል።
ይህ ችሎት በበኩሉ በዚህ መዝገብ የቀረበውን ጉዳይ ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በዚህም መሰረት በተያዘው ጉዳይ ከሕጉ አኳያ ላመረመሩ የሚገባቸውን የክርክር ነጥቦች፡ - 1ኛ/ እቃ አስመጪው ከውጭ አገር ወደ አገር ያስገባው እቃ በጉምሩክ መጋዘን ለቆየበት ጊዜ እንዲከፍል የተደረገው ኪራይ 121 122 ይመለስልኝ ብሎ የሚጠይቅበት የሕግ ምክንያት አለ ወይንስ የለም?
የጉምሩክ ባለሥልጣንስ እቃው በመጋዘን ለቆየበት ጊዜ ያስከፈለውን ኪራይ ላመልስ ይገባል የሚባልበት ምክንያት ይኖራል?
2ኛ/ የጉምሩክ ባለሥልጣን እቃ አስመጪው ከውጭ አገር ወደ አገር ያስገባው እቃ ብዛት በቅድመ ጭነት ምርመራ ሪፖርት ላይ ተገልጾ ከቀረበው መጠን በላይ በሚል እና ከቀረጥና ታክስ ጋር በተያያዘ ምክንያት ዲክላራሲዮን አልሰጥም ብሎ መከልከል ይችላል አይችልም?
3ኛ/ የአሁኑ ተጠሪ እቃውን ከተረከብኩ በኋላ ዲክላራሲዮን ባለማግኘቴ የተነሣ ላሸጥ ባለመቻሉ ልላ መጋዘን ተከራይቼ ለማቆየት አውጥቻለሁ የሚለውን ገንዘብ የጉምሩክ ባለሥልጣን ለመክፈል ይገደዳል አይገደድም? የሚሉት መሆናቸውን ከመዝገቡ ለመገንዘብ ተችሐል።
በቅድሚያ እቃው በጉምሩክ መጋዘን ለቆየበት ጊዜ ተከፍሐል የተባለው ኪራይ ላመለስ ይገባል አይገባም የሚለው ክርክር ሲመረመር ከሣሽ የሆነው የአሁኑ ተጠሪ ከውጭ አገር ወደ አገር ያስገባው 1600 ካርቶን የፎቶ ኮፒ ወረቀት በጉምሩክ መጋዘን ለቆየበት ጊዜ በባለሥልጣኑ እንዲከፍል የተጠየቀውን ኪራይ ብር 11,793.10 ከፍሎ እቃውን በመረከብ ወስዶ ከቆየ በኋላ ይህንኑ ገንዘብ ላመልስልኝ ይገባል ብሎ ላከሰው የቻለው እቃው ወደ አገር እንደገባ እንዲያስረክብ ሲጠየቅ የእቃው ብዛት በቅድመ ጭነት ምርመራ ሪፖርት ላይ ተገልጾ ከቀረበው በላይ ሆኖ ተገኝቷል በሚል ሣቢያ እቃውን ይዞ በመጋዘን በማራገፍ እንዲቆይ ያደረገው ያለአግባብ ነው በሚል ምክንያት መሆኑን የክሱ ፍሬ ነገር ያስረዳል።
123 124 በሕጉ በኩል ያለው ሲታይ የጉምሩክ ባለሥልጣንን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 43/ሀ/ ላይ ወደ ጉምሩክ መጋዘን የገባ እቃ አስፈላጊው የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ተፈጽሞበት እስኪወጣ ድረስ መጋዘን ለቆየበት ጊዜ ኪራይ የሚከፈልበት መሆኑ ተመልክቷል። ኪራዩም የሚከፈለው ለባለመጋዘኑ የጉምሩክ ባለሥልጣን ነው። የአሁኑ ተጠሪም በዚሁ ሕግ መሰረት እቃው በጉምሩክ መጋዘን ለቆየበት ጊዜ ኪራይ መክፈል የሚገባው መሆኑን አውቆ የተጠየቀውን ኪራይ ከፍሎ እቃውን አውጥቷል።
ተጠሪው የጉምሩክ ባለሥልጣን እቃውን በመጋዘን ያቆየው ያለአግባብ ነው በሚል የሚያቀርበውን የክርክር ምክንያት በተመለከተም የጉምሩክ ባለሥልጣን ተጠሪው ወደ አገር ያስመጣው 1600 ካርቶን የፎቶ ኮፒ ወረቀት በቅድመ ጭነት ምርመራ ሪፖርት ላይ እያንዳንዱ ካርቶን በውስጡ አንድ ፓኬት እንደያዘ ተደርጐ የቀረበለት ቢሆንም ሲፈተሽ እያንዳንዱ ካርቶን 5 ፓኬት የያዘ መሆኑን ላያረጋግጥ በመቻሉ በሕጉ መሰረት ላከፈልበት ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ጋር በተያያዘ ምክንያት ይዞ ያቆየ ሆኖ የሚታይ እንጂ ከሕጉ ውጪ ፈጽሟል የሚባል ነገር የለም። የእጥፍ እጥፍ ሆኖ የተገኘው እቃ በህገወጥ መንገድ የገባ ነው ተብሎ ባይታይ እንኳን የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ሣይፈጽምበት ከጉምሩክ መጋዘን ላወጣ አይችልም። ተጠሪው ይኸው የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ሣይፈፀም የጉምሩክ ባለሥልጣን ወዲያው እቃውን እንዲያስረክብ ሲጠየቅ ማስረከብ ነበረበት፣ በጉምሩክ መጋዘንም ማቆየት አልነበረበትም በማለት የማያቀርበው ክርክር በሕግ ተቀባይነት የለውም።
እቃው በጉምሩክ መጋዘን ለቆየበት ጊዜ የከፈለው ኪራይ ይመለስልኝ ብሎ የሚጠይቅበት የሕግ መሰረት የለም። የጉምሩክ ባለሥልጣን በሕጉ መሰረት የተከፈለውን የመጋዘን ኪራይ የሚመልስበት ምክንያት የለም።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ስለእቃው ብዛት የተሣሣተ መረጃ የሰጠው የቅድመ ጭነት ምርመራ አድራጊው ኤል.ጂ.ኤስ የተባለው ኩባንያ ስለሆነ አቃው በጉምሩክ መጋዘን ለቆየበት ጊዜ የተከፈለው የኪራይ 125 126 ገንዘብ ላመለስለት ይገባል በሚል የወሰነው የጉምሩክ ሕግን ያገናዘበ አይደለም።
የጉምሩክ ባለሥልጣን ዲክላራሲዮን ለመስጠት ይገደዳል አይገደድም የሚለውን ጭብጥ በተመለተም የአሁኑ አመልካች እቃውን የሚመለከት ዲክላራሲዮን ለሰጠው አይገባም በማለት አጥብቆ የሚከራከረው በእቃው ላይ ላከፈል የሚገባው ቀረጥ ተሟልቶ ሣይከፈል ዲክላራሲዮን ላሰጠው አይችልም በሚል ምክንያት ሲሆን ተጠሪው ደግሞ ቀረጡ ተሟልቶ ባይከፈልም የጉምሩክ ባለሥልጣን ዲክላራሲዮን አልሰጥም ብሎ ላከለከል አይችልም፣ በእቃው ብዛት አገላለጽ ላይ ስህተት የፈፀመው የቅድመ ጭነት ምርመራ ያደረገው ኤስ.ጂ.ኤስ የተባለው ኩባንያ በመሆኑ በቀረጥና ታክስ ጉዳይ በኃላፊነት መጠየቅ ያለበት ይኸው ድርጅት ነው ባይ ነው።
በተጠቀሰው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 2/18/ ላይ እንደተመለከተው “የጉምሩክ ዲክላራሲዮን” ማለት ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ፣ ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ወይም ተላላፊ እቃዎች ዝርዝር የሚገለጽበትና የጉምሩክ ሥነ ሥርአት የሚፈፀምበት በባለሥልጣኑ የሚዘጋጅ ቅጽ ሲሆን ከዚህ የሕግ አገላለጽ ዲክላራሲዮን በዋናነት የጉምሩክ ሥነ ሥርአት የሚፈፀምበት ሰነድ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። የጉምሩክ ሥነ ሥርአት መፈፀም የሚለውም ሲታይ በቀረጥና ታክስ ላይ የሚያተኩር ነው። የጉምሩክ ባለሥልጣንም ዲክላራሲዮን አዘጋጅቶ ላሰጥ የሚችለው በሕጉ መሰረት ተገቢው ቀረጥና ታክስ እንዲከፈልበት ተደርጐ የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ለፈፀመበት እቃ ነው። በሕጉ አግባብ የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ላልተፈፀመበት እቃ ግን የጉምሩክ ባለሥልጣን ዲክላራሲዮን እንዲሰጥ ሕጉ አይፈቅድም። እቃ አስመጪው በበኩሉ ወደ አገር ውስጥ እንዲያስገባ የተፈቀደለትን እቃ አይነት፣ ብዛትና ክብደት በትክክል ገልጾ ለባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት በማቅረብ በታሪፍ መሰረት ተወስኖ የማጠየቀውን ቀረጥና ታክስ በመክፈል የጉምሩክ ሥነ ሥርአት እንዲፈፀምበት ላላደረገው እቃ ዲክላራሲዮን ይሰጠኝ ብሎ የመጠየቅ መብት ላኖረው 127 128 አይችልም። በቀረበው ጉዳይ ደግሞ የአሁኑ ተጠሪ ከውጭ አገር ወደ አገር ባስገባው እቃ ላይ ላከፈል የሚገባው ቀረጥና ታክስ ተሟልቶ ያልተከፈለ መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። በቅድመ ጭነት ምርመራው ሪፖርት ላይ የአሁኑ ተጠሪ ከውጭ አገር ወደ አገር የሚያስገባው 1600 ካርቶን የፎቶ ኮፒ ወረቀት እያንዳንዱ ካርቶን አንድ ፓኬት የፎቶ ኮፒ ወረቀት የያዘ መሆኑ ተገልጾ ለጉምሩክ ባለሥልጣን የተላከ ቢሆንም ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ሲፈተሽ አንዱ ካርቶን አምስት ፓኬት የያዘ ሆኖ መገኘቱም ተረጋግጧል።
ተጠሪው ይህንኑ እያመነና በክርክሩም ሂደት በልዩነቱ ላይ ያልተከፈለ ቀረጥና ታክስ ብር 49.024.78 መኖሩን እየገለጸ ስህተቱን የፈፀመው የቅድመ ጭነት ምርመራ ያደረገው ኤስ.ጂ.ኤስ የተባለው ኩባንያ ስለሆነ ቀረጥና ታክስ ተሟልቶ ባይከፈልም የጉምሩክ ባለሥልጣን ዲክላራሲዮን ላሰጠኝ ይገባል በሚል ያቀረበው ክርክር በሕጉ ተቀባይነት የለውም። የአሁኑ አመልካች የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ላልተፈፀመበት እቃ ለተጠሪው ዲክላራሲዮን መስጠት አለበት በሚል የተሰጠው ውሣኔም ሕጉን መሰረት የደረገ ስላልሆነ የሚሰረዝ ነው።
በመጨረሻም የአሁኑ ተጠሪ እቃውን ከተረከበ በኋላ ዲክላራሲዮን ባለማግኘቱ ምክንያት መጋዘን ተከራይቶ እቃውን ለማቆየት አወጣሁ የሚለውን ገንዘብ አመልካች ለመክፈል ይገደዳል አይገደድም የሚለው ሲመረመር ከላይ እንደተገለጸው የጉምሩክ ባለሥልጣን በሕጉ መሰረት የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ተሟልቶ ላልተፈፀመበት እቃ ዲክላራሲዮን ለመስጠት የማይገደድ ሆኖ ስለተገኘ አስመጪው እቃውን ካስወጣ በኋላ ዲክላራሲዮን ባለማግኘቴ ምክንያት ለመጋዘን ኪራይ አውጥቻለሁ የሚለውን ብር 96,600 የጉምሩክ ባለሥልጣን የሚከፍልበት የሕግ ምክንያት የለም።
ሲጠቃለል አንድ እቃ በጉምሩክ መጋዘን ለቆየበት ጊዜ በሕጉ መሰረት የተከፈለ ኪራይ አይመለስም።
129 130 የጉምሩክ ባለሥልጣን በሕጉ መሰረት የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ተሟልቶ ላልተፈፀመበት እቃ ዲክላራሲዮን ለመስጠት አይገደድም።
የጉምሩክ ባለሥልጣን የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ተሟልቶ ላልተፈፀመበት እቃ ዲክላራሲዮን ባለመስጠቱ ምክንያት በሕግ የሚጠየቀው ኪሣራ የለም።
በዚህ ጉዳይ እቃው በጉምሩክ መጋዘን ለቆየበት ጊዜ በሕጉ መሰረት የተከፈለውን ኪራይ የጉምሩክ ባለሥልጣን ለአሁኑ ተጠሪ እንዲመለስለት፣ የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ተሟልቶ ላልተፈፀመበት እቃ ዲክላራሲዮን እንዲሰጥ ዲክላራሲዮን ባለመስጠቱ ምክንያት የተጠየቀውን ኪሣራ እንዲከፍል በሚል በተሰጠው ውሣኔም የሕግ ስህተት ተፈጽሟል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ውሣኔም ሆነ ጉዳዩራ በይግባኝ የተመለከተው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 32978፣ በ16/2/97 ዓ.ም. ይግባኝ የተባለበት ውሣኔ ጉድለት የልለው ነው በሚል የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.348/1 መሰረት ተሽሯል።
ጉዳዩ ስለተወሰነ መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።