#### የሰ/መ/ቁ 17429 / ወ/ሮ ሎሚ ሆርዶፋ እእና አአቶ ተስፋዬ ከበደ/ በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ ኑዛዜው መነበቡን የሚያመለክት ከሆነ በግልጽ “ተነቧል” የሚል ቃል አአለመኖሩ ኑዛዜውን ፈራሽ የሚያደርግ ስላለመሆኑ
No summary available.
ጥቅምት 21 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡
ውሣኔ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያፀናው ውሣኔ በድምጽ ብልጫ ተሽሯል።
ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ሲናዘዙ ሰምተናል፤ አይተናል ተብሎ የተገለጸው የኑዛዜውን መነበብ የሚያመለክት ነው።
ኑዛዜው ተነቧል የሚል ቃል በግልጽ አለመስፈሩ ብቻ ኑዛዜውን በምስክሮቹና በተናዛዥ ፊት አልተነበበም በማለት ኑዛዜውን ፈራሽ ለማድረግ በቂ ምክንያት አይደለም።
ጥቅምት 21 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ አቶ ተገኔ ጌታነህ ወ/ሮ ሆሣእና ነጋሽ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ሮ ሎሚ ሆርዶፋ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተስፋዬ ከበደ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፈርደናል።
የአሁኗ አመልካች በሥር ፍ/ቤት የሟች ባለቤቴ አቶ ከበደ ዳዲ የኑዛዜ ወራሽ መሆኔ ተረጋግጦ ማስረጃ ይሰጠኝ ብላ አመልክታ ተጠሪ በተቀዋሚነት ቀርቦ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ የአባቴ /የሟች/ አይደለም፣ ኑዛዜው እንዲሻር እኔም ልላ መዝገብ ያስከፈትሁ ስለሆነ መዝገቦቹ በአንድነት ታይተው ይወሰንልኝ በማለት አመልክቷል።
109 110 የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ሁለቱን መዛግብት መርምሮ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ በተናዛዡና በአራት ምሰክሮች ፊት ካልተነበበ ይህም ሥርዓት መፈፀሙንና የተፃፈበትን ቀን የማያመለክት ካልሆነ ፈራሽ ነው፣ በኑዛዜው ሰነድ ላይ ኑዛዜው በተናዛዡና በአራቱም ምስክሮች ፊት ስለመነበቡ በግልጽ ያልተፃፈ በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ.
881/2/ መሰረት ፈራሽ ነው ሲል ወስኗል። ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ውሣኔ አፅንቷል። አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው።
የሰበር አቤቱታው ፍሬ ሃሣብ የኑዛዜው ፅሁፍ መነበቡን ኑዛዜው የሚያሣይ ሆኖ ሣለ ውድቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ሲሆን፣ ተጠሪ በሥር ፍ/ቤቶች የተፈፀመ የሕግ ስህተት ስለልለ ፍርዱ ይፅናልኝ ሲል ተከራክሯል።
በዚህ ችሎት ምላሽ ላያገኝ የሚገባው ነጥብ ኑዛዜው በፍ/ሕ/ቁ. 881/2/ መሰረት የተደረገ አይደለም መባሉ ተገቢ መሆን ያለመሆኑ ነው።
ጳጉሜ 5 ቀን 1990 ዓ.ም. በተፃፈው የአቶ ከበደ ዳዲ ኑዛዜ ላይ የኑዛዜው ዝርዝርና የአራት ሽማግልዎች /ምስክሮች/ ስም ከተፃፈ በኋላ #እኛ ከዚህ በላይ ስማችን የተጠቀሰው ሽማግልዎች በትክክለኛ አእምሮዋቸው ሆነው ሲናዘዙ ሰምተናል፤አይተናል; ተብሎ ተጠቅሷል። ከተናዛዡና ከአራቱ ምስክሮች ፊርማ ቀጥሎ ደግሞ #ይህንኑ ቃል ለመስማታችን በፊርማችን እናረጋግጣለን ; ይላል።
የፍ/ሕ/ቁ.881/2/ #ኑዛዜው በተናዛዡና አራት ምስክሮች ፊት ካልተነበበና ይኸም ሥርዓት /ፎርማላቲ/ መፈፀሙንና የተፃፈበትንም ቀን የሚያመለክት ካልሆነ በቀር ፈራሽ ነው; በማለት ሲደነግግ የፍ/ሕግ ቁጥር 881/3/ ደግሞ #ተናዛዡና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ወዲያውኑ ፊርማቸውን ወይም የአውራ ጣት ምልክታቸውን ካላደረጉበት በቀር ፈራሽ ነው; ይላል።
እነዚህ ሁለት ንኡሳን አንቀጾች አንድ ኑዛዜ አራት ነገሮችን ማለትም ኑዛዜው የተደረገበትን ቀን፣ በአራት ምስክሮች ፊት መደረጉን፣ ኑዛዜው በተናዛቹና በምስክሮች መፈረሙንና መነበቡን ማሣየት እንዳለበት ይደነግጋሉ፤ ከፍ ሲል ከኑዛዜው ፅሁፍ ላይ ወስደን ካሰፈርነው መረዳት የተቻለው ኑዛዜው ጳጉሜ 3 ቀን 1990 በሚል ቀን የተፃፈበት፣ የአራት ምስክሮች ስም ያለበት፣ ምስክሮቹና ተናዛዡ 111 112 የፈረሙበት መሆኑን ነው። ከዚህ ልላም በኑዛዜው ላይ #ሲናዘዙ ሰምተናል፣ አይተናል; ተብሎ መገለፁም የኑዛዜውን መነበብ የሚያመለክት ነው። ሕጉ የኑዛዜውን መነበብ አስፈላጊነት ያስቀመጠው በሚነበብበት ወቅት ሟች/ተናዛዥ የተናገረው በትክክል በፅሁፍ መስፈሩን እንዲረዳና የተናዛዡ ፈቃድ መሟላቱን ማረጋገጥ እንዲቻል ነው። ከላይ በተጠቀሰው የኑዛዜው ክፍል #ሲናዘዙ ሰምተናል፣ አይተናል; በሚል የሰፈረው ምስክሮች ያዩትና የሰሙት ኑዛዜው ሲደረግና የተፃፈው ኑዛዜ ሲነበብ ነው ተብሎ መገመት ይኖርበታል።
የሥር ፍ/ቤቶች ኑዛዜውን ለማፍረስ የሚያበቃ የሕግ መሰረት በልለበት በኑዛዜው ፅሁፍ ላይ ኑዛዜው #ተነቧል; የሚል ቃል ባለመኖሩ ብቻ ኑዛዜው በምስክሮችና በተናዛዡ ፊት ስለመነበቡ አልተፃፈም በማለት ፈራሽ ማድረጋቸው ተገቢ ሆኖ አልተገኘም።
ው ሣ ኔ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 71/93፣ እንዲሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.03644 የሰጧቸው ውሣኔዎች ተሽረዋል።
ኑዛዜው በፍ/ሕ/ቁ. 881 በተደነገገው መሰረት የተከናወነ በመሆኑ የፀና ነው ብለናል፤ ይፃፍ፤ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.