የሰበር መ/89 /የሸቀጦች ጅምላ ንግድና አአስመጪ ድርጅት እእና አአቶ ንጉሴ ዘለቀ/ በአሰሪ “ገንዘብ” ላይ ሰራተኛው ያደረሰው ጉዳት በአሰሪው “ንብረት” የደረሰ ጉዳት ስለመሆኑ እእና ሰራተኛ የስራ ውል ተቋርጦ ስራ ያልሰራበት ጊዜ ደመወዝ የሚያገኝበት የህግ ምክንያት ስላለመኖሩ/
No summary available.
ጥቅምት 17 ቀን 1998 ዳኞች፡
ውሣኔ፡ - የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ በድምጽ ብልጫ ተሽሯል።
“ገንዘብ” አንድ ግዙፍነት ያለው ተንቀሣቃሽ “ንብረት” ነው።
በአሰሪ “ገንዘብ” ላይ የደረሰ ጉዳት በአሰሪ “ንብረት” ላይ የደረሰ ጉዳት ነው።
የአዋጅ ቁ.42/85 ድንጋጌዎች የስራ ውል በአሰሪው አነሳሽነት በተቋረጠበትና የስራ ውሉ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው የሚል ውሣኔ በሚሰጥበት ወቅት ሰራተኛው ያልሰራበትን ጊዜ ደመወዝ እንዲያገኝ የሚፈቅዱ አይደሉም።
የመ.ቁ. 17189 ጥቅምት 17 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብድልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካች፡- የሸቀጦች ጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጀት - አልቀረበም።
ተጠሪ፡- አቶ ንጉሤ ዘለቀ - አልቀረበም
ተጠሪ በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ክስ መስርቶ የሥራ ውልን ከሕግ ውጭ ስላቋረጠው ውዝፍ ደመወዜን ከፍሎ ወደ ሥራ እንደመልሰኝ ይወሰንልኝ ሲል ጠይቋል። ይህ ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራ ቀኙ በጉዳዩ ያቀረቡለትን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ እና የአመልካችን Oዲተር በምስክርነት ከሰማ በኋላ ተጠሪ ከሥራ የተሰናበተው በአመልካቹ ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት 91 92 ጉዳት በማድረሱ ምክንያት ስለሆነ ስንብቱ በሕብረት ስምምነቱ እና በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 27/1//በ/ የተደገፈ ነው ሲል ወስኗል።
ይህ ውሣኔ ይግባኝ በቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተሽሮ ተጠሪ የሦስት ወር ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ሥራው እንዲመለስ እንዲሁም ብር 100.00 ወጭና ኪሣራ እንዲከፈለው ተወስኗል።
አመልካች ተጠሪው ወደ ሥራ ላመለስም ሆነ ውዝፍ ደመወዝ ላከፈለው አይገባም በማለት አቤቱታውን ለዚህ ችሎት አቅርቧል። ተጠሪው ደግሞ በሰጠው መልስ ውዝፍ ደመወዙን የማላገኝበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል።
ወደ ሥራ መመለስን አስመልከቶ ስለቀረበው አቤቱታ የሰጠው መልስ ግን አለመኖሩን ማመልከቻው ያስረዳል።
ይህም ችሎት ጉዳዩን መርምሯል።
በክርክሩ ላፈቱ የሚገባቸው ጭብጦችም የተጠሪ የሥራ ውል መቋረጥ በሕግ የተደገፈ ነው? ወይስ አይደለም? ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈለው መወሰኑስ የሕግ መሰረት አለው የሚሉት መሆናቸውንም ተገንዝቧል።
ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው አመልካቹ የተጠሪን የሥራ ውል ያቋረጠው በቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅነቱ የየእለቱ ገቢ ተሰብስቦ ባንክ መግባቱን ማረጋገጥ ሲገባው በጊዜው ገንዘብ ያዥ የነበረው አቶ ስለሺ ታደለ ባዘጋጀው የገንዘብ እና የባንክ መዝገብ ላይ በመፈረም ወይም ሳይፈርም በመተው ጉድለት እንዲፈጽም ረድቶታል በሚል ዋነኛ ምክንያት ነው። በየቀኑ ከሽያጭ የተሰበሰበውን ገንዘብ የመቆጣጠር ጉድለት ቢገኝ ገንዘብ ያዡን መተማመኛ አስፈርሞ በመመሪያው መሰረት እርምጃ የመውሰድ እንዲሁም ገንዘቡ ባንክ ገቢ መደረጉን የማረጋገጥ ጉዳይ በሥራ መዘርዝሩ ላይ የተጠቀሰ የተጠሪ የሥራ ድርሻ መሆኑም በሥር ውሣኔ ተመልክቷል።
ተጠሪ ይህ ኃላፊነት እንዳለበት አልካደም። የሚከራከረው ገንዘብ ያዡ E.ኤ.A.
በሰኔ ወር 1999 ላደረሰው ጉድለት እርሱም ቢሆን ከሥራ አልተሰናበተም ይልቁንም በዚህ ጥፋቱ በተግሳፅ ታልፏል። ልሎች ጉድለቶች ተገኝተዋል በተባለበት ጊዜ ደግሞ እኔ እረፍት ላይ የነበርኩ በመሆኑ አይመለከተኝም በሚል አይነት መሆኑን መዝገቡ ያሳያል። በመሰረቱ ገንዘብ ያዥው E.ኤ.A. በሰኔ ወር 1999 አጉድሐል የተባለው 93 94 ብር 6,221.93 ሲሆን በዚህ ጊዜ ተጠሪው በሥራ ላይ የነበረ መሆኑ አላከራከረም።
እንዲሁም ተጠሪው ገንዘብ ያዥው በዚህ ጥፋቱ በተግሳጽ ብቻ ታልፏል በሚል በቀር እርሱ በእለቱ ጉድለቱን በማግኘትና በመመሪያው መሰረት ተገቢውን በማድረግ የሥራ ድርሻውን በአግባቡ የተወጣ መሆኑን አላስረዳም። እንደውም በዚህ ረገድ ያቀረበው ክርክር የለም። ይህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪው ያለበትን የሥራ ግድታ ተወጥቷል ለማለት አይቻልም። ገንዘብ ያዡ በዚህ ድርጊት በተግሳጽ ታልፏል ማለቱም የእርሱን ኃላፊነትና ግድታ የሚያስቀርለት አይሆንም።
እንግዲህ ክርክሩን አስቀድሞ የዳኘው የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዳዩን ከፍ ሲል ከተጠቀሰው አግባብ በማየት ድርጊቱ ተጠሪው በአመልካች ላይ ጉዳት ማድረሱን ለማረጋገጥ ይበቃል የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል። በዚህም ምክንያት ልሎች በተጠሪው ተፈጽመዋል ወደተባሉ ጥፋቶች መሄድ እንደማያስፈልግ በውሣኔው ጠቅሶታል። በልላ በኩል ግን ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ በሥራ ላይ በነበረበት ጊዜ እንደተፈፀመ የተረጋገጠው ከላይ የተጠቀሰው የገንዘብ ጉድለት ተጠሪውን ከሥራ ለማሰናበት የሚበቃ መሆን አለመሆኑን አልመዘነም። በተጠሪ ተፈጽመዋል ወደተባሉ ልሎች ጥፋቶች ዘልቆ መፈጸም አለመፈጸማቸውንም ለማጣራት አልሞከረም። ለፍርዱ መሰረት ያደረገው ገንዘብ ያዥው ገንዘብ ባጎደለበት ጊዜ ተጠሪው ሥራ ላይ ስላልነበረ ወደ ሥራ ሲመለስ አልተቆጣጠርክም ተብሎ መሰናበቱ ትክክል አይደለም የሚለውን ምክንያት ነው። ይህ ደግሞ ፍ/ቤቱ በአመልካች የተነሱትን የክርክር ነጥቦች በሙሉ ቃኝቶ ፍሬ ነገሩን በማጥራት ፍርድ አለመስጠቱን የሚያመላክት ነው። እንዲሁም የሥር ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ፍሬ ነገር የደረሰበትን መደምደሚያ አሳማኝ ምክንያት ላይ ሳይመሰረት የለወጠው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።
ወደ ሕጉ ስንመለስ በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 27/1/ ስር ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ላያቋርጡ የሚችሉ ምክንያቶች የተዘረዘሩ ሲሆን ለዚህ ጉዳይ አግባብነት የሚኖረው በአሰሪው ንብረት ወይም ከሥራው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኛነት ጉዳት ማድረስ የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ እንደሚያቋርጥ የሚደነግገው አንቀጽ 27/1//በ/ መሆኑን 95 96 ችሎቱ አምኖበታል። ችሎቱ እዚህ እምነት ላይ የደረሰው ጉዳዩን ከፍትሐብሕር ሕግ አንቀጽ 1126 እና 1127 ጋር አገናዝቦ በማየትና # ገንዘብ ; አንዱ ግዙፍነት ያለው ተንቀሳቃሽ # ንብረት ; መሆኑን በመቀበል ነው። በተጨማሪም አንድ ሰራተኛ በአሰሪው የተሰጠውን ኃላፊነት ሆነ ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት አንድን ነገረ በማድረግም ይሁን ባለማድረግ ሳይወጣው ቢቀርና በዚህ ድርጊቱ ልላው ሰው በአሰሪው ገንዘብ ላይ በቀጥታ ጉዳት እንደያደርስ ተባብሮ ቢገኝ እራሱ በአሰሪው ንብረት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ላቆጠር ይገባዋል የሚል ትርጓሜ ለተጠቀሰው የአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 27/1//በ/ በመስጠቱ ነው። ከፍ ሲል እንደተመለከተው ተጠሪው ሥራ ላይ በነበረበት ወቅት ገንዘብ ያዥው ያደረሰውን የገንዘብ ጉድለት መቆጣጠር ሲገባው አልተቆጣጠረም። ይህ ደግሞ ቢያንስ በከባድ ቸልተኛነት በአመልካች ንብረት ላይ ቀጥተኛ ባልሆነ ሁኔታ ጉዳት ማድረሱን ያረጋግጣል። ስለሆነም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥራ ውሉን መቋረጥ ሕገ ወጥ በማድረግ ተጠሪ ወደ ሥራ እንደመለስ መወሰኑ ከተጠቀሰው ድንጋጌ ጋር ያልተጣጣመ ሆኖ አግኝተነዋል።
ቀጥሎ ተጠሪ ከሥራ ከተሰናበተ ጊዜ ጀምሮ ያለው ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈለው ሕጉ ይፈቅዳል ወይስ አይፈቅድም የሚለውን ነጥብ እናያለን። ከላይ እንደተጠቀሰው ፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ የሦስት ወር ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈለው ተወስኗል። ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል የታዘዘው ሥራ ያልተሰራው በሰራተኛው ጉድለት ባልሆነ ምክንያት ነው በማለትና የአዋጁን አንቀጽ 54/2/ መሰረት በማድረግ እንደሆነ ይታመናል። ይህም ውሣኔ በአንቀጽ 54/2/ ላይ የሰፈረው ድንጋጌ አባባልና መንፈስ የሚመለከተው የሥራ ውሉ ተቋርጦ የቆየን ሰራተኛ ነው ወይስ ከዚህ የተለየ አኳኋን ያለውን ሰራተኛ ነው የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል። ይህንኑ ለመረዳት ለዚህ አንቀጽ መሰረት የሆኑትን የ53/1/ እና የ54/1/ን ድንጋጌዎች መመልከት ያስፈልጋል።
የአዋጁ አንቀጽ 53/1/ ደመወዝ ማለት # አንድ ሰራተኛ በሥራ ውሉ መሰረት ለሚያከናውነው ሥራ የሚከፍለው መደበኛ ክፍያ ; ነው በማለት ይደነግጋል። የአዋጁ አንቀጽ 54/1/ም እንደዚሁ በአዋጁ ወይም አግባብ ባለው ሕግ በተለየ አኳኋን ካልተወሰነ ደመወዝ የሚከፈለው ለተሰራ ሥራ ብቻ መሆኑን በግልጽ ያስቀምጣል።
97 98 ከነዚህ ሁለት የተያያዙ የሕግ ድንጋጌዎች የደመወዝን ምንነት እና የአከፋፈል ሁኔታ መገንዘብ ይቻላል። በአንድ በኩል አንድ ሰራተኛ ደመወዝ የሚከፈለው ከውል የመነጨ ግድታውን መፈፀም ሲችል እንደሆነ እናያለን።
የሰራተኛ እና የአሰሪ ግንኙነት የሚመነጨው ሁለቱም ወገን ከሚገቡት ውል ነው።
ይኸው ውል እንደማንኛውም ልላ ውል ለሁለቱም ወገን መብት ያመነጫል ግድታንም ይጥላል። ከነዚህ ተያያዥ መብትና ግድታዎች አንዱ ሰራተኛው በውል ለማከናወን ቃል የገባውን ሥራ የማከናወን በተሰራው ሥራ መጠን ደግሞ በውሉ በተጠቀሰው ጊዜና መጠን ደመወዝ የማግኘት መብትና ግድታ ነው። በዚህ መሰረት አሰሪው ከሰራተኛው ግልጋሎት ያገኛል። ባገኘው ግልጋሎት መጠንም በውሉ የተጠቀሰውን ደመወዝ የመክፈል ግድታ ይኖርበታል። በመርህ ደረጃ እነዚህ መብትና ግድታዎች ከውል የሚመነጩ አንዱ ያለልላው ላታሰቡ የማይችሉ የአንድ ሕጋዊ ግንኙነት ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ስለዚህ ሥራ ሳይሰራ ደመወዝ ላከፈል አይችልም። ደመወዝ ሳይከፈል ደግሞ ሥራ ላከናወን አይችልም። ይህ አጠቃላይ አባባል ከውል ሕግ መሰረተ ሃሳብ ጋር የሚጣጣም ነው።
ይህ አጠቃላይ መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ ሕጉ ሰራተኛው ሥራ ባይሰራም ደመወዝ ላከፈለው የሚችልበትን ሁኔታ በተለየ አስቀምጧል። በዚህም መሰረት በአዋጁ አንቀጽ 54/2/ ከሁለት ሁኔታዎች አንዱ ተሟልቶ ከተገኘ ሰራተኛው ሥራ ባይሰራም አሰሪው ደመወዝ የመክፈል ግድታ ተጥሎበታል። እነዚህ ሁኔታዎች አንደኛ ሰራተኛው ዝንጁ ሆኖ እያለ አሰሪው ለሥራው አስፈላጊ የሆነውን መሣሪያና ጥሬ እቃ ሳያቀርብለት የቀረ እንደሆነ ወይም ሁለተኛ ሰራተኛው ሥራ ሳይሰራ የዋለው በራሱ ጉድለት ባልሆነ ምክንያት እንደሆነ የሚሉት ናቸው። እነዚህ ሁለት የተለዩ ሁኔታዎች ከሥራ ውልም ሆነ ከአጠቃላይ የውል መሰረታዊ መርሆዎችና ድንጋጌዎች ጋር ተያይዘው መተርጎም ይኖርባቸዋል።
ከላይ እንደተገለፀው የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት የሚመነጨው ከሥራ ውሉ ነው። የአሰሪ ደመወዝ የመክፈል ግድታም የሚመነጨው እንዲሁ ከሥራ ውሉ ነው። በልላ በኩል የሥራ ውል ቢኖርም ደመወዝ 99 100 የሚከፈለው ለተሰራ ሥራ ብቻ በመሆኑ ሰራተኛው ሥራ ሳይሰራ ደመወዝ እንዲከፈለው ላጠይቅ አይችልም። ሰራተኛው በርሱ በኩል ያለውን የመሥራት ግድታ ሳይወጣ አሰሪው ደመወዝ የመክፈል ግድታውን እንዲፈጽም ላጠይቅ የሚችለው ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ምክንያቶቹ አንዱ መኖሩን በማስረዳት ነው።
ስለዚህ በአዋጁ አንቀጽ 54/2/ ያሉት ሁለት መስፈርቶች ተፈፃሚ ላሆኑ የሚችሉት በአሰሪና በሰራተኛ መካከል ያለው የሥራ ውል ፀንቶ በሚቆይበትና ሰራተኛው በሥራ ገበታው በሚገኝበት ጊዜ ብቻ ነው። የሥራ ውል በልለበት ወይም የነበረ የሥራ ውል በተቋረጠበት ሁኔታ የአዋጁ አንቀጽ 54/2/ ተፈፃሚ ላሆን አይችልም።
የሥራ ውል በሁለቱም ወገን ላከበር እንደሚገባና ላቋረጥ የሚችለውም በሕጉ በሰፈሩ ምክንያቶች ብቻ እንደሆነ ግልጽ ነው። በልላ በኩል አንድ አሰራ በአዋጁ አንቀጽ 27 የተጠቀሱ ሁኔታዎች ተሟልተዋል ብሎ ሲያምን ያለማስጠንቀቂያ፣ በአንቀጽ 28 የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ተሟልቷል ብሎ ሲያምን ደግሞ ሕጉን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ውሉን ማቋረጥ እንደሚችል ሕጉ ይደነግጋል። በዚህም መሰረት የሥራ ውልን ለማቋረጥ አሰሪው ክስ መመስረት ሳያስፈልገው የተናጠል እርምጃ የመውሰድ ሕጋዊ መብት አለው። አሰሪው በዚህ ረገድ የሰጠው ውሣኔ የሥራ ክርክርን መርምሮ የመወሰን ሥልጣን ባለው አካል ታይቶ እስካልተሻረ ድረስ በሁለቱም ወገን የነበረውን የሥራ ግንኙነት ቀሪ እንዲሆን ያደርጋል።
አሰሪው የሥራ ውሉን ያቋረጠው ሕግ በማይቀበለው ምክንያት የሆነ እንደሆነ ሰራተኛው ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ወደአለው አካል ማቅረብ መብት አለው። ጉዳዩ የቀረበለት አካል አሰሪው የወሰደው ውሣኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ መሆን አለመሆኑን በመመርመር ውሣኔ መስጠት ይጠበቅበታል። ቀድሞውኑ አሰሪው የሥራ ውሉን ያቋረጠው በሕጉ መሰረት አይደለም ወደሚል መደምደሚያ ከደረሰ ለሰራተኛው የሚሰጠው መፍትሕ /remedy/ ሕጉ የሥራ ውል አለአግባብ ባቋረጠ አሰሪ ተፈፃሚ እንዲሆን የፈቀደውን መፍትሕ ብቻ ነው። የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 43 የሥራውል አለአግባብ ወይም ሕገወጥ በሆነ ሁኔታ ሲቋረጥ ለሰራተኛው የሚሰጠው መብት በአማራጭ ወደ ሥራ መመለስ ወይም እነደነገሩ ሁኔታ የካሣ ክፍያ 101 102 የማግኘት መብት ብቻ ነው። ሰራተኛ ወደ ሥራ እንዲመለስ ከማድረግ በተጨማሪ ሰራተኛው ሥራው ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ያለው ደመወዝ እንዲከፈለው የሚያዝ የሕግ አንቀጽ የለም። በመሆኑም አለአግባብ ከሥራ የተሰናበተ ሰራተኛ ወደ ሥራ እንዲመለስ ከማድረግ በተጨማሪ ሥራ ላይ ላልነበረበት ጊዜ ደመወዙ እንዲከፈለው ማድረግ ሕጉ አይፈቅድም። ከላይ እንደተገለፀው በመሰረቱ መክፈልም ከተቻለ ደመወዝ የሚከፈለው የሥራ ውል ላለው ሰራተኛ ነው። የሥራ ውሉ የተቋረጠው ሕገወጥ በሆነ መንገድ ነው ቢባል እንኳ የሥራ ውሉ ውሣኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ እንዲቀጥል ከማድረግ አልፎ ውሣኔው ወደ ኋላ ተመልሶ አሰሪው የሰጠውን ውሣኔ እንዳልተሰጠ መቁጠርና የሥራ ውል እንዳልተቋረጠ በማሰብ ሰራተኛው ሳይሰራ የቀረው በርሱ ጥፋት ባልሆነ ምክንያት ነው ማለት የሚቻል አይደለም። ሰራተኛው በአሰሪው ውሣኔ ከሥራ እንዲሰናበት ከተወሰነበት ጊዜ ጀምሮ ሰራተኛው በፍርድ ወደ ሥራ እንዲመለስ በተወሰነበት ጊዜ መካከል የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት አለ ላባል አይችልም። ለዚህ ጊዜ ደመወዝ እንዲከፈል ማዘዝም አይቻልም።
በአጠቃላይ ፍርድ ቤቱ አመልካች ውዝፍ ደመወዝ ይከፈል በማለት የሰጠው ውሣኔ አግባብነት በአላቸው የአዋጅ ቁ. 42/85 ድንጋጌዎች ትክክለኛ ትርጉም ላይ የተመሰረተ አይደለም። በልላ በኩል ፍርድ ቤቱ እያንዳንዱ ባለጉዳይ የሚያቀርበውን የሕግ ክርክር መርምሮ ውሣኔ የመስጠት ኃላፊነት አለበት። ተከሣሹ ወገን በሕግ ነጥብ ላይ መልስ ሰጥቶ ባይገኝ ደግሞ የሕግ ጉዳይ የቀረበለት ፍ/ቤት በእራሱ አነሳሽነት በጉዳዩ ጭብጥ ይዞ ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ይጠበቅበታል። ውዝፍ ደመወዝ መከፈል አለበት ወይስ የለበትም የሚለው ነጥብ የሕግ ጥያቄ እንደመሆኑ መጠን ፍርድ ቤት ከተከሳሹ ወገን የቀረበለት ክርክር ያልነበረ ቢሆን እንኳ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥበት ያስፈልጋል።
ው ሣ ኔ
የተጠሪ የሥራ ውል መቋረጥ በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀፅ 27/1//በ/ የተደገፈ ስለሆነ ወደ ሥራ ላመለስ አይገባም በማለት ተወስኗል።
እንዲሁም ይህ ችሎት አግባብነት ያላቸውን የአዋጅ ቁ. 42/85 ድንጋጌዎች በመተርጎም ሕጉ አንድ የሥራ ውል በአሰሪው አነሳሽነት በተቋረጠበትም ሆነ የተቋረጠው ከሕግ ውጭ ነው በሚል ውሣኔ በሚሰጥበት ሁኔታ ሰራተኛው ያልሰራበትን ጊዜ ደመወዝ እንዲያገኝ የሚፈቅድ አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ተጠሪ ውዝፍ ደመወዝ ላከፈለው አይገባም በማለት ተወስኗል።
103 104 3. የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 16329 ሐምል 16 ቀን 1996 ዓ.ም.
በዋለው ችሎት ተጠሪ የሦስት ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ሥራ እንዲመለስ የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት በድምጽ ብልጫ ተሽሯል። ይኸው ይፃፍ።
የሐሳብ ልዩነት እኔ ስሜ በተራ ቁጥር 5 ላይ የተመለከተው ዳኛ በዚህ ጉዳይ የአሁኑ ተጠሪ ለፈፀመው ተግባር የሥራ ውሉ እንዲቋረጥ በማለት በአብላጫው ድምፅ በተሰጠው መደምደሚያ የምስማማ ቢሆንም፣ አብላጫው ድምፅ ተጠሪ ፈፀመ ለተባለው ተግባር ለውሣኔው ዋቢ አድርጐ የጠቀሰው አንቀጽ 27/1/ /በ/ በተጠሪ ተፈፀመ ከተባለው ድርጊት ጋር ግንኙነት የልለው በመሆኑ በዚህ የህግ ድንጋጌ ላሸፈን ባልተገባው ነበር እላለሁ።
የተጠሪ የሥራ ውል በአሰሪው እንዲቋረጥ የተደረገው ተጠሪ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በሚሰራበት ቅርንጫፍ በሥሩ የሚገኘውን ገንዘብ ያዥ በተገቢው ሁኔታ ባለመቆጣጠሩ የአሰሪው ድርጅት ገንዘብ እንዲመዘብር ምክንያት ሆኖአል በሚል ነው።
አብላጫው ድምፅ ይህ አይነቱ ድርጊት በአዋጁ አንቀጽ 27/1/ /በ/ ሥር ይጠቃለላል በማለት መደምደምያ ላይ ደርሷል። ምንም እንኳን በዚህ አንቀጽ #ንብረት; የሚለው ቃል አገላለጽ #ገንዘብን; የሚያጠቃልል መሆኑን ብስማማበትም በዚህ ጉዳይ ተመዝብሯል ወይም ልላ ሰው ጥቅም እንዲውለ ተደርጓል የተባለን የአሰሪ ገንዘብ ሆነ ተብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት በአሰሪ ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስን በሚመለከተው አንቀጽ ሥር ይጠቃለላል ብሎ ማለት አግባብ ሆኖ አላገኘሁትም።
በአብላጫው ድምፅ የተጠቀሰው የሕግ አንቀጽ የአሰሪውን ንብረቶች በተለይ በማምረት ተግባር ውስጥ ቀጥተኛ ግንኙነት 105 106 የሚኖራቸውን ንብረቶች ሆነ ተብሎ ወይም በሚያስቀጣ ቸልተኝነት ከሚፈፀሙ የጉዳት ተግባሮች ለመጠበቅ የተደነገገ ድንጋጌ እንጂ የሥራ ተግባርን በመጣስ /Neglect of Duty/ የሚፈፀሙ መሰል የገንዘብ ብክነቶችን የሚሸፍን አይደለም በማለት በመደምደሚያ ሃሣቡ ተስማምቼ በሕጉ አተረጓጐም ላይ በሃሣብ ተለይቻለሁ።