የሰበር መ/77 /ዝቋላ ስቱል ሮላንግ ሚል እእና አአዋሽ ኢኢንሹራንስ ኩባንያ/ የእዳ መክፈያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ባለገንዘቡ ለባለእዳው የሚያደርገው የእዳ ክፍያ ጊዜ ማራዘም ዋሱን ከዋስትናው ነፃ የሚያደርገው ስላለመሆኑ/
No summary available.
ጥቅምት 14 ቀን 1998 ዳኞች፡
79 80
የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1928 (2) ዓላማ ከውሉ መፈፀም በኋላ በባለገንዘቡና በባለእዳው መካከል የዋሱን ግድታዎች የሚያባብሱ አዲስ ስምምነቶች እንዳይደረጉና ዋሱን ለተጨማሪ ጉዳት እንዳይዳርጉት ለመጠበቅ ነው።
የመፈፀሚያ ጊዜ የተያዘላቸውና ዋስትና የተገባላቸው ግድታዎች የግድታ መፈፀሚያ ጊዜያቸው ሲጠናቀቅ ዋስ ላልተፈፀመው ግድታ ተጠያቂ እንደሚሆን ሁሉ ከግድታው መፈፀሚያ ጊዜ በኋላ ባለገንዘቡ በራሱ ፈቃድ በችሮታ መልክ የሚያደርገው የክፍያ ጊዜ ማሻሻያ ሆነ ልሎች እርምጃዎች ዋስትና ከተገባለት ከቀድሞ ግድታ ጋር የማይገናኝ በመሆኑ ለበሰለው እዳ ከመጠየቅ አይድንም።
ጥቅምት 14 ቀን 1998 ዳኞች፡
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር ማመልከቻ መነሻ የሆነው ጉዳይ የሥር ፍ/ቤቶች የአሁኑ አመልካች የእዳ መክፈያ ጊዜውን ዋስ የሆነውን የአሁኑን ተጠሪ ሳያስፈቅድ ያራዘመ በመሆኑ ዋሱ ከገባው ግድታ ነጻ ነው ብለው ውሣኔ በማስተላለፋቸው ነው።
81 82 የአሁኑ አመልካች በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ፤
ተጠሪ ስለደንበኛው በመሆን አውጥቼው ለበረው የብረት ግዢ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ አመልካችን ተጠቃሚ በማድረግ የሰጠ ስለሆነ የተጠሪ ደንበኛ የሆነው ድርጅት በጨረታ አሸናፊነቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና በ10 ቀናት በማቅረብ ውሉን እንዲፈርም ቢጠየቅ ይህን ባለመፈፀሙ የቢድ ቦንድ ዋጋውን ተጠሪ እንዲከፍለው ጠይቋል። የአሁኑ ተጠሪ በበኩሉ የተለያዩ ነጥቦች ያካተተ መልስ የሰጠ ሲሆን በዋነኛነት ከሳች የተከሳሽ ደንበኛ ማሸነፉን ገልጾ ደብዳቤ ሲጽፍለት ከጨረታ ቅድመ ሁኔታና ከተከሣሽ ፈቃድ ውጭ የፊርማውን ቀን በ10 ቀናት አራዝሟል። በዚህም ሳያበቃ ለተጨማሪ 5 የሥራ ቀናት እንዲራዘም አድርጓል። በመሆኑም ከሳሽ ያለተከሳሽ ፈቃድ የግድታ ጊዜውን በማራዘሙ ከተጠያቂነት ነጻ ነኝ በማለት መልስ ሰጥቷል። የሥር ፍ/ቤትም አመልካች የተጠሪ ደንበኛ ጨረታ ያሸነፈ መሆኑን በመግለጽ ጥር 6 ቀን 1994 ዓ.ም. በቁጥር ዝስሮሚ/200/07/94 በተጻፈ ደብዳቤ ውሉን በመፈረም የመልካም ሥራ አፈጻጸሙን በአሥር ቀን ውስጥ እንዲያቀርብ፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለማደርስ ጉዳት ተከሣሽ በገባው ግድታ መሰረት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን በመግለጽ ለተከሣሽ ደንበኛ በጻፈው ደብዳቤ ገልጿል። የአሁኑ አመልካች በመቀጠል ጥር 21 ቀን 1994 ዓ.ም ቁጥር 2 ዩኤስO ኤም/200/05/94 በሆነ ደብዳቤ የተባለውን ጊዜ በ5 ቀናት ያራዘመ መሆኑን ለተከሣሽ ደንበኛ ገልጾ ጽፏል። እነዚህ ደብዳቤዎች የተጠሪ ደንበኛ ውል እንዲዋዋልና ዋስትናውን እንዲያቀርብ የተሰጠውን 10 ቀናት ያለ ዋሱ ፈቃድ ማራዘማቸውን የሚያስረዱ በመሆናቸው በሕ.ቁ.1928/2/ መሰረት ዋስ የሆነው የአሁኑ ተጠሪ ከገባው ግድታ ነጻ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የአሁኑ አመልካች ይግባኝ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ይግባኙ ውድቅ ሆኖ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቷል።
አመልካች በሰበር እንዲታይለት ያቀረበው ማመልከቻ ይህንን ነጥብ የሚመለከት በመሆኑና የሕግ ትርጉም የሚያስነሳ ነጥብ ያለው መሆኑን በማመን ጉዳዩ ለሰበር እንዲቀርብ ተደርጐ የተጠሪ መልስና የአመልካች የመልስ መልስ እንዲቀርብ ተደርጓል።
83 84 ይህ የሰበር ችሎት ጉዳዩን መርምሯል። በዚህ ጉዳይ የሕግ ትርጉም የማያስፈልገው ነጥብ፣ በዋስትና ውል የተመለተን የአንድ ግድታ መፈፀሚያ ጊዜ፣ የመፈፀሚያ ጊዜ ካበቃ በኋላ ባለገንዘቡ የዋሱን ፈቃድ ሳይጠይቅ በራሱ ችሮታ ተጨማሪ የማስፈፀሚያ ጊዜ ለባለእዳው ሰጥቶ ቢገኝ ድርጊቱ ዋሱን ከተጠያቂነት ነፃ ያደርገዋል ወይስ አያደርገውም? የሚለው ይሆናል።
እንደሚታወቀው ለአንድ ግድታ አፈጻጸም ዋስ የሚሆን ሰው ባለእዳ እንዲፈጽም የሚጠየቀውን ግድታ በተስማማበት ሁኔታ ወይም ጊዜ ያልፈፀመ እንደሆነ ይህንኑ ግድታ ለባለገንዘቡ ለመፈፀም የሚገደድ ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1920 ላይ ተደንግጓል። ግድታውን እንዲፈጽም የሚጠራ ማንኛውም ዋስ ከውሉ መፈፀም በኋላ በባለገንዘቡና ባለእዳው መካከል የእርሱን ግድታዎች ያባባሱ አዲስ ስምምነቶችን በማንሳት ግድታውን ላለመፈፀም መከራከሪያ ላያደርጋቸው የሚችል መሆኑን ቁጥር 1928/1/ ያስገነዝባል።
በዚህ አንቀጽ በተለይ በንኡስ ቁጥር 2 የዋሱ ፈቃድ ሳይኖር በባለገንዘቡ የሚደረግ የመክፈያ ጊዜ ማራዘሚያ ተግባር ዋሱን ከነጭራሹ ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገው መሆኑ ተመልክቷል።
በያዝነው ጉዳይ የተጠሪ ደንበኛ በውሉ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትናውን እንዲያቀርብና ውል እንዲዋዋል አመልካች ደብዳቤ መጻፉ ተረጋግጧል። ዋሱን ጨምሮ ግድታ የገቡበት የግድታ መፈፀሚያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ደግሞ አመልካች ልላ ተጨማሪ ቀናት የሰጠ ደብዳቤ መጻፉ ታውቋል። የአሁኑ ተጠሪ አመልካች በራሱ ፈቃድ ያደረገው የተጨማሪ ጊዜ ችሮታ የእኔን ዋስትና ቀሪ ያደርገዋል በማለት ተከራክሯል። በዚህ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት በዋንኛነት ላታይ የሚገባው ነጥብ፣ የአሁኑ አመልካች የግድታ መፈፀሚያ ጊዜውን ካለዋሱ ፈቃድ አራዝሟል የተባለው መቼ ነው? የሚለው ይሆናል። ከጉዳዩ በግልጽ መረዳት እንደተቻለው የአሁኑ አመልካች ጥር 6 ቀን 1994 ዓ.ም የተጠሪ ደንበኛ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈጻጸም እንዲያቀርብና ውል እንዲዋዋል ሲገለጽለት ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚደርስ ጉዳት የአሁኑ ተጠሪ በገባው ግድታ መሰረት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ገልጿል። ከሕጉና 85 86 ከዚህ ደብዳቤ መንፈስ መረዳት የሚቻለው ነገር ከተባለው 10ኛ ቀን በኋላ ማለትም ከግድታው መፈፀሚያ ጊዜ ማብቂያ በኋላ ባለእዳው የተመለከቱትን ግድታዎች ፈጽሞ ካልተገኘ ዋሱ በባለእዳው እግር ተተክቶ ግድታውን መፈፀም እንደሚገባው ነው። በአንጻሩ ከዋሱ ፈቃድ ውጭ ከግድታ መፈፀሚያ ማብቂያ ጊዜያት በፊት በዋናው ባለእዳ ግድታ ላይ የሚደረግ ለውጥ ዋሱን ነጻ የሚያወጣው መሆኑን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1928/2/ ያስገነዝባል። የዚህ ድንጋጌ ዓይነተኛ አላማ ከፍ ብለን ለመግለጽ እንደሞከርነው ከውሉ መፈፀም በኋላ በባለገንዘቡና ባለእዳው መካከል የዋሱን ግድታዎች የሚያባብሱ አዲስ ስምምነቶች እንዳይደረጉና ዋሱን ለተጨማሪ ጉዳት እንዳይዳርጉት ለመጠበቅ ነው።
በዚህ መሰረት ጊዜ የተያዘላቸውና ዋስትና የተገባላቸው ግድታዎች የግድታ መፈፀማያ ጊዜያቸው ሲጠናቀቅ ዋስ ለግድታው ተጠያቂ እንደሚሆን ሁሉ ከግድታው መፈፀሚያ ጊዜ በኋላ ባለገንዘቡ በራሱ ፈቃድ በችሮታ መልክ የሚያደርገው የክፍያ ጊዜያት ማሻሻያም ሆነ ልሎች እርምጃዎች ዋስትና ከተገባለት ከቀድሞ ግድታ ጋር የማይገናኝ በመሆኑ ለበሰለው እዳ ከመጠየቅ የሚያድን አይሆንም። የሥር ፍ/ቤት ሕጉ ላጠብቀው ከተነሳው ዓላማ በመውጣት የአሁኑ አመለካች የግድታ መፈፀሚያ ጊዜው ያለፈበትን ግድታ ከዋሱ ፈቃድ ውጪ አራዝሞአል በማለት ዋሱ ከተጠያቂነት ነጻ እንዲሆን የተከተለው አካሄድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሆኑም ግድታ የተገባባቸው መፈፀሚያ ጊዜያት ከተጠናቀቁ በኋላ ባለገንዘቡ ለዋናው ባለእዳ የሚሰጣቸው የችሮታ መፈፀሚያ ጊዜያትም ሆኑ ልሎች እርምጃዎች ዋሱ ግድታ የገባበትን የቀድሞውን ግድታ መፈፀሚያ ጊዜያት ማራዘሚያ ተደርገው ላወሰዱ አይገባም በማለት ይህን ፍርድ ሰጥተናል።
ውሣኔ
የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ተሽሯል።
ተጠሪ በገባው ግድታ መሰረት የቢድ ቦንድ ዋጋ ብር 239,600 (ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ብር) ይህ ውሣኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር ለአመልካች ይከፈል።
87 88