የሰበር መ/20 ወ/ሮ አአበራሽ ጉቱ እእና የመካከለኛው አአዋሽ፣ አአበባ፣ ተንዳሆ፣ የሰሜን Oሞ እእርሻ ልማት ድርጅቶች/ በከፊል የፍርድ ባለመብት የሆነ ሰው ባለመብት የሆነበት የፍርድ ክፍል እእንዲፈጸምለት የአፈፃፀም ክስ ካቀረበ በፆላ በመጀመሪያ ፍርድ ባለእዳ የሆነበት ፍርድ በይግባኝ አአሽሮ የፍርድ ባለእዳ የሆነበትን ፍርድ በይግባኝ አአሽሮ የፍርድ ባለመብት ሲሆን አአዲስ የአፈፃፀም መዝገብ መክፈት ሳያስፈልገው ቀደም ሲል የተከፈተውን የአፈፃፀም መዝገብ ቢዘጋም እእንኳን ማንቀሳቀስ ስለመቻሉ እእና በአፈፃፀም ደረጃ ወለድ የሚከፈለው በዋናው ፍርድ ወለድ እእንዲከፈል ከተወሰነ ስለመሆኑ/
No summary available.
መ/ቁ. 1672A ጥቅምት 22 ቀን 1998 ዳኞች፡-
አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
አቶ ተገኔ ጌታነህ
አቶ መስፍን እቁበዮናስ
ወ/ት ሒሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ሮ አበራሽ ጉቱ ወኪል ሚደቅሳ ጉቱ ቀረቡ ተጠሪ፡-
የመካከለኛ አዋሽ እርሻ ልማት ድርጅት - አልቀረቡም።
አቦቦ እርሻ ልማት ድርጅት አልቀረቡም።
ተንዳሆ እርሻ ልማት አልቀረቡም።
የሰሜን Oሞ እርሻ ልማት ድርጅት - አልቀረቡም።
ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው የአሁኑ አመልካች ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በ7/7/93 ጽፈው ያቀረቡትን የአፈፃፀም ማመልከቻ መሰረት በማድረግ ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ ነው። የአሁኑ አመልካች ለሥር ፍ/ቤት በፃፉት አቤቱታ 61 62 የአሁኑዎቹ ተጠሪዎች ለአመልካች .94 /አንድ መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ አንድ ብር ከዘጠና አራት ሳንቲም/ እንዲከፍሉ ሲወስንባቸው በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ለተጠሪዎች .5A /አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሁለት ብር ከሀምሳ ሳንቲም/ እንዲከፍሉ ወስኖባቸዋል። ሆኖም አመልካች ለተጠሪዎቹ እንዲከፍሉ የተወሰነውን ገንዘብ በተመለከተ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ውሣኔው የተሻረ በመሆኑ ቀደም ሲል ፍ/ቤቱ የአፈፃፀም ትእዛዝ ሲሰጥ አመልካች ለተጠሪዎች እንዲከፍሉ የተወሰነውን .5A ቀንሶ ቀሪውን ገንዘብ ብቻ ተጠሪዎች እንዲከፍሉ የሰጠውን ትእዛዝ እንዲያስተካክል እና እንዲሁም በዋናው ገንዘብ ላይ ወለድ እንዲከፈል ትእዛዝ እንዲሰጥ አመልክተዋል።
ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን መርምሮ ለአፈፃፀም መሰረት በሆነው በመ/ቁ 639/82 ሐምል 3A ቀን 1983 ዓ.ም በተሰጠው ውሣኔ መሰረት እንዲፈፀም የአፈፃፀም ማመልከቻ ሲቀርብ አመልካች የጠቅላይ ፍ/ቤትን ውሣኔ ከመዝገቡ ጋር ስላላያያዙ ፍ/ቤቱ የአፈፃፀም ትእዛዝ የሰጠው በዚሁ ውሣኔ መሰረት ሲሆን ትእዛዝ በተሰጠበት ወቅት ፍ/ቤቱ የጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ትእዛዝ መሰረት በማድረግ ሂሣቡን ላሰራ ስለማይችል የሰጠው ትእዛዝ ትክክለኛ ስለሆነ የሚታረም አይደለም፣ በተፈረደው ገንዘብ ላይም ወለድ እንዲከፈል የተሰጠ ውሣኔ ስለልለ የወለድ ይከፈለኝ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም የፍ/መ/ደ/ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። አመልካች ያቀረቡት ቅሬታም የጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች ለተጠሪዎች .5A እንዲከፍሉ የተሰጠውን ውሣኔ በመሻር ይህንኑ ገንዘብ ተጠሪዎች ለአመልካች እንዲከፍሉ የሰጠውን ውሣኔ የሥር ፍ/ቤት እንዲፈፀም ትእዛዝ አለመስጠቱ የተሰጠውን ውሣኔ የሚለውጥ ወይም የሚሽር ስለሆነ የሕግ ስህተት ነው። ስለዚህ ገንዘብ እንዲከፈለኝ እና በዋናው ገንዘብ ላይ ወለድ እንዲከፈለኝ የሚል ነው።
ተጠሪዎችም የአመልካች የሰበር አቤቱታ ደርሷቸው በሰጡት መልስ ቀደም ሲል አመልካች በመ/ቁ 639/82 ሐምል 3A/1983 በተሰጠው ውሣኔ መሰረት እንዲፈፀምላቸው የአፈፃፀም ማመልከቻ አቅርበው በውሣኔው መሰረት ተፈጽሞ ጉዳዩ አብቅቷል። በወቅቱ የጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ ከአፈፃፀም ማመልከቻው ጋር አያይዘው አላቀረቡም። ስለዚህ አዲስ አፈፃፀም መዝገብ ከሚከፍቱ በቀር የጠቅላይ ፍ/ቤቱን ውሣኔ መሰረት አድርገው የቀድሞ አፈፃፀም ትእዛዝ እንዲስተካከል ያቀረቡት ጥያቄ ሥነ-ሥርዓትን ያልተከተለ ነው በማለት ተከራክረዋል።
አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል።
ከላይ የተመለከተው የግራ ቀኙ ክርክር ሲሆን በዚህም ጉዳይ ላታይ የሚገባው ነጥብ አንድ ፍርድ እንዲፈፀም የሚቀርብ ማመልከቻን የአቀራረብ አና የአፈፃፀም ሥርዓት ነው።
አንድ የአፈፃፀም ሥነ-ሥርዓት የሚጀምረው የተፈረደለት ሰው /የፍርድ ባለመብት/ በፍርዱ መሰረት እንዲፈፀምለት የአፈፃፀም ማመልከቻ ለፍ/ቤቱ ሲያቀርብ ነው /የሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378/1/ ይመለከቷል/።
በመሆኑም አንድ የአፈፃፀም ማመልከቻ ከማቅረቡ በፊት የተፈረደ ፍርድ ላኖር ይገባል። ይህ እንዲፈፀም በሚቀርበው የፍርድ ውሣኔ ደግሞ ከሳሽ ከጠየቀው የዳኝነት ጥያቄ ውስጥ ከፊሉ ተወስኖለት ከፊሉ ውድቅ የሚደረግበት ወይም በከፊል አንደኛው ተከራካሪ ወገን በከፊል ደግሞ ልላኛው ተከራካሪ ወገን ባለመብት ላሆኑ የሚችሉበት አጋጣሚ ይኖራል። በመሆኑም በከፊል ባለመብት የሆነው ወገን ወይም ከፊል የዳኝነት ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ወገን በተወሰነበት ጉዳይ ወይም ውድቅ በተደረገበት የዳኝነት ጥያቄ ላይ ይግባኝ ጠይቆ በተፈረደለት መጠን ብቻ የአፈፃፀም ማመልከቻ ላያቀርብ ይችላል። ነገር ግን ይግባኝ የተባለበት ጉዳይ የመጨረሻ ውሣኔ ሲያገኝ ባለመብቱ አዲስ የአፈፃፀም መዝገብ መክፈት ሳያስፈልገው አዲስ የአፈፃፀም ማመልከቻ በማቅር ብቻ የቀድሞውን የአፈፃፀም መዝገብ ከማንቀሳቀስ የሚከለክለው ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይ የሚለው በዚህ ጉዳይ ላነሳ የሚገባው ጥያቄ ነው።
65 66 በመሰረቱ የአፈፃፀም ሥነ-ሥርዓት ዓላማው በአንድ ውሣኔ ወይም ትእዛዝ ባለመብት የሆነውን ሰው ውሣኔው ወይም ትእዛዙ ያስገኘለት መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ በመሆኑ አንድ ፍ/ቤት ላፈፀም የሚችል ውሣኔ እስከቀረበለት ድረስ ውሣኔው እንዲፈፀም ተገቢውን ትእዛዝ መስጠት ይገባዋል።
በመሆኑም በአንድ ውሣኔ ላይ ከፊል ባለመብት የሆነ ተከራካሪ ወገን ባለመብት የሆነበት የውሣኔ ክፍል ላፈፀም የሚችል እስከሆነ ድረስ ይኸው የውሣኔ ክፍል እንዲፈፀም ማመልከቻ ከማቅረብ የሚከለክለው ነገር የለም። የአፈፃፀም ማመልከቻ የቀረበለት ፍ/ቤትም፣ ውሣኔው ካልታገደ በቀር አፈፃፀሙ ላያቆም ስለማይችል /የሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 332 ይመለከቷል/፣ አፈፃፀሙን ላቀጥል ይገባዋል። ይግባኝ የተባለበት ከፊል የውሣኔው ክፍል ግን ላፈፀም የሚችለው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የመጨረሻ ውሣኔ ከሰጠ በኋላ መሆኑ ግልጽ ነው። ምክንያቱም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ የመሻር፣ የመለወጥ፣ ወይም የማሻሻል ስልጣን አለውና ነው። በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኝ ባዩን የሚጠቅም ውሣኔ ከሰጠ ባለመብቱ፣ አዲስ የአፈፃፀም መዝገብ መክፈት ሳያስፈልገው፣ ልላ የአፈፃፀም ማመልከቻ በማቅረብ ብቻ የቀድሞ የአፈፃፀም መዝገብ እንዲንቀሳቀስ እና ውሣኔው እንዲፈፀምለት ለማድረግ ይችላል።
የመጀመሪያው የአፈፃፀም ጥያቄ የቀረበበት ጉዳይ ተፈጽሞ ያለቀ ቢሆንም እንኳን የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ በቀድሞው መዝገብ ላይ እንዳይቀጥል የሚከለክል ነገር የለም። የፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ ቁጥር 378/3/ረ/ እና ቁጥር 384ም አንድ የአፈፃፀም ማመልከቻ ከቀረበ በኋላ የሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከማለፉ በፊት በተለያየ ጊዜ ልላ ማመልከቻ እየቀረበ ነገሩን ለማንቀሳቀስ እንደሚቻል ማመልከታቸው ባለመብቱ አዲስ መዝገብ መክፈት ሳያስፈልገው በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ በቀድሞ መዝገብ እንዲፈፀም ማድረግ የሚቻል መሆኑን ያስገነዝባሉ። የዚህም አላማ በአንድ ጉዳይ የተሰጠ ውሣኔ በአንድ መዝገብ ተጠቃሎ እንዲፈጸም ለማድረግ ነው። ስለዚህም በከፊል የውሣኔው ክፍል ቅር ተሰኝቶ ይግባኝ ያቀረበ ወገን ይግባኝ ያለበት ጉዳይ እስኪወሰን ሳይጠብቅ የፍርድ ባለመብት የሆነበት ጉዳይ ብቻ እንዲፈፀም ላያመለክት ይችላል። ይግባኝ ያለበት ጉዳይ ከተወሰነለት ደግሞ አዲስ 67 68 መዝገብ መክፈት ሳያስፈልገው ልላ የአፈፃፀም ማመልከቻ በማቅረብ ብቻ የቀድሞውን መዝገብ አንቀሳቅሶ በይግባኝ የተወሰነለትን ፍርድ ላያስፈጽም ይችላል።
ከዚህ በመነሳት ወደ ያዝነው ጉዳይ ስንመለስ በመ/ቁ. 639/82 በ3A/11/83 የከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ተጠሪዎች ለአ ብር እና የዳኝነቱን ገንዘብ እንዲከፍሉ ሲወስን አመልካች ደግሞ .5A ብር ከነዳኝነቱ እንዲከፍሉ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ አመልካች ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ በመ/ቁ. 657/84 በ26/9/84 በዋለው ችሎት የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ውሣኔ .5A ብር ተጠሪዎች ለአመልካች እንዲከፍሉ ወስኗል። በመሆኑም አመልካች በከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲከፈላቸው ከተወሰነላቸው በተጨማሪ .5A እንዲከፈላቸው ተወስኗል።
ነገር ግን አመልካች የመጀመሪያ የአፈፃፀም ማመልከቻ ሲያቀርቡ እንዲፈጸምላቸው የጠየቁት በመ/ቁ. 639/82 የተሰጠው ውሣኔ ነው።
በወቅቱ የጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ እንዲፈጸም የቀረበ ጥያቄ አልነበረም።
በመሆኑም ፍ/ቤቱ በከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረት እንዲፈፀም የሰጠው ትእዛዝ ትክክል ነበር። ነገር ግን አመልካች ይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው አስወስነዋል። በመሆኑም አዲስ መዝገብ መክፈት ሳያስፈልጋቸው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት እንዲፈጸምላቸው ልላ የአፈፃፀም ማመልከቻ በማቅረብ ብቻ ጉዳዩ እንዲንቀሳቀስላቸው መጠየቃቸው የሥ/ሥ/ሕጉ የሚፈቅድላቸው ነው። በእርግጥ አመልካች ማመልከቻውን ሲያቀርቡ የጠየቁት የአፈፃፀም ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል የሰጠውን የአፈፃፀም ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 32A እና 2A8 መሰረት እንዲያስተካክል በመሆኑ ለጥያቄአቸው መሰረት ያደረጓቸው የሥ/ሥ/ሕጉ ድንጋጌዎች ለጉዳዩ አግባብነት የልላቸው ቢሆንም አንድ ባለጉዳይ አቤቱታውን ለፍ/ቤቱ ሲያቀርብ ሕግ የመጥቀስ ኃላፊነት የልለበት በመሆኑ አመልካች የተሳሳተ የሕግ አንቀጽ በመጥቀሳቸው ብቻ አቤቱታቸው ውድቅ ላደረግ አይገባም። የቀረበለትን ማመልከቻ አግባብነት ካለው የሕጉ ድንጋጌ ጋር መመርመር ተገቢውን መፈፀም የፍ/ቤቱ ኃላፊነት ነው። ፍ/ቤቱ የአፈፃፀም ማመልከቻው በሥነሥርዓት ሕጉ መሰረት አልቀረበም የሚልበት ምክንያት ካለው እንኳን አቤቱታው ተስተካክሎ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል /የሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 385/1/ ይመለከቷል/።
69 70 አመልካች በይግባኝ ፍ/ቤት የተሰጣቸውን ፍርድ ለፍ/መ/ደ ፍ/ቤት ስላቀረቡ ፍ/ቤቱ ውሣኔው መሰጠቱን አውቋል። ስለዚህም በውሣኔው መሰረት እንዲፈፀምላቸው ተገቢውን ትእዛዝ ከመስጠት ፋንታ አመልካቹ የተጠቀሱት የሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌ በመሣሣቱ ብቻ አቤቱታውን ውድቅ በማድረጉ የሕግ ስህተት ፈጽሟል።
ልላው አመልካች የጠየቁት በተፈረደው ዋና ገንዘብ ላይ ወለድ እንዲከፈላቸው ነው። በርግጥ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378/3/ሰ/ የአፈፃፀም ማመልከቻ ሲቀርብ በፍርዱ መሰረት የሚጠየቀው የገንዘብ ልክ ከነወለዱ እንዲገለጽ ያዛል።
ነገር ግን ይህ የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌ በዋናው ውሣኔ ላይ ወለድ እንዲከፈል የተሰጠ ውሣኔ ካለ ይኸው ወለድ ተሰልቶ ትክክለኛው አሀዝ በአፈፃፀም በማመልከቻው እንዲገለጽ የሚያዝ እንጂ ውሣኔ ያልተሰጠበትን የወለድ ክፍያ የአፈፃፀም ፍ/ቤቱ እንዲያስከፍል ስልጣን የሚሰጠው አይደለም። ምክንያቱም አንድ የአፈፃፀም ፍ/ቤት በውሣኔው መሰረት ከማስፈፀም አልፎ ውሣኔ ያልተሰጠበትን ጉዳይ እንዲፈፀም የማድረግ ስልጣን የለውም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ ረገድ በሰጡት ውሣኔ ላይ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚባልበት ምክንያት የለም።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 1A3/9A በመጋቢት 2A ቀን 1993 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ እና የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 8A76 በግንቦት 17 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሐል።
ተጠሪዎች .5A /አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ከሃምሣ ሳንቲም/ እና የዳኝነቱን ብር 671.00 /ስድስት መቶ ሰባ አንድ/ .5A /አስራ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ሃምሣ ሦስት ብር ከሃምሣ ሳንቲም/ ለአመልካች ይክፈሉ።
አመልካች በጠየቁት የገንዘብ መጠን .5A /አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሁለት ብር ከሃምሣ ሳንቲም/ ወለድ ላከፈላቸው አይገባም።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።
No topics extracted.